ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን ከሰማያዊ ፓርቲ መሪነት ለማስወገድ የተጀመረው ዘመቻ አንድ ደረጃ ወደ ፊት ሄዷል። ወያኔ ኢህአዴግ በትንሽ ገንዘብ በተላላኪነት የገዛቸው አንዳንድ አመራሮች ኢ/ር ይልቃል ጌትነትና ጥቂት ጓዶቹ ላይ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ጥቃትና ወከባ እያደረሱ መሆኑ ታውቋል። አብረው ሲታገሉ ከነበሩ አንዳንዶችም በቀጥታ የወያኔ ኢህአዴግ አባልና ካድሬዎች መሆናቸው በጥርጣሬ ሳይሆን በገሃድ ታውቋል። የፓርቲውን አሰራር በከፊል የሚቆጣጠሩ የኢህአዴግ ተላላኪዎች የሰማያዊ ፓርቲ ቀኝ እጅና አይን የሆኑትን ወጣቶች ከፓርቲው አሰናብተዋል። የወያኔ ተላላኪዎች በፓርቲው የተሰጣቸውን ሹመት ተመርኩዘው ፓርቲው የማይደፈውን ሃሳብ ጽፋችኋል በሚል ሰበብ ያሰናበቷቸው ታጋዮች: - 1. (ማዕከላዊ እስር ላይ ያለው) Yonathan T. Regassa 2. Eyasped Tesfaye 3.
Yonas Kedir 4. ጋሻዬነህ ላቀ ናቸው።
ፓርቲው ለሙሉ የመናገር መብት የቆመ መሆኑና ከሚታገልባቸው ፖለቲካዊ ራዕዮች አንዱ የግለሰቦች መብት ተከብሮ ዜጎች የፈለጉትን መናገርና ራሳቸው በጽሁፍ የመግለጽ መብታቸው እንዲከበር ማድረጉ ቢሆንም የተባረሩት ግለሰቦች ጽፈዋል በተባሉት የሃሳብ መግለጫ ጽሁፎች ከፓርቲው መባረራቸው ውሳኔው የወያኔ ኢህአዴግ ኢ-ዲሞክራሲያዊ ካድሬዎች ስራ መሆኑን አጋልጧል። ይህ አልበቃ ብሏቸው እንደለመዱት የወያኔ ጋዜጣ አዲስ አድማስ ላይ ወሬ ብለው ማስጻፋቸው ፓርቲውን ለማፍረስ እየሰሩ መሆናቸውን የሚያመላክት ነው።
ከላይ የተጠየቁት 4 ወጣቶች የተባረሩበት ዋናው ምክንያት በአብላጫ ድምጽ በብዙሃን ተመርጦ ፓርቲውን በመምራት ላይ የሚገኘው ኢ/ር ይልቃል ጌትነትን በህወጥ እና የሃሰት ክስ ከመሪነቱ ለማባረር የተሸረበውን የወያኔ ሴራ በመቃወማቸው ነው።

No comments:
Post a Comment