በተቃዉሞ እንቅስቃሴዉ ዉስጥ አንድ ያልተፈታ መምታታት ይታያል፡፡ህዝብንና ድርጅትን መለየት አለመቻል፡፡አንዳንዴ እንደስልትም ሆን ተብሎ ይሰራበታል፡፡ግን አክሳሪ ስልት እንደሆነ ትምህርት ሊወሰድ አልተቻለም፡፡ህወሓት በትግራይ ህዝብ ዉስጥ የተፈጠረ ድርጅት ሲሆን ህዝቡ ብዙ ታሪክ እየሰራ ለብዙ ዘመናት እንደኖረ የምንስማማ ይመስለኛል፡፡ለወደፊቱም ይኖራል፡፡
እነሓጎስ ድርጅቱ ውስጥ በአባልነትና በደጋፊነት ሊኖሩ ይችላሉ፡፡በህዝቡ መሃል እየተረገጡም ሊኖሩ ይቻላሉ፡፡በተቃዋሚዉ ጎራም ይኖራሉ፡፡ከሃገር እንዲወጡና እነዳይመለሱ የተደረጉም ይኖራሉ፡፡ተሰፋ ቆርጠዉ አንገት ደፍተዉ የተቀመጡም ይኖራሉ፡፡እነሓጎስ ብዙ ናቸዉ፡፡እነሓጎስን ከህወሓት ጋር ስናቀላቅላቸዉ ለደህንነታቸዉ ይሰጋሉ፡፡እናም ልዩነታቸዉን ረስተዉ አብረዉ ይቆማሉ፡፡
በዚህኛዉ ወገን ያለዉ ደጋፊም አቅም ያጣል፡፡የወገኖቹን ደህንነት ይፈልጋልና ነዉ፡፡የህወሃቶቹን እነሃጎስ ያገኘን(ለማሸማቀቅም ይሁን ለማስፈራራት) መስሎን ቀላቅለን ስናያቸዉ በተቃራኒ ያሉትን ሓጎሶች(ለምሳሌ የዓረና አመራሮችና አባላትን) ሁሉ አቅም እያሳጣናቸዉ ነዉ፡፡መሰረታቸዉን እያናጋነዉ ነዉ፡፡በህዝባቸዉ ፊት በህወሓት እንዲቀጠቀጡ ዱላ እያቀበልን ነዉ፡፡ሲሆን እንሰልጥንና የሁሉም ሓጎሶች ምርጫ ህወሓት ከሆነ ሌሎቻችን እኛን ራሳችንን ነጻ እናዉጣና ያገሪቱ ህግ በሚፈቅደዉ መሰረት አብረናቸዉ ለመስራት ዝግጁ እንሁን፡፡እነሱን ከነሓጎስ ጋር ለማጥፋት ከመስራት እዛዉ ራሳቸዉን እንዲያስተዳድሩ ራስን ማሳመን ዋጋዉ ይቀላል፡፡ሁሉን አቀፍ ድርድር (inclusive
negotiation) እኮ
አንዱ
እፊታችን
የሚኖር
አማራጭ
ይመስለኛል፡፡ራሳችንን
ነጻ
ለማዉጣት
ከህወሓት
ጋር
ያሉትን
ድጋፍ
መጠበቅ
ተገቢ
አይመስለኝም፡፡ግን
እስኪ
ሌሎቻችን
በወጉ
እንስማማ፡፡
መንግሰትን የሚያክል ግዙፍ ተቋም ለመለወጥና አገር ለመምራት የተናጠል አመጽ ብቻዉን በቂ አይመስለኝም፡፡ህዝብን እንወክላለን የሚሉ ቡድኖች ቢስማሙ፤ቅስቀሳና አስተምህሮቶች ሁሉ ባንድነት ቢቆሙ ኢትዮጵያ ዉስጥ አመጽ ለመቀስቀስ መስራት አይጠበቅም፡፡ለዚህ ኢህኣዴግ ራሱ ተግቶ እየሰራ ነዉ፡፡ የተቃዉሞዉ ጎራ አንድነቱን ጠብቆ አማራጭነቱን ከሳየ ህዝባዊ አመጽ ከሆነ ቦታ በሆነ ምክንያት ተነስቶ ስርኣት እንደሚለዉጥ በአለም ላይ በቂ ተሞክሮ አለ፡፡እኛ የተለየን አንሆንም፡፡
ሳጠቃልለዉ እነሓጎስን ከህወሓት አለመለየት ለትግሉ መዳከምና ለመከራችን መራዘም አስተዋጽኦ ማበርከት ነዉ፡፡እንዳለመታደል ሆኖ በተናጠልም ቢሆን እየተከፈለ ያለዉን ዉድ መስዋእትነት ማራከስ ነዉ፡፡እነሓጎስን በሙሉ ከራሱ ጋር መቀላቀልና የተቀላቀሉ ማስመሰል የሚፈልገዉ ህወሓት ብቻ ነዉ፡፡ህዝብና ድርጅት የመለየት ጥበብ ይኑረን፡፡ልቦናችን ካላሰበዉ ካፋችን አይጣምና ልቦና ይስጠን፡፡ተገቢ ቃላትን መጠቀም ለትግሉ ወሳኝነት ይኖረዋል፡፡ህወሓትና ወያኔም አንድ አይደሉም! ለዚህም ነዉ ገዥዉ ቡድን ህዝባዊ ጥያቄዎችን ሁሉ ረብሻ እያስመሰለ የሚያቀርበዉና ህይወት እየበላ እንዲቀጥል እድል እተሰጠዉ ያለዉ፡፡በእዉነት ያማል!!!!
Source: Millions of voices for freedom - UDJ
No comments:
Post a Comment