*‹‹ጠበቆቻቸውን አገናኟቸው›› ፍ/ቤት
*‹‹ጠበቃ አታስገቡ ተብለናል›› የማዕከላዊ ጥበቃዎች
*‹‹ጠበቃ አታስገቡ ተብለናል›› የማዕከላዊ ጥበቃዎች
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ማዕከል በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ እና የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ጠበቆቻቸውን ማግኘት እንዳልቻሉ ታውቋል፡፡
ዛሬ ጥር 20/2008 ዓ.ም ረፋድ ላይ በማዕከላዊ ታስረው የሚገኙትን ደንበኞቻቸውን ለማነጋገር አምርተው የነበሩት የዮናታን ተስፋየ እና የጌታቸው ሺፈራው ጠበቆች ‹‹ጠበቃ አታስገቡ ተብለናል›› የሚል መልስ ከማዕከላዊ ጥበቃዎች ተሰጥቷቸው መግባት ተከልክለው ከበር ተመልሰዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከታሰሩ አንድ ወር ቢያልፋቸውም እስካሁን ጠበቆቻቸውን ማነጋገር አልቻሉም፡፡
አቶ ዮናታን ተስፋየ እና ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ፍርድ ቤት ቀርበው ጊዜ ቀጠሮ በተሰጠባቸው ወቅት በጠበቆቻቸውና እና በቤተሰቦቻቸው እንዳይጎበኙ መደረጋቸውን ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ማሰማታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የአራዳ ፍርድ ቤትም ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸውም ሆነ በቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙ እንዲፈቀድላቸው ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን በሰጠበት ማግስት ጠበቆቹ ደንበኞቻቸውን ለማነጋገር እንደተከለከሉ ከጠበቆቹ ለማወቅ ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment