‹‹ውሳኔው ከፓርቲው መሰረታዊ ሀሳቦችና እምነቶች ተቃርኖ የተላለፈ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም›› ኢ/ር
ይልቃል ጌትነት
የሰማያዊ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ በአራት አባላቱ ላይ የብሄራዊ ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ ያስተላለፈውን ከፓርቲው የማሰናበት ውሳኔ እንደማይቀበለው አስታወቀ፡፡
የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ዛሬ ጥር 9/2008 ዓ.ም
ከሰዓት በኋላ ባካሄደው ስብሰባ አቶ ዮናታን ተስፋየ፣ አቶ እያስጴድ ተስፋየ፣ አቶ ዮናስ ከድር እና አቶ ጋሻነህ ላቀ ላይ የተላለፈውን ውሳኔውንም ሆነ ሂደቱን እንዳልተቀበለውና ውሳኔውም በሰማያዊ ደንብ መሰረት ተግባራዊ እንደማይሆን፣ ተባረሩ የተባሉት አባላትም በሙሉ ኃላፊነታቸው እንደሚቀጥሉ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የሰማያዊ ሊቀመንበር ኢ/ር
ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
‹‹የተላለፈው ውሳኔ የሰማያዊን መሰረታዊ ሀሳቦችና እምነቶች፣ ማለትም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትና የግለሰብን ነጻነት የተጋፋ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም›› ብለዋል ሊቀመንበሩ፡፡
የክስ አቀረራረቡም ሆነ የውሳኔ አሰጣጡ በሰማያዊ ደንብ መሰረት ምላዕተ-ጉባኤ ሳይሟላና ቃለ ጉባኤ ሳይፈረም የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ ውሳኔው ተቀባይነት የለውም ሲል ስራ አስፈጻሚው በሙሉ ድምጽ መወሰኑን ኢ/ር
ይልቃል አስረድተዋል፡፡
Source: ነገረ ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment