Saturday, April 25, 2015

ኢትዮጵያዊያኑ ጦማሪዎች ፍትህ ሲጠብቁ አንድ አመት ሞላቸው

የግንቦቱ ምርጫ ሲቃረብ ተቃውሞ ላይ ጥቃት ሲበረታ ስድስቱ ወጣት ጦማሪያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞችም በእስር ላይ እንዳሉ ነው ::ነገርግን ምእራባዊያን ዝም ብለው ይመለከታሉ:: ግሎባል ቮይስስ
  • Zone 9
  • በ2004 ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያን ወንዶች እና ሴቶች ዞን 9 የተሰኘ የጦማሪዎች ቡድን ለመመስረት ተሰባሰቡ። የፖለቲካ ሙሰኝነት በሰፊው በተንሰራፈበት: የመገናኛ ብዙሃን በመንግስት ፍጹም ቁጥጥር ስር ባሉበት እና አምባገነን ስርአት ስር በሰደደበት ሀገር ላይ ይህ በጣም ድፍረት የሚፈልግ ተግባር ነው።
    በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ በመጻፍ ጦማሪዎቹ የአገሪቷን አንዳንድ ፈታኝ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በመዳሰስ በሃገሪቷ መገናኛ ብዙሃን ለማይነገሩ ታሪኮች ህይወት ሰጥተዋል።
    ዞን 9 የመናገር ነጻነትን እና የመሰብሰብ መብትን በማስከበሩ ስለሚወደሰው፣ እንዲሁም በየአምስት አመቱ ምርጫ እንዲደርግ ስለሚያስገድደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ህገ መንግስት በአደባባይ መናገር አስፈላጊ ነው ብለው ያምናሉ። ጦማሪዎቹ ዜጎች ነጻ የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም መንግስታቸውን ተጠያቂ ቢያደርጉ የሃገሪቷ ማህበራዊ ትስስር ጠንካራ ይሆናል ብለው ያስባሉ። ዜጎች ሃገራቸው እንዴት እንደምትተዳደር ድምጻቸውን የማሰማት መብት ሊኖራቸው ይገባል።
    ት ፋንታሁን ነሃሴ
    መግባባት ባለመቻላችን የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ተለያይተናል ብዬ አምናለሁ። የህዝብ ተወካይ ተብለው ምክር ቤቶችን ጨምሮ በተለያየ ቦታ የሚገኙ ሰዎች ጥረታቸው ገዢው ፓርቲው የሚለውን ሁሉ ለህዝብ ለማሳመን እንጂ የወከላቸውን ሃሳብ ለመንግስት ሲያቀርቡ አይደለም። በስም ብቻ የህዝብ ተወካይ ተባሉ እንጂ በስራቸው የገዢው ፓርቲ ተወካዮች ናቸው ማለት ነው።
    ከአመት በፊት እንነኚህ ጸሃፊዎች ከየቤታቸው ተወስደው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። በእስር ለ11 ሳምንታት ከቆዩ በኋላ በኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ ተከሰዋል።
  • አዲስ ነገር የለም

    የጋዜጠኞች ጠባቂ ኮሚቴ የጋዜጠኞች መብት ተካራካሪ ድርጅት በዚህ ሳምንት ባወጣው ሪፖርት መሰረት ከአለማችን ከባድ ቅድመ ምርመራ ከሚካሄድባቸው ሃገራት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
    እስከ ግንቦቱ ምርጫ መዳረሻ ድረስ መንግስት “አሸባሪነትን ያበረታታሉ” ብሎ በመውንጀል ስድስት የህትመት ውጤቶች ላይ ክስ መመስረቱን፣ 16 ጋዜጠኞች ለስደት መዳረጋቸውን ፣ የአገሪቷ ብቸኛ ኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ኢትዮቴሌኮም ትችታዊ ሀተታ የሚጽፉ የዜና ድረ ገጾችን በሃገሪቷ እንዳይነበቡ ዘውትር እንዲገዱ ማድረጉን ዘገባው ያሳያል።
    ምንም አዲስ ነገር የለም ላለፉት 24 አመታት ሀገሪቱን እየመራ ያለው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲ ግንባር (ኢሀዴግ) ማህበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ቁጥጥሩን በረቀቀ መንገድ ሲዘረጋ በምእራባዊያን መንግስታት ዘንድ ግን ከድህነት ጋር ተያይዞ የሚነሳውን የሀገሪቱን ስም በመለወጥ በማደግ እና በለውጥ ላይ ያለች የተረጋጋች ሀገር እንደሚመራ ሁሉ ምስጋና ተቸሮታል::
    ዞን ዘጠኞች የመጀመሪያ አይደሉም:: ኢትዮጵያን በተከታታይ የመሩ እርስ በርስ እጅግ የሚቃራኑ ሶስት የተለያዩ አገዛዞች ማለትም – 1991 ላይ ከስልጣን የተባረረውን የመንግስቱ ሀይለማሪያም ወታደራዊ አገዛዝን ጨምሮ በአጼ ሀይለስላሴ የሚመራው የአጼው ስራአት እና አሁን ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ የሚያመሳስላቸው አንድ የጋራ ገጽታ አላቸው:–ይህውም ሁሉም ጋዜጠኞችን: የተቃዋሚ ፖለቲካ አራማጆችን: እና የመብት ተሟጋቾችን አስረዋል ወይም ገድለዋል::
  • የዞን ዘጠኝ ስም በከፊልም ቢሆን ከዚህ ታሪክ መነሻነት የመጣ ነው። ቃሊቲ የተባለው ከአዲስ አበባ ከተማ መውጫ ላይ የሚገኘው እስር ቤት በስምንት የተለያዩ ዞኖች የተከፋፈለ ሲሆን የመጨረሻው እና በመጥፎነቱ የሚታወቀው ስምንተኛው ዞን የጋዜጠኞች፣ የሰባአዊ መብት ተሟጋቾች እና የተቃዋሚዎች ማጎሪያ ነው።
    እንዳልክ የተባለው ካልታሰሩት ሶስት የዞን ዘጠኝ አባላት አንዱ የሆነው ስለ ጦማሩ አመሰራረት ሲናገር “የጦማሩን ስያሜ ያወጣነው ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚኖርበትን ምሳሌያዊ እስር ቤትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው። ይህ ዞን ዘጠኝ ነው።”
  • የኢትዮጵያ መንግስት ጦማሪዎቹን “በህዛባዊ አመጽ፣ ህገ መንግስታዊ ስረአቱን ለመለወጥ አሲረዋል” በማለት ከሷቸዋል።
    ጦማሪያኑ በዚህ አመት ግንቦት ወር አጋማሽ ላይ የፍርድ ሂደታቸው ይቀጥላል። ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ በእያንዳንዳቸው በትንሹ የስምንት አመት እስር ሊፈረድባቸው ይችላል።
    ኢትዮጵያ ካደጉት ሃገራት ወታደራዊ እና የበጎ አድራጎት እርዳታ ተጠቃሚ ናት። ይህም በብሔሮች መካከል ያለ ውጥረት፣ ሙስና እና ወንጀለኝነት በከፍተኛ ደረጃ በሚገኝበት በአፍሪካ ቀንድ ሃገሪቱን የጸጥታና የደህንነት ስፍራ ለማድረግ በማሰብ የተደረገ ነው።
    ከጎረቤት ሃገር ሶማሊያ በሚመጣው እውነተኛ የሽብርተኝነት ስጋት መንግስት ከአለም አቀፍ መንግስታት ባገኘው እርዳታ ጠቅላይ የጸረ ሽብር አዋጅ አውጥቷል። ነገር ግን እነኚህን ህጎች በአብዛኛው ጊዜ መንግስት የራሱን ህዝቦች ለማፈኛነት ይጠቀምባቸዋል።
    ከ1997 መጨረሻ እስከ 2005 በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደረግ ምንም አይነት የህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ የለም። በተጨማሪ በኢትዮጵያ በጣት የሚቆጠሩ ለህልውናቸው የመንግስት ይሁንታን ያገኙ ኤፍኤም ራዲዮ ጣቢያዎች እና ከአንድ የመንግስት ቴሌቭዝን ጣቢያ በስተቀር ምንም አይነት ነጻ በየቀኑ የሚታተም የግል ጋዜጣ የለም።
    ከ1997ቱ ብሔራው ምርጫ በኋላ አገዛዙ ተቃዋሚ ቡድኖችን እና የሰራተኛ ማህበራትን እና የሐይማኖታዊ ተቋማትን በማገድ መንግስታዊ ቁጥጥር በድረ ገጾቻቸው ላይ አድርጓል።

    መንግስት 99% በፓርላማው የሚገኙትን ወንበሮች አሸንፊያለሁ ካለበት ከ2002 ምርጫ በኋላ አገዛዙ የሀገሪቷን ተቋማት ማለትም ፍርድ ቤቱን፣ መገናኛ ብዙሃንን፣ መስጊዶችን፣ አቤያተ ክርስቲያናትን ፣ ትምህርት ቤቶችን እና ዩኒቨርስቲዎችን በቁጥጥሩ ስር አስገብቷል። በ2002 ብቸኛው ለማህበራዊ ተዋጽኦ የሚጠቅም የመገናኛ ብዙሃን አማራጭ ኢንተርኔት ብቻ ነበር::
  • Zone 9
  • እንደ ነውር የሚቀጠረው የመናገር ነጻነት

    ከ8 እስከ 18 አመት እስራት በተፈረደባቸው አለም አቀፍ የጋዜጠኝነት ሽልማት አሸናፊ ጋዜጠኞች እንደ እነ እስክንድር ነጋ፣ ሪዮት አለሙ፣ ውብሸት ታዬ እና ሌሎች ዘጠኝ ጋዜጠኞች ላይ መንግስት በሚያደርስባቸው ጫና የተነሳ ስጋት ውስ ነበሩ። በ2006 አጋማሽ ላይ ዞን 9ኞች ማስፈራራቱ እና ክትትሉ ሲጨምርባቸው ጦማራቸውን ለስድስት ወር ያህል አቁመውት ነበር። ነገር ግን በሚያዚያ 2006 ጥማሪያኑ ከዛ በላይ እንደማይቆዩ ወሰኑ። የጠፉበትንም ምክኒያት ምን እንደነበር የሚያብራራ ደብዳቤ ለጠፉ።
    “ከዞን 9 ነዋሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ ከዞኑ ጽሑፍ ያነበቡት ደሞ የዛሬ ስድስት ወራት ገደማ ነው። አገራችን ኢትዮጵያ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በሚገባ የሚታፈንባቸውአገራት አንዷ መሆኗን ከዚህ ቀደም ከምናውቃቸው ምሳሌዎች በተጨማሪ በተለይ ባለፋት ስድስት ወራት በተግባር አይተነዋል። ለነገሩ የዜጎች ሐሳብን መግለጽ በገዢዎቻችን ዓይን የነውር ያክል እንደሚቆጠር የተረዳነው ገና ቡድናችን ሥራውን በይፋ የጀመረ ሰሞን አንድ ዞን ዘጠኛዊ ላይ በደረሰ ግልጽ ማስፈራሪያ ነበር፡፡ከማኅበራዊ አውታሮች እምብዛም ያልወረዱ እንቅስቃሴዎችን ዝም ብለን ስንቀጥል፣ በከፊል የተረሳን መስሎንም ነበር፡:” ነገር ግን አልተረሱም
    በሚያዚያ 18 ደብዳቤውን ከለጠፉ ከአንድ ሳምንት በኋላ ስድስት የጦማሪያኑ አባላት እና ከነርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሦስት ጋዘጠኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
    ይህው ከአንድ አመት በኋላም የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ ነው። በጦማሪያኑ የክስ መዝገብ ላይ ሴኪዩሪቲ ኢን ኤ ቦክስ የተባለ የግንኙነት መስመር ማመስጠሪያ የዲጂታል ደህንነት መሳሪያዎች ልምምድ እንደ ወሰዱ ያትታል:: በተጨማሪም በርካታ ኢትዮጵያዊያንን በማህበራዊ ተዋጽኦ እንዲሳተፉ እና ስለ ሰብአዊ መብቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አንዲወያዩ የበይነ መረብ ዘመቻ ማዘጋጀታቸውን ያመለክታል።
    በተጨማሪም በርካታ ኢትዮጵያዊያንን በማህበራዊ ተዋጽኦ እንዲሳተፉ እና ስለ ሰብአዊ መብቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አንዲወያዩ የበይነ መረብ ዘመቻ ማዘጋጀታቸውን ያመለክታል።
    በእስር ቤት ስላጋጠመው እና ስለ ወደፊት ተስፋው ናትናኤል በቅርቡ ከእስር ቤት በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ ይላል “እውነቱን ለመናገር በአሁኑ ሰአት በጣም የሚያስጨንቀኝ ነገር በእስር ቤት ምን ያህል ጊዜ እንደማሳልፍ አይደለም። የሚያሳስበኝ ነገር የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚያፈሰው ዶላር በምርህ ላይ የተመሰረተ እና ዲሞክራሲያዊ እድገተቻንን ከግምት ሳያስገባ ከቀጠለ እንዴት እንደምሆን ነው”
    “በመጨረሻም” ናትናኤል ቀጠለ“ኔልሰን በማንዴላ ቃላት እድላችን የሚወሰነው ለአላማችንሚከፈለውንዋጋ ለመክፈል ባለን ፍቃደኝነት እና ዝግጁነት መጠን ይወሰናል”
  • Source: theguardian

No comments: