በሰሜን አሜሪካ የሚገኙት የሰማያዊና የአንድነት ማህበራት ኮሚቴ አቋቁመው በጋራ ለመስራት መወሰናቸውን ለነገረ ኢትዮጰያ በላኩት መግለጫ አሳወቁ፡፡ ማህበራቱ ዛሬ የካቲት 19 2007 ዓ/ም በጋራ ባወጡት መግለጫ ገዥው ፓርቲ ፓርቲያቸውን ያፈረሰባቸው የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አድንቀው ‹‹ይህ ዓይነቱ የአባላት ቆራጥ ውሣኔ ሊበረታታና ሞራል ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለን እናምናለን፡፡ እኛም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የሁለቱ የድጋፍ ማህበራት ሙሉ በሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡›› ብለዋል፡፡
‹‹በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአንድነትና የሠማያዊ የድጋፍ ማህበራት በጋራ በኮሜቴ ደረጃ ተዋቅረን በዋና ዋና ጉዳዬች ላይ ማለትም በፋይናንስ፤ በእስረኞች ጉዳይ እና በዲኘሎማሲው ዙሪያ ሙሉ በሙሉ በትብብር አብረን እየሠራን የሰማያዊ ፓርቲንና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሣኔ አሣልፈናል፡፡›› ያለው መግለጫው በቀጣይም በጋራ ኮሚቴ በኩል ውይይቶችን እያደረገ ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስፈልጉ የሞራልና የማቴሪያል ርዳታ እንደሚሰጥ ገልጾአል፡፡ የጋራ ኮሚቴው በመግለጫው አገር ቤት ያለው የሰላማዊ ትግል ሊበረታታ ይገባዋል ብሏል
No comments:
Post a Comment