Wednesday, February 18, 2015

የኮምቦልቻ ከተማ ቃሉ ቁ/1 ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎችን በይፋ በማገድ አሰናብቷቸዋል፡፡

‹‹እኛ የታዘዝነውን ነው የፈፀምነው›› አቶ ታደሰ ሻረው/ የምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ፡፡
ዛሬ በቀን 10/06/2007 ዓ.ም በደቡብ ወሎ የሰማያዊ እጩዎን የማፅዳት ዘመቻ አንዱ አካል የሆኑት የኮምቦልቻ ሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች በይፋ ታግደው ያስገቡት ዶክሜንት ተመላሽ ተደርጎላቸዋል፡፡ በትናንትናው እለት በአቶ ትግስቱ አወሉ ተወክያለሁ የምትለው ወ/ሮ ሰብል ይመር የተባለች የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪ በተሰጣት ተልእኮ መሰረት ተወስኖ የመጣላትን ውሳኔ በደቡብ ወሎ በሚገኙ ከ20 በላይ የምርጫ ወረዳዎች በመሄድ ህጋዊ ደብዳቤ እንኳ ሳትይዝ የእጩዎችን ስም ዝርዝር ብቻ በመያዝ ለምርጫ ቦርድ ሀላፊዎች ትእዛዝ ስታስተላልፍ እንደነበርና ትእዛዙን ተከትሎ የምርጫ ቦርድ ሀላፊዎች የማስፈፀም ተልእኳቸውን እንደጀመሩ መግለፄ ይታወቃል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለትየኮምልቻ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች ትናንት ክሊራንስ አላቀረባችሁምበሚል ክስ እንደቀረበባቸውና ክሊራንስ እንዲያመጡ በተጠየቁት መሰረት ውሳኔው ፖለቲካዊ መሆኑን አስቀድመው የሚገነዘቡት ቢሆንም በታጋሽነት ከኮምቦልቻ አንድነት ሰብሳቢ አቶ ሰይድ መሀመድ ክሊራንስና መልቀቂያ ይዘው ቢቀርቡም፤ ቦርዱ ‹‹ግለሰቡን እውቅና አልሰጠነውም›› በሚልምላሽ መመለሱን ተከትሎ የቀድሞው አንድነት ፓርቲ በኮምቦልቻ ሙሉ በሙሉ መፍረሱን ተከትሎ የሚጠየቅ ሰው ባለመኖሩ፤ ጉዳዩን ወደዞኑ አንድነት ፅ/ቤትበመሄድ በወቅቱ በእጃቸው ማህተም ከያዙ የዞኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ህጋዊ ክሊራንስና የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው ቢመጡም በድጋሜ ቦርዱ ‹‹ህጋዊ ደብዳቤ ብታመጡም አንቀበልም››ሲል ምላሽ የሰጠ ሲሆን ይህን ተከትሎ እጩዎቹ ጋር ከፍተኛ እሰጣ ገባ ውስጥበመግባት ለረዥም ሰዓት ቢከራከሩም እልባት እንደሌለውና በ24 ሰዓት ክልል ምርጫ ቦርድ ይግባኝ አቅርባችሁ ውሳኔው ተሸሮ ካልመጣ በቀር የወሰነው ውሳኔ አይሻርም ብለዋል፡፡ እጩዎቹ በበኩላቸው የእናንተ ውሳኔ ያላስረከቡትን ንብረት ያስረክቡ፤ክሊራንስ ያምጡ የሚል ነው፤ እኛም ምንም እንኳ ከፓርቲው መታወቂያን ጨምሮ ቁራጭ ወረቀት እንኳ ያልተሰጠንና ለትግሉ ከቤት ኪራይ አንስቶ ሌሎች ወጭዎችን ከግላችን አዋጥተን፤ከገንዘብ እስከ ውድ ጊዜያችን ሰውተን የለፋንለት ሰላማዊ ትግልና ፓርቲያችን በዚህ ሁኔታ ወድቆ በመፈራረስ የሆነው ነገር ቢያሳዝነንም ዙራችሁ ባለእዳ ካደረጋችሁን በማለት ከዞን ህጋዊ ክሊራንስና ህጋዊነቱ በደብዳቤ ካልተሻረ ሀላፊ ክሊራንስ አምጥተን አንቀበልም መባሉ አስቀድሞ የተወሰነ ውሳኔና ምርጫ ቦርድም የአጥቂውን ሚና እየተጫወተ እንደሆነ አረጋግጠናል›› …..በማለት ተናግረዋል፡፡
የምርጫ ቦርዱ ሀላፊ አቶ ታደሰ ሻረው የተባሉ ግለሰብ ከእጩዎቹ ጋር ባደረጉት ንግግር ውስጥ፤……‹‹እኛ ስሜታችሁንና እውነታውን እናውቃለን፤ነገር ግን ከበላይ ታዘን በመሆኑ የምናደርጋችሁ ነገር የለም አትልፉ፤ …..ከየትም ደብዳቤ ብታመጡ በአቶ ትግስቱ የተፈረመ ካልሆነ በስተቀር እንዳንቀበል ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቶናል ስለዚህ ያላችሁን መረጃ ውሰዱ በማለት ለእጩዎች የመለሱላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በቃሉና በሌሎች የደቡብ ወሎ ወረዳዎች የሚገኙ የሰማያዊ እጩዎች ተመሰሳይ እጣ እንደገጠማቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments: