Thursday, June 30, 2016

ወታደሮችንና ከባድ ማሳሪያዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ግንባር እየተጓዙ ነው

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- ከደቡብና ከመሃል አገር የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲሁም አዳዲስ የገቡና ነባር የጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ግንባር እየተጓዙ ነው። የህዝብ ማመላለሻ ተሽካርካሪዎች በግዳጅ ወታደሮችን እንዲያመላልሱ እየተደረገ መሆኑን የሚናገሩት የአይን እማኞች፣ ከባድ መሳሪያዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከዚህ ቀደም ባልታዬ መልኩ በብዛት ወደ ግንባት እየተጓዙ ነው ብለዋል።
ከትናንት በስቲያ ወደ ትግራይ ሲጓዝ የነበረው የመከላከያ ሰራዊት ኮንቮይ ኮምቦልቻ ላይ ሁለት ተሽከርካሪዎች ተጋጭተው መንገድ ዘግተውበት 5 ሰአታት በላይ መንገድ ዘግቶ መቆየቱንም የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ አዲስ አበባ ፖሊስ አባላትን በሰፊው በተደራጀ አግባብ እየሰለሉዋቸው መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል። ይህንን ተከትሎ በደንብ ማስከበር ስራ ላይ የተሰማሩ ካድሬዎች ጭምን ድንጋጤ ውስጥ  መግባታቸው ታውቋል።
ስለላው ለምን እንደሚካሄድ ባይታወቅም፣ በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ እየጨመረ የመጣው አለመተማመን ምክንያት ሳይሆን አይቀርም በማለት ምንጮች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። ከፌደራል ፖሊስና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስራቸውን ጥለው የጠፉትን  ፖሊሶች አዲስ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየታደኑ መሆኑን ምንጮች አክለው ግለጸዋል።


No comments: