Wednesday, June 29, 2016

አቶ ሀብታሙ አያሌው በአስቸኳይ የውጭ ሀገር ህክምና እንዲያገኙ ሰማያዊ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚንሲትሩ አሳሰበ!!!

አቶ ሀብታሙ አያሌው በአስቸኳይ የውጭ ሀገር ህክምና እንዲያገኙ ሰማያዊ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚንሲትሩ አሳሰበ!!! በግለሰቡ ሕይወት ላይ ለሚደረስው አደጋ መንግሥት ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን ጭምር ፓርቲው አክሎ ገልጾአል

መንግስት የዜጎችን ደህንነትና ጤንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም በሀገራችን በሕግ ከለላ ስር ያሉ ዜጎች ተገቢውን ሕክምና ባለማግኘታቸው ሕይወታቸው አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ በእስር ቤት እያሉ ተገቢውን ሕክምና ማግኘት ባለመቻላቸው ለሞት የተዳረጉ እንዳሉ የሚታወቅ ነው፡፡
አቶ ሀብታሙ አያሌው በተለምዶ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በመባል በሚታወቀው ተቋም በምርመራ ወቅት በደረሰባቸው ህመም ሕክምናውን በሀገር ውስጥ ባሉ የጤና ተቋማት መታከም እንደማይችሉና ወደውጭ ሀገር ሄዶ ህክምና ማግኘት እንዳለባቸው የተገለፀ ቢሆንም ከሀገር እንዳይወጡ በፍ/ቤት ታግደዋል፡፡
በመሆኑም አቶ ሀብታሙ አያሌው በፍ/ቤት የተጣለባቸው ዕግድ ተነስቶ ወደ ውጭ ሀገር ሂደው እንዲታከሙ አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ እየጠየቅን ይህ ባይሆንና ህክምና ባለማግኘቱ በግለሰቡ ሕይወት ላይ ለሚደረስው አደጋ መንግሥት ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን እናሳስባለን።
ግልባጭ፣
ለኢፊዲሪ ለሕዝብ ተወካዮች /ቤት
፨ለሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ለፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ


No comments: