(በዘላለም ክብረት)
የእስረኛ ፊት ብዙ ነው፡፡ ታሪኩም ብዙ ነው፡፡ ብሶቱም ብዙ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ‹ዎክ› የሚያደርግበትመንገድ እንኳን ብዙ ነው፡፡ የሆነ በፅሁፍ ለመግለፅ የሚያስቸግር ከአራት እስከ ስድስት የሚሆኑ ርምጃዎችን ተጉዞ መመለስ ከዛ እንደገናመመለስ … ከዛ እንደገና መመለስ …በጣም በተደጋጋሚ … የሚደረገው ‹ደረስ - መለስ› የዎክ አይነት ግን የእስር ቤት መገለጫ ነው፡፡አብዛኛው እስረኛ ወደ ሰፊው ‹ማረፊያ ቤት› ከመምጣቱ በፊት በፖሊስ ጣቢያዎች ስለሚቆይና ጣቢያዎች ደግሞ ጠባብ በመሆናቸው ምክንያትወይም በራቸው ተዘግቶ ስለሚውል እዛው እዛው ‹ደረስ - መለስ› ዎክማድረግ እዛ ጣቢያ የተለመደ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ የዎክ አይነት በተለየ ደግሞ ማታ ቆጠራ ከመካሔዱና ‹በየበዓታችን› ከመስፈራችንበፊት ባሉት ደቂቃዎች በዛ ያለ ሰው አንድ ላይ ሁኖ ክብ ሰርቶ የሚርመሰመስበት ‹አዙሪት› የዎክ አይነት አለ - በኢትዮጵያ እስርቤት፡፡ በአብዛኛው እኔና አቤላ የዚህ አዙሪት አካሎች ነበርን፡፡
አንድ ቀን አዙሪቱ መሃል እየተጓዝን እያለ አቤላ ‹ፖሊስ ጣቢያ› በነበርንበት ወቅት መጀመሪያ የተደበደበበትንምክንያት ሲነግረኝ፤ ‹የሱማሌ ተራ ልጅ ነኝ› በማለቴ ምክንያት ‹አንተ ማነህ ብሔር የለኝም የምትል?› ተብየ ነበር መጀመሪያ የተደበደብኩት፡፡ዞላ ከ40 እና 50 ዓመታት በፊት ሰዎች ‹ብሔሬ እንትን ነው› በማለታቸው ይሰቃዩ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ‹ዜግነት እንጅ ብሔር የለኝም›ማለት የሚያስገርፍ ሀጢያት ሁኗል›› አለኝ፡፡ ተከዝን፡፡ አቅማችን ‹ሕምምም› ማለት ብቻ ነበርና ‹ሕምምም› ከማለት ውጭ አማራጭአልነበረንም፡፡ መሬት በፀሃይ ዙሪያ ትሽከረከራለች ማለትም ያስገርፋል፡፡ ፀሃይ በመሬት ዙሪያ ትሽከረከራለች ማለትም ያስገርፋል፡፡‹ሕምምም›፡፡ ከአቤላ ጋር ብዙ ትካዜዎችን አሳልፈናል፡፡
ሌላ አንድ ቀን ደግሞ እስር ቤት ካገናኝናቸው በጣም ብዙ ሰዎች አንዱ ወዳጃችን ‹ገ› እኔና አቤላወዳለንበት መጣና ‹ክሳችሁ ምንድን ነው› ብሎ ጠየቀን፡፡እኛም ‹ሽብርተኝነት› አልነው፡፡ እሱም ትንሽ ደንገጥ በማለት ‹እንዴ ኢትዮጵያዊያንአይደላችሁም እንዴ› አለን፡፡ ‹ኧረ ኢትዮጵያዊያን ነን› አልነውእየሳቅን፡፡ ‹አይዋ! ብረት (መሳሪያ ማለቱ ነው) እና ፌፍ - ዎን (የቦምብ አይነት ነው) ተይዞባችኋል ማለት ነው?› አለን፡፡በፍፁም! እኛ (አቤላም እኔም) የታሰርነው ከቢሯችን ከስራ ላይ ተይዘን እንደሆነ ነገርነው - ለየዋኹ ‹ገ›፡፡ እሱም በጣም ተገርሞታዲያ ‹በሽብርተኝነት› እንዴት ተከሰሳችሁ› ሲለን ሳቃችን መቆጣጠር አልቻልንም ነበር፡፡ ሳቅን፡፡ ከአቤላ ጋር በእውነት ብዙ ሳቆችንተካፍለናል፡፡ በሳቅ ሆዳችን ታሟል፡፡
Frank MacCourtን አንብበን በሳቅ ጠሽ ብለናል፣ Robert Fiskን አንብበን ስለ ዓለምብዙ አውርተናል፣ Tariq Ramadanን አንበብን በለውጥ ሰባክዎች ቀንተናል…፡፡ ብቻ አብረን ያሳለፍናት እጅግ በጣም አጭር አንድዓመት የምታስቀና ነበረች፡፡
ብዙ ጠያቂዎቻችን ሊጠይቁን ይመጡና ጓደኝነት ማለት ‹ታቦት አብሮ ማንገስን› አልያም ‹ሶላት አብሮመስገድ› ይመስል ሃይማኖት እያነሱ ‹እንዴት ተመቻችታችሁ ትኖራላችሁ› አይነት ነገር ሲሉን ብዙ እንገረም ነበር፡፡ ጓደኝነት እኮበጣም ትልቅ ነገር ነው፡፡ ከአንድ የመሰሎች ጎራ ወደ ሌላው የሚያሸጋግር ድልድይ!
ሰዎች ያለፍንበት ከአንድ ዓመት የሚበልጥ አስቸጋሪ ጊዜ (እነ አቤል አሁን ያሉበት) ብዙ የሚያበሳጨንይመስላቸው ይሆናል፣ በፍጹም፡፡ አቤላ ፍ/ቤቱን ተዳፍረሃል ተብሎ ቅጣት በተወሰነበት ጊዜ እየሳቀ መጥቶ ‹3 ዳገት ተለመጥኩ›(በእስር ቤት ቋንቋ ‹3 ዓመት ተፈረደብኝ› እንደማለት ነው) ነበር ያለን፡፡ እኛም ቀልድ መሆኑን ተረድተን ወደ ብስጭትና ቁጭትአልገባንም፣ ይልቁን ስለ Freedom of speech in the court of law እያነሳን ተወያየን እንጂ፡፡ ምንም እንኳንታላቁ ዳኛ Justice Holmes “The court is not a market of ideas” ቢሉም ከእርሳቸው ተከትለው የመጡትዳኞች ደግሞ “A judge should show a higher moral character which refuse to be offendedin every statements” እያልን ነበር የምንሳሳቀው፡፡ በጣምየሚገርም ዓመት እኮ ነው አብረን ያሳለፍነው፡፡
አቤላ ወዳንተ ስመጣ፣
ይህችን አጭር ሜሞ ባልተመቻቸ ሁኔታ መንገድ ላይ ሁኜ ነው የምፅፍልህና በማጠሯ አትዘንብኝ እሺ፡፡
እንዲህ ነው፣
እኔም አንተም በማናዉቀው ምክንያት እኔ ተፈትቼ አንተና ወንድሞቻችን አሁንም አበሳችሁን እያያችሁነው፡፡ ለዚህ ልቤ ይደማል፡፡ ምን ላድርግ? ብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወ/መስቀል የተባሉ ሊቅ ስለ ወዳጅነት ምን አሉ?
“ወዳጅ ‘ማ ማለት አብሮ ባካኝእንጂ፤
እንደ አይን፣ እንደ ዦሮ፣ እንደ’ግርእንደ’ጅ፡፡
አቤላ እኔ አሁን አይንም፣ ዦሮም፣ እጅም፣ እግርም ላልሆንህ ካንተ ርቄያለሁ፡፡ ያማል፡፡ ግን ቢያንስሃሳቤ ውስጥ ትመላለሳለህ፡፡
በመጨረሻ ልደትህን ከአምናው ለየት የሚያደርገው አምና መሬት ላይ “እየተደቦቅን” (እየተኛን) ነበርያከበርነው ዘንድሮ ግን አልጋ ላይ ሁነህ ማክበርህ ነው፡፡ GTP -2ን ያስታውሷል፡፡
መልካም ልደት አቤላ!
ወንድምህ ዘላለም
Source: Zone9
No comments:
Post a Comment