Sunday, November 9, 2014

“ልማት ልማት” በሚለው ፕሮፓጋንዳ ደንዝዘን


አንዲት እናት ልጇን ለማስተኛት አሊያም መነጫነጩን እንዲተው የማደንዘዣ ዘዴ አላት፡፡እሽሩሩ….” የሚለውን ቃል መደጋገም ብቻ ነው፡፡ ልጇም በመጨረሻ ወደ ፀጥታው የእንቅልፍ አለም ይሄዳል፡፡እሹሩሩማለት ማንቃት አይደለም፡፡ የማስተኛ ማደንዘዣ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ስማችንን/ የምናውቀውን ሰው ስም ለተወሰነ ጊዜ በተደጋጋሚ ብንጠላው ከዚህ በፊት የሰጠነው የአይነት፣ መጠን ቀለምና የመሳሰሉት ተመሳስሎሾች ይጠፋብናል፡፡ ከዚያም ብሶ ራሳችንን/ የጠራነውን ሰው ወደ አለማወቅ የሚደርስ ብዥታ ይጠፋብናል፡፡ ከዚያም ብሶ ራሳችንን /የጠላነውን ሰው ወደ አለማወቅ የሚያደርስ ብዥታ ይፈጥርብናል፡፡ እንደነዝዛለን፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ሕዝብእሹሩሩ በመደጋገም ያደነዝዛል፡፡ በመደንዘዛችን ደግሞ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ አካባቢ እንዳለን ጭምር ይጠፋብናል፡፡ የቃሉ ድግግሞሽ የፈጠረብን ውዥንብር፣ በህልም አለም ስለሚያሰክረን ድህነት ላይ ሆነን ድህነትን እንረሳለን፡፡ አሊያም ድህነትንበልማትስም የበለጠ እንላመደዋለን፡፡ እየተለማመድነውም ነው፡፡የቸኮለ ሰው ሲቆም የሄደ ይመስለዋልበድህነት የኖረ ደግሞ ሲያወራ የበለፀገ ይመስለዋል፡፡ ጉንጭ አልፋ የማይላቀቀን የድህነት ኑሮ በልማታዊ በፕሮፓጋንዳ ድህነት ተጭኖን ደህነትን ረስተነዋል፡፡ባለፉት አምስት አመታት በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅና እጅግ የምንኮራበት ልማት ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ የዚህን ድል ታላቅነት አቃሎ ማየት ፍፁም አይችልም
“ስለልማት ሲነሳ ኢትዮጵያ እንደ አገር …. ለምሳሌ የሚጠቀስ እንኳን የሚኖርባት አገር ነበረች፡፡ ዛሬ ምሳሌዎችን ጠቅሰን አንዘልቀውም፡፡ እድገቱና ልማቱ ደግሞ ልዩ ባህሪ አለው” ይህ ዘዴ፣ ለነገሮች ያሉን የመጠን እና አይነት ግንዛቤን ያደበዝዛል፤ ያደነዝዛል፡፡ ለምሳሌ ደርቅና ርሃብ ማለት የ1966ቱ እና የ1977ቱ መጠን እና ዓይነት መሆን አለበት ብለን ካሰብን እውነትም የችጋርን አለንጋ ለምደናል፡፡ በችጋር ውስጥ ሆነን ችጋር ማለት ልክ እንደ 19977ቱ ሁሉ የሚላስ የሚቀመስ ሙሉ በሙሉ የሚጠፋበት ጊዜ እንጂ ቁርስ በልቶ ምሳ እና እራት ያለመድገም ወይም ያልተመጣጠነ ምግብ መጠረቅ ስለማይመስለን “ዲማ ከዚህ መንደር ይርቃል?” በማለት ባሰብነው ግዝፈት ልክ እንጤቃለን፡፡

ያን ባሰብኩ ቁጥር አለማወቅ ምን ጨለማ፣ ምን ከባድ፣ ምን የተምታታ ድፍን ያለ ነገር ነው? እላለሁ፡፡ እየራበን ከችጋር ላይ ቁመን፣ ችጋር እየጠበሰንልማት ልማትበሚለው ፕሮፓጋንዳ ደንዝዘን ርሃቡ ጥጋቡ፣ ደህነታችን ልማት እየመሰለን በቁማችን ሙተን ኖርን እንላለን!!


No comments: