በቃ ብለን በጋራ እንነሳ
(ብርቅአየሁ መቀጫ)
ኢትዮጵያ ሀገራችን ብዙ የሰዉ ጉልበት፣ የተለያየ የዐየር ፀባይ የአለዉ መልክዐ ምድር የሚገኝባት በመሆኗ በህዝብ የተመረጠ ዲሞክራሲየዊ መንግስት ተመስርቶ መልካም አስተዳደር ቢሰፍን በአጭር ጊዜ ዉሰጥ አለምን የሚያስደምም የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ እንኳን ለእራሷ ዜጎች ስራ መፍጠር ቀርቶ የሌላ ሀገር ዜጎችንም መርዳት የሚያስችል አቅም መገንባት እንደምትችል ኢትዮጵያን ተዘዋዉሮ ያያትና የሚያዉቃት ይመሰክራል።
ይሁን እንጂ ለእዚህ ባለመታደላችንና የህዝብ ፍቅርና የሀገር ክብር በዉስጣቸዉ ያልሰረፀ እና ህዝቡን በዘር በመከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማራ ጎጠኛ ቡድን በስልጣን ላይ በመዉጣቱ እና ህዝቡም ከአንዱ ክልል ወደ ሌላዉ ክልል ተዘዋዉሮ መስራት ካለመቻሉም በላይ በሙስና የተጨማለቀ አስተዳደር የሰፈነበት በመሆኑ ሀገሪቱና ህዝቧ በልመና ከመታወቅ አልፎ በየአረብ አገሩ ለግረድናና ለአሽከርነት ሀገሩን እየጣለ ስደተኛ በመሆኑ ለእንደዚህ አይነቱ ሰብዐዊነት ለማይሰማቸዉ መጫወቻ ለመሆን በቃን።
ገዥዎቻችንም ይህ በሳዑዲ አራቢያ እየደረሰ ያለዉ የግፍ ግፍ እንኳን ብሄራዊ ዉርደት በመሆኑ እነሱም የእዚህ ሀገር እና ህዝብ መሪዎች ናቸዉ በመባል ስለሚታወቁ ሌላዉ ቢቀር የእነሱዉ መሰል ጓደኞቻቸዉ እንኳን እንደሚስቁባቸዉ እና እንደሚንቋቸዉ መገንዘብ አልቻሉም። በስራቸዉም የአሉት ደጋፊና ኣጋሮቻቸዉም በሚጣልላቸዉ ፍርፋሪ ተደልለዉ ሆዳቸዉን በመሙላት ብቻ አሜን በማለት በማገልገል ላይ ናቸዉ።
በተለይ የተማሩ ናቸዉ የሚባሉት የገዥዉ ሀይል ደጋፊዎች በሚጣልላቸዉ ፍርፋሪ ተደልለዉ በገሀድ የሚያዩትን እና የሚሰሙትን ዕዉነት በማካድ ነጩን ጥቁር ነዉ ድንጋዩን ዳቦ ነዉ ሲሉ ስሰማ ምንኛ አዕምሮዬ ይደማል።
በተቃዋሚዉ ጎራ ያለዉም ቢሆን በጥቃቅን ልዩነቶች ተወጥሮ ከመናቆር አልፎ የጋራ ሀይሉን በማቀናጀት ለሀገር ትረጉም የሚስጥ ስራ መስራት መጀመር አለመቻሉ ምንኛ እርግማን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም።
የተወሰኑትም ቢሆኑ ከጎሳ ፖለቲካ ተላቀዉ ከወንድሞቻቸዉ ጋር ህብረት ፈጥረዉ በጋራ በመታገል ዲሞክራሲያዊ መንግስት ቢመሰረት ሁላችንም ተጠቃሚ እንደምንሆን እና ከዚህ ስቃይ እንደምንገላገል መገንዘብ ባለመቻላቸዉ የወገኖቻቸዉንና የሀገራቸዉን መከራና ስቃይ እያራዘሙት መሆኑን አልተገነዘቡትም።
አሁን እንኳን በሳዑዲ አራቢያ እየተፈጸመ የአለዉ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ እስራት፣ ግርፋት፣ በእየቤቱ በግዞት አስቀምጦ የባለጌ ጎረምሶች መጫወቻ ማድረግ በአጠቃላይ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ይፈፀማል ተብሎ ሊገመት የማይችል ኢሰብአዊ ድርጊት በጎሳና በቋንቋ ተለይቶ አለመሆኑ ትምህረት ሊሆነን በተገባ ነበር።
http://www.youtube.com/watch?v=sVH70NJcKjk
ማሰቢያ አዕምሮ ያለዉ የሰዉ ልጅ ይህ ሰሞነኛዉ በሳዑዲ አረቢያ በንፁሀን ወገኖቻችን ላይ የደረሰዉን እና እየደረሰ ያለዉን መከራና ስቃይ የተመለከተ የሚበላዉ ምግብ እየጣፈጠዉ በጉሮሮዉ አልፎ እንዴት ሊስማማዉ ይችላል? የሚለብሰዉስ ልብስ ሳይኮሰኩሰዉ እንዴት ተስማምቶት ሊለብሰዉ ይችላል? እንዴትስ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለማለትና በሰዉ መሀል አንገታችንን ቀና አድረገን ለመራመድ እንቸላለን?
በመሆኑም በሀገራቸዉ ምድር ሰርተዉ ኑሮአቸዉን ለማሸነፍ ባለመቻላቸዉ በሰዉ ሀገር ተሰደዉ የእራሳቸዉን እና የቤተሰቦቻቸዉን ህይወት ለመለወጥና የተሻለ ኑሮ ለመኖር ተመኝተዉ በተሰደዱት እህትና
ወንድሞቻችን ላይ እየደረሰ የአለዉን የመከራ ዉርጅብኝ በመመልከት በአገር ዉስጥም በዉጪ አገርም የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን በሙሉ አሁን እንኳን ዉርደት በቃ! ግፍ በቃ! ሰቆቃ በቃ! ብለን በቁጭትና እና ምሬት በተሞላበት ሁኔታ የጀመርነዉ እንቅስቃሴ የአንድ ሳምንት ጫጫታ ብቻ ከመሆን አልፎ የዉሰጥ ችግራችንን በሰከነ ሁኔታ በመወያየት እና በመፍታት ለአፈራሾች እና ለጸጉር ሰንጣቂዎች ጆሮአችንን ሳንሰጥ ወጣቶችና ሴቶችን ወደፊት በማስቀደም በጋራ እጅ ለእጅ ተያይዘን በመታገል ከዚህ ብሄራዊ ዉርደት ለመዉጣት እንቅስቃሴ መጀመር ይኖርብናል።
በስልጣን ላይ የአለዉም ሀይል ቢሆን ስልጣን ዘለአለማዊ አለመሆኑን ተረድተዉ ወደ ህሊናቸዉ በመመለስ ለብሔራዊ ዕርቅ እጃቸዉን በመዘርጋት የትግሉን ጊዜ እንዲያሳጥሩትና ከታሪክ ተጠያቂነት ለመዳን የበኩላቸዉን ድርሻ ቢወጡ ጠቃ
No comments:
Post a Comment