አንድነት የአገርን ጥቅምና ህልውና የሚመለከቱ ጉዳዮች
በተመለከተ በስትራቴጂ ሰነዱ ምን ይላል?
1. አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሁኔታ ግምገማ
1.1. የአገርን ጥቅምና ህልውና የሚመለከቱ ጉዳዮች
ሃገራችን ኢትዮጵያ በሰው ዘር መገኛነትዋ የምትታወቅ ሀገር ናት፡፡ በአካባብያችንም በስልጣኔ ማእከልነት ታሪክ
ከሚያውቃቸው ጥቂት አገሮችም አንዷ ነች፡፡ ኩሩና አገር ወዳድ ዜጎች፣ ነጻነትን ጠብቀው ያወረሱን ጀግኖች
አባቶችን ያበቀለች፣ በነጻነቷ፣ በመንፈሳዊ ሃብቷና uስልጣኔዋ የምትታወቅ' ልጆችዋ የሚኮሩባትና እሷን
ላለማስደፍር የሚሞቱላት አገር ነች፡፡
የቅርቡ የአገራችን ገጽታ ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል፡፡ ያለፉት ሰላሳና አርባ ዓመታት ታሪካችን ረሃብና ጦርነት
የነገሱበት ነበር፡፡ አገራችን አሁን ድረስ በዜጎችዋ ሰቆቃና የመብት ጥሰት በተደጋጋሚ የምትጠቀስ አገር ሆናለች፡፡
ድህነቱና የመብት ጥሰቱ ተጣምረው አገራችንን “ዜጎችዋ ሊኖሩባት የማይመርጡዋት” አገር እያሰኛት ነው፡፡
የተማሩት ዜጎች ካገር ለመውጣት አጋጣሚውን ባገኙ ቁጥር በየደረሱበት የውሃ ሽታ ሆነው ለመቅረት ይፈልጋሉ፡፡
ወይም በሃገር ውስጥ እያሉ እንደሌሉ ሆነው ይኖራሉ፡፡ የኮሌጅ ተማሪዎች ሳይቀሩ ትምህርታቸውን ቸርሰው ፤
በአገራቸው ለቁምነገር ከመብቃት ይልቅ ከኢትዮጵያ የሚወጡበትን አጋጣሚ የሚመርጡበት ሁኔታ ተከስቷል፡፡
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሕዝብ እድገት ካለባቸው አገራት አንዷ መሆንዋ ቢታወቅም በቅርቡ የወጣ ዘገባ
እንደሚያመለክተው ዜጎችዋ እንደፈለጉት አገራቸውን መልቀቅ ቢችሉና ወደፈለጉት አገር ለመግባት እድል
ቢሰጣቸው ሀገራችን ከፍተኛ የሕዝብ ፍልሰት ሊያጋጥማት እንደሚችል አመላክተዋል፡፡ የሕዝቧ ብዛት መሆን
ከሚገባው በ46% ሊቀንስ እንደሚችልም ተገምቷል ፡፡ አገሩን የሚለቀው የተማረውና አምራቹ ትኩስ ሃይል መሆኑ
ሲታሰብ፣ በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ምክንያት የሰው ዘር መገኛ የሆነችው አገራችን ሰው የሚሸሻት አገር
ትሆናለች ሲባል ዘራችንና ማንነታችን ሊጠፋ እንደሚችል አመልካች ሊሆን ይችላል፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ በግዙፍ ብዝሃ-ሕይወት ባለቤትነትዋ ትታወቃለች፡፡ ይህም ሆኖ አካባቢያችን ከፍተኛ የአየር
ንብረት መዛባት የሚታይበትና ውሃ የጠማው መሬትና ፈጣን የበረሃነት መስፋፋት የሚታይበት መሆኑ ሌላው
ኢትዮጵያውንን ሊያሳስበን የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ውሃችን እየቀነሰ፣ ጫካዎቻችን እያነሱ፣ አፈራችን እየተከላ፣
አካባቢያችን ህይወትን ለመሸከምና ለማቆየት ያለው እድል እየተመናመነ ሲሄድና አገራችን የብዝሃሕይወት ጸጋዋን
እያጣችና በዚያውም ሰውንም የማኖር ችሎታዋ እየተመናመነ እንደሚሄድ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡
አገራችን ውሃ በተጠማ በረሃማ አካባቢ የምትገኝ ብትሆንም በዚህ አካባቢ ብቸኛ የበርካታ ትላልቅ ወንዞች መነሻ/
አመንጪዋ አገር ናት፡፡ ይህ ዕውነታ በአንድ በኩል ለመኖርና ለማደግ እድል ያለን መሆኑን ሲያመለክት በሌላ በኩል
ደግሞ በዚህ ሳብያ ከጎረቤትና የአካባቢ አገራት ጋራ ትልቅ ፍጥጫ ውስጥ ሊያስገባን የሚችል መሆኑን መገንዘብ
ይኖርብናል፡፡ ከዚህ በመነሳት የአገራችን የመሬት ገጽታ፣ የአየር ንብረትና እደምታውን መመልከቱ ለሀገራችን
ፖለቲካ ትንተና አስፈላጊ ይሆናል፡፡
ወንዞቻችን የሚፈልቁት ከከፍተኛውና ደጋማው የአገሪቱ አካባቢ ነው፡፡ ይህ አካባቢ አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ
እጅጉን በተጣበበ ሁኔታ የሚኖርበት፣ በብዝሃ ህይወት ተሸካሚነቱም ከፍተኛ ድርሻ ያለው ነው፡፡ አብዛኛዎቹ
ወንዞች ደጋውን ለቀው ሜዳማውንና ቆላማውን የአገራችንን አካባቢ አቆራርጠው ድንበር ይሻገራሉ፡፡ ቆላማው
የአገራችን አካባቢ ውሃ የተጠማ ቢሆንም በጣም ለም አፈር ያለውና ለዘመናዊ ሰፋፊ እርሻ ምቹ ነው፡፡ ይህም ሆኖ
በአሁኑ ወቅት ለኑሮ አስቸጋሪ በመሆኑ በእንስሳት እርባታ የሚተዳደር አነስተኛ ሕዝብ የሚኖርበት አካባቢም ነው፡፡
ውሃውን በደጋው በመያዝ ለመለስተኛ መስኖዎችና ለሃይድሮ አሌክትሪክ ሃይል አመንጪነት መጠቀም የምንችልበት
ዕድል አለን፡፡ በቆላው አከባቢም እንደዚሁ ለሃይድሮ አሌክትሪክ ሃይል፤ ለሰፋፊ የመስኖ እርሻዎችና አግሮ
ኢንዱስትሪ የማዋል ተስፋውና እድሉ ያለን ቢሆንም የአገራችን የውስጥ ፖለቲካዊ ችግሮችና ከውሃ ጋር የተያያዘው
የአካባቢ አታካራ ትልቅ ፈተና እንደሚሆኑብን መገንዘብ ይገባል፡፡
እኛ የምንገኝበት ከአፍሪቃ ቀንድ ማዶ የባሕረ ሰላጤ (የጋልፍ) አገሮች ይገኛሉ፡፡ በመካከላችን የቀይ ባሕርና
የባብኤል መንደብ መተላለፍያ ውሃዎች ይገኛሉ፡፡ የገልፍ አካባቢ ትልቁ የነዳጅ አመንጪ አካባቢ መሆኑ
ይታወቃል፡፡ ከዚህ አካባቢ የሚቀዳው ነዳጅ፤ ከአውሮፓ ወደ ምስራቅ አፍሪቃና ኤስያም ሆነ ከምስራቅ አፍሪካና
እስያ ወደ አውሮፓ የሚደረገው የመርከብ ምልልስ በቀይ ባሕርና በባብኤል መንደብ ውሃዎች ያልፋሉ፡፡ ይህ
አካባቢ ቀውስ ውስጥ ቢገባ የዓለም ኢኮኖሚ”ና ህይወት” የሚያቆም አካባቢ እንደመሆኑ የዓለም ሃያላን ጥቅም
ያለበትና እጅጉን የእነሱን ትኩረት የሚስብ አካባቢ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ያለን ብንሆንም ግን
የባሕር በር የሌለን ብቸኛ አገር ነን፡፡ እነዚህ ዕውነታዎች ስለ እኛ ህልውናና ደህንነት የሚሉት ብዙ ነገር አላቸው፡፡
በዚህ አካባቢ በርካታ ትናንሽ አገሮች ባለ ወደብ የሆኑበት፣ ኢትዮጵያ ደግሞ ወደብ አልባ የሆነችበት ሁኔታ መኖሩ
አጅግ የተወሳሰበ ሁኔታ የመፍጠር አደጋ አለው፡፡ በዚህ አካባቢ የሚከሰት የአገሮች የጥቅም ግጭት የሚቀሰቅሰው
አምባጓሮ እኛንም ጎትቶ ችግር ውስጥ የማስገባት አደጋ አለው፡፡ ስለሆነም ሌሎች ጭረውት በሚነድ ሰደድ እሳት
ውስጥ እንዳንገባ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ የመሆኑን ያክል ጥቅማችን እንዳይነካብንም በትኩረትና በጥንቃቄ
መከታተል ይጠበቅብናል፡፡
የምንገኝበት የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ በድህነት፣ በበረሃማነትና በደፈረሰ ጸጥታው የሚታወቅ ቢሆንም ትልቅ የነዳጅና
የማዕድን ይዞታ አለው ተብሎ የሚገመት አካባቢ ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው በርካታ ወንዞችና እጅግ ለም አፈር
ባለበት በዚህ አካባቢ አገራችን ኢትዮጵያ ቁልፍ ስፍራ ያላት መሆኑም አንድና ሁለት የለውም፡፡ ምክንያቱም
ሌላውን እምቅ ሃብትዋን አቆይተን ለም መሬትዋንና የውሃ ሃብትዋን ብቻ ለማቀናጀት ብነችል ትልቅ የኢኮኖሚ
ኃይል የመሆን ዕድል አላት፡፡ በሌላ በኩል ይህ እውን እንዳይሆን የሚፈልጉ ወገኖች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ በዚህ
ሁኔታ እነዚህ ትናንሽ ባለወደብ አገሮች የሚኖራቸው ሚና እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ አማራጮቹን ስንመለከት እነዚህ
አገሮች አንድም የኢትዮጵያ እሴቶች የመጀመርያ ደረጃ ባለመብት ነን በማለት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ኢትዮጵያ
ሰላምና ልማት እንድታገኝ፤ እነሱም ከዚህ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራሉ፡፡ አልያም ጊዚያዊ ጥቅሞችን በማገትና
ኢትዮጵያን መተንፈሻ በማሳጣት፤ እድገትዋን በማገትና ሰላምዋን በማወክ የበለጠ እንጠቀማለን ከሚሉ ሃይሎች ጋር
ይሰለፉና በኢትዮጵያ ላይ ችግር መፍጠርን እንደዋነኛ ተልእኮ ይወስዳሉ፡፡ የኢትዮጵያ የባህር በር መብት ጥያቄ እና
የአካባቢው ልማትና መረጋጋት እጅግ የተሳሰሩ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸውም ይኸው እውነታ ነው፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች አገር የመሆንዋን ያክል የተለያዩ የሃይማኖት እምነት ተከታዮች
የሚኖሩባት ሃገር ነች፡፡ ፖለቲካችን እነዚህን እውነታዎች የሚገነዘብ እና መቻቻልና እኩልነትን የሚቀበል እንዲሆን
ማድረጉ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በሌላ ወገን መረን የለቀቀ የብሄርና የሃይማኖት አክራሪነት የአገራችንን ፖለቲካ
እንዳያናጋብን በጥንቃቄና በብስለት መጓዝ ግድ ይለናል፡፡ ከፍ ብሎ ከተገለጸው የውሃ ፖለቲካና በአካባቢያችን
እየታየ ካለው ሴኩላሪዝምን የመጋፋት አዝማሚያ አንፃር ሲታይ ብዙIነታችን የሚፈጥራቸው አንዳንድ ቅራኔዎች
የሚስተናገዱበት ሁኔታ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ይሆናል፡፡
በዚህ የተወሳሰበ ከባቢ ውስጥ መገኘታችን ሳያንስ የአገራችን የውስጥ ፖለቲካም እጅጉን የተወሳሰበ ነው፡፡ በስልጣን
ላይ ያለው መንግሥት (ፓርቲ) uውሃ ሃብት፣ uባሕር በር፣ uአገር ዳር ድንበር፣ uአገርና የሕዝቧ ደህንነትና
በመሳሰሉት መሰረታዊ የአገር ጥቅም ጥያቄዎች ላይ የተአማኒነት ችግር ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመላው
ኢትየጵያውያን ዘንድ ዕምነትና ተቀባይነት ያጣ ጠባብ ሕዝባዊ መሰረት ያለው አገዛዝ ነው፡፡ ሕዝባዊ መሰረቱ ደካማ
መሆኑን በመገንዘብ ስጋትና ጭንቀት ውስጥ የሚኖር እና ከዚህ መዳኛየ ጉልበትና አፈና ብቻ ነው ብሎ የተሳሳተ
አቋም የወሰደ አገዛዝ ነው ያለን፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ በዓለም በአምባገነናዊ አገዛዝ መዳፍ ስር ከሚገኙ አገሮች
ውስጥ 9ኛ ደረጃን በመያዝ በአምባገነንነት የምትገዛ አገር ናት፡፡ በዚህ የደረጃ ሰንጠረዥ የአንደኝነት ደረጃውን
የወሰደችው ሰሜን ኮርያ ስትሆን ኤርትራ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀም»ለች፡፡
ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያውያን የአገራችን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ/ግልጽ ሀብትነት እንዲለወጥ ማድረግ
ይጠበቅብናል፡፡ ይህንን ለማሳካት መጀመርያ የአገራችንን ውስጣዊ ሁኔታ ማስተካከል ፈፅሞ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ
አይደለም፡፡

No comments:
Post a Comment