Thursday, December 12, 2013

የማይከሰሱ ወንጀለኞች

የማይከሰሱ ወንጀለኞች

በወያኔ የአገዛዝ ዘመን ሀገራቸን ላይ እየታየ ላለው  የፓለቲካ አለመረጋጋትም  ሆነ ከጊዜ ወደጊዜ አየተባባሰ የመጣው የኢኮኖሚ ድቀት መባባስ ከሚጠቀሱት ዋነኛ ምክንያቶች ወስጥ  አንዱ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ መሰፋፋት ነው ።
  ሀገራቸን ላይ አየታየ ያለው የኑሮ ገጽታ ሰፊ ለዩነት መፈጠር ፤የፍት ህ መዛባት ፣ ወነጀል መስፋፋት ፣ዜጎች አንደሰው የመመኖር ህልውናቸው  በአስከፊ ሁኔታ ማሽቆልቆል  እና የመሳሰሉ ችግሮች መስፋፋት ዋነኛ ምክኒያት  ነው ።
   በሙስና የተጨማለቁ መሪዎች በዘረጉት ብልሹ ኣስተዳደር የህዝብ መገልገያ  ሆኑ  ተቋማተን ጨምሮ አያንዳንዱ ደርጀቶች ፣ ቢሮዎች  ውስጥ ህጋዊ አገልገሎት ለማግኘት  መስተናገድ የዜግነት መብት መሆኑ ቀርቶ  ግዴታ አስኪመስል ጉቦ አንዲሰጡ በግልጽ ይጠይቃሉ ።     
  የፍትህ አካላት ከተራው ፓሊስ ጀምሮ አስከ ከፍተኛ ሀላፊዎች በር ለማለፍ ገንዘብ ከዜጎች መብት ይቀድሟል የባለጉዳዩ አጅ ካልተፈታ  ጉዳዮን ለማስፈጸም ማሰብ ቀላል አይደለም ያለ አገባብ በመመላለስ የመጉላላት ቸግር ያጋጥማል 
  ፍርድ ቤት ለከሳሽም ሆነ ተከሳሽ ባለጉዳይ ከተጻፈው ህግ ይልቅ ባለጉዳዩ ባለው ስልጣን ወይም ግለሰቡ ባቀረቡት የጉቦ መጠን ይዳኛሉ ብዙ ወንጀለኞች ከፍርድ ነጽ የደረጋሉ ፣ በአንጻሩ ደሞ ንጹሃን ጉቦ ባለመስጠታቸው (አቅማቸው ባለመፍቀዱ) ፍት ህ ተጓድሎባቸዋል ፤ ዳኞች ፣ ኣቃቤህጎች አና ጠበቃዎች ጉቦ በመቀበል  ፍርድ ያዛባሉ ።
የጤና ተቋማተም ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ከሚፈጸምባቸው ቦታዎች ወስጥ ይጠቀሳሉ፤ ከክፍያ ነጻ የሆኑ   መድሀኒቶች ለህሙማን በሽያጭ ይቀርባሉ ፤ የቅርብ ክትትል  የሚያስፈልጋቸው ሀሙማን ለሰራተኞች የሚከፍሉት  ጉቦ በማጣታቸው ብቻ በቂ ህክምና ባለማግኘታቸው ለሞት ያዳረጋሉ ።
በእምነት ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት ፣ በሰራተኛና ኣሰሪ ቅጥር ሂደት ፣ጉምሩክ ባለስልጣን መ`\ ቤት ፣ የጸረ ሙሰና መስሪያ ቤቱን ጨምሮ እያንዳንዱ የመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ በግልጽ እና በአስከፊ ሁኔታ ሙስና አየተስፋፋ ይገኛል ።
  የመቅጫ ህጉ የማይመለከታቸው ይመስል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት (ህውሀት አባላት) ስልጣንን ያለ አገባብ በመተቀም የሀገሪቱን ገንዘብ ወደ ግል ካዝናቸው ሲያስገቡ ፣ የመንግስት ንብረት የሆኑ ትልልቅ ተቋማትን ወደግለሰብ ነብረትነት ሲያዞሩ፣ የውጭ ንግድ እና ምንዛሬው በጥቂት የህውሀት አባላት እጅ ቁጥጥር   ውስጥ ሲወድቅ የሀገሪቱን መሬት ለጎረቤት ሀገር በመጽሸጥ የወንጀል ስራ ላይ ሲሰማሩ፣ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በጥቂት ባለስልጥናት እጅ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ሳለ (በ2013  በወጣው መረጃ መሰረት ሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ባለሀብቶች የመጀመሪያውን 10 ደረጃ የያዙት የህውሀት አባላት አና ከፍተኛ ባለስልጣናት መሆናቸው ይታወቃል ) ፤ የህ የሙስና መረብ ሁሉንም ባለስልጣናት ያስተሳሰረ በመሁኑ   የክስ ሂደቱ ተገባራዊ እንዳይሆን ብሎም ሀገሪቱም ከገባችበት ዘቅት አንዳትወጣ እንቅፋት ሆኖኣል።
   በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል ተብለው የቀረቡት የህውሀት አባል ባለስልጣናት ጉዳይ  (ሌባ ሲሰርቅ ተስማምቶ ሲካፈል ይጣላል ) እንዲሉ የስልጣን ክፍፍል በፈጠረው ችግር ጠልፎ መጣያ የባለስልጣናቱ የግል ጸብ እንጂ ህግን ለማስፈጸም የተደረገ ሂደት አይደለም ፤ እውነት ሙስናን ለመዋጋት ቅርንጫፎቹን ሳይሆን ግንዱ የሆነውን (የህውሀት ባለስልጣናትን አና ስር አቱን ) ማስወገድ ብቻ ነው መፍሄው ።
source 

No comments: