Thursday, July 9, 2015

በኢንሳና በሃኪንግ ቲም መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር መረጃዎች አጋለጡ



ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሃኪንግ ቲም ለተባለ ኩባንያ 1 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል የስለላ መሳሪያዎችን የገዛው በአብዛኛው በህወሃት አባላት የሚመራው የደህንነት መስሪያ ቤት፣ ከኩባንያው ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቶ እንደነበርና ውዝግቡ ሳይፈታ መረጃው ይፋ መሆኑን ለህዝብ ይፋ ከሆነው መረጃ ለመረዳት ተችሎአል። ቢኒያም ተወልደ በተባለ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ምሩቅ በኩል ግንኙነቱን የሚያደርገው የኢትዮጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት ፣ የስለላ ሶፍት ዌሮችን ለማግኘት 1 ሚሊዮን ዶላር ከከፈለ በሁዋላ፣ የሶፍትዌሩ የጊዜ ገደብ በማለቁ ፣ በኩባንያውና በወኪሉ ቢኒያም መካከል ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር። የሃኪንግ ቲሙ ባለስልጣኖች በውስጥ በተጸጻፉዋቸው ኢሜሎች ቢኒያምን " ትእቢተኛ" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ ቢኒያም በበኩሉ የባለይ አለቆቹ አዲስ ሶፍትዌር ካልተሰጣቸው እንደሚቆጡት ገልጾላቸዋል። የሃኪንግ ቲም አባላት በበኩላቸው አዲስ ሶፍትዌር ለመስጠት ዝግጁ ቢሆኑም ፣ ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት በቅድሚያ ስልጠና እንደሚያስፈልግ ከቢኒያም ተወልደ ጋር ባደረጉት የኢሜል ልውውጥ ገልጸዋል። በሃኪንግ ቲምና በደህንነት መስሪያ ቤቱ መካከል አዲስ ውል ለመዋዋል የኢሜል መልእከቶች በሚለዋወጡበት ወቅት፣ የሃኪንግ ቲም መረጃዎች ባልታወቁ መረጃ በርባሪዎች ይፋ ሆኗል። እስከ ሰኔ 15 ድረስ በኢህአዴግ የደህንነት መስሪያ ቤት እና በሃኪንግ ቲም መካከል የኮንትራት ስምምነት አለመፈረሙ ከኢሜል ልውውጡ ለማየት ይቻላል። ከመረጃ ለውውጡ ለመረዳት እንደሚቻለው ሃኪንግ ቲም መረጃዎችን ለመስረቅ የሚውለውን ሶፍት ዌር ከመሸጥ ውጭ በራሱ ስለላ አያደርግም።

Source: ethsat

No comments: