Thursday, July 16, 2015

“እስቲ አንነጋገር የማስረጃን ነገር 1 “



ባለፉት 14 ወራት መንግሰት በቂ ማስረጃ አለኝ እያለ ተከሳሾች ደሞ “እንኳን የሽብርተኛነት ድርጊት ወንጀልን አንዳች ደምብ መተላለፍ እንኳን የሚያስረዳ ወንጀል የለም” እያሉ ሂደቱ ቀጥሏል ፡፡ ብይኑ በመጪው ሰኞ ሃምሌ 13 ዓ/ም ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ ከመጪው ብይን አስቀድሞ ቀረቡትን የማስረጃዎች ምንነት ማየትም ጉዳዩን ግልጽ ያደርገዋል፡፡ 
ብርጋዴር ጀነራል ታጠቅ ታደሰ “ የማስረጃ መሰረተ ሃሳቦች በሚለው መጽሃፋቸው የማስረጃን ምንነት ሲገልጹ “ ማስረጃ ማለት የአንድን አከራካሪ ነገር መኖር ወይም አለመኖር የዳኛው አእምሮ አንዲያምን የሚያደርግ ነገር ነው በአጭሩ ዳኛው ከፊቱ የቀረበለትን ጥያቄ እውነት ወይም ሃሰት መሆኑን ለመረዳትና ከውሳኔ ላይ ለመድረስ ግምት ለመውሰድ አእምሮው የሚመራበትን ነገር የያዘ ነው፡፡ ይህም ነበሰው ምስክርነት እና በልዬ አዋቂ ምስክርነት የሚሰጥ ማስረጃ፣ በሰነድ ማረጋገጫ የሚሰድ ማስረጃ እንዲሁም ተጨባጭ ወይም በኤግዚቢትንት የሚሰጥ ማስረጃን ከነአቀራረቡ ያለውን አሰራር የያዘ ነው” በማለት ነው ፡፡ የ5ስቱን ክሳቸው የቀጠለው ጦማርያን ጉዳይም ከዚህ ልዩ ትርጉም አንጻር መመልከት ጉዳዩን የበለጠ ለመረዳት ይጠቅማልና ጉዳዬን እንደሚከተለው እንመልከተው ፡፡ 
ከሳሽ በተከሳሾች ላይ ያቀረባቸው ማስረጃዎች ሙሉ ለሙሉ የሰነድ ማስረጃዎችን ብቻ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህም ማለት በከሳሾች የቀረቡት ሁሉም የሰው ምስክሮች ( 22 ምስክሮች) የሰነድ ማስረጃው በፍተሻ ሲገኝ የተመለከቱ በመሆን የሰነድ ማስረጃውን እውነተኛነት ለማረጋገጥ የተገኙ ናቸው ፡፡ በፍተሻ ወቅት የተገኙ ላፕቶፕ ስልኮች ሲዲዎች ፍላሽና ሃርድ ዲስኮች በአጠቃላይ ከሳሽ ላቀረባቸው ሰነድ ማስረጃዎች ማረጋገጫ በመሆን የቀረቡ ናቸው፡፡ በተከሳሾች ላይ የተመሰረተው ክስ ያስረዳል በማለት የቀረቡት ሁሉም ማስረጃዎች የሰነድ ማስረጃዎች ብቻ ናቸው ማለት ነው፡፡ በአስገራሚ ሁኔታ “ ማስረጃ” ይሆናሉ ተብለው ቀረቡት ሰነዶች ተከሳሾቹ መሆናቸው ተከሳሾቹ መሆናቸው ታምኖ እያለ ምስክር ሊኖር የሚገባው በአንድ ወገን የተካደን ጉዳይ ለማስረዳት ቢሆንም ለክርክሩ አስፈላጊነት የሌላቸው ታዛቢዎች ከሳሽ አቅርቦ ለወራት የፍትህ ሂደቱን ጊዜ በልቷል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሚሰጠው ቀረበለትን “የሰነድ ማስረጃ “ ብቻ መሰረት አድርጎ ነው ማለት ነው ፡፡
1. “Human rights underpin the aspiration to a world in which every man, woman, and child lives free from hunger and protected from oppression, violence, and discrimination, with the benefits of housing, health care, education, and opportunity.” 
Navi Pillay, የቀድሞው United Nations High Commissioner for 
Human Rights ከፃፉት የተወሰደ
2. “ስሜ በፍቃዱ ሃይሉ ነው፡፡ አዲሱ አመት ሲጠባ በአዲስ መንፈስ አዲስ ህልም ለአገሬ ማለም እና የነበረኝንም ማጠናከር እፈልጋለሁ፡፡ ኢትዬጵያችን የብሄር የሃይማኖት የሃብት የትምህርት የፓለቲካ አመለካከት እና ሌሎችም ልዬነቶቻችን አብሮነታችንን የማያደናቅፉባት ከነልዬነታችን በጋራ ለታላቅነት የምንጠቀምባት ፣ ለሁላችንም እኩል እድል እና ተጠቃሚነት የሚቀርብባት፣ ሁላችንም እንደችሎታችን ለጋራ ደህንነታችን ፣ ነጻነታችን እና ብልጽግናችን የምንሰራባት ብቻ ሳይሆን በጋራ ስኬታማ የምንሆንባት ፣ እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሚያፈቅራት ኢትዮጵያ አንድትሆን እመኛለሁ ይህ የእኔ ኢትዬጵያዊ ህልም ነው፡፡ “ 
በፍቃዱ ሃይሉ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ቡድን ከነሃሴ 30/2005 - ጷጉሜ 02/2005 ድረስ ካደረገው ኢትዮጵያ ህልም በይነ መረብ ዘመቻ ላይ ከጻፈው የተወሰደ 
3. Micro – Economics Theory 11
Chapter 4 
Factor market and income distribution 
4.1 Perfectly competitive factor market 
4.1.1 Demand for factors of production
Demand for single variable factor 
Assumptions 
a. A farm produce a single good in a PCM 
b. A farm objective is profit maximization
c. Production and good requires one variable factor , the price of each constant 
d. Technology is fixed 
VMPc= PA * MPP
VMPc= Value of marginal production 
PCM= perfectly competitive market 
MPP= Marginal Physical production 
ከአጥናፍ ብርሃኔ ማክሮ ኢኮኖሚክስ ደብተር የተወሰደ
4. “በአገራችን ሚዲያ መልክአምድር ላይ ሚገኙት እድሜ ጠገብና ሰፊ ጂኦግራፊያዊ ተደራሽነት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን ኢቴቪ፣የኢትዬጲያ ሬዲዬ እና አዲስ ዘመን ጨምሮ በየክልሉ የሚገኙትን መገናኛ ብዙሃን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው መንግስት ነው ፡፡ ይህም በአዋጅ የተረጋገጠ መብቱ ነው፡፡ ነገር ግን ግለሰብም ሆነ መንግሰት በባለቤትነት የሚያስተዳድረው የትኛውም መገናኛ ብዙሃን ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ትርፉን ከማጋበሻነት በተጨማሪ የባለቤቱን የፓለቲካ አቋም ማራመጃ ለመሆን ምቹ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ መገናኛ ብዙሃንን ፓለቲካዊ ኢኮኖሚ ( political economy of the mass media ) በመተንተን እውቅ የሆኑት ናሆም ቾምስኪን እና ኤድዋርድ ሃርማን በ1988 “ይሁንታን ማምረት”( manufacturing consent , the political economy of the mass media ) በሚል ርእስ ካሳተሙት መጽሃፍ የፕሮፓጋንዳ ሞዴል የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ሃገራችን የመገናኛ ብዙሃን መልከአምድርና ፓለቲካዊ ኢኮኖሚ በደምብ አድምቶ ስለሚገልጽልኝ ዋቢ አደርጌ ከዚህ አንደሚከተለው እጠቅሰዋለሁ፡፡ “
እንዳልካቸው ሃይለሚካኤል በነሃሴ 2005 በዞን9 ጦማር ላይ ልማታዊ ጋዜጠኝነት ወይስ ይሁንታን ማምረት በሚል ከጻፈው ጽሁፍ የተወሰደ
ከዚህ በላይ ከተራ ቁጥር 1 – 4 ላይ የተጠቀሱት ጉዳዬች የሚያነብ ሰው አንድ ሚያደርጋቸው ነገር ምንድነው ብሎ መጠየቁ አይቀርም ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የቀድሞው ከፍተኛ ኮሚሽነር ወይዘሮ ናቬይ ፒሌይ ከሙሁሩ ናሆም ቾምስኪ ጋር አንድ ላይ መጠቀሳቸው ግራ የሚያጋባ ሊመስል ይችላል፡፡ ጉዳዩ እነዲህ ነው ከተራ 1-4 ድረስ ተጠቀሱት ጽሁፎች ከሳሽ የፌደራል አቃቤ ህግ በቀን 08/11/2006 ጽፎ በሰባት የዞን9 ጦማሪዎች እና በሶስት ጋዜጠኞች ላይ ባቀረበው ክስ ( አሁን ክሱ በአምስት ጦማርያን ላይ ብቻ ሆኗል) በማስረጃነት ካቀረባቸው ሰነዶች የተወሰዱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰነዶች ያስረዱታል የተባለው ወንጀል ድርጊት ደግሞ
“ ……የፓለቲካ የሃይማኖታዊ ወይም የአይዲዬሎጂ አላማን ለማራመድ በማሰብ በመንግሰት ላይ ተጽእኖ ለማሳደር ህብረተሰቡን ወይም የህብረተሰቡን ክፍል ለማስፈራራት ወይም አገሪቱን መሰረታዊ ፓለቲካዊ ህገ መንግስታዊ ኢኮኖሚያዊ ወይም ማህበራዊ ተቋማትን ለማናጋት ወይም ለማፍረስ ( በማሰብ) ህብረተሰቡን ወይም የህብረተሰቡን ከፍል ደህንነት ወይም ጤና ለከፍተኛ አደጋ ለማጋለጥ ( ማቀድ መዘጋጀት ማሴር ማነሳሳትና መሞከር) …….” ነው ፡፡
ይህ ብዙ ሰዎች ቀልድ ሊመስል ይችላል ፣ ነገር ግን በእውነት የሽብርተኛነትን ወንጀል ለማስረዳት በ5 የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ላይ ቀረቡ ማስረጃዎች ናቸው( ክሱ ከመቋረጡ አስቀድሞ የተከሳሾች ቁጥር 10 አንደነበር ይታወሳል)፡፡ እነዚህ ማስረጃዎች በዞን 9 የተሰሩ አራቱም የበይነ መረብ ዘመቻዎች የማስረጃው አካል ሆነው ቀርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ እነዚህ ሰነዶች ለሽብር ክስ መዘጋጀት ማሴር እና ማቀድ መሆን አለመሆናቸውን ይመረምራል፡፡

Source: Zone9

No comments: