Thursday, July 16, 2015

"እስቲ አንነጋገር የማስረጃን ነገር 2''

“በጻፉት ጽሁፍ አልከሰስናቸውም “
ተከሳሾች በታሰሩበት ወቅት የኢትዮጲያ መንግሰትየመናገር ነጻነትን ለመገደብ የወሰደው እርምጃ አንደሆነ በተለያዬ አካላት ትችት ሲቀርብበት የተለመደ መልሱን “ በጻፉት ጽሁፍ አልከሰስናቸው”በማለት በተደጋጋሚ መልስ ሲሰጥ አንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህ መንግስት ገለጻ ግን ቆየው ተከሳሾች ላይ መደበኛ ክስ እስኪመሰረትድረስ ብቻ ነበር ፡፡ ከግማሽ በላይ የሆኑት አንደማስረጃ የቀረቡት የተከሳሾች የግል ጦማርና በዞን9 ጦማር ላይ እና ፌስቡክ ላይየተጻፉ ጽሁፎች ናቸው ፡፡
በተከሳሾች የሽብር ክስ ላይ በማስረጃነት ከቀረቡትጽሁፎች መካከል ጥቂቹን ለአብነት ያህል ብንጠቅስ
ልማታዊ ጋዜጠኝነት ወይስ ይሁንታን ማምረት እንዴት እደመጥ  የመለስ ውርስና ራዕይ ፣ ነጻነትና ዳቦ ሰብዓዊ መብቶች በሕገ-መንግስትና መንግስት  ግልፅ ደብዳቤ ለጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ  ሕግ ምርኩዝ ወይስ ዱላ   መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ መፅሄቶች  አራማጅነት በኢትዮጵያ ፣  የእነርሱ እና የእኛ ሕዳሴ ፣  ልማት ሲሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ልማ አለ ማለታቸው ነውን የ1966 ዓ.ም አብዮት እና የሲቪል ማኅበራት ሚና  የሥርዓትና ሐይማኖት ለውጥ  ኬንያ ከነፃነት እስከ ምርጫ እና በሀገሩ ጉዳይ የሚያገባው ትውልድ ፍለጋ ……”
ከላይ ለአብነት የጠቀስናቸው ሃያ ጽሁፎች በዞን9ጦማር ላይ ወጥተው መንግስት "በጻፉት ጽሁፍ አልከሰስናቸውም" በማለት ላቀረበው ክስ በዋነኛ ማስረጃነት ያቀረባቸው ጽሁፎች ናቸው፡፡እንግዲህ እነዚህና መሰል ጽሁፎች ናቸው የህብረተሰቡን ደህንነትና ጤና አደጋ ላይ ጥለዋል ተብለው የሽብርተኝነት ድርጊትን ለማስረዳትየቀረቡት፡፡ ጽሁፎቹን ያነበበ ማንኛውም ሰው አንኳን ማህበረሰቡን ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ቀርቶ የአንድን ግለሰብ መብት አንኳንየሚጥሱ እንዳልሆነ ማንም ያነበበ ሰው ሊረዳቸው ይችላል፡፡
“የሚያስደነግጡ ማስረጃዎች”
ከላይ ያሉ ጽሁፎችን አንብቦ ለተገረመ ሰው በቀሪዎቹማስረጃዎች የበለጠ ሊደነግጥ ይችላል፡፡
1.     “Ethiopiathousands protest political repression – June 02/2013 Associated Press (AP) byKirubel Tadesse
2.    የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ፓርቲውንጸረ ህገ መንግሰታዊ እንቅስቃሴ ያጋለጠ ነው- ኢህአዴግ ግንቦት 26.2005 ( ፋና ብሮድ ካስቲን ኮርፓሬሽን ኤፍ ቢሲ) ጥላሁንጎሳ
3.    Thousands marchfor rights in rare Ethiopia protest June 02/2013 – Reutors Aron Masho
4.    Ethiopiathousands stepped anti government protest June 02/ 2013 Posted by Daniel Brhane ( by Marthe vanaderwolf)
5.    ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍግንቦት 25 /2005 አም በአዲስ አበባ ተካሄደ ( ERTA reporter Kebede Kassa)
6.    Thousands ofEthiopian Opposition activily demonstrate in Addis Ababa June 02/2013 VOA byPeter Hailen
7.    Beware of wishfulthinking one swallow does not make a swimmer – June 03/ 2013 Tigray onlineDilwenberu Nega
8.    ሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፍአካሄደ ጁን 02/2013 ሶደሬ ዜና
እነዚህከላይ የጠቀስናቸው የዜና ርእሶች ጽሁፎች በሙሉ ተከሳሾች ላይ የተገኙ ማስረጃዎች ናቸው በመባል እንግሊዘኛዎቹ በ56 ገጽ ተተርጉመውተከሳሾች ላይ ማስረጃ ሆነው ቀርበዋል፡፡  የመንግሰት የመገናኛ ብዙሃን ( ኢቢሲ፣ ፋና …)ሳይቀር ያወጧቸውን ዜናዎች ሳይቀር የሽብር ህግ ያስረዳሉተብሎ የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ እነዚህን ሰነዶች ይመረምራል፡፡

Source: Zone9

No comments: