Friday, July 17, 2015

“እስቲ አንነጋገር የማስረጃን ነገር 4"

ምሁራን በሰነድ ማስረጃው
እስቲ ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ግለሰቦች ስሞች ይመልከቱ
“Amartya Sen ,Richard Nixon , Edward Hermon , Noam Chomsky, Navi Pillay , Franz Kafka, Carl Bernstein, Bob Woodward , Eleanor Roosevelt, Kenneth Roth, Hina Jilani, Michael D. Watkins, John wade , Jay Heinrichs, Bernard Mayer , Terie S Skjerdal” ከላይ የተጠቀሱት ምሁራን የሃገር መሪዎች የህግ ባለሞያዎች ጋዜጠኞች የስነጽሁፍ ሰዎች አንድ የሚያደርጋቸው ብቸኛ ነገር ቢኖር በክሱ ማስረጃዎች ላይ የሽብርተኛነት ድርጊትን ለማስረዳት አንድ ላይ መቅረባቸው ነው፡፡
“Where after all do universal human rights begin? In small place close to home” ብለው ወይዘሮ ኢላኖር ሩዝቬልት መናገራቸው በክሱ ማስረጃነት የቀረበ ጉዳይ ነው ፡፡ “Thank you for arguing what Aristotle, Eminem and Homer Simpson can teach us about the art of persuasion” በማለት ጄ ሄንሪች የጻፉት መጽሃፍ በማስረጃው ዝርዝር ውስጥ ያገኛል፡፡ ይህ ቀልድ አይደለም “There had never been a famine in any country that has been a democracy with a relatively free press” በማለት ፕሮፌሰር አማርተያ ሲን የጻፉትን የጻፉት ሃሳብ ተተርጉሞ ለክሱ የማስረጃነት ተያይዟል፡።
“Believing means liberating the indestructible element in one self or more accurately being indestructible or more accurately being “ በማለት ቼካዊው የስነጽሁፍ ሰው ፍራንስ ካፍካ የጻፈው ጽሁፍ እንደሃሳብ ማበልጸጊያ የተጻፈ ጽሁፍም በማስረጃነት ይገኛል፡፡
“All human beings are born free and equal in dignity and rights. They are endowed with reason and conscience and should act towards one another in a spirit of brotherhood." ብሎ አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ Universal Declaration of Human Rights (UDHR) በአንቀጽ አንድ ላይ የደነገገው ድንጋጌ ወንጀል ለመፈጸም በመዘጋጀት እና ማቀድን ለማስረዳት ከሰነድ ማስረጃዎቹ ተቀላቅሎ ይገኛል፡፡ እነዚህ ከላይ ለአብነት የጠቀስናቸው የማስረጃ ክፍሎች እንዲሁ በአጋጣሚ የተቀላቀሉ አይደሉም ፡፡ ይልቅም ፓሊስ የተከሳሾች ቤት እና ቢሮ እና መገልገያዎች መርምሮ ለክሱ አስፈላጊ ናቸው የሽብር ድርጊትን ያስረዱልኛል ብሎ በአማርኛ ቋንቋ ቃል በቃል አስተርጉሞ ለፍርድ ቤት ያቀረባቸው ናቸው፡፡ መቼም ከ Homer Simpson እስከ UDHR በስህተት የተካተቱ ሊመስለን ይችላል፡፡ ነገር ግን በፍርድ ቤቱ የስራ ቋንቋ ተተርጉመው መቅረባቸውን ስናይ ከሳሾች ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ከታላላቅ ምሁራን እስከ ካርቱን ፊልም ባህሪያት ድረስ መሆኑን እንረዳለን፡፡ ፍርድ ቤቱ ይህንን መርምሮ ለመወሰን ቀጠሮ ይዟል፡፡

Source: Zone9

No comments: