ደረጄ መላኩ
በያዝነው 2007 ዓ.ም በዚች ሀገር ላይ የንግግር ነፃነት (freedom of expression)፣ በነፃነት የመሰብሰብ መብት (free assembly)፣ የህግ የበላይነት (rule of law) እውን እንዲሆኑ፣ እንዲሁም በፖለቲካዊ አመለካከታቸውና መጤ እየተባሉ በርካታ ንፁሀን ዜጎች ዘብጥያ ሲወረወሩ አግብተው ከከበሩበት፣ ወልደው ከሣሙበት ቀዩ፡፡ በግፈኞችና በአምባገነን አሽከሮች ተገፍተው ምድራዊ ሲዖል ውስጥ ሲገቡ ዛሬም ከንፈር እንመጥ ይሆን? ዛሬም በዚች ሀገር ላይ የብሉና ተበሉ ህገ አራዊት ገቢራዊ ሲሆን አላየንም አልሰማንም እንል ይሆን? ጎበዝ የገናዋ በግ እንዲሉ ዲሞክራሲያዊ መብቶቻችንን ለማስከበር በፍፁም ሰላማዊ የትግል አንድነት ጥላ ስር ሆነን እንነሳ ለሃያ ሶስት አመት ያህል በግፈኞችና ማንአህሎተኞች የደረሰብን ሥቃይ በቂ ወይም ከበቂ በላይ ነው፡፡
እምቦቀቅላ ህፃናትን በጆፌ አሞራዎችና የሎሶች መነጠቃቸው መቆም አለበት፡፡ ታላላቆችና መሪዎቻችን የሆኑ መንፈሰ ጠንካራ ወጣት ፖለቲከኞች በአባ ውቃው እስር ቤት ውስጥ የሚደርስባቸው ውርደትና ሥቃይ ምዕራፍ እንዲዘጋ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የህብረት ፍልስፍና መከተል ይገባናል፡፡ ጎበዝ የግፍ ፅዋ ሞልቶ ፈሷል፡፡ እንዲህ አይነት ብሔራዊ ውርደት ውስጥ የገቡ የዓለም ህዝቦች ጥቂቶች ይመስሉኛል፡፡
ምን እንኳና አገዛዙ የሀገሪቷን አንጡራ ሀብት በእጁ መዳፍ ስር በማስገባት የሚሰራውን ቢያሳጣውም ብረት ቢታጠቅም እኛ በህብረት ከተነሳን መብታችንን ማስከበር ይቻለናል፡፡ ውድ ወገኖቼ የአንድነትን ጥቅም ከእንሰሳቶች መማር ይቻላል፡፡ እነ አባ ኮርማ፣ ተራ ጋጭ ዋርዴ፣ ድንጉላ ጥርኝ በግና ፍየሎች፤ እንዲሁም ግመሎች ተፈጥሮ ባደላቸው ሥልት በመጠቀም እራሳቸውን ከአጥቂዎች ሲከላከሉ እንደኖሩ የምናውቅ ይመስለኛል፡፡ እግዚአብሄር ከደካሞችና ከሰነፎች ጋር ሳይሆን ሰልፍ ከብርቱዎች ጋር ይመስለኛል፡፡
ጥንታዊ አባቶቻችን እና እናቶቻችን የዛሬዋን ኢትዮጵያ ያስረከቡን በብዙ ጀግኖች መስዕዋትነት እንደነበር ለአፍታም መዘንጋት የለብንም፡፡ በፖለቲካ ድውያን እና በአገዛዙ ካድሬዎች ውሸት ተቦክቶና ተጋግሮ እንደሚቀርበው ሳይሆን ኢትዮጵያን የብዙ ዘመን ታሪክ ያላት ናት፤ ኢትዮጵያ ተብላ የምትታወቀው ሀገር ከሰው ልጅ አፈጣጠር እድሜ እኩል ርዝመት እንዳላት ጠበብት ይናገራሉ፡፡ ይሁንና የትውልድ ቅብብሎሽ ከተቋረጠ የምንወዳትና የምናከብራት ሀገራችን በነበረችበት ለመቀጠል አስቸጋሪ ሳይሆንባት አይቀርም፡፡ በዓለም ላይ የረዥም እድሜ ዘመን ባለቤት የነበሩ ሀገራት ሊጠፋ እንደሚችሉ ማወቅ ይገባናል፡፡ ዛሬ እናት ኢትዮጵያ በህይወት ብትኖርም በታላቅ ችግር ውስጥ ትገኛለች፤ ስለሆነም ሀገርን ለማዳን በአንድነትና በፍቅር እንነሳ፡፡
የሀገሩን ታሪክ በቅጡ ያልተረዳ ማህበረሰብ ምንም የህይወት ልምድ እውቀትና ጥበብ እንደሌለው ግለሰብ ይቆጠራል፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ባለፉት 23 አመታት የፈፀመውን የታሪክ ክህደት ህሊና ላላችሁ ትቼዋለሁ፡፡ አገዛዙ አሁን ድረስ ከኢትዮጵያ የእውነት ታሪክ ጋር የተጣላ እኩይ ሥርዓት ነው፡፡ ስለሆነም ኢትዮጵያዊን ሁሉ ታሪካችንን እናጥና ለልጆቻችን እናስተምር፡፡
የሰው ልጅ የወደፊት አቅጣጫውን ለመተለምና ሙሉ ሰው ለመሆን ከተፈለገ ታሪኩን ማወቅ ይገባዋል፡፡ የሰው ልጅ ከእንሰሳ የተለየ ነው፡፡ የእንስሳት ኑሮ የተመሰረተው ከታሪክ ጋር አይደለም፡፡ እንሰሳት ኑሮአቸው የተመሰረተው የተፈጥሮ ችሮታ ነው፡፡ ታሪካቸውን ለመገንዘብ አይችሉም፡፡ በዚች ሀገር ላይ ታሪኩን የሚያወቅና ስለ ሀገሪቱ የረጅም ዘመን ታሪክ የሚገነዘብ ትውልድ በከፍተኞ ደረጃ ቁጥሩ መጨመር ይገባዋል፡፡
የአክሱም ሀውልትና በዘመኑ የነበሩ ገናና ነገስታት ታሪክ፣ የላሊበላ ውቅር ቤተ ክርስቲያናት የስነ ህንፃ ጥበብ፣ የጎንደር ቤተ መንግስት፣ በአፍሪካ ብቸኛው ሀገር በቀል ቋንቋ የሆነው የአማርኛ ቋንቋ፣ የ3000 አመት የኢትዮጵያ ታሪክ አፈ ታሪክ ወይም ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሀገሪቱን እያስተዳደርን ነው የሚሉት ጌቶቻችን የኢትዮጵያን ታሪክ በመካድ ይታወቃሉ፡፡ አባቶቻችን የከፈሉትን ከባድ መስዕዋትነት ማንሳት አይፈልጉም የታላላቅ ነገስታትን ታሪክ (ለምሳሌ እምዬ ምኒልክን) ያንቋሽሻሉ፡፡ በዘመናቸው የተከሰተውን ታሪክ በመምዘዝና ቀለም ቅብ በመቀባት ተውልድን ያሳስታሉ፡፡
ጥንታዊ የሀገራቸውን ታሪክ ከመካድ አኳያ የህወሓት/ኢህአዴግና የእስላማዊ መንግስት ለመመስረት ቆርጠን ተነስተናል የሚለው ቡድን (ISIS) ተመሳሳይ ሳይሆኑ አይቀርም፡፡ አሜሪካኖችና ሌሎች ሀገራት በጥንት ዘመን የደረሰባቸውን በደል ሳይቀር እንደ ትምህርት በመውሰድ የጥንት አባቶቻቸውን ሥራና ታሪክ ያከብራሉ፡፡
እንደ ሰው ልጅ ታሪክ ሁሉ በአሜሪካን ሀገር የባሪያ ንግድ (ባርነት) የእርስ በርስ ጦርነት (American civil war) ከብዙ ዘመን በፊት ተካሂዶ የነበረ ቢሆንም የዛሬው ትውልድ አሜሪካውያን በአባቶቻቸው ታሪክ የሚኮሩ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው ወደ ታላቅ ደረጃ ላይ የደረሱት፡፡ ጎበዝ እኛም ብንሆን ይህን ከፋፋይና ዘረኛ ቡድን ለመገላገል ከፈለግን የአባቶችን ታሪክ እንመርምር ለልጆቻችንም እናስተምር፡፡
አገዛዙ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን የሚያስረውና ሲሻውም የሚገለው በፍፁም ኢትዮጵያዊነት ፍልስፍና ቆመው ሲታገሉት እንደሆነ ለአፍታ እንኳን መዘንጋት የለብንም፡፡ በመጨረሻም ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በአንድ ላይ በመቆም የኢትዮጵያዊያን ትንሣኤ ለማምጣት እንታገል እያልኩ ልሰናበት፡፡
(አቶ ደረጄ መላኩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸው፡፡)

No comments:
Post a Comment