Tuesday, October 28, 2014

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ 3 አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት

Photo: ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ 3 አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው ቀን በዋለው ችሎት 3 አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት፡፡ ፍትህን ሲያሳትም የነበረውና ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው  ማስተዋል ህትመትና ማስታወቂያ በ10 ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎበታል፡፡  

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጥቅም 3/2007 ዓ.ም የመንግስትን ስም ማጥፋት፣  ህዝብን ማነሳሳትና የህዝብን አመለካከት ማናወጽ በሚሉ ሶስት ክሶች ጥፋተኛ  የተባለ ሲሆን አሁን የተፈረደበት በትኛው እንደሆነ ባይታወቅም በአንደኛው ክስ ነው ተብሏል፡፡ የጥፋነኝነት ክሱ በተነበበት ወቅት ግን ‹‹መንግስት ይገድላል፣ ያፍናል፣ ይጨቁናል ብሎ ጽፏል፡፡›› በሚል ጥፋተኝ ነው ተብሏል፡፡

አቃቢ ህግ የቅጣት ማክበጃ ያላቀረበ ሲሆን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም ሆነ ጠበቃው የቅጣት ማቅለያ አላቀረቡም፡፡ በሌላ በኩል የጋዜጠኛው ጠበቃ አምሃ መኮንን ይግባኝ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል፡፡

(ነገረ ኢትዮጵያ)

No comments: