ግንቦት 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ ስምንት ሰዓት ሲሆን ከምሳ በኋላ ቡና እየጠጣሁ ወጪ ወራጁን ራጁን አያለሁ:: ቡና እየጠጣሁበት ያለው ካፌ የሚገኘው ከቦሌ መድኃኔዓለም ወደ ብራስ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ዳር ላይ ነው::
በረንዳው ላይ ተቀምጬ ወጪ ወራጁን ሳማትር ከፊት ለፊቴ አንድ የአውሮፓ ገጽታ ያለው ፈረንጅ ባየው ነገር እየተደናገጠ በፍጥነት ይራመዳል:: ምን ሆኖ ነው ብዬ ወደሚያየው አቅጣጫ ፊቴን ሳዞር አንዲት የእኔ ቢጤ ከሦስት ልጆቿ ጋር ተቀምጣለች::
ይኼ ፊቱ በድንጋጤ ድርቅ ያለ ፈረንጅ እየተንደረደረ ሄዶ ሴትዮዋ አጠገብ ከደረሰ በኋላ ለማናገር ይሞክራል::
የእኔ ቢጤዋ ፈረንጁ ምን እንደሚል ስላልገባት በመገረም ታየዋለች:: እሱ ቁጣ በተቀላቀለበት ሁኔታ መናገር ሲጀምር በመንገዱ ላይ በመተላለፍ የነበሩ ሰዎች ከጉዞአቸው ተገተው ቆሙ:: ፈረንጁ የእኔ ቢጤዋ አጠገብ ከተቀመጡት ልጆቿ መካከል አንዱ ላይ እያነጣጠረ፣ ‹‹ይኼን ልጅ ከየት አመጣሽው?›› በማለት ነበር ጥያቄ የሚያቀርበው::
ዓይኖቼን ወደ ልጆቹ ስመልስ አንደኛው ሕፃን ቁርጥ ፈረንጅ ይመስላል:: ቆዳው ሙሉ በሙሉ የፈረንጅ ሆኖ ፀጉሩ
የነጣና ሉጫ (ብሎንድ) የሆነውን ሕፃን ከእኔ ቢጤዋ ጋር ያገኘው ፈረንጅ፣ ከዚህ ቀደም የገዛ ልጁ የጠፋበት ወይም
ዘመዱን ያጣ ይመስል ሕፃኑን እያየ፣ ‹‹ይህቺ ሴት ይህንን ሕፃን ከየት እንዳመጣችው ማወቅ እፈልጋለሁ፤›› እያለ
ሲወራጭ ዙሪያውን የከበቡት ሰዎች ዝም ብለው ያዳምጣሉ::
ፈረንጁ እየተንቆራጠጠ ሲውረገረግ ሴትየዋን ደብድቦም ቢሆን ልጁን ከየት እንዳመጣችው ለማወቅ የሚፈልግ ይመስላል::
በፈረንጁ አኳኋን ግራ የተጋቡት ሕፃናትና እናታቸው ምን መዓት መጣብን ብለው ኩርምት ብለው ተቀምጠዋል::
እኔ ሒሳቤን በቶሎ ከፍዬ ወደ ግርግሩ ቦታ በመሄድ ፈረንጁ ለምን ይህንን ጥያቄ እንደሚያቀርብ ለማወቅ ስጠጋ
በችኮላ ከአካባቢው ፈትለክ ብሎ ሄደ:: በዚህ መሀል እዚያ ከተሰባሰቡ ሰዎች አንዱ፣ ‹‹ይኼ የአንቺ ልጅ ነው?›› በማለትእናትየዋን ሲጠይቅ፣ ሦስቱም ልጆች ከአንድ አባት የተወለዱ መሆናቸውን ትነግረዋለች:: አንዱ፣ ‹‹ፈረንጅ ይመስላል እኮ?›› ሲላት ሴትየዋ በተኮለታተፈ አማርኛ፣ ‹‹አባቱም እንደዚህ ሰው ቀይ ነው…›› እያለች ወደ አንዱ አመላከተች::
ፈርጥጦ ሄዶ የነበረው ፈረንጅ ከአፍታ ቆይታ በኋላ አንድ የትራፊክ ፖሊስ ባልደረባ ይዞ መጣ:: የትራፊክ ፖሊሱ ሴትየዋንና ልጆቹን ወደ ሕግ በመውሰድ ሴትዮዋ ነጭ የሚመስለውን ሕፃን ከየት እንዳመጣች እድትጠየቅ እንዲያደርግ ፈረንጁ ትዕዛዝ መሰል ጥያቄ ሲያቀርብ ውስጡ በዘረኝነት የተሞላ ይመስል ነበር::
አንዲት አፍሪካዊት ለማኝ እንዴት የፈረንጅ ልጅ ይዛ መንገድ ላይ ትገኛለች የሚል ቁጭት ያለበት ይመስላል:: ዓይኖቹምያሳብቃሉ:: በዚህ መሀል አንድ ሌላ ሞተረኛ የትራፊክ ፖሊስ ባልደረባ ደርሶ ለሴትየዋ ጥያቄ ማዥጐድጐድ ሲጀምርየተወሰኑ ሰዎች ማጉረምረም ጀመሩ:: እስከዚያ ሰዓት ድረስ የሐበሻ ልጆች ፀጥ ብለው ድራማ የሚያዩ ይመስሉ ነበር::
እኔ የትራፊክ ፖሊሶቹ አኳኋን ስላላማረኝ ጠጋ ብዬ ለመገሰፅ ስዘጋጅ አንድ ወጣት ተንደርድሮ መጣ:: ወጣቱ ንዴት ፊቱ ላይ እየተንቦገቦገ ፈረንጁን፣ ‹‹አንተ ማነህ?›› በማለት ጥያቄ አቀረበለት:: ፈረንጁ፣ ‹‹ጋዜጠኛ ነኝ›› አለው:: ወጣቱ ተናዶ፣ ‹‹አትመስለኝም:: ጋዜጠኛ እንዲህ አይደለም፤›› ካለው በኋላ፣ ‹‹ከዚህ ልጅ ጋር የሚያገናኝህ ትውውቅ አለህ?›› ሲለው ፈረንጁ ትውውቅ እንደሌለው ተናገረ:: ወጣቱ አበደ ማለት ይቻላል:: ‹‹በማያገባህ ገብተህ ምን ትፈተፍታለህ? የማያገባህ ከሆነ ዘወር በል ከዚህ፤››
ብሎ ወደ ትራፊክ ፖሊሶቹ ዞረ:: ‹‹ይህቺ ደሃ ሴት በገዛ አገሯ ከነልጆቿ በማታውቀው ፈረንጅ ስትዋከብ እንዴት
ትተባበራላችሁ? ድህነቷ አልበቃ ብሎ ከነልጆቿ እንደ አውሬ ስትከበብ እንዴት ዝም ትላላችሁ?›› ሲላቸው የብዙዎችን ድጋፍ አገኘ:: የትራፊክ ፖሊሶቹ ምላሽ አጥጋቢ ባይሆንም ጉዳዩን ለማጣራት መምጣታቸውን ተናገሩ:: ፈረንጁም ከአካባቢው ሹልክ ብሎ ጠፋ::
በእንዲህ ዓይነቱ አሳዛኝ አጋጣሚ እኔን ያስገረመኝ የእኛ ባህሪ ነው:: ከወጣቱ በስተቀር የሌሎች ዝምታ፣
የትራፊክ ፖሊሶቹ ፈረንጁን ተከትለው መጥተው ሴትዮዋን እንድትበረግግ ማድረጋቸውና እንግዳ ተቀባይ የሚባለው
ወገናችን ፈረንጅ በገዛ አገሩ ሲደነፋበት ችላ ባይነቱ አናዶኛል::
በተለይ እኛ ከተሜ የምንባል ሰዎች በየማኪያቶና በየቢራ ጠረጴዛው ላይ ስንትና ስንት ጉዳዮችን እያነሳን ስንደፋ
እንደማንውልና እንደማናመሽ፣ በጠራራ ፀሐይ መሀል ቦሌ ላይ አንዲት ደሃ ወገናችን ከነልጆቿ በፈረንጅ ስትዋከብ ዝም ብለን ተመልክተናል::
ያ ብልህና ቁጡ ወጣት ፀጥታችንን ሰብሮ ወሳኝ የሆነ ዕርምጃ ባይወስድ ኖሮ እነዚያ ሕፃናትና ያቺ ደሃ እናት በዚያ
ጠራራ ፀሐይ ይደርስባቸው የነበረው እንግልት ሲታሰበኝ አሁንም ድረስ ያበሳጨኛል:: የእኛ ነገር ‹‹ባለቤቱ ያቀለለው አሞሌ…›› እየሆነ ነው እንጂ፣ ታሪካችንማ እንዲህ ዓይነቱን ወራሪ ፈረንጅ አባቶቻችንና እናቶቻችን ሲያርበደብዱ እንደነበርይነግረናል:: ለማይረባ ጉዳይ አሳራችንን ከምናይ ለአገራችንና ለወገናችን ጉዳይ እስቲ እንጨነቅ:: በአያገባኝም ስሜትየተሞላውን መንፈሳችንን አስረነው እስከመቼ እንዘልቃለን?
ሕፃኑ ልጅ ፈረንጅ መስሎት የውጭ ዜጋ ሽንጡን ገትሮ ሲከራከር ብዙዎች ዝም ከማለት አልፈው፣ የጥቃት ስሜት
እንኳ አይሰማቸውም ነበር:: ‹‹አልቢኖ›› በመባል የሚታወቀው የቆዳ፣ የፀጉርና የዓይን ንጣት በበርካታ አገሮች እንደሚታወቅ እንኳ ለማስረዳት ከዚያ ወጣት በስተቀር የደፈረ አልነበረም::
አንዳንዴ እኮ ነገራችን ሁሉ ግራ ያጋባል:: ግራ የተጋባ ፈረንጅ ‹‹አልቢኖ›› የሚባለው በዓለም የሚታወቅ የተፈጥሮ
ክስተት እንዳለ ትንሽ እውቀት ሳይኖረው ግራ ሲያጋባንና ድሆቹን ሲረብሽ ማየት ቢገርምም፣ የእኛ አላዋቂነት ደግሞ
ያናድዳል:: በተለያዩ ጉዳዮች ከባለሙያዎች በላይ ለመራቀቅ የምንፈልገው ከተሜዎች በመሃይም ፈረንጅ ስንዋከብ
አያሳዝንም? ዋናው ዕውቀት ባይኖር እንኳ ጠቅላላ ዕወቀት እኮ አስፈላጊ ነው:: ተግባባን?
(ናኦድ ዓለማየሁ፣ ከ24)

Source: sodere
No comments:
Post a Comment