አንድነትና መኢአድ የሚያደርጉትን የቅድመ ውህደት ስምምነት ከአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ክፍል ኃላፊ የዕውቅና ደብዳቤ ፓርቲዎቹ ቢጠይቁም ስብሰባ ናቸው በሚል ሰበብ በሆቴል ዝግጅቱን ማከናወን ስላልተቻለ ሆቴሎች ለፓርቲዎቹ አዳራሽ ለማከራየት በመቸገራቸው የቅድመ ውህደት ስምምነታቸውን በመኢአድ አዳራሽ ሊያደርጉ ተገደዋል፡፡ ትብብር፣ቅንጅትና ግምባር በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ተፈትኖ እንደማይሰራ ተደጋግሞ በሚነገርበት ወቅት ሁለቱ ፓርቲዎች በአንድነት ለመስራት የሚያስችላቸውን የቅድመ ውህደት ስምምነት በመፈራረም መተባበር መተባበር ብቻ እንደሚገባ የፓርቲዎቹ አመራሮች ገልጸዋል፡፡
በተናጠል በሚደረግ ትግል ሁልግዜም ተጠቃሚ የሚሆነው የገዢው ፓርቲ እንደሆነ ከዚህ ቀደም የነበሩ ክስተቶችን መለስ ብሎ መመለከት ተገቢ ነው፡፡ በአንድ የምርጫ ጣቢያ በተለያዩ ስሞች ተቃዋሚዎች እየተወዳደሩ አስተኛ ድምጽ የሚያገኘው ኢህአዴግ አሸናፊ ሆኖ የሚወጣበት እንቆቅልሽ እንዲፈታና የሁለቱ ፓርቲዎች ውህደት ሌሎችም ሊከተሉት እደሚገባቸው በፊርማው ሥነ- ስርዓት በሁለቱ ፓርቲ መሪዎች ተገልጧል፡፡
No comments:
Post a Comment