ችግሮች እንዲቆሙ የተመኘንባቸው ወይም የሞከርንባቸው ዘመናት ገና ያኔ ያኔ አልፈዋል። ወያኔ ግን በችግር ላይ ችግር በመከራ ላይ መከራ ደራረበብን እንጅ መፍትሄ አላገኘንም። "እምብዛም ዝምታ ለበግም አልበጃት ሃምሳ ራሷን ሆና አንድ ነብር ፈጃት" ነው ብሂሉ። እኛ ለመብታችን መከበር እስቃልቆምን ድረስ ህወሓት በየጊዜው ሌሎች አዳዲስ ምክንያቶችን እየፈጠረ ለማሰር ለማሰደድና ለመግደል አይቦዝንም። በፊት በፊት በአሸባሪነት፣ በአልቃይዳና በሌሎችም እያመካኘ ያስርና ያንገላታ የነበረው ህወሓት አሁን ደግሞ የሕዝብ ሃይል መደራጀትና መመስረትን ተከትሎና በዚሁ ሃይል እያመካኘ ወጣቱን እያሰረና እያሰደደ መሆኑ ይሰማል፣ይታኛል። እና እኛስ እስከ መቼ ነው እንተገረፍንና እንደተሰደድን የምንቀጥለው? አንተም ከማባረር አልተመለስክ እኔም ሁሌ መባረር መሮጥ ሰለቸኝ የምንለውስ ዛሬ ሊሆን ካልቻለ ለመቼና ለእንዴት ያለ ጊዜ ይቆጠባል?
ህወሓት ከበቂ በላይ የስቃይና የጥፋት ማስጠንቀቂያዎችን ሰጥቶናል። የግድ በግል በራሳችን ለይ ደርሶ ማየት እንሻለን እንዴ? ለዚያውም ባለፉት የህወሓት ያገዛዝ ዘመናት ችግር ያልዳሰሰው ቤት ካለ መለቴ ነው። ይህን የጥፋት ሃይል አንድ ሆነን ቆመን መመከት ካልቻልን ዝምታን ከመረጥናና ወያኔ ባዘጋጀልን ወጥመድ ተጠልፈን ከገባን ኢትዮጵያ የምትባልን ሀገርም ሆነ የሕዝባችንን ከብር እንደገና ለመመለስ በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። "ለሁሉም ጊዜ አለው" ሀገርንና ሕዝብን ለማዳንም ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ረፍዷል ካልተባለ ጊዜው አሁን ነው። አንድ ላይ በመተባበር በውስጥ ሽኩቻ በአመራር ብቃት ማነስ በሕዝብ በመተፋት እና መጠላት የዘመመውን ህወሓት ገፍተን እንጣለው።
ከሰብኣዊ

No comments:
Post a Comment