Friday, April 1, 2016

የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን መሥራትም ኾነ ከሀገር መውጣት እንደተከለከሉ ገለጹ

የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ከእሥር ከተፈቱ በኋላ

የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ከእሥር ከተፈቱ በኋላ
አጋሩ
·          
·          
·          
ከአምስት ወራት በፊት ከእሥር የተለቀቁት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች፤ ከእስር ከተለቀቁም በኋላ አገር ውስጥ በነጻነት መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ እንዲሁም ለሽልማት፣ለትምሕርትና ለሥልጠና ላገኟቸው ዕድሎች ከአገር መውጣት እንደተከለከሉ ገለጹ፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ — 
ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ ከእሥር ከተለቀቀ በኋላ ያለበትን ሁኔታ ለአሜሪካ ድምጽ ሲናገር፤ ከመታሠሩ በፊት ይሠራበት የነበረው መጽሔት በመዘጋቱ ምክኒያትሥራ እንደሌለው ገልፆ ነገር ግን ጀርመን አገር በሚገኘው ዜድ.ኤ.ፍ ZDF) ለሥልጠና ተጋብዞ ደርሶ ሲመለስ፤ “መጀመሪያ እንዴት ወጣህ?፣የሚጣራ ነገር አለ” በሚል የጉዞ ሰነዱን ወይም ፓስፖርቱን እንደተቀማ ተናግሯል፡፡
በአምቦ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምሕር የነበረው ጦማሪ ዘላለም ክብረት በበኩሉ ገና እሥር ቤት እያለ ከሥራ መሰናበቱን ተናግሯል። ከተፈታም በኋላ ሽልማት ለመቀበል ለተደረገለት ጥሪ ከሀገር ለመውጣት ሲሞክር ፓስፖርቱን እንደተቀማ ተናግሯል፡፡
ለአምስት ወራት ያሕል ፓስፖርቱን ለማግኘት በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርግም ማግኘት እንዳልቻለም ይገልፃል፡፡ እንዲሁም ለዚህ ዓመት አሜሪካ ውስጥ ለሚሰጠው የወጣት አፍሪካውያን መሪዎች ፌሎሽፕ (Young African Leaders Initiative (YALI) ቢያሸንፍም እስካሁን የጉዞ ሰነዱን ማግኘት ባለመቻሉ ዕድሉ ያልፈኛል የሚል ስጋት እንዳለው ይናገራል፡፡
ጦማሪ ዘላለም ክብረትና ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ ከእስር በኋላ ስላለው ሕይወታቸው ጽዮን ግርማ ጠይቃቸዋለች፡፡ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ ሁኔታውን በማብራራት ይጀምራል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Source: VOA

No comments: