ታድያ ለዚህ ዘግናኝ እልቂት የተቃዋሚው ጎራና አክቲቪስቶች ያነሳው ጥያቄ “ብሔራዊ የሀዘን ቀን ይታወጅ” የሚል ነው። በቃ ይኼው ነው። ይህም እንቅስቃሴና ጥያቄ ሆኖ፣ “የኛ ልጆች ሲሞቱ ምነው ብሔራዊ ቀን ይታወጅ አላላችሁ” የሚሉ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ደግሞ ተነስተዋል። ታድያ ጎበዝ፣ ይህን ህዝብ የሚያስፈጀው ወያኔ ብቻ ነው ማለት ይቻላል? በቁማችን ሞተን በክተናል እኮ! እኛው ራሳችን እኮ ነን ህዝቡን የምናስፈጀው። ይህንን አሰቃቂ እልቂትም ለጨረባው ፖለቲካችን ጠማዝዘን ስናውለው፣ እንዴት ዓይነት የተረገምን ፍጡራን ብንሆን ነው። መጥኔ!
በተለይ እነዚህ ገገማ የኦሮሞ ብሔርተኞች፣ ምንም ዓይነት ነገር በዛች አገር ቢከሰት ልዩነትን ለማስፋትና ህዝቡን የበለጠ ለመነጣጠል ነው የሚጠቀሙበት። ኦሮሞው ሲሞት ሌላው እንደማያገባው ሲንግሩን ነበር። ተመልሰው ደግሞ ዓይናቸውን በጨው አጥበው ምነው ዝም አላችሁ ብለው ለመክሰስ ወደ ኋላ አላሉም። ከዛም አልፈው በእንዲህ ዓይነት አስቃቂ እልቂት ያንን ተንከሲስ ቁማራቸውን ይጫወታሉ። እኩያን!
Source: Satenaw
No comments:
Post a Comment