Saturday, December 20, 2014

ባህርዳር እና አምቦ ላይ ለተደገሩ ህዝባዊ ተቃውሞዎች የተሰጠው ምላሽ ከምን ጊዜም በላይ የኢህአዴግን ባህርይ እና ትልም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡


በየትኛውም ሀገር ቢሆን ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች በአደገኛ ሁናቴ ለፖሊስ አስቸጋሪ ቢሆኑ፣ አደለም መጮህ ድንጋይ መወርወር ቀርቶ ለመደባደብ ቢጋበዙ እንኳን፤ ከውሃ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ የፕላስቲክ ጥይት እና የመሳሰሉት ታልፎ የሰው ልጅ ላይ መሳሪያ አይተኮስም፡፡ በፍጹም! የሰው ልጅ ክቡር ነው - አንድያ ህይወቱን እንዲህ በቀላሉ ማጣት የለበትም፡፡ የገደለ እንኳን ምህረት ይደረግለታል፡፡

ሰላማዊ ታጋዮች ነን፣ ድንጋይ ከመወርወር ጀምሮ መኪና ማቃጠልና ንብረት ማውደም ድረስ የሚሄድ ትግል ቢካሄድ እንኳን የሰው ልጅ ክቡር ህይወት ንብረት ወደመ ተብሎ በፍፁም ሊጠፋ አይገባውም!

እርግጥ ኢህአዴግ ከሰብዓዊነት ጋር የማይጣጣም ባህርይ ያለው አገዛዝ ነው፡፡ ይህ ሊገባው አይፈልግም፡፡ ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀ እንደሆነ ቀድሞ በመተኮስ በተደጋጋሚ ጊዜ እያመላከተን ነው፡፡ ከሀይል ውጪ የትኛውንም አማራጭ ለመጠቀም በፍፁም አይፈልግም፡፡ ይህ ባህርይውን በማጋለጥ በተለያየ ጊዜ እና ኮዝ ህይወታቸውን ጭምር በመክፈል ለስርዓት ለውጥ የሚካሄደውን ትግላችንን መልክ እያስያዙት ላሉ ወገኖቼ በሙሉ ፈጣሪ በቀኙ እንዲያውላቸው እመኛለሁ!

በየትኛውም አካባቢ የሚደረገው ትግልም ያለመስዋዕትነት ድል እንደሌለ በመረዳት በቁርጠኝነትና ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ይፋፋም! አገዛዙ ያለርህራሄ ሊገድለን ሲያሰፈስፍ እኛም አንድ ህይወታችንን ለልጅ ልጆቻችን ሰላም ተስፋ እና አንድነት ስንል ለመስጠት እንቁረጥ!

ይህ ከአገዛዝ ወደ ፍትኃዊ ስርዓት የሚደረግ የነፃነት ትግል ነው!

እየሞትን እናሸንፋለን!

No comments: