Thursday, December 25, 2014

የአውሮፓ ህብረት ቀጣዩ ምርጫን (ምርጫ 2007) እዳይታዘብ ተከለከለ።

በአንጻሩ የኢትዮጵያ መንግስት የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ሚሽን ራሱ ባጋጠመው የበጀት እጥርት ምክንያት ምርጫውን መታዝብ አልችልም ብሎ እንደቀረ በጠ/ ሚኒስቴሩ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የተነገረው ውሸት መሆኑ ተረጋግጧል።
የችግሩ መንስኤ የ28 ለጋሽ ሃገሮች ስብስብ (Development Assistance Group) ለሰባቱ ራሳቸውን ዲሞክራሲያዊ ተቋማት ብለው ለሚጠሩት በUNDP በኩል ይሰጡ የነበረውን ከ40 ሚሊዮን ዶላር በላይ የአቅም ግንባታ ገንዘብ በማቆማቸው ምክንያት የኢትዮጵያ መንግስት ተበሳጭቶ ነው።
እርዳታው የቆመበት ምክንያት ተቋማቱ የገዢው ፓርቲ ቅኝ እጅ ሆነው ከመስራት አልፈው የሰብዓዊ መብት እንዲጣስና ዲሞክራሲያዊ አሰራር እንዲፈርስ በማድረጋቸው መሆኑ ታውቋል። በተጨማሪም ለጋሽ ሃገሮች የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች ታስረው ምርጫ ማካሄድ የገንዘብ እርዳታውን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ በማስገባቱ መሆኑ ታውቋል።
በአፋኝነትና በኢ-ዲሞክራሲያዊነታቸው እርዳታ የተከለከሉት ተቋማት እነዚህ ናቸው:-
1) የተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ)
2) የፈዴሬሽን ም/ቤት
3) የኢፌዲሪ የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም
4) የኢፌዲሪ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን
5) የኢፌዲሪ ፀረ ሙስና ኮሚሽን
6) የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ እና
7) ምርጫ ቦርድ ናቸው

No comments: