Thursday, August 1, 2013

ከቆራጥ ሙስሊም ወንድሞቻችን ምን እንማራለን?

ሙስሊም ወንድሞቻችን ምን እንማራለን?

ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸው የመብት ጥያቄዎች ወደጐን በመተው የመንግስት ባለስልጣናት የሚከተሉትን ህዝብን የማሸማቀቅ አካሄድ መልስ እንዲሆን የተዘጋጀ ሰነድየእምነት ነፃነት ጥሰት መቃወም ከጀመርን እነሆ በነዚህ ጊዜያትም ጥያቄዎቻችንን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እያቀረብን ብንገኝም ሊሳካልን የቻለው ያማረ አካሄድ ማስመዝገባችን እንጂ ያማረ ውጤትን አይደለም፡፡ሲል የአካሄዱን ሰላማዊነት ገምግሟል፡፡

 የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቃውሞ መንገድ የተደመሙ ውጭ ሚድያ ና ምሁራን በዝተዋል፡፡ከእንግዲህ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴን ለማጥናት የውጭ መፃህፍትን ማገላበጥ አያስፈልግም የሀገሬ ሙስሊሞች ሁኔታ ከምንም ይበልጣል ፡፡ ለዚህ አባባ መነሻ የሆኑ ሁለት ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል፤ የመጀመሪያው ሀገሪቱ የተደራጀ የሰላማዊ ተቃውሞ ታሪክ የሌላት መሆኑ ሲሆን ሌላው ስማቸው የሽብርተኝነት ጅሃድና ብጥብጥ መገለጫ ወደ መምሰሉ ያደላው ሙስሊሞች ፍፁም ሰላማዊ ሆነው መንቀሳቀሳቸው ነው፡፡ እንደማንም መደዴ ሰው እስልምናን ከጦርነት ጋር ማያያዝ የተለመደ ነውየኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከዚህ በተቃራኒ በመንቀሳቀሳቸው ሁሉንም አስደምሟል፡፡

በአብዛኛው ሀገሮች አብዮትን ያስጀመሩ መሪዎች እስከ አብዮቱ ፍፃሜ አይጓዙም፤የታለመለትን ግብ የሚመቱ አብዮቶችም እስከዚህም ናቸው፤ አብዛኛዎቹ አብዮቶች የተደበላለቀ አካሄድ ነበራቸው፡፡ ወቅታዊው የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ከአብዮት በመለስ የተደራጀ በውስጡ በወል የታወቁ መሪዎች ያሉት፣ እና ማንም ተነስቶልሙላው አልሙላውየሚለው አይደለም፡፡

የትኛውም የተቃውሞ ጎራ ላይ ያለ ቡድን የመጀመሪያው ስራ ሊሆን የሚገባው የሚቃወመውን ወገን ባህሪ ማጥናት ነው፡፡ ባለፉት 22 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩት ተቃዋሚዎች ይህ ስራ የጎደላቸው ነበሩ፡፡ በዚህ ወቅት የዚህን የቀድሞ ችግር እየቀረፉ የመጡት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለዚህ ያበቃቸው የመጀመሪያ ስራቸውን ያደረጉት ኢህአዴግን በመረዳት ላይ ማድረጋቸው ነው፡፡

ከሀይል በተጨማሪ መንግስት በካድሬዎች አስገዳጅነት የተቀነባበሩ የፀረ ተቃውሞ የተቃውሞ ሰልፎችን በመላ ሀገሪቱ ማደራጀቱን ማየት ተችሏል፡፡ አንዳንድ የመንግስት ካድሬዎች ከዚህ እንቅስቃሴ ጀርባ የሌሉና ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ለመቃወም እንዲወጣ ቢናገሩም አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸውበከሚሴና በደሴና አዲስ አበባ  የተደረጉት `የተቃውሞ` ሰልፎቹ መፈክሮች በይዘት አንድ መሆን ብቻ ሳይሆን የተፃፈበት ፊደል መጠንም ተመሳሳይ ነበሩ፡፡

ከሙስሊሞቹ ተቃውሞ የምንወስደው ትልቁ ትምህርት በምንም ሁኔታ ከሰላማዊነት ያለመውጣት ፡፡ ሰላማዊ ተቃውሞውን ለማደፍረስና ሙስሊሙን ወደ አመፅ ለማምጣት መንግስት ጥረት ያደረገ ነው፡፡ ተቃዋሚዎቹ ወደ የኃይል አመጽ ያለመምጣታቸው መንግስት የኃይል እርምጃ ለመውሰድ መንገድ አልሰጠውም፡፡ የሙስሊሞቹ ሌላው አስተማሪ ነገር አንዱ ደፋር መሆን ሲሆን ሌላው ቀጣይነት ላለው ጊዜ መቃወም መቻል ነው፤ አብዛኛው ተቃውሞ በሆነ አጋጣሚ ተነስቶ ወዲያው የሚከስም ነው ቀጣይነት ላለው ጊዜ መቃወም መቻል ነው ፡፡ ለዚህ ያበቃው ደግሞ ዋናው ነገር ተቃውሞው ስርዓት የተዘረጋለት (system) ነው፡፡

የወቅቱን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞን የተለየ ደረጃ የሰጠው ተለዋጭ የተቃውሞ ስትራቴጂ ማዘጋጀት መቻላቸው ነው፡፡ የተቃውሞን እንቅስቃሴ የሚመሩ ሰዎች የመጀመሪያ ስትራቴጂ የነበረው ተቃውሞን መታገስ የማይሆንለትን የኢትዮጵያ መንግስትን በምን መልኩ ማለፍ እንዳለባቸው ነበር፡፡ እንደ አስተያየት ሰጪዎች ሙስሊሞቹ እንቅስቃሴውን ከሚመሩ ሰዎች እስከ የተቃውሞ አካሄድ ድረስ ሁለተኛና ሦስተኛ አማራጭ ማስቀመጣቸው ነው፡፡ በተለይ የተቃውሞው አመራሮች ከታሰሩ ሌሎች የሚተኳቸው ሰዎች ከወዲሁ መመረጣቸው ጉዳዩን በቀላሉ እንዳላዩት ያሳያል፡፡

ኢህአዴግ በፈለገው ቀን እንደበግ እየጎተተ ወደ ወህኒ የሚወረውራቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በዚህ መልኩ ከወዲሁ መተካት ቢችሉ የተሻለ ይሆናል፡፡ አንድነት ፓርቲዎች መሪዎቻቸው ሲታሰባቸ የተለየ እቅድ ቢኖራቸው ኖሮ የመጎዳት መጠኑን፡፡ መተካት ያለመቻሉ የዚሁ plan B” እጦት ፡፡
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ


ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተጠረጠሩ ኃላፊዎችንና ባለሀብቶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ቀጥሏል

የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተጠረጠሩ ኃላፊዎችንና ባለሀብቶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ቀጥሏል


የኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኪራይ ጋር በተያያዘ በሙስና የጠረጠራቸውን የክልሉ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ኃላፊዎችንና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ባለሀብቶች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ሲቀጥል፣ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እየተዘጋጀ መሆኑን ምንጮች ገለጹ፡፡
የክልሉ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ ማካሄዱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ውጭ አገር ይኮበልላሉ ተብለው የተጠረጠሩ ከአገር እንዳይወጡ መመርያ መተላለፉ ታውቋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከአንድ ሳምንት በፊት በሙስና የጠረጠራቸውን የክልሉ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አሥር ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

እነዚህ ኃላፊዎች በሙስና የተጠረጠሩት ከኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ግዥ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ኮሚሽኑ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ጨምሮ በኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ግዥ ሒደት 25 የሥራ ኃላፊዎች ተጠርጣሪ ሆነዋል፡፡

በሙስና ከተጠረጠሩት መካከል የውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢፋ በዳዳና ምክትላቸው አቶ ጎዳና ዳባ ይገኙበታል፡፡

የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቁጥጥር ሥር ያልዋሉትን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንቅስቃሴ ከማድረጉ ጐን ለጐን፣ በክፍል ሁለት ዘመቻው ከማሽነሪዎች ግዥ ጋር በተያያዘ የጠረጠራቸውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል
እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮማሽን ኮሚሽነር አቶ ታከለ እንኮሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የክልሉ ውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሚያካሂዳቸው ሥራዎች የኮንስትራክሽን ማሽኖችን የሚያገኘው በሁለት መንገድ ነው፡፡ የመጀመሪያው በግዥ ሲሆን ሁለተኛው በኪራይ ነው፡፡

‹‹ረዘም ላለ ጊዜ ጥናት አካሂደን ሕግ ወደ ማስከበር ገብተናል፤›› ያሉት አቶ ታከለ፣ ኮሚሽኑ ከኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ግዥ ጋር በተያያዘ የጠረጠራቸውን በቁጥጥር ሥር ከማዋሉም በተጨማሪ፣ ያልተያዙትን ለመያዝ ሰፊ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም ከኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኪራይ ጋር በተያያዘ ዕርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በክልሉና በፌዴራል ደረጃ በርካታ ግንባታዎችን በማካሄድ የሚታወቅ ግዙፍ የልማት ድርጅት ነው፡፡

ኢንተርፕራይዙ የመጠጥ ውኃ ሥራዎች የማሳያ ግድቦችን ከመገንባቱ በላይ እንደየሁኔታው ስታዲየምና መንገድ ሲገነባ ቆይቷል፡፡ ኢንተርፕራይዙ የተቋቋመው በ500 ሚሊዮን ብር የተከፈለና በሁለት ቢሊዮን ብር የተመዘገበ ካፒታል ነው፡፡

የሪፖርተር ምንጮች በኢንተርፕራይዙ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ግዥ ጋር በተያያዘ በርካታ ሚሊዮን ብሮች እንደተመዘበረ ቢናገሩም፣ አቶ ታከለ የገንዘቡን መጠን ለጊዜው ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡
ሠሞኑን በአንድነት ፓርቲ ‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት› በሚል 

መሪ ቃል የተጀመረው ዘመቻ አካል አንዱ በተለያዩ ከተሞች 

የሚደረገው ሠላማዊ ሰልፍ ነው፡፡ ታዲያ በየከተሞቹ ያሉ 

የፓርቲው አባላቶች ሠላማዊ ሰልፉን የማስተዋወቅ ስራ 

በሚሰሩበት ወቅት የመታሰር እና የመደብበድ አደጋ 

እየደረሰባቸው እንደሆነ በየቀኑ ከፓርቲው የሚወጡ መረጃዎች 

ይጠቁማሉ፡፡ ይህ በእውነት በጣም የሚያም ነገር ነው፡፡ 

ብሮሸር መበተን ጥፋት የሆነው ከመቼ ጀምሮ ነው? ወይስ 

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሲያረጉት ጥፋት ይሆናል? 

በጣም የሚደንቀኝ ደግሞ የመንግስት እና የመንግስት ደጋፊ 

የሆኑ ጋዜጠኞች/ሚዲያዎች ጉዳይ ነው፡፡ ህዝብን ሳይሆን 

መንግስትን ማገልገል ተቀዳሚም ተከታይም ስራቸው ሆኗል፡፡ 

እንዴት አንዳቸው እንኳን ጉዳዩን በማጣራት ወይም 

የመንግስትን ምላሽ ጠይቀው አይዘግቡም? 

አልሰማንም ማለት የሚችሉ አይመስለኝም፡፡

እንዲያው ነገሩን ለማለት እንጂ፤ ይህን ማሰብ ሞኝነት እንደሆነ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡

ሰበር ዜና ከደሴ


ሰበር ዜና ከደሴ



የሼክ ኑሩ ቤተሰቦች በመንግስት ሚዲያዎች ዘገባ እና ድራማ ነው !! በተባለው 

የአባታቸው ግድያ ! በሰላማዊ ሰልፎች የፖለቲካ ፍጆታ የስነ ልቦና ቀውስ 

እየደረሰብን ነው። አፋጣኝ መፍትሔ እንፈልጋለን አሉ።

የቤተሰቦቻቸው የቅርብ ምንጮች ባወጡት መረጃ እኛ ከደሴ ህዝብ ጋር በፍቅር እና 

መቻቻል ነው መኖር የምንፈልገው ነገር ግን በአባታችን ግድያ ደህንነቶች 

ከሚያስሩዋቸው ንፁሀን ቤተሰቦች የማህበራዊ ህይወት መገለል እየደረሰብን ነው 

ብለዋል።

አያይዘውም መንግስት በየከተማው በአባታች ሞት የሚያካሄደው ሰልፍ ለምን ታስቦ 

መሆኑን እና ያለፍቃዳችን በሚዲያ የሚተላለፉ ቃለ መጠይቆች ይቁሙልንም 

ብለዋል።

ከፍተኛ የስነ ልባና ጫና ፈጠረብን የሚሉት ድራማ ነው የተባለው የአባታችን ግድያ 

መንግስት ድራማ አይደለም እያለ በሚድያ መዘገቡ የአባታችንን ገዳይ አውቀን 

ከሐዘናችን እንዳንፅናና ጫና ፈጥሮብናልም ብለዋል።

የቤተሰቦቻቸው የቅርብ ምንጮች ከደሴ،،،،،

አላህ ሆይ እርዳታህን አቅርብላቸው አንተ ለእነሱ ሁናቸው!

Decisive CAR-Ethiopia qualifier in Rep. of Congo Read more here: http://www.islandpacket.com/2013/07/31/2605219/decisive-car-ethiopia-qualifier.html?#storylink=cpy

Decisive CAR-Ethiopia qualifier in Rep. of Congo
 — FIFA has moved Ethiopia's crucial World Cup qualifier away to Central African Republic in September to neutral Republic of Congo, the Ethiopian Football Federation said on Wednesday.
FIFA also decided that Senegal will play its decisive final group game against Uganda in Morocco because of the ban on Senegal's main football stadium.
Both games are scheduled for Sept. 7.
Ethiopia's final Group A game was meant to be hosted by Central African Republic but was relocated to Brazzaville for security reasons after CAR's president was overthrown this year. The country's qualifier against South Africa last month was played in neutral Cameroon.
Ethiopia now must win to guarantee its progression to Africa's 10-team playoffs for next year's World Cup after it forfeited a victory over Botswana for fielding an ineligible player earlier in the competition. A draw could be enough for the Ethiopians depending on the result of South Africa's game with Botswana on the same day.
Ethiopia, which has never been to the World Cup, leads the group by two points ahead of the final round after the point totals were readjusted when Ethiopia was stripped of the Botswana win by FIFA.
Senegal's place in the playoffs will be decided in Marrakech against Group J challenger Uganda in their winner-take-all match. Senegal leads that group by a point but hasn't been allowed to play at Leopold Senghor Stadium in Dakar after being punished for a riot at an African Cup qualifier against Ivory Coast late last year.

Read more here: http://www.islandpacket.com/2013/07/31/2605219/decisive-car-ethiopia-qualifier.html?#storylink=cpy




Read more here: http://www.islandpacket.com/2013/07/31/2605219/decisive-car-ethiopia-qualifier.html?#storylink=cpy




Read more here: http://www.islandpacket.com/2013/07/31/2605219/decisive-car-ethiopia-qualifier.html?#storylink=cpy

Read more here: http://www.islandpacket.com/2013/07/31/2605219/decisive-car-ethiopia-qualifier.html?#storylink=cpy

UN Helicopter With Russian Crew Crash-Lands in Ethiopia

UN Helicopter With Russian Crew Crash-Lands in Ethiopia

Mi-8 helicopter
23:53 31/07/2013
Tags: helicopter crashMi-8Ethiopia


MOSCOW, July 31 (RIA Novosti) – A United Nations helicopter with a Russian crew crash-landed in Ethiopia on Wednesday, a Russian Embassy official said, adding that all four crewmembers were alive but three were in a serious condition.
All of the crewmembers are at a hospital in Addis Ababa, Pavel Temnenko, deputy head of the embassy’s consular section, told RIA Novosti.
A representative of the company that owns the Russian-made Mi-8 helicopter, which was reportedly being operated under contract with the UN, told RIA Novosti that the craft was en route from Djibouti to Ethiopia when it made a “hard landing.”