Sunday, May 18, 2014

የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች የግንቦት 9, 2006 የፍርድ ቤት ውሎ

zone9jpgl-3250490_p9
ዛሬ በጊዜ ቀጠሮው መሰረት ፍርድ ቤት ቀርበው የተነበሩ ስድስቱ ታሳሪዎች ላይ ሁሉም የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል፡።
ፓሊስ ለምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ጠበቆቹ እስካሁን በተደረገው ምርመራ ከአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው ከመባሉ ውጪ የተገኘ ማስረጃ እነደሌለ ያ ደግሞ በህግ የተከለከለ ወንጀል እነዳልሆነ ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት ለደምበኞቻቸው ዋስትና እነዲሰጥ ጠይቀዋል፡።
ፓሊስ በመልሱ መንግስት እነዚህ አሜሪካን እና እንግሊዝ የሚገኙ አለም አቀፍ የሰብአዊ ድርጅቶች የሚሰሩትን ስራ መንግስት አንደማይቀበለው የተናገረ ሲሆን እስካሁን በደረሰበት ፍንጭ መሰረት ለሽብር ወንጀል የሚጠቁም ነገር እነዳለው የትኛው የሽብር ድርጅት እነደሆነ ግን ለመናገር ምርመራው ይበላሽብኛል ሲል ተጨማሪ ግዜው እንዲፈቀድለት ጠይቋል ፡፡ፓሊስ የታሳሪዎቹ ግብረአበሮች ፓሊስን እያስፈራሩ ነው ያለ ሲሆን ፍርድ ቤቱ እስካሁን ፓሊስ ምስክሮችን በማሰባሰብ ረገድ ፓሊስ ምን ላይ እንደደረሰ ጠይቆ ፖሊስ ያልተያዙ ግብረአበሮቻቸው ምስክሮቹን እስፈራሩብኝ ነውም ብሏል፡፡
ጠበቆች በመልሱ ፓሊስ ምስክሮችን በፈለገ ጊዜ አስሮ መጠየቅ እነደሚችል ቢያነሱም ገብረአበሮቹ አድራሻ እነዲቀያይሩ እየተነገራቸው ለመያዝ አልቻልኩም ሲል ምክንያት አቅርቧል፡፡
ጋዜጠኛ አስማማው በተደጋጋሚ ወደ ምርመራ እየተጠራሁ የዞን 9 አባልነትህን እመን የምታውቀውን ተናገር ስለዞን 9 ታውቃለህ ተናገር እያሉ ከፍተኛ ጫና እንዳሳደሩበት እንባ እየተናነቀው የተናገረ ሲሆን የዞን ዘጠኙ አጥናፍ ከሌሊቱ ስምንት ሰአት ጭምር ወደ ምርመራ እየተወሰደ ድብደባ እንደተፈጸመበት ገልጿል፡፡ ፍርድ ቤቱ በታሳሪዎቹ አያያዝ ላይ የሰጠው ምንም ትእዛዝ የለም፡፡
ዞን ዘጠኝ የዞን ዘጠኝ አባላት ምንም አይነት የወንጀል ተግባር ላይ ተሰማርተው እነደማያውቁ አሁንም እያረጋገጠ የክሱ ፓለቲካዊነት ግልጽ በመሆኑ አባል ጦማርያኑ እና ወዳጅ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ አንዲፈቱ አሁንም ጥሪውን ያቀርባል፡፡
Source: Zone9

No comments: