እነሆ ምላሻቹህ
(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)
በቅርቡ “የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ የቅሱፋን?” በሚል ርእስ አንድ ጽሑፍ መጻፌ ይታወሳል፡፡ የማስፈራሪያና የዛቻዎቹን ትቸ በርካታ ወንድሞች የመቃወሚያ አስተያየታቸውን አድርሰውኝ ነበር፡፡ ከእነርሱ መሀል አንደኛው የሁሉንም ባካተተና ሰፋ ባለ መልኩ ጽፎልኛል፡፡ ከዚህ አንጻር ለእርሱ መመለስ ለሁሉም እንደመመለስ ነውና አስተያየት የሰጣቹህኝ ወንድሞች ሁሉ በዚሁ አንጻር እዩትና ምላሻቹህን ውሰዱልኝ፡፡ በእውነት እውነትን ለመረዳት የመሰላቹህንም ለመግለጽ ስለተጋቹህ ሳላመሰግንህ አላልፍም፡፡ ነገር ግን እባካቹህ ስታነቡ ልብ ብለቹህ አንብቡ ካነሣቹሀቸው ጥያቄዎች የብዙዎቹ እዚያው ላይ መልሳቸው በበቂ ተገልጾ ያለ ነበር፡፡ በእርግጥ ደግሞ ምላሽ የሚያሻቸው ጥሩ ጥሩ ጥያቄዎችንም አንሥታቹሀል ምላሻቸውም እነሆ፡-
ወንድሜ ከ1928-1933ዓ.ም. በነበረው የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ወቅት በየካቲት12-1929ዓ.ም. ለፈጃቸው ከሕፃናት እስከ አረጋዊያን ለተፈጁት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ወገኖቻችን የመታሰቢያ ሐውልት ከቆመላቸው በአሩሲና ሔጦሳና በሐረር ጨለንቆ ተጎጂ ለሆኑ ወገኖቻችንስ ሐውልት ቢቆምላቸው ችግሩ ምንድን ነው? መብታችንስ አይደለም ወይ? ብለህ ጠይቀሀል እዛው ላይ በሰፊው ተገልጧል እንዴት እንዳልተረዳኸው ገርሞኛል ልብ ብለህ አንብብ፡፡ ሲጀመር ይህ ተፈጽሟል የተባለው ግፍ እመነኝ ፍጹም ፈጠራ ነው፡፡ ለምን እቦታው ሔደህ ታሪክ የሚያውቁትን የኦሮሞ ሽማግሎችን አትጠይቅም? ይሔንን የሚልህ አንድ እንኳን ታገኛለህ? በጠላት ለትፋት ዓላማ የተሰበኩት ካልሆኑ በስተቀር እውነቱን የሚናገሩቱ አንዳቸውም እንኳን ተፈጽመዋል አይሉም፡፡ እንዳንተ ያሉ የዋሀንን ለመመረዝ የተፈጠረ የጠላት ወሬ ነው፡፡ ይሄንን ስልህ ግን የተቻለውን ያህል የኢትዮጵያን ግዛት ለመመለስ ዐፄ ምኒልክ በዘመቱበት ወቅት የሄዱት ከእንቢተኞችና ከከሀዲያን ጋራ ተዋግተው ግዛቷን ለመመለስ እንጅ ለስብከት አይደለምና በጦርነቱ የተገደሉ የሉም እያልኩህ አይደለም፡፡ እኔ እያልኩህ ያለሁት ግን ለእኩይ ዓላማው ሲል ፋሽስት ጣሊያን በዚህ የታሪክ እውነታ ላይ መርዘኛ መርዘኛ የፈጠራ ወሬ ጨምሮበታል ነው፡፡ እነደ ምታየውም የእሱ ቡችሎች (ልጆች) ወያኔ ኦነግና ሻቢያ ሌሎችም የሱን ድርሰት ድርሰት እንደሆነ እያወቁም በሚገባ አስፋፍተው ተጠቅመውበታል እየተጠቀሙበትም ይገኛሉ፡፡
በታሪክ እንደምታስታውሰው ፋሽስት ጣሊያን ኦሮሞዎችን በአማራው ላይ ለማነሣሣት ያላደረገው ጥረት አልነበረም፡፡ ኦሮሞዎችን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዳለ በዘር በሃይማኖት በሞያ(በሥራ) ሳይቀር እየከፋፈለ አንድነታችንን ለማሳጣት ጥንካሬያችንን ለማድከም ለመከፋፈልና እንደምንመቸው ለማድረግ በሰላይ ሚሲዎኖቹና በአሳሾቹ አማካኝነት የፈጠራ ድርሰት እያስዘጋጀ በአሩሲና ሐረር ተፈጸመ እንደተባለው ያሉ አእምሮን የሚመርዙ ቂም በቀልን እስከወዲያኛው የሚተክሉ ክፉ ክፉ መርዘኛ የፈጠራ ወሬዎችን እየፈጠረ ይቀሰቅስበት ያነሣሣበት ነበር፡፡ በወቅቱ ብዙ የኦሮሞ ሽማግሎች ይሄንን በመቃወምና እውነቱን በማጋለጣቸው የታሰሩና የተገደሉ ሁሉ ነበሩ፡፡ ፋሽስት ይሄንን ሲያደርግ በወቅቱ ለሚያገኝበት ወቅታዊ ጥቅም ብቻ አስቦ አልነበረም፡፡ ነገር ግን እንደጠላትነቱ ለዘለቄታው ኢትዮጵያን የችግር ማጥ ውስጥ ለመዝፈቅም እንጅ፡፡ እስኪ ፋሺዝም የነበረውን የአገዛዝ ስልት (ስትራቴጂ) የሚያትቱትን መጻሕፍት አንብብ? ሁሉንም እዚያው ትረዳዋለህ፡፡ የፋሽስት ጣሊያንን እርኩስነት አረመኔነት ክፋት ሸረኝነት እንዲህ በቀላሉ ለመግለጽ በጣም ከባድ ነው፡፡ አንድ መረዳት ያለብህ ነገር ቢኖር ፋሺስት ሀገራችንን ከመውረሩ በፊትና ከወረረም በኋላ አምስት ዓመታት ሙሉ ሲሠራ የኖረው ሌላ እንዳይመስልህ እንዲህ ዓይነቱን ሸር ሲተበትብ ሲሸርብ ሲያሴር እንጂ፡፡ ለዚህ እኩይ ሴራቸው ዐፄ ምኒልክን ሰለባ ያደረጉበት ምክንያት አድዋ ላይ በእግዚአብሔር ኃይል ድል ስለነሷቸውና በዓለም መድረክ ላይ ስላዋረዷቸው በዚያ ክፉኛ በማቄማቸው ነው፡፡ ይሄ ብቻ አይደለም በእሳቸው ዙሪያ እንዲሁም በአጠቃላይ በሀገራችን ታሪክ ከጥንት ጀምሮ የታሪክ ጸሐፊ ነኝ የሚሉ ሚሲዮናዊ ሰላዮችና አሳሾች ሌላ ብዙ የስም ማጥፋት የፈጠራ ወሬዎችንም ዘርተዋል እውነትን በትክክል የጻፉት ከዐሥር አንድ እንኳን አይገኙም፡፡
እውነቱ ግን ዐፄ ምኒልክ እንኳን ለወገናቸው ይቅርና ያን ያህል ግፍና ክፋት ለፈጸመው ለጠላት ፋሽስት ጣሊያን ምርኮኞች እንኳን የሚጨክን አንጀት አልነበራቸውም የእኛን ጸሐፍት እንኳን ባታምን ባዕዳን የታሪክ ጸሐፍት ስለ አድዋ ጦርነት የጻፏቸውን መጻሕፍት ብትመለከት የሩህሩህ መጨረሻና በዚህ ዓይነቱ ጉዳይ የተለዩ ፍጥረት መሆናቸውን መረዳት በቻልክ ነበር፡፡ አንተስ ስታስበው ዐፄ ምኒልክ በኦሮሞዎች ላይ እንደዛ ዓይነት ጭካኔና ጥላቻ ያላቸው ቢሆኑ ኖሮ በዚያ ወቅትና ከዚያም በፊት ራስ ጎበና ዳጬን የጦራቸው አበጋዝ (ዋና ኃላፊ) ያደርጉ ነበር? ዘምተው ከተመለሱም በኋላ ማርከው ካመጧቸው ውስጥ አንድ ሁለቱን ብንጠቅስ እነ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴን በፊታውራሪነት እነ ባልቻ አባነብሶን በደጅ አዝማችነት ሌሎቹንም እንደዚያው ይሾሙ ይሸልሙ ነበር ብለህ ታስባለህ? እባክህን ከሀገር ተላቶች መርዘኛና አሳሳች የፈጠራ ወሬ እራስህን ጠብቅ ዓላማውም ይግባህ፡፡
ወደ ጥያቄው ስመለስ የካቲት 12 1929ዓ.ም. ያለቁት ወገኖቻችን ያለቁት የተፈጁት ለኢትዮጵያ ነጻነት፣ ክብር፣ ሉዓላዊነት ሲሉ እንጂ እንደ አሩሲና ሐረር ላይ በጦርነቱ መጀመሪያ ፋሺስት ከዚያም ወያኔና አጋሮቹ ኦነግ ሻቢያ ተቀብለው እያናፈሱ እንዳስወሩት የኢትዮጵያ አካል አንሆንም ለመንግሥት አንገብርም በማለታቸው በግፍ ተፈጁ ብለው ፈጥረው እንደሚያወሩላቸው ይህ መፈጸሙ እውነት ቢሆንም እንኳ “ልብ በል እውነት ነው እያልኩ አይደለም” ኢትዮጵያን ለማፍረስ አንድነቷን ለመበታተን ሉዓላዊነቷን በመዳፈር ለማዋረድ ባለመሆኑ አዎ በትክክልም ሐውልት ሊቆምላቸው ይገባ ነበር ቆሞላቸዋልም፡፡ ሁለቱ ፍጹም የተለያዩና የማይገናኙ ነገሮች ናቸው፡፡ ክብር የሚገባው ከራሱ በላይ ለሀገርና ለወገን ላሰበ ለሉዓላዊነቷ ለነጻነቷ ለክብሯ ለተሠዋ እንጂ በተቃራኒው ተሰልፎ ለጠላት ላደረ ሀገርን ለከዳ ለወጋ አይደለም፡፡ በዚህ ዓይነት እኮ ለፋሽስት ጣሊያንና አብረው ተሰልፈው ለወጉን ለባንዳዎቹም የመታሰቢያ ሐውልት ይቁምላቸው በክብር እናስባቸው ልንል ነው? ይሄ ይሆናል እንዴ? ሐውልት እኮ ሲሠራ የከበረ ዓላማና ታላቅ ትርጉም አለው ዝም ተብሎ ለማንም አይደለም የሚሠራው፡፡ እናም ጉዳዩ የአሸናፊና የተሸናፊ ጉዳይ ሳይሆን የእውነትና የውሸት፣ የእምነትና የክህደት ጉዳይ ነው የሠሩትና ዓላማቸውም ሀገርን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ወይስ የሚጎዳ የሚያፈርስ የሚለው ነው የሚታየው እሽ? ወያኔ ይሄንን የሚያደርግበት ምክንያት ኢትዮጵያን በተመለከተ እንዲህ ዓይነት የጥፋት ዓላማ ስላለው ነው፡፡
ከዚሁም ጋራ አያይዘህ ለጄኔራል ግራዚያኒ በሀገሩ ላይ ሐውልት ሲቆምለት ተቋውሞ ያሰሙ ኢትዮጵያዊያንን ተቋውሞ ማሰማታቸው ተችተሀል ነቅፈሀል፡፡ ጨፍጫፊ እያልክ ጭፍጨፋን አጥብቄ እቃወማለሁ እያልክ በሌላ በኩል ደግሞ ታፈርሰዋለህ፡፡ እንዴት ነው “የጠላቴ ጠላት” ሆኖ ነው ሒሳቡ? እዚህስ ላይ ሰብአዊነትህ እንዴት ሳይታይ ቀረ? ምን ነው ወንድሜ ያውም ለፋሽስት ጣሊያን? ለማንኛውም እኛ ኢትዮጵዊያን ለግራዚያኒ የቆመውን ሐውልት የተቃወምነው ከሕፃናት እስከ አረጋዊያን ያሉ ወገኖቻችንን በግፍ ስለጨፈጨፈ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ፋሺዝምና ተዋናዮቹ ወንጀልና ወንጀለኛ ተደርገው ስለተፈረደባቸው የፋሺዝም ተዋናዮችን ማሰብ መደገፍ ወንጀል ስለሆነም ነው እሽ? አንተም እንደኢትዮጵያዊ ባይቆጭህ እንኳን እንደ ዓለም አቀፍ ዜጋ፣ እንደ የሰው ልጅ አብረኸን ልትቃወም በተገባህ ነበር፡፡ በእርግጥ በጠባብነትና አመክንዮ አልባ ዘረኝነት ከተጠቃህ እንዲህ ብሎ ለማሰብ ሊከብድህ ይችላል፡፡ ይህችን ነገር ተጠንቀቅባት፡፡
ወደ ሌላው ጥያቄህ ሳልፍ እኛ ኦሮሞዎቹ መቸ ነው እርስ በእርሳችን ተጨፋጭፈን ጡትና እጂ የተቋረጥነው? ከሆነም አያገባህም የራሳችን ጉዳይ ነው ብለሀል፡፡ ስንቱን ልጥቀስልህ? እስላሞቹ እስላም ያልሆኑትን እንደጨፈጨፉ፣ በሌላም ምክንያት ልክ ሰሞኑን ጉጂና ቦረናዎች እንዳደረጉት ይፋጁ እንደነበር እንዴት አታውቅም እንደ ራስ ጎበና ዳጬ ያሉ እድሜ ዘመናቸውን የደከሙት ይሔንን የእርስ በእርስ ችግር ለመፍታት ሲሯሯጡ አይደለም እንዴ? ደሞስ እንዴት አያገባህም ትለኛለህ ወገኖቸ ኢትዮጵያዊያን አይደሉም እንዴ? እንዴት ነው የምታስበው?
ሌላኛው ጥያቄህ ደግሞ ኦሮሞ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ ከሆነ፤ የራሱ(የእኔ የአምሳሉ) ደብተራዎቹ ከጻፉት ብለህ (የግራኝ ወረራ ገጽ 803) ጠቅሰህ ከግራኝ መሐመድ ወረራ በፊትም “በጋላ” ስም አይሁን እንጅ በሌላ ነገድ ስም ከዐፄ ልብነ ድንድል (ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን) በፊትም በቤተ መንግሥት አካባቢም በኢትዮጵያ ምድርም ነበሩ ይላል ብለሀል፡፡ ስምም ጠቃቅሰሀል፡፡
ምን መሰለህ ነገሩ እንዲህ ነው ይሔ ማለት በሌላም ስም ሆነ በምን ኦሮሞዎቹ በዚያ ዘመን አሁን ባለችዋ የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ነበሩ ማለት አይደለም፡፡ የሚገርምህ ዐፄ ዳዊት ተንባላት ግብጽን ተቆጣጥረው በነበረበት ጊዜ የግብጽ ክርስቲያኖች እንዲታደጓቸው የእርዳታ ጥሪ ባቀረቡላቸው ጊዜ ከጦር አበጋዞቻቸው ጋር የመከሩት ስብሰባ ያደረጉት ሞቃዲሾ ላይ ነበር፡፡ ከተማዋ ሞቃዲሾ የሚለውን ሥያሜ ያገኘችው መቀደሻ ከሚለው የግእዝ ቃል ነው፡፡ እዚያች ከተማ ውስጥ እስከ ሰባት የሚደርሱ አብያተክርስቲያናት ነበሩ፡፡ ዛሬም ድረስ ፍርስራሻቸው እንዳለ ይነገራል፡፡ በዚያ ጊዜ እዚያ የነበሩ ወገኖቻችን ዘሮች ዛሬም ድረስ እቦታው አሉ፡፡ ታንዛኒያ ብትሔድ እንደ ባዕድ የሚታዩ እነሱም ምንጫቸውን ከኢትዮጵያ የሚያደርጉ በአንድ ወቅት ለተልእኮ መጥተው እዚያ እንደቀሩ የሚናገሩ በመልክም በምንም ከእኛ የማይለዩ ጎሳዎች እንዳሉ ታውቃለህ? ከፍ ስትልም ወደ ሩዋንዳ ቡሩንዲ ዩጋንዳ “ቱትሲዎችን” ታገኛለህ፡፡ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ስትሔድም ተመሳሳይ ታሪክ የሚናገሩ ማሊ፣ ኒጀር፣ ቻድ ታገኛለህ፡፡ ምን ልልህ ፈልጌ ነው፤ አዎ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን በፊትም እንደጠቀስካቸው ያሉ የኦሮሞ ተወላጆች ኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ፡፡
በዚያ ዘመን ሊገኙ የቻሉትም እንደሚታወቀው የኦሮሞ ብሔረሰብ ከማዳስካር ሞዛምቢክ ከዚያ ታንዛኒያ ከዚያ ኬንያን (ኬኛ) የኛ ብለው ስም አውጥተው ለረጅም ዘመናት እዚያ ቆይተዋል፡፡ እዚያ በነበሩበት ጊዜ መነሻቸውን ኬንያ እያደረጉ ልክ አንተ እንደጠቀስከው 1480 ዓ.ም. “በእርግጥ የጠቀስከው ማስተካከያ አለው የመጀመሪያ ወረራ የሚለው ትክክል አይደለም” “‐‐ Oromo, The first mention of the name “Galla” in The Abyssinian History of the Kings (“Tarika Negest”) is attributed to 1480 A.D. During the reign of Iskander, the Oromo made their first invasion into Abyssinian land and destroyed the monastery of Atones Maryam.” የዚህን ተመሳሳይ ወረራ እያደረጉ አንተ ራስህ እንደጠቀስከው ገዳማትን አብያተ ክርስቲያናትን ያወድሙ ያቃጥሉ ይዘርፉ ሕዝብ በጭካኔ ይጨፈጭፉ ነበር፡፡ ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት መቀመጫውን ማዛወሩ እዚያም በኦሮሞዎቹ ከመጠቃት ባያድነውም መቀመጫውን ከሸዋ ወደ ጎንደር ያዛወረበት ምክንያት ይሄው ነበር፡፡ ታዲያ እንዲህ ዓይነት ጥቃት ይፈጽሙ በነበረበት ጊዜ በመከላከል እርምጃ ተማርከው የሚቀሩ የኦሮሞ ተወላጆች ነበሩ፡፡ እነዚያ አንተ የጠቀስካቸው ከዐፄ ልብነ ድንግል በፊት ነበሩ የተባሉት የኦሮሞ ተወላጆች በእነዚያ ዘመናት ለዝርፊያና ለወረራ መጥተው ተማርከው ከቀሩት አንዳንዶቹ ናቸው እንጂ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልክ አሁን ኢትዮጵያ ብለን በምንጠራት ቦታ አሁን ያለበትን ሥፍራ ይዞ የነበረ ሆኖ አይደለም እሽ? እነ አዛዥ ጫላም በላቸው ሌሎች ለዚያ ሹመት ሊበቁ የቻሉት ጠላት ሆነው ከጦርነት አውድ የተማረኩም ቢሆኑም ከዚያ በኋላ ባሳዩት በታማኝነታቸውና በአገልግሎታቸው ብቃት ልክ ዐፄ ምኒልክ ማርከው ካመጧቸው በኋላ እነ ፊት አውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴን እነ ደጃዝማች ባልቻ አባ ነብሶን ሹመት ሰጥተው እንዳደረጉት ሁሉ ያኔም እንደዚሁ ይደረግ ነበር ወዳጀ፡፡ ጠላት ነው ስም የሚያጠፋው እንጂ አማራ ይሄንን ያህል የሠለጠነ አስተዋይና ብሩክ በእግዚአብሔር ቃል የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ሕዝብ ነው፡፡ ለም የእርሻ መሬቱን አስረክቦ አሳልፎ ሰጥቶ ለእርሻ ቢሉት ለኑሮ በማይመቸው ተራራ ላይ የሰፈረ ምስኪን ሕዝብ፡፡ እስኪ ጠላት ተጨቁናቹሀል ተረግጣቹሀል ተበዝብዛቹሀል የሚላቸውን ብሔረሰቦች የሰፈሩበትን ቦታ ተመልከት ለሙን ሀገር የያዘው ማን ነው? ጠላት እንደሚያወራው አማራ እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ዓይነት የመሬት አሠፋፈር ይኖር ነበር ብለህ ትገምታለህ? እባካቹህ ፈጣሪ ይታዘባቹሀል ግፍን ፍሩ?
በነገራችን ላይ “ጋላ” ማለት ኦሮሞ ማለት እንዳይመስልህ፡፡ እንደቤተክርስቲያን መጻሕፍት ጋላ ማለት አረማዊ ወይም ኢአማኒ ማለት ነው፡፡ ተአምረ ማርያም ላይ ምን የሚል ንባብ አለ መሰለህ ታሪኩ ስለ አንዲት በግብጽ ሀገር ስለነበረች ቤተክርስቲያን የሚናገር ነው፡፡ በዚህ ዘመን የለችም ጠፍታለች ስለ አጠፋፏ ሲናገር ያፈረሷት ጋሎች እንደሆኑና እንዴት እንዳፈረሷትም ያትታል፡፡ አሁን ኦሮሞዎቹ ግብጹ ኖረው ወይም ከዚህ ወደ ግብጽ ሔደው እነርሱ አፍርሰዋት እንዳልሆነ ይገባሀል ብየ እገምታለሁ፡፡ ነገር ግን ኢአማንያን አፈረሷት ማለቱ ነው፡፡ በሌሎች የቤተክርስቲያን መጻሕፍትም ጋላ የሚለው ቃል ትርጉም እንደዚያሁ ነው፡፡ በመሆኑም “ጋላ” ማለት ኦሮሞ ማለት አይደለም፡፡ ኢአማኒ ማለት እስከሆነ ጊዜ ድረስ የአማራም የትግሬም የጉራጌም የሌላም ጋላ አለ ማለት ነው እንጂ የብሔረሰብ ስም አይደለም፡፡
አንዳንድ የበጌምድርን አውራጃዎች እየጠቀስክ ኦሮሞዎች በእነዚያ ቦታዎች እንደነበሩ ተናግረሀል ልብ ብለህ አላነበብከውም እንጂ እኔም እኮ ተናገሬያለሁ፡፡ ዐፄ ሱስኒዮስ ዐፄ ያዕቆብን ድል አድርገው ሥልጣን ሲይዙ በጦርነቱ እንዲረዷቸው ከወለጋ ላመጧቸው የኦሮሞ ተወላጆች የአብያተ ክርስቲያናትን ርስትና ጉልት ነጥቀው እያከፋፈሉ ሰጡ ብየ ነበር፡፡ እዚያ ቦታ የመገኘታቸው ምስጢር ይሄው ነው ሌላ አይደለም፡፡
ስለኦሮሞ በግብጽ የዩኒቨርስቲ መምህር ፕሮፌሰር መሐመድ ሸምሰዲን የተናገረው ነው ብለህ የጠቀስከውን ጽሑፍ እውነት ነው ብለህ ተቀብለኸው ከሆነ እጅግ ተላላ ሰው ነህ፡፡ በእርግጥ Meroites የተባሉት የኩሽ ነገዶች ናቸው፡፡ እነሱም ዛሬም ድረስ እዚያው እሱ የጠቀሳቸው ቦታዎች ላይ ያሉ የኩሽ ነገዶች ማለትም ቅማንቶች፣ አገዎች፣ ሺናሻዎች፣ ጋፋቶች፣ ዳሞቶች ወዘተ. ናቸው፡፡ አጅሬው ኦሮሞን እየሸረበው ላለው እኩይ ዓላማው መጠቀሚያ ለማድረግ ይቺ “ኩሽ” የምትለዋን የማገናኛ ክር ይዞ ቢስበው ቢስበው ተበጠሰበት እንጅ ሊገናኝለት አልቻለም፡፡ ምክያቱም ሌሎቹ የኩሽ ነገዶች አሁንም ድረስ እዚያው እቦታቸው ያሉ ሆነው እያሉ ኦሮሞ በጌምድር ከነበረ ሴማዊያን በኩሻዊያን ላይ ፈጸሙባቸው ባለው ማፈናቀል ኦሮሞ ከሌሎቹ የኩሽ ነገዶች ብቻውን ተነጥሎ እዚያ ታች ሊወርድ የሚችልበት አንድም አመክንዮ የለምና፡፡ “ኩሽ” የምትል ቃል ስላለች ብቻ በሕንድ ወይም በደቡብ አፍሪካ ወይም ደግሞ በምዕራብ አፍሪካ ያሉ የኩሽ ነገዶች ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ ማለት አይደለም፡፡ ይሄንን እውነት ያለመረዳት ችግር በስፋት አስተውየብሀለሁ፡፡ ኩሽ በተጠቀሰበት ቦታ ሁሉ ኦሮሞ እንዳለ አድርገህ ትቆጥራለህ፡፡ ስለ ሌሎች የኩሽ ነገዶች የተነገረውን ሁሉ የኦሮሞ እንደሆነ ትቆጥራለህ፡፡ ወንድምዬ እንደሱማ አይደለም፡፡ እንደሱማ እኮ ከተባለ የሴም፣ የካም(ኩሽ)፣ የያፌት ነገዶች አባቶች እኮ የኖኅ ልጆችና ወንድማማቾችም ናቸው እኮ፡፡
ይህ የጠቀስከው ሰው በአሁኑ ሰዓት ምን እየሠራ እንዳለ በሚገባ የምታውቅ ይመስለኛል፡፡ ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ላላት የጥፋት ተልእኮ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ያለ አሸባሪ ነው፡፡ ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ገንጥሎ ከሱዳን ጋር በመቀላቀል “የኩሽ ምድር” ሲል የሚጠራውን ሀገር እንመሰርታለን ይላል፡፡ በርካታ ሐሰተኛና ጥፋትን የሸረቡ ጽሑፎችን በኦሮሞ ሕዝብ ዙሪያ ጽፏል፡፡ አንተ እንደጻፍክልኝ ሁሉ ይህ ሰው ጽፎልኝ ነበር፡፡ ከጽሑፎቹ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ቅንጣት ታክል እንኳን ለኦሮሞ ሕዝብ ክብር እንደሌለው ነው፡፡ ይሔን ግጥም አንብበው፡፡ እውን የኦሮሞ ሴት እንዲህ ትታሰባለች?
I got a good laugh out of your unwise and cold,
by repeated story which abba Yirgu told,
when I was a child,
the sad story that a White man is God.!
by repeated story which abba Yirgu told,
when I was a child,
the sad story that a White man is God.!
But practically everything you guys have is totally false,
your Calendar and your alphabet is the case,
and your views are narrow,
and all the things you got to borrow,
the story about your Jewish race,
your light skin and fabulous face,
Just tell me what is your’s?
your Maxaaf qidus?
or your history?
or the Awude Negest mystery?
in which your Dabtara father declared,
your Calendar and your alphabet is the case,
and your views are narrow,
and all the things you got to borrow,
the story about your Jewish race,
your light skin and fabulous face,
Just tell me what is your’s?
your Maxaaf qidus?
or your history?
or the Awude Negest mystery?
in which your Dabtara father declared,
“He who slept with Galla women is condemned,
“because he is considered,
unholy and unclean for sleeping with an Animal,
but if she is converted to Amhara, she will be clean”
“because he is considered,
unholy and unclean for sleeping with an Animal,
but if she is converted to Amhara, she will be clean”
that’s why your false God doesn’t thrill me at all,
because it is addictive cocaine,
a poisonous substance that destroyed your brain!
because it is addictive cocaine,
a poisonous substance that destroyed your brain!
Hence, worshiping a White man would bore me,
and I think it is also a sin,
to destroy your brain,
like those low life and insane,
the Pentecostalist lame!
Your situation too is the case,
you lack confidence and faith,
but you think you can fly with some White guy,
Up! …up,… way… up!.. in the sky,
shouting……….
Abunee… zeb.. Semayaat,..
Yitqede Simikee..
Timxaa feqaadikee..
Kemahuu.. bee seemayii..
feeling high!…. way high!
with Jesus.. the addictive cocaine!
and I think it is also a sin,
to destroy your brain,
like those low life and insane,
the Pentecostalist lame!
Your situation too is the case,
you lack confidence and faith,
but you think you can fly with some White guy,
Up! …up,… way… up!.. in the sky,
shouting……….
Abunee… zeb.. Semayaat,..
Yitqede Simikee..
Timxaa feqaadikee..
Kemahuu.. bee seemayii..
feeling high!…. way high!
with Jesus.. the addictive cocaine!
አየኸው አይደል ድንቁርናውን? እስኪ አንተን ልጠይቅህ ነጭም በለው ጥቁር ቢጫም በለው ቀይ እንደዚያ ዓይነት የሰው ዘር እንዲሆን እራሱን የፈጠረ አለ? ነጮች ነጭ የሆኑት ነጭነትን ፈልገው አራሳቸውን ነጭ አድርገው ፈጥረው ነው? ጥቁሩም ቢጫውም ቀዩም እንደዚያው፡፡ እኛም ያለንን የቆዳ ቀለምና እሱ እንዳለው ልዩ ድንቅ ውብ ገጽታ እኛ ለእኛ መርጠን ፈልገን የሆነው ያደረግነው አይደለምና በዚህ ልንወቀስ ወይም ልንመሰገን አይገባም፡፡ አልገባውም እንጂ እሟገትለታለሁ የሚለው የኦሮሞ የቆዳ ቀለምና የፊት ገጽታ ከእኛ የተለየ አይደለምና የሰደበው እናንተንም እንደሆነ ልብ በል በዚህም ለኦሮሞ አለኝ የሚለው ተቆርቋሪነት የውሸት መሆኑን ተረዳ፡፡ እኛም ብቻ ሳንሆን ሌላውንም፡፡ አንተ ነጭ ነህ ጥቁርን አንተ ጥቁር ነህ ነጭን ወይም ሌላን አትውደደው አታክብረው ብሎ ጥላቻን መስበክ ከባድ ድንቁርና ነው የሰው ልጅ መመዘን ያለበት በሥራው በአስተሳሰቡ ብቻ ነው፡፡
ዘረኝነት የእኩያን ሰዎች ችግር እንጂ የፈጣሪ አለመሆኑንም አስረግጨ ለመናገር እወዳለሁ፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ለምን ነጭ ሆነ ስለሆነም መመለክ አይኖርበትም አይባልም፡፡ እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹህ ክርስቶስ በሁሉም የሰው ዘር ሁሉ የዘረኝነት ጥያቄ ሳይነሣበት ያለልዩነት እንዲመለክ ከነማን መወለድ ነበረበት? ከጥቁሮቹ? ከቢጫዎቹ? ከቀዮቹ? ወይስ እንደ ውኃ ቀለም አልባ ሆኖ መምጣት ነበረበት? የግድ ደግሞ ከሰው መወለድ እንደነበረበት አትርሱ፡፡ ከነጭ ሳይሆን ከሌሎቹ ቢወለድ ኖሮ በእኩያን ሰዎች አሁን እየተነሣ ያለው ቅሬታ የዘረኝነት ጥያቄ ሳይነሣበት መመለክ ይችል ነበር? ስለዚህ ይህ ችግር የእኩያን እንጂ የፈጣሪ አይደለም፡፡ ፈጣሪ የሚያውቀው አንድ አዳምን መፍጠሩንና ሁላችንም የሱ ልጆች መሆናችንን ነው፡፡ ልዩነቱን የፈጠረው የአየር ንብረት ነውና ጥቁሩም፣ ነጩም፣ ቢጫውም፣ ቀዩም እንዲያ በመሆኑ ሊወቀስ ሊከሰስ አይችልም አይገባምም፡፡ ከሌላ ወስዳቹህ ነው እያለ የጠቀሳቸው የሥልጣኔ ፍሬዎቻችን የኛ የራሳችን ለመሆናቸው ከዚህ ቀደም በዚሁ መካነ ድር የጻፍኳቸውን ጽሑፎች ተመልሰህ ተመልከት፡፡ ለሱም ሊገባው በሚችል አገላለጽ መልሸለታለሁ ተስፋ አደርጋለሁ የሚረዳ ጭንቅላት ካለውና የዐዋቂ አጥፊ ካልሆነ ይማርበታል፡፡
ስለ መስለብ የተናገርከው ይመስለኛል አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች የመስለብና ጡት የመቁረጥ ባሕል ያለው ኦሮሞ እምጂ አማራ አይደለም የሚለውንና እኔም ይህ ግፍ የተፈጸመው እዚያው እርስ በእርሳቸው ሲጫረሱ ነው የተፈጸመው ላልኩት የመልስ ምት መሆኑ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንተ ከገለጽከው ጋራ ፍጹም የተለየ ነው፡፡ ምክንያቱም አንተ በማጣቀሻነት እንደገለጽከው የሚሰለበው ሰው የሚሰለበው በቤተሰቦቹ ሙሉ ፈቃድ እንጅ በግዳጅ አይደለምና፡፡ የተሰላቢዎቹ ቤተሰቦችም ከሚያገያገኙት የተለያየ ዓይነት ጥቅም የተነሣ ልጆቻቸው ለዚህ በመመረጣቸው እንደ እድለኛነትና እንደ ክብር እነደሚቆጥሩት ገልጸሀል፡፡ ይህ የሚፈጸምበት ምክንያትም እነዚያ የተመረጡ አገልጋዮቹ በዝሙት እንዳይረክሱ ቅድስና እንዲጠብቁ፣ በተልእኮ ላይም ሴትን እያሉ ወደ ኋላ የሚጎትታቸው እንቅፋት መሰናክል እንዳይኖር ለአገልግሎት እንዲሰሉ እንዲሳለጡ እንደሆነ ማጣቀሻህ በራሱ አማርኛ ገልጧል፡፡ የሆነ ሆኖ ግን ጉዳዩ በቤተሰቦቻቸው መልካም ፈቃድ የሚፈጸም ቢሆንም እንኳን ፍጹም ትክክል አይደለም፡፡ ይህ ድርጊት መፈጸም የተጀመረውም ሕግና ሥርዓት ጠፍቶ በነበረበትና ዐፄ ቴዎድሮስ ድራሹን ባጠፉት በዘመነ መሳፍንት ነው፡፡ እረጂም ታሪክ ያለውና እንደ ባሕል ሊቆጠር የሚችል አይደለም፡፡
በተቀረው ስለ አማራ የት መጣ ማን ነው የሚለው ላይ አንጋደህ ስለጻፍክ ማስተካከያ ልሰጥህ ነበር በጣም ስለረዘመ ከሰሞኑ በሌላጽሑፍ ጠብቅ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ደብተራ አምሳሉ
amsalugkidan@gmail.com
http://www.goolgule.com
No comments:
Post a Comment