እስክንድር ነጋ እስርና ወከባ (ጫና)
በግርማ አንድሪያስ (ኔዘርላንድ፡ ኣምስተርዳም)
''....ጋዜጠኞችና ኣስታሚዎች በጥብቅ መታሰርና በገንዘብ መቀጣት የጀመሩት የፕሬስ ኣዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ከሶስት ወር በኋላ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የካቲት 1984 በአትዮጵያ ኣቆጣጠር። ታስረው በፕሬስ ህጉ የተከሰሱና ለመጀመሪያ ጊዜ በፍርድ ቤት ተከራክረው ነጻ የወጡት፣ በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደረው የአዲስ ዘመን ጋዘጣ ኣዘጋጆች ናቸው። ኣዘጋጆቹ የታሰሩትና የተከሰሱት በጋዜጣው ላይ በ ኢትዮጵያ የዲሞክራሲን ጎጂና ጠቃሚ ገጽታዎች የሚዳስስ ጽሑፍ በማውጣታቸው ነው።''
ይህን ያገኘሁት ተድባበ ጥላሁን (ዲማፅ) ''የኢትዮጵያ የግል ፕሬስ አድገትና ችግሮቹ'' በሚል ኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ ጽሑፍ ክፍል ኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርስቲ 1990 '' ካቀረበው ጥናታዊ የመመረቂያ ጽሑፍ ያገኘሁት ነው።
በ ነጻው ፕሬስ ኣባላቶች ላይ ዱላውን ለማዝነብ የተሰራው የመጀመሪያ ድራማ ይህን ይምሰል አንጂ፣ በውቅቱ ድራማ መሆኑን ያስተዋለው ኣልነበረም። አንዲያውም በዚህን ወቅት የ '' ኣዲስ ዘመን ጋዜጠኞች ካለማንም ቅድመ ሁኔታ የመጻፍና የመናገር መብታቸው ይጠበቅ'' በማለት የነጻው ፕሬስ ኣባላቶች ጮኽውላቸዋል። በወቅቱ መንግስት የራሱን ሰዎች አንደሚፈታቸው ኣውቆ... የከተታቸው በመሆኑ፣ በሚጮሁት የ ነጻው ፕሬስ ውጤቶችና ኣባላቶች ላይ ተሳልቆባቸዋል። ኣላግጦባቸዋልም። ታስረው የተፈቱት የመንግስቱ ልሳን ኣዘጋጆች የነበሩትም፣ የነጻው ፕሬስ ኣባላቶች ላይ ብአ ር ለመቀሰር ጊዜ ኣልወሰዱም። በዚያን ጊዜ ከመጀመሪያዎቹ ሰለባዎች የነበረው... አስክንድር ነጋ ነበር። አስከኣሁንም መከራው ከላዩ ላይ ኣልወረደም።
ተድባበ ጥላሁን (ዲባጽ):- የብዙ ጋዜጠኞችን አንግልት ስቃይና ውጣ-ውረድ በግንባር አየቀረበ ጊዜ ወስዶ ባዘጋጀው ጥናታዊ የመመረቂያ ጽሑፍ ''...ከዚህ በታች ባለፉት 6 ዓመታት ከ 22 ጊዜ በላይ የታሰረና የተፈታ፣ በ ዋና ኣዘጋጅነት፣ በኣሳታሚነት የሰራና በኣሁኑ ውቅት በኣሳታሚነት የሚሰራ ጋዜጠኛ የደረሰበትን ለናሙናነት አንመልከት'' ይላል ''HABESHA'' የሚባለውን የ አንግሊዝኛ ጋዜጣ በዋና ኣዘጋጅነት በኣስታሚነት አየሰራ፣ ''ኣበሻ'' በሚል ስም የ ኣማርኛ ጋዜጣ ለማሳተም በዝግጅት ላይ አያለ ነበር ጥር ወር 1988።
ቃለ መጠይቅ አስክንድር ነጋ
''...ጠዋት ኣሰሩኝና ባዶ ቤት ኣስቀመጡኝ ...ሌሊት ፮ ሰዓት ላይ በሩ ተንጓጓ፣ መብራቱ ጠፋ.... ኣንድ ሰው በብርድ ልብሽ ተሸፋፈን ኣለኝ። ግን ላየው ኣልቻልኩም። ጭንቅላቴን በብርድ ልብስ ጠመጠመው... ትከሻየን ኣንጠለጠለና ከክፍሉ ኣስወጣኝ። ኣቅጣጫውን ባላውቅም ፎቅ ላይ ወደ ኣንድ ክፍል ኣስገባኝ። የሌላ ሰው ድምጽ ይሰማኛል። ቁጭ ኣደረጉኝና በመጀመሪያ አጄን የፊጥኝ በካቴና ኣሰሩኝ... ኣስተኙኝና በኮረንቲ ገመድ ይመስለኛል አግሬን ኣሰሩኝ። ብቻ ኣንድ ሲስተም ነበር...በኋላ ብድግ ሲያደርጉኝ አግሬ ተነሳላቸው...ውስጡን በኣለንጋ መደበደብ ጀመሩ...ለስንት ጊዜ አንደሆነ ኣይታወቅኝም በኋላ ኣቁመው ብድግ ኣድረጉኝ። ''ኣክችዋሊ'' ሰውነቴ ኣይችልም ነበር...ሁዋላ ኣንጠልጥለው ክፍል ጣሉኝ...ጠዋት ሃኪም መጣ። ከዛ አስካገግም ድረስ ወር ሙሉ ከምንም ዓይነት ሰው ጋር ሳልቀላቀል ሰው ስላይ...ከተሻለኝ በሁዋላ ፍርድ በት ወሰዱኝ። ፍርድ ቤቱ ሰውነቴ መጎዳቴን ኣይቶ ለቀቀኝ። በዚህም ጉዳይ ቃል ኣልሰጠሁም።ክስም ኣልተመሰረተብኝም። ከዛ በኋላ ስራ ኣቆምኩ። ''
ከላይ ያነበብነው ከ 12 ጊዜ አስር በሁዋላ፣ ኣጥኚው አስክንድርን ቃለ መጠይቅ ኣድርጎት የተናገረው ነው... ይህ ሁሉ በዚህ ወጣት ጋዜጠኛ ላይ የሆነው ከጅምሩ ነው።አስክንድር በራሱ ላይ ብዙ ጉዳቶች ደርሶበታል። ግን በግሉ የሚደርስበትን ኣይናገርም። ይልቅስ በ ሃገሩ የሚደርሰው ስንዝር ጉዳት... ያመዋል። የወገኑ ሰቆቃ... ያናግረዋል። ያጽፈዋል። ሌላ ዓላማ ያልነበረው አስክንድር ያልተናገረውን ...ኣንድ ህመም አኔም ላክልበት።
ሰባ ደረጃ ...
በነበረን ቢሮ አስክንድርም የራሱን ስራ አኔም የራሴን ስራ አሰራለሁ። ፍቃድ ኣውጥተን በግልጽ ከምንሰራው ስራ የተለየ ኣጀንዳ ኣልነበረንም። አስክንድር ከዚህ በፊት በለቀቀው ጽሑፉ አንደገለጸው ሁሉም ነገር ጥድፊያ ነበር። አንዲያም ተጣድፈን ሌሊቱ ኣይበቃንም ነበር። ስለዚህም ማደር የግድ ነው። የብዙዎቹ የነጻው ፕሬስ ውጤቶች ኮምፒውተር ስራ አኔ ዘንድ ሲለሚሰሩ... ከ አነዚሁ ውስጥ ኣንዱ የ አስክንድር ጋዜጣ ነበር። ሃበሻ።
አስክንድር ከጎኔ ሆኖ ይጽፋል። አኔ ከስር-ከስር አስራለሁ። ከዚያም ሊነጋጋ ሲል ወደ ጠዋቱ ...'' አኔ አስክመጣ ይህቺን ሰርተህ ጨርሳት፣ አርግጠኛ ነኛ ለማተሚያ ቤት አንደምንድረስ...''በማለት ስራዎቹን ትቶልኝ ሄደ። አስክንድር በዚያ ጠዋት ሁሌም አንደሚያደርገው 'ሰባ ደረጃ' ን አላይና አታች ስፖርት ለመስራት ነው። የአስክንድር መዝናኛ ከማንኛውም ሰው ጋር መወያየትና ስፖርት ነበርና። ነገር ግን አስክንድር የደከመባቸውን ስራዎች አኔ ብጨርስለትም ማተሚያ ቤት ይዞ ለመሔድ ኣልታደለም። ስፖርት በሚሰራበት ሰባ ደረጃ ላይ አየደበደቡት ነበር።ያለ ብአር ምንም የሌለውን ጋዜጠኛ በስርዓቱ በተሰማሩና የኣጋዚ ሲቪል ለባሾች አጁን ሰባብረው፤ ሁለመናውን አንዳልነበረ ኣድርገው ጣቢያ ነበር የጣሉት።
አስክንድር ግን ስለደረሰበት አንዲህ ያሉ ኢ-ሰብኣዊ በደሎች ቅድሚያ ሰጥቶ ሲያወራ ኣይደመጥም። የ ራሱ በሆኑት የህትመት ውጤቶቹም ቢሆን ብሶቱን ሲያላዝን ኣይስተዋልም። ''ጅራፍ አራሱ ገርፎ አራሱ ይጮሃል'' አንዲሉ... የፕሬስ ኣዋጁ ከታወጀ ከ 1984 ጀምሮ አስክንድር ነጋ በገመድ ይታሰራል፣ በ ኤሌትሪክ ገመድ ይታሰራል፣ በጭለማ ይታሰራል፣ በብርሓን ይታሰራል፣ በብርድ ይታሰራል፣ በጸሓይ ይታሰራል። አስክንድር ግን... ኣይጮህም!...ያሰሩት ይጮሃሉ... የሚገርፉት ያለቅሳሉ... ፊት ለፊት አየተራመዱ ይገላመጣሉ።ጥላቸውን ኣያምኑም። አንቅልፋቸው ህልም- የለውም። የዶሮ አንቅልፍ ነው። ይሄን ጊዜ ታዲያ አስክንድርን ኣስታውሰዋለሁ። በተፈረደበት አስር ቤት ሆኖ፣ ያሰሩትን በፈገግታ ሲመለከታቸው። በጭለማ ውስጥ ኣይደል ብርሓን መኖሩን የምንለየው? አስክንድር የሚያየው ጭላንጭል ብርሓን ውስጥም.... ብዙ ነገር ኣለ። ትልቅ ሰላም።
http://www.ethiopiazare.com
No comments:
Post a Comment