Monday, December 22, 2014

የወደፊቱ የተሻለ የህይወት ተስፋ ያለው ወያኔ መቃብር ላይ ነው!!

ግንቦት 7
ወያኔ በሀገራችን የዘረጋው ማህበራዊ ፖለቲካዊና የኢኮኖሚ ስርአት ለጠቅላላ ህዝባችን፣ በተለይ ለወደፊቱ ሀገር ተረካቢ ወጣት ሲኦል መሆኑ ቅጥሏል። በሀገሬ ውስጥ፣ ሰርቸ የተሻለ ህይወት እኖራለሁ ብሎ ማለም ቅዠት ሆኗል። ከዚህ ይልቅ ያብዛኛውን ወጣት ተስፋ ሀገር ጥሎ በገፍ መሰደድ ከሆነ ውሎ አድሯል።
በእጅጉ በሚዘገንን ሁኔታ በግፍ ተሰቃይተው ከሳውዲ አረቢያ ወደሀገራቸው ከተመለሱት ከ160 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ግማሽ ያህሉ ተመልሰው መሰደዳቸውን በቅርቡ የወጣ ጥናት አረጋግጦል። በዚህ ሁኔታ ከተሰደዱ ወገኖቻችን ውስጥ ቁጥራቸው ከ70 በላይ የሚሆኑት ቀይ ባህር ላይ የነበሩበት ጀልባ ሰምጦ አልቀዋል። እነዚህ ወገኖቻችን ጉዞቸው በሞትና ህይወት መሃል መሆኑን አስቀድመው ያውቃሉ። ይህንን ያስመረጣቸው ግን የወያኔ ስርአት ነው። የወያኔ ስርአት የተመቻቸው ለስርአቱ ሹመኞችና ለዘመድ አዝማድ ከዚያ ከተረፈ ለጎሳ ተወላጆቻቸው ብቻ ነው። ሀገሪቱ ውስጥ ተገኘ የሚባል የኢኮኖሚ እድገት ካለም ከዚሁ ከጠባብ ቡድን ጥቅም አልፎ መከረኛውን ህዝብ የሚጠግን አልሆነም።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ከተስፋ ቆራጪነትና ሞትና ህይወትን ከሚያስመርጥ አስከፊ ህይወት ያለፈ ምርጫ አለ። ዋናው ምርጫቸውም ይህ ሊሆን ይገባል፤ ምርጫው ለዚህ መከራና ሀዘን ውርደት የዳረገንን ጨካኝ የወያኔ ስርአት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ነው።
ወያኔ የህዝቡ ጉስቁልናና ስቃይ ጉዳዩ አለመሆኑን ባለፉት ሳምንታት ከ70 በላይ ወገኖቻችን ቀይ ባህር ውስጥ ሰምጠው: አለም በሀዘን በሚመለከተንና መንግስት አለ ብሎ የሀዘን መግለጫ በሚልክበት ሰአት የብሄረሰብ ቀን በሚባል የቦልት በአል የወያኔ ሹሞች ብዙ ሚሊዮን ብር አውጥተው በውስኪ እየተራጩ ይጨፍሩ ነበር።
ይህ አልበቃ ብሎ አሻንጉሊቱ ሃይለማርያም ደሳለኝ በስደተኛው ላይ ለሰሚ የሚቀፍ የወረደ አሉባልታና ስድብ ሲያወርድ ሰምተናል፣ ራሱን ያወረደ ተረት ተረትም ተናገረ። በሥልጣን የመባለግ ዝንባሌያቸው ሳይውል ሳያድር በሚጠቀሙት የባለገ አዋራጅ ቃላት የመጠቀም ርሃባቸው አሳየን።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፦ በምድረ ኢትዮጵያ የተስፋ መቁረጥና ለወያኔ ሎሌዎቹ መሳለቂያ እንድንሆን ያበቃን ይህ የነቀዘ ዘራፊ የወያኔ ስርአት ብቻ ነው። ይህ ሁሉ ስቃይና ውርደት የሚቆመው ወያኔ ሲወገድ ብቻ መሆኑን ሁላችንም ጠንቅቀን ልንረዳ ይገባል። በቅርቡ ዱላውንና ግፉን ሁሉ ለመቀበል ቆርጠው ወያኔን ከተጋፈጡት የሰማያዊ ፓርቲ አባልና ደጋፊ ወጣቶች ብዙ ልንማር ይገባል። እንደእባብ በጭካኔ መቀጥቀጣቸው አጠነከራቸው እንጂ አላዳከማቸውም።
ወያኔ ዛሬ ከመቸውም በበለጠ ነቅዞል። የጭካኔውና የፍርሀቱ ምንጪ ጣር ሞቱ እንጂ ሌላ አይደለም።
ሞትና ህይወትን ከሚያማርጥ ስደት የደረሰው ወጣቱ አርበኝነትን መምረጥ አለበት። ከቀን ጅቦች ራስን በማዳን ውርደትን፣ ስደትን ማስወገድ ይቻላል። ይህ የነገ ሳይሆን የዛሬ ውሳኔ መሆን ይኖርበታል።
በመሆኑም ግንቦት 7 ወጣቱ በያለህበት በራስህ አነሳሽነት እንድትደራጅ ያበረታታል። አመች ሁኔታ ያለህ ወጣት ደግሞ ተቀላቀለን። ሰራዊቱ ውስጥ ያለህ ወጣትና ሎሌነት የሰለቸህ ሁሉ የነጻነት ሀይሎችን ትቀላቀል ዘንድ ጥሪያችን ይድረስህ።
የሀገራችን የህዝባችንና የያንዳንዳችን የተሻለ ህይወትና ዘመን ተስፋ የተቀመጠው ወያኔ መቃብር ላይ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
ድል ኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ለሰላማዊ ዜጎች ጥያቄ ጥይት መፍትሄ አይሆንም!
በባህርዳር ከተማ ለዘመናት የእምነት ቦታ ሆኖ ለአምልኮ አገልግሎት ሲውል የነበረ የህዝብ ይዞታ በማያውቁትና ባልመከሩበት ሁኔታ ባለሀብት እንዲያለማው በከተማው መስተዳድር ተሰጥቷል መባሉን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ባዶ እጃቸውን ሆነው በሰላማዊ መንገድ ባሰሙት የተቃውሞ ድምጽ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን በወሰደው ዘግናኝና አሰቃቂ በጥይት የታገዘ የኃይል እርምጃ እስካሁን የአምስት ንፁኃን ዜጎች ህይወት ተቀጥፏል፡፡ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ አዛውንት እማሆይንና አካል ጉዳተኛ ጨምሮ በርካቶችን በማቁሰል የአካል ማጉደል ደርሶባቸዋል፡፡ ይህ የኃይል እርምጃ በምንም መለኪያና ሁኔታ፣ ባለሥልጣናት ጥያቄው ያስከትላል ብለው የቱንም ታሳቢ ቢያደርጉ የህግም ሆነ የሞራል መከራከሪያ ሊቀርብለት የማይችል ህገወጥና ኃላፊነት የጎደለው ‹‹መንግሥት ነኝ›› ከሚል አካል የማይጠበቅ ዘግናኝ የአረመኔ ተግባር ነው፡፡
ከዚህ ባለፈም የከተማ ልማትም ሆነ የመሰረተ ልማት መስፋፋት ህዝብን በማሳመን በህዝብ ተቀባይነት ካላገኘና ለህዝብ ጥቅም ካልሆነ ለማን እንደሚሆን ያልገባቸው እብሪተኛ ባለሥልጣናት ፍርኃትና ሥጋት ወለድ አምባገነናዊ እርምጃ ነው፡፡ በመሆኑም የኃይል እርምጃው እስከዛሬ ‹‹ይህ መንግሥት የማን ነው፣ የቆመውስ ለማን ነው?›› ለሚለው ተደጋጋሚ ጥያቄ ‹‹የሥልጣኑና ለሥልጣኑ ብ ›› መሆኑን በግልጽ ያሳየበትና በህገ አራዊት ስለመመራቱ የማያሻማ ምላሽ የሰጠበት በመሆኑ ትብብራችን እርምጃውን አበክሮ ያወግዛል፡፡ የተወሰደው እርምጃ እንዲፈጸም ትዕዛዝ በሰጡ ባለሥልጣናትና እርምጃ በወሰዱት ላይ ተገቢው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣ ለተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ካሳ እንዲከፈል ይጠይቃል፣ ለተፈጻሚነቱም ከተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ጎን በመቆም ይታገላል፡፡
ይህ አምባገነናዊና የጭካኔ እርምጃ በቅርቡ ህዳር 27/07 ዓ.ም በህጋዊና ሠላማዊ መንገድ ለሠላማዊ ሠልፍ የወጡ የትብብራችን አባላትና ደጋፊዎች ላይ የተወሰደውን ዘግናኝ የኃይል እርምጃ፣ በየጊዜውና በተለያዩ ቦታዎች በተናጠል ለተደረጉ ሠላማዊ የህዝብ ተቃውሞዎችና ጥያቄዎች (የሙስሊሙ ማኅበረሰብ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች፣...) ላይ ገዢው ፓርቲ/መንግሥት የተጠቀመውን ተመሳሳይ የኃይል እርምጃ፣ በፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ በነጻው ፕሬስ አባላት፣… በሽብር ሥም በፈጠራ ወንጀል የፈጸመውን፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ በሚገኙ ዜጎች ላይ ‹‹በከፋፍለህ ግዛ›› ስልት እያሳደረ ያለውን የማስፈራሪያ ተግባራት ያስታውሰናል፡፡
በዚህ መሠረት የዚህ እርምጃ ግልጽ መልዕክት ኢትዮጵያዊያን እኔ ፖለቲከኛ ወይም የዚህ ወይም የዚያ ፓርቲ አባል አይደለሁም፣ እኔ ሙስሊም ወይም ክርስቲያን አይደለሁም፣ እኔ አማራ ወይም ኦሮሞ፣ የዚህ ወይም የዚያ ብሄረሰብ አባል አይደለሁም፣ እኔ ተማሪ፣ መምህር፣ የመንግስት ሠራተኛ ወይም ነጋዴ፣ … ከዚህ ከዚያ ማኅበረሰብ ክፍል አይደለሁም፣… አይደለሁምና ጥያቄውና ትግሉ አይመለከተኝም በሚል የወር ተራችንን ከመጠበቅ እንድንላቀቅና ይህን አምገነናዊ ሥርዓት ለማስወገድ በአንድነት ቆመን በጽናት ለመታገል እንድንነሳ ወቅቱ መሆኑን፤ በተናጠል በየተራ በህገ ወጥ እርምጃ የሚደርስብንን በአንድነት ቆመን እስካልመከትን በየተራ የያንዳንዳችንን በር ማንኳኳቱ የማይቀር መሆኑን ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ ዓይነቱ የኃይል እርምጃ እየከፋና እየተስፋፋ፣ ጭቆናው እየከፋና የህዝብ ብሶት እየጨመረ ሲሄድና ከማናችንም ቁጥጥር ውጪ ሲሆን በአገራችን የሚያስከትለውን ፖለቲካዊ ቀውስ፣ ኢኮኖሚያዊ ውድመትና ማኅበራዊ ትርምስ ቀድሞ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ስለሆነም፡-
1ኛ/ ገዢው ፓርቲ የተያያዘው የአፈና መንገድ ለጥያቄዎች መልስ ሊሆን ወይም ትግሉን ሊያቆም እንደማይችል በቅርቡ ከታየው ያለፈው ጁምኣ የቤኒ መስጂድ የሙስሊሞች ተቃውሞ ስልትና አተገባበር ተረድቶ ቆም ብሎ እንዲያስብና ለህዝብ ጥያቄዎች ጆሮውን፣ ለህዝብ ብሶት ልቡን ፣ለመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና ለህግ የበላይነት በሩን እንዲከፍት፤
2ኛ/ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የእያንዳንዱ በር እስኪንኳኳ ሳንጠብቅ ይህን ዓይነቱን ኢ-ህገመንግሥታዊና አረመኔያዊ እርምጃ በአንድነት ቆመን እንድናወግዘውና እንድንታገለው፤
3ኛ/ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፓርቲ ጥቅምና ፍላጎት የአገርና ህዝብ ጉዳይ የበላይና ቀዳሚ ስለሆነ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከትብብራችን ጋር በጋራ ለመስራት ትብብሩን እንድትቀላቀሉ፤ ጥሪያችንን እያቀረብን፤
በእኛ በኩል ትግሉ የሚጠይቀው ዋጋ እየጨመረ የመጣ ቢሆንም ከዓላማችን ሳናፈገፍግ ይህን አምባገነናዊ ሥርዓት በመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመተካት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች እስኪመለሱ ድረስ የተያያዝነውን የጋራ ትግል አጠናክረን ለመቀጠል የገባነውን ቃል እንጠብቃለን!
በዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለው ህገወጥ አረመኔያዊ እርምጃ እስከሚያበቃ የጋራ ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ታህሳስ 13 ቀን 2007 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ

ግፍና አፈና ዐመጽን ይወልዳሉ!

(ያሬድ ኃይለማርያም)
fist2

የዐመጸኛ አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው (መ. ምሳሌ ም. 22፣  ቁ. 14)
ሰብአዊ መበቶችን በመጣስ፣ ግፍ በመፈጸምና አፈናን በማጠናከር እደሜ የሚሸምት የአገዛዝ ሥርዓት የእያንዳንዱን ሰው መንፈሳዊና አካላዉ ጥንካሬ የማዳከም፣ ቅስምን የመስበርና ፍርሃትን የማንገስ ከፍተኛ አቅም እንዳለው ሁሉ በብሶት የሚወለዱ፣ እምቢኝ ለግፈኞች፣ እምቢኝ ለአንባገነኖች፣ እምቢኝ ለነጻነቴ የሚሉ መንፈሰ ጠንካራ ጀግኖችንና ታጋዮችንም ይወልዳል:: የአለማችን ስመ ጥርና ዘመን የማይረሳቸው የነጻነት ታጋዮች እነ ማህተመ ጋንዲ፣ ማርቲን ሉተር ኪነግ፣ ማንዴላ፣ ኡንግ ሳን ሱ ኪ እና ሌሎችም ብዙዎች የፈለቁት በብሶት ከተሞላ፣ ጭቆና ካንገሸገሸውና በአፋኝ ሥርዓት ከታመቀ ማኅበረሰቡ ጉያ ነው:: አንድን ማኅበረሰብ በአፈሙዝ፣ በሕግና በገንዘብ ኃይል ጭፍሎቆና አፍኖ ማቆየት የሚቻለውም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ መሆኑን የእነዚህ ታጋዮች ገድልና የአለም ታሪክም ይመሰክራል:: አንድ ሕዝብ በላዩ ላይ ገዢዎች እየተፈራረቁበት ረዘም ላለ ጊዜ በአገዛዝ ሥርዓት ሥር ሊቆይ ይችል:: ይሁንና እድሜ ልክ የገዛ አፋኛ ሥርዓት ግን የለም:: ሥርዓቱም እንደ ድርጅት፣ ሹማምንቱም እንደ ሰው የጉብዝና እድሜያቸው የተወሰነ ነው:: የአፈናን ስልት በመለዋወጥና ሸምቀቆውን በማጥበቅም እድሜን ማራዘም የሚቻል ቢመስልም በተቃራኒዉ ውድቀትንም ያፋጥናል:: ግፉ እየበረታና የመብት ጥሰቱም መረን እየለቀቀ በሄደ ቁጥር የሕዝብ ትእግስት ይሟጠጣል:: ሕዝብ መቆጣት ከጀመረና ቁጣውም ወደ አደባባይ አመጽ በተቀየረ ጊዜ የግፍ አገዛዝ ወደ መቃብር፣ ግፈኞቹም ወደ ዘብጥያ እንደሚወርዱ እርቀን ሳንሄድ ባለፉት አምስትና አሥርት አመታት ውስጥ በአለም የታዩ ሕዝባዊ ነውጦችንና ያስከተሉትን መዘዝ ማጤን በቂ ነው::
ትልቁ ጥያቄ በግፍ አገዛዝ ውስጥ ያለ ሕዝብ መቼ እና ብሶቱስ ምን ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው የሚቆጣው? መቼ ነው ቁጣውንስ በየመንደሩ ከማጉረምረም አልፎ ባደባባይ የሚገልጸው? ቁጣውስ ወደ አመጽ ሊያመራው የሚችለው በምን ሁኔታ ነው? የሚለው ነው:: የሕዝብ ቁጣ ወደ አመጽ የሚለወጥበት ጊዜና ደረጃው የሚለካው በተለየ ሳይንሳዊ ቀመር ስላልሆነ መቼና በምን ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቸግራል:: ይህ አይነቱ ሁኔታ በእያንዳንዱ ማኅበረሰቡ ባህላዊ፣ ኃይማኖታዊና ማኅበራዊ አመለካከቶችና የፖለቲካ ንቃተ ህሊና ላይ ይወሰናል:: በትንሽ በትልቁ አደባባ እየወጣና በሚሊዮን የሚገመት የመንግሥትና የሕዝብ ንብረትን እያወደመ ተቃውሞውን የሚገልጽ ሕዝብ አለ:: በሌላ መልኩም አገሩን ቢሸጡበት፣ መሬቱን ቢነጥቁት፣ ሚስቱን ቢያስጥሉት፣ ልጆቹን ቢደፍሩበት፣ ቢገድሉበት፣ ቢያስሩበትና ቢያፍኑበት፣ ቤቱን በላዩ ላይ ቢያፈርሱበት፣ ቀየውን ለቱጃሮች ሰጥተው ቢያፈናቅሉት፣ ግብር እየከፈለ ያስተማራቸውን ልጆቹንና አመራቹን ኃይል እያዋከቡ ከአገር ቢያሰድዱበትና ለባርነት ቢዳርጉት፣ ከሰው ተራ አውርደው በየጎዳናው ቢጥሉትም ‘አዬ ጉድ፣ አዬ ጉድ’ ከማለት ባለፈ ቁጣውን የማያሳይም ሕዝብ አለ:: በከፋ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ታዋቂ የነበሩት ሟቹ ጠ/ሚ መለስ ያረፉ ወቅት አስከሬናቸውን ይሳለሙ ከነበሩ ሰዎች በኑሮው እጅግ የተጎዳና የተጎሳቆለ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ በመንግሥት የቴሌቪዥን ማሰራጫ ሃዘኑን የገለጸበት መንገድ ጥሩ ማሳያ ሊሆን ይችላል:: የአዞ እንባውን እያነባ “እኔ እኮ እሳቸውን ተማምኜ ነው ጎዳና ላይ የማድረው” ነበር ያለው::
በሳንቲም ደረጃ የዋጋ ጭማሪ ተደረገብኝ ብሎ ወደ አደባባይ እየደጋገመ የሚወጣውን የኬኒያን ሕዝብ ቁጣ ለማየት በሚያዚያ ወር 2011 (እ.ኤ.አ) የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብን ተከትሎ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት በመቃወም በናይኖቢ የተካሄደውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ማየት ይቻላል:: እኛ ዘንድ የነዳጅ ዋጋ ስንት ጊዜ አሻቀበ? በእያንዳንዱ የእለት ተዕለት መገልገያ ቁሳቁሶች ላይ በምን ያህል መጠንና ስንት ጊዜ የዋጋ ንረት ታየ? የቤት ኪራይ፣ የትራንስፖርት፣ የጤና አገልግሎት፣ የመድሃኒቶች እና ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች ዋጋስ በስንት እጥፍ ናረ? እኛስ ስንት ጊዜ ቁጣችንን ገለጽን? በኑሮ መማረራችንንስ በምን መልኩ ለገዢዎቻችን አሳየን? ከኑሮ ዋስትና ማጣት ባሻግር የሹመኞች ከሕግ በላይ መሆን የዜጎችን በሕገ-መንግሥቱ የተደነገጉ መሰረታዊ የፖለቲካና የሲቪል መብቶችንና ነጻነቶችንም ትርጉም አልባ ሲያደርጋቸው እያየን ምን አደረግን? ለዚህም ነው የሕዝብ ብሶትና ምሬት የት ደረጃ ላይ ሲደርስ ቁጣ ወደተቀላቀለበት ተቃውሞ ሊያመራ እንደሚችል ሳይንሳዊ በሆነ ቀመር ማረጋገጥ ወይም መገመት የማይቻለው:: ምክንያቱም ግፍና በደሉን የተሸከመው ሕዝብ ያለው የታጋሽነት ልክ፣ ሆደ ሰፊነቱ፣ አርቆ አሰተዋይነቱ፣ የተዋጠበት የፍርሃት ጥልቀት ወይም ሌሎች ስነ-ልቦናዊ ሁኔታዎች ናቸው ይህን የሚወስኑት:: በዛሬዎቹም ሆነ በትላንት ገዢዎቹ ጭካኔና የማስተዳደር ብቃት ማነስ የተነሳ ለከፋ ድህነት የተጋለጠውና በልቶ ማደር ፈተና የሆነበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ምሬቱንም ሆነ ተማጽኖውን የሚያሰማው ለፈጣሪው ብቻ ነው:: ሲመረውም ‘ምነው ዝም አልክ? ወይ ፍረድ ወይ ውረደ’ እያለ ካምላኩ ጋር መሟገት ይቀለዋል:: ትንሽ ሲደሰትም ‘ተመስጌን ይችን አትንሳኝ’ እያለ የነገን እጣፈንታውን እያሰላሰለ ፈጣሪውን ያመሰግናል:: ስለዚህ መንግሥት በሕዝብ ላይ ያሻውን ቢያደርግም ሕዝብ የልቡን የሚወያየውም ሆነ ይግባኝ የሚለውም ከመንግስት ዘንድ ሳይሆን ከፈጣሪው ጋር ነው:: ይህ አይነቱ የኅብረተሰብ ምላሽ ገዢዎችን ያማግጣል፣ ያሻቸውን እንዲያደርጉም ያበረታታል፣ ሕዝብን እንዲንቁና እራሳቸውንም ከሕግ በላይ አድርገው እንዲያስቡ ያደርጋል::
በዚህ አይነት ማኅበረሰብ ውስጥ ትልቁ ቀውስና ፖለቲካዊ ነውጥ የሚጀምረው የገዢዎቹ መረን መልቀቅ እየበረታ፣ የሕዝቡም ክፌት እየገነፈለ ሕዝብ የሚጠብቀው የፈጣሪው ምላሽ ግን የዘገየ ዕለት ነው:: ያኔ የሕዝብ ትግስት ይሟጠጣል፣ ሰፊውም ሆድም በቂም፣ በክፌትና በጥላቻ ይሞላል፣ አርቆ አሰተዋይነቱም ወደ ግብታዊነትና ንዴት ይለወጣል፣ ፍርሃቱም ተስፋ መቁረጥ ወደሚያሰከትለው ጨለምተኝነትና ጀብደኝነት ይቀየራል:: እዛ ደረጃ ከተደረሰ በኋላ የሚሆነውን መገመት አይከብድም:: በቅርቡ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በተለይም በቱኒዚያ፣ በግበጽ፣ በሊቢያ፣ በዩክሬንና ሌሎች አገሮች የተከሰቱት የሕዝብ ቁጣዎች ለዚህ ጥሩ ማሳያዎች ናቸው:: ባለፉት አራት አመታት ውስጥ በሕዝብ ቁጣና አመጽ ሲናወጡ የከረሙትን፣ በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመቶችን ያሰተናገዱትንና የመንግሥታትም ለዉጥ የታየባቸውን የአረብ አገራት መለስ ብለን የተመለከትን እንደሆነ አብዛኛዎቹ በቡዙ መልኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚገኝበት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሁኔታዎች እጅግ በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው:: ጥሩ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው፣ ሕዝብ በምግብ አጦት የተነሳ በርሃብ የማይሰቃየባቸውና የማይሞትባቸው፣ እጅግ የተሻለ የእሌክትሪክ፣ የውሃ፣ የነዳጅ፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የኢንተርኔትና ልሎችም መሰረታዊ አቀርቦቶች የተሟሉባቸው አገሮች ናቸው:: ከፖለቲካ ነጻነቱም አንጻር ብዙዎቹ ከኢትዮጵያ በተሻለ ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት፣ ባደባባይ የመሰብሰብና ተቃውሞንም የመግለጽ ነጻነትም የሚታይባቸው ናቸው:: ይሁንና በእነዚህ አገራት ውስጥ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ የሥልጣን ባለቤት ባለመሆኑና ብለሹ በሆኑት የፖለቲካ ሥርዓቶች እጅግ ተከፍቶ የቆየ ስለነበር በቀላሉ ወደ አመጽ ሊያመራ ችሏል:: አንዳንዶቹም ዘላቂ ለሆነ ቀውስ መዳረጋቸው ይታወቃል::
በእነዚህ አገራት የሕዝብ የነጻነትና የመብት ጥያቄ የሥርዓት ለውጥን ለማምጣት ወደሚችልበት ሕዝባዊ አመጽና ኃይል ወደታከለበት ግጭት እንዲያመራ የውጪው አለም ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ አይካድም:: ቢሆንም ዋነኛው ምክንያት ግን የተጠራቀመው የሕዝብ ክፌትና ብሶት ነው:: በእነዚህ አገሮች በተነሱት የሕዝብ አመጾችና በተከሰቱት የፖለቲካ ቀውሶች ማን አተረፈ የሚለው እራሱን የቻለ ሰፊ የመወያያ ርዕስ ነው:: ነገር ግን በግልጽ እንደሚስተዋለው የመጀመሪያዎቹ ተጠቂዎች ሕዝብን ሲያሰቃዩ፣ ሲያፍኑ፣ ሲገደሉና ሲያስገደሉ፣ ሚሊዮኖችን እያደኸዩ ሃብት ሲያካብቱ የነበሩ ሹማምንትና ዙሪያቸውን የከበቡዋቸው ባለሃብቶች ለመሆናቸው በጋዳፊና በሙባረክ እንዲሁም በዙሪያቸው የነበሩ ሰዎችን እጣ ፈንታ ማየት በቂ ነው:: ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሕዝብ ክፌትና ብሶት፣ የአፈናው ደረጃ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመሰረታዊ አቅርቦቶች መጓደል፣ የባለሥልጣናቱ ሙሰኝነትና ከሕግ በላይ መሆን፣ የሥራ አጡ ቁጥር፣ የድኅነቱ ደረጃ፣ ተሰፋ ማጣትና ጨለምተኝነት በምንም መልኩ ቢሆን ከሌሎች በአገዛዝ ሥርዓት ውስጥ ከሚገኙ አገሮች ጋር የሚወዳደር አይደለም:: የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ከገጠሙት ክፉና አንባገነናዊ ሥርአቶች ውስጥ የወያኔን አገዛዝ የተለየና የከፋ የሚያደርገው የዘረኝነት ፖሊሲው ብቻ ሳይሆን በአገር ሃብትና ንብረት የከበሩ የንግድ ድርጀቶች ባለቤትና ከታጋይነት ወደ ሚሊየነርነት የተቀየሩ ቱጃር ባለሥልጣናትንና የጦረ አዛዦችን የያዘ ድርጅት መሆኑ ነው:: ብሶት የወለዳቸው የወያኔ ባለሥልጣናት ዛሬ በተራቸው ሕዝብን ሆድ ከማስባስ አልፈው ማቆሚያ ወደማይኖረው የእርስ በርስ ግጭት፣ አመጽ፣ ቀውስና የዘር ቁርሾ ውስጥ እንዲገባ እየጋበዙት ነው::
የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔ ሥርዓት አራሱን እንዲያርቅና አገሪቱንም ከተንጠለጠለችበት የገደል አፋፍ እንዲታደግ ከሃያ ዓመታት በላይ እድል ሰጥቶታል:: ፍጹም ሰላማዊና ስልጡን በሆነ መልኩም በ1997ቱ ምርጫ የማስጠንቀቂያ ደውሉን አቃጭሏል:: ይሁንና ይህን ማስጠንቀቂያ የወያኔ ባለሥልጣናት የተረጎሙበት መንገድ ሕዝብ ማስተላለፍ ከፈለገው መልዕክት እጅቅ የራቀና በተሳሳተ መልኩ መሆኑን ለመረዳት ምርጫውን ተከትሎ የወሰዱትን የኃይል እርምጃና ከዛም ወዲህ ያሳዩትን አፈናውን በሕጎች አጠናክሮ የመቀጠል ፍላጎት ማጤን በቂ ነው:: ለሕዝብ ያላቸውን ንቀትና እብሪትም በደንብ ያመላክታል:: ከዚህ በመነሳት ከፊታችን የሚጠብቀን ምርጫ ሊኖሩት የሚችሉትን ሁለት ገጽታች መገመት ይቻላል::
  • የመጀመሪያው ወያኔ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት ምርጫዎች ብቻውን ተወዳደሮ ወይም አጃቢ ተቃዋሚዎችን አስከትሎ ያለምንም ችግር 99% ወይም ተቀራራቢ በሆን አሃዝ ጠቅልሎ ይቀጥላል:: አለያም የተወሰኑ ግጭቶችን ባስከተሉ ተቃዉሞዎች ውስጥ አልፎ ከ 10% እስከ 20% መቀመጫን ለተወሰኑ ተቃዋሚዎች ለቆ የፖለቲካ መዘውሩን እንደያዘ ተደላድሎ ይቀጥላል::
  • ሁለተኛው ግምት ደግሞ በተቃዋሚዎች አበሮ መስራት ላይ በተመሰረት ጥንካሬና ከሕዝብ በሚገኝ ድጋፍ ምርጫው ለምክር ቤት ወንበር ሽሚያ ሳይሆን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከአንባገነናዊ ሥርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማላቀቅ፣ ሕዝብንም የሥልጣን ባለቤት ለማድረግና እና አገሪቱንም ካንዣበበባት አደጋ ለመታደግ የሚደረግ የነጻነት ወይም ሞት ትግል ይሆናል::
በመጀመሪያው ሂደት ውስጥ የሚከሰቱት ነገሮች መሰረታዊ ለውጦችን ለማምጣት የታለሙ ሳይሆን የአገዛዝ ሥርዓቱ ያስቀመጠውን የጨዋታ ሕግ በማክበር ተቃዋሚ የሆነው የፖለቲካ ኃይልም ሆነ ሕዝቡ ሥርዓቱን በረዥም ጊዜ ሂደት እንለውጠዋለን ወይም በራሱ ጊዜ ይከስማል ወይም አራሱን በሂደት ያርቃል የሚል ተስፋ ሰንቀው እድሜውን እንዲያራዝም የሚፈቅዱበት ሁኔታ ነው:: ባጭሩ “ያለ ምንም ደም ወያኔ ይቅደም” ነው:: በዚህ አካሄድ አትራፊዎቹ ወያኔ እና በወያኔ መቆየታ ላይ ተማምነው በኢኮኖሚም፣ በጸጥታ ዘርፍም እና ሆነ በአካባቢው የፖለቲካ መረጋጋት ለማትረፍ ከሥርዓቱ ቃር የተወዳጁ የውጪ ኃይሎችና የዘመኑ ባለሃብቶች ብቻ ናቸው:: ሰፊውና ድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ አገሩን ለቀማኞች አስረክቦ የስቃይ ዘመኑን በየአምስት አመቱ በሚደረጉ የማደናገሪያ ምርጫውዎች እያደሰ የግፍ እንቆቆውን መጋቱን ይቀጥላል::
ይህ አይነቱ በምርጫ ስም የሚደረግ ማደናገሪያ ከቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ወዲህ በበርካታ የሦስተኛው አለም አገሮች ተደጋግሞ የሚታይ ክስተት ሆኗል:: ባለፉት አስርት አመታት እንደተስተዋለው ምርጫ አንድ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባትና የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚረዳ መንገድ የመሆኑን ያህል ድሃ ሕዝብን አፍኖ ለመግዛትና የአንባገነኖችንም እድሜ ለማራዘም እያገለገለ መሆኑን ነው:: በዚህ ሂደት ውስጥ ዋነኛ ተዋናዮቹ የአገዛዝ ሥርዓቶቹ ብቻ ሳይሆኑ የምዕራቡ አለም እና የአለም ከበርቴዎችም ናቸው:: የቅኝ ግዛት ታሪክ ካከተመ በርካታ አመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም አገሮችን በቅኝ ለመግዛት የምዕራቡ አለም ቆርጦ የተነሳባቸው ዋነኛ የኢኮኖሚና የፖለቲካ መንስዔዎች ዛርም እጅግ በከፋና ባፈጠጠ መልኩ ይታያሉ::
የምዕራቡ አለምና ከበርቴዎቹ የቅኝ ግዛት ፖሊሲዎቻቸውን ለማስቀጠልና ጥቅሞቻቸውንም በእነዚህ ድሃ አገሮች ላይ፣ በተለይም በአፍሪቃ አገሮች ውስጥ እንደተጠበቀ ለማቆየት እንደ አማራጭ ከወሰዱት መንገድ አንዱ ከትቢያ እያነሱ ወደ ስልጣን እንዲመጡ የረዷቸውን የጫካ ሽፍቶች በስልጣን ለማቆየት በገንዘብና በጦር መሳሪያ ከሚያደርጉላቸው ድጋፍ ባሻገር አንጻራዊ የሆነ የፖለቲካ መረጋጋትም እንዲኖር የእነዚህን አፋኝ ቡድኖች እድሜ በይስሙላ ምርጫ እንዲታጀብ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ማድረግ ነው:: ይህ አካሄድ ሁለት ግቦች አሉት:: አንዱ እነዚህ አንባገነኖች ሙሉ በሙሉ በምዕራቡ አለም ድጋፍ ነው የቆሙት ወደሚል ድምዳሜ ከተደረሰ የዳግም ቅኝ ግዛት እቅዳቸውን ከማጋለጡም በላይ የምዕራቡ አለም ከአንባገነኖችና የሰብአዊ መብቶችን በገፍ ከሚጥሱ ቡድኖች ጎን አብሮ በመቆም የደሃ አገር ሕዝቦችን በማሰቃየትና ሃብታቸውንም በመዝረፍ ተግባር ውስጥ መጠመዳቸው ፈጦ እንዳይታይ ይጋርዳል:: ሌላው ምርጫው የተጭበረበረ ቢሆንም የሕዝብ ተሳትፎ እስከታየበት ድረስ ገዢዎቹ እራሳቸውን ትክክለኛና ተቀባይነት (legitimate) ያላቸው አድርገው እንዲቆጥሩና ሕዝብም ይህን አምኖ እንዲቀበል ለማስገደድ ይረዳል:: በምርጫ ወቅት የሚታዩ ግድፈቶችም ሆኑ ያፈጠቱ ውንብድናዎች በእነዚህ ድሃ አገሮች ውስጥ እስከሆነ ድረስ የተከሰቱትና በሥልጣን ላይ ያሉት ቡድኖችም የምዕራቡ አለም ወዳጆች እስከሆኑ ድረስ ችግሮቹ የዲሞክራሲያዊ ግንባታው ሂደት አካል ተደርገው እንዲወሰዱ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረትና የሚዲያዎች ቅስቀሳም ይደረግበታል::
ሁለተኛው ሂደት ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ማካሄድ የሚቻለው ነጻ የፖለቲካ መድረክ፣ ነጻነት የሚሰማውና የሌሎችንም ነጻነት የሚያከብር መንግሥት፣ በነጻነት ማሰብና ሃሳቡንም በነጻነት መግለጽ የሚችል ሕዝብ፣ በነጻነት መደራጀትና መንቀሳቀስ የሚችሉ ጠንካራና ተፎካካሪ የፖለቲካ ኃይሎች እና ነጻ ተቋማት በተለይም ገለልተኛ የሆኑ ምርጫ አስፈጻሚዎችና የፍትሕ ተቋማት ሲኖሩ ብቻ ነው ከሚል እምነት ይመነጫል:: ይህ ደግሞ በወያኔ ዘመን እስካሁን ያልታየና ወደፊትም እነዚህ ነገሮች በሂደት ሊሟሉ ስለመቻላቸው ምንም አይነት የሚታዩ ምልክቶች፣ ዋስትና ወይም መተማመኛ ሊሆን የሚችል ነገር የለም:: እንዚህ ፖለቲካዊና ተቋማዊ አደረጃጀቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች ጭርሱኑ በሌሉበት ሁኔታ ነጻ ምርጫ ሊካሄድ አይችልም:: ያለፉት አይነት ምርጫዎች ቢካሄዱም ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ቀላል ነው:: ሰለዚህ ምርጫው ሊሆን የሚገባው በቅድሚያ የሕዝብን ነጻነት ማረጋገጥ ወይም በግዞት ውስጥ ሆነን ወያኔ የመረጠልንን ሕይወት መቀጠል ነው:: የእነሱን ቋንቋ ልጠቀምና ባጭሩ “ሃርነት ወይስ ባርነት”::
ይህ የሁለተኛው ሂደት በሕዝብ እምቢተኝነት ላይ የተመሰረተና ፍጹም ሰላማዊ በሆነ የትግል ሂደት ሊመጣ የሚችል ስኬት ነው:: ብዙዎች በሕዝብ እምቢተኝነት ላይ የተመሰረተን ሰላማዊ ትግል ከምርጫ ውድድር ጋር ሲያምታቱት ይሰታዋል::  በአገሪቱ ውስጥ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች አለመሟላት ወይም በነጻነት የመደራጀት፣ የመሰብሰብ፣ ሃሳብን የመግለጽና ተቃውሞ የማድረግ መብቶችና ነጻነቶች አለመኖርን ለሰላማዊው ትግል ማክተም እንደ አስረጂነት ያቀርቡታል:: ይህ እጅግ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው:: የእነዚህ ሁኔታዎች አለመሟላት የሚያሳየው በምርጫ ሂደት ተወዳድሮ ሥልጣን መያዝ የሚቻልበት እድል አለመኖሩን በቻ ነው:: እነዚህ ነጻነቶች በተከበሩበትና ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ የተወሰኑ ነገሮች እንኳን ከተሟሉ ሂደቱ ሰላማዊ ትግል መሆኑ ቀርቶ በፓርቲዎች መካከል የሚደረግ ውድድር ነው የሚሆነው:: በአሜሪካም ሆነ በሌሎች ዲሞከራሲያዊ ሥርዓት በጎለበተባቸው አገሮች ፓርቲዎች ለሥልጣን ይወዳደራሉ እንጂ ሰላማዊ ትግል ውጥስ አይደለም ያሉት:: ብዙዎቹ ይህን የትግል ምዕራፍ ከዘጉ ዘመናቶች ተቆጥረዋል:: ሰላማዊ ትግል የሚካሄደው እነዚህ ነጻነቶች ፈጽሞ በሌሉበት፣ አፈና እና ጭቆና በተንሰራፋበት የአገዛዝ ሥርዓት ውስጥ ነው:: ትግሉም ጠመንጃ ያነገበና በኃይል ሕዝብን በሚደፈጥጥ አካል እና በልበ ሙሉነትና ከፍ ባለ የመንፈስ ልዕልና ተሰባስበው ሕዝብንና አገራዊ ዕራእያቸውን ጋሻ በማድረግ ያለ ነፍጥ ሥርዓቱን በሚያርበደቡዱ የሰላም መልዕክተኞች መካከል ነው:: አንደኛው ወገን ይገድላል፣ ያስራል፣ ያሰቃያል:: ሌላኛው ወገን እየሞተ፣ እየታሰረ፣ እየተደበደበና እየተዋከበም ስለ ነጻነት፣ ስለ ፍትሕ፣ ስለ እኩልነት፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ ሰላምና ስለ ሕግ የበላይነት በአደባባይ ይዘምራል፣ ይሰብካል፣ ሕዝብን ያደራጃል፣ ይታገላል::
ከወያኔ የአገዛዝ ሥርዓት ለመላቀቅ በ1997ቱ ምርጫ ወቅት ታይቶ የነበረው የሕዝብ ተነሳሽነትና የተጀመረው ሰላማዊ ትግል ሥርዓቱ በወሰደው የጭቃኔ እርምጃ ቢቀለበስም በአገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትቶት ያለፋቸው በርካታ ነገሮች አሉ:: ከዚህ ሂደት ትምህርት በመውሰድ የተጀመረውን ሰላማዊ ትግል ለመቀጠል በአገር ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ባርቲዎች እየከፈሉት ያሉት መስዋትነት ሊበረታታና ሊደገፍ የሚገባው ነው:: በተለይም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ ደጋፊዎችና አመራሮች እንዲሁም የዘጠኙ ፓርቲዎች ጥምረት በመባል የሚጠሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያሳዩ ያሉት እንቅስቃሴና ከሥርዓቱ ጋር የገጠሙት የእምቢተኝነት ግብግብ ሰላማዊ ትግልን በኢትዮጵያ ውስጥ ማካሄድ እንደሚቻል ብቻ ሳይሆን መጀመሩንም ያረጋግጣል:: ሕግን ማክበርና በሕግ የበላይነት ማመን ከእያንዳንዱ ዜጋ ይጠበቃል:: ግድታም ነው:: ይሁንና ዜጎች በዚህ ግዴታ የሚወሰኑት እያንዳንዱ ሕግ የሕገ-መንግሥቱን የበላይነት እስካልጣሰና በውስጡም የተደነገጉትን መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ባረጋገጠ መልኩ እስከ ተደነገገና በአግባቡም እስከ ተተገበረ ድረስ ብቻ ነው:: ልክ እንደ ደቡብ አፍሪቃው አፓርታይድ ሕግን የማፈኛ መሳሪያ አድርጎ በሚጠቀም ሥርዓት ውስጥ የሚደረግ ሰላማዊ ትግልና ሕዝባዊ እምቢተኝነት የዜጎችን መሰረታዊ ነጻነቶችን ለሚያጠቡ ወይም ጭርሱኑ ለሚያግዱ ሕጎች፣ ደንቦችንና መመሪያውችን አለመገዛትንም ይጨምራል:: በአገር ውስጥ ያለውም ሆነ ከአግር ውጭ ያለው የአገሩ ጉዳይ የሚያሳስበው ኢትዮጵያዊ ለእነዚህ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ብዙ መከራዎችን እየተቀበሉ አንባገነናዊ ሥርዓትን ታሪክ አድርገው ለማስቀረት ከሚታገሉ መንፈሰ ጠንካራ ኢትዮጰያዊያን ጎን በመቆም ትግሉ እንዳይደናቀፍና አገሪቱም አሰከፊ ወደ ሆነ ደም አፋሳሽ ሁኔታ እንዳታመራ ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል::
አምባገነናዊ ሥርዓትን ታሪክ አድርገን ለማስቀረት ከሰላማዊ ታጋዮቹ ጎን እንቁም!
በቸር እንሰንብት!
ያሬድ ኃይለማርያም
ብራስልስ፣ ቤልጂየም
ታኅሣሥ 10፣ 2007

Sunday, December 21, 2014

ጋዜጠኞችን በማሠር ኢትዮጵያ አሁንም ከአፍሪካ 2ኛ ሆናለች

መራው አበበ
አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) እየተገባደደ ባለው የፈረንጆቹ 2014 አመት በመላው ዓለም 220 ጋዜጠኞች መታሠራቸውንና ቻይና በቀዳሚነት የጋዜጠኞች ሲኦል መሆኗን ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርቱ ያመለከተ ሲሆን ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሠር በአለም 4ኛ፣ በአፍሪካ ኤርትራን አስቀድማ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
eskinderandreeyotcropped
በኢትዮጵያ በ2014 እ.ኤ.አ የታሣሪ ጋዜጠኞች ቁጥር ከአምናው ከሰባት እጥፍ በላይ ጨምሮ ወደ 17 ከፍ ማለቱን የድርጅቱ ሪፖርት ይጠቁማል፡፡ በኢትዮጵያ ጦማሪያን ጭምር መታሰራቸውንና ከወትሮው በተለየ በርካታ ጋዜጠኞች መሠደዳቸውንም አመልክቷል፡፡ በአለማቀፍ ደረጃ ጋዜጠኞችን በማሰር ተወዳዳሪ ያልተገኘላት ቻይና፤ 44 ጋዜጠኞችን ዘብጥያ እንዳወረደች በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ አምና በሀገሪቱ ታስረው ከነበሩት 32 ጋዜጠኞች ሌላ ዘንድሮ 12 ተጨማሪ ጋዜጠኞች መታሠራቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ቻይና ለጋዜጠኞች ሲኦል መሆኗን አጠናክራ ቀጥላለች ብሏል፡፡ ሁሉም ጋዜጠኞች የመንግስትን ፖሊሲና አሰራር በመንቀፋቸውና አበክረው በመተቸታቸው ለእስር እንደተዳረጉም ተጠቁሟል፡፡ ኢራን ደግሞ ከቻይና ለጥቃ በሁለተኛነት ተቀምጣለች፡፡
የታሣሪ ጋዜጠኞች ቁጥር ከዓምናው በአምስት ያህል ቢቀንስም አሁንም ከዓለም ለጋዜጠኞች የማትመች ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች ብሏል – ሪፖርቱ፡፡ አምና በኢራን 35 ጋዜጠኞች ታስረው የነበረ ሲሆን ዘንድሮ አምስቱ ተለቀው 30ዎቹ በእስር ላይ አብዛኞቹ ጋዜጠኞች የታሰሩበት ምክንያት እንደማይታወቅ ተገልጿል፡፡
በአለም ላይ ጋዜጠኞችን በማሠር የሚስተካከላቸው አልተገኘም ተብለው ከተለዩት 10 ሀገራት መካከል ኤርትራና ኢትዮጵያ በ3ኛ እና 4ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን እነሱን በመከተል ቬትናም፣ ሶሪያ፣ ግብፅ፣ በርማ፣ አዘርባጃንና ቱርክ ተጠቅሰዋል፡፡ በኤርትራ ስለታሰሩት 23 ጋዜጠኞች ጥናት ለማድረግ መሞከሩን የጠቆመው ሲፒጄ፤ ለበርካታ አመታት የታሠሩ ጥቂት ጋዜጠኞች በህይወት መኖራቸውን ከማረጋገጡ ውጪ በምን ምክንያት እስከዛሬ እንደታሠሩ ለማወቅ ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካለት ገልጿል፡፡ ኢትዮጵያና ግብፅ ከቀደመው አመት ጋር ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ ጋዜጠኞችን እንዳሰሩ የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ግብፅ የአልጀዚራ ጋዜጠኞችን ጨምሮ 12 ጋዜጠኞች ማሠሯን ጠቅሶ የታሠሩበት ምክንያት ግን አልታወቀም ብሏል፡፡ ጋዜጠኞችን በማሰር በ8ኛ ደረጃ የተቀመጠችው በርማ፤ “መንግስትን ተቃውማችኋል” በሚል 10 ጋዜጠኞችን ያሰረች ሲሆን፤ አብዛኞቹም የ10 አመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል፡፡
በአዘርባጃን 9 ጋዜጠኞች ወህኒ ቤት የሚገኙ ሲሆን ዘንድሮ ብቻ አራት የማህበራዊ ሚዲያ “የመብት ተሟጋቾች” በሀገሪቱ ያለውን ሙስናና የሠብአዊ መብት ጥሰት በመተቸታቸው ከያሉበት ተለቃቅመው ለእስር መዳረጋቸው ተጠቁሟል፡፡ ከሁለት አመት በፊት ጋዜጠኞችን በማሠር በ1ኛ ደረጃ ላይ የነበረችው ቱርክ፤ ዘንድሮ በርካታ ጋዜጠኞችን ከእስር በመልቀቅ ደረጃዋን አሻሽላ፣ 10ኛ ሆናለች፡፡ በአሁን ሰአት በቱርክ 7 ጋዜጠኞች ታስረው እንደሚገኙም ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡ በአህጉር ደረጃ ለጋዜጠኞች ተስማሚ ሆናለች ተብላ የተጠቀሰችው አሜሪካ ነች፡፡ የኩባና የሜክሲኮ መንግስታት እያንዳንዳቸው አንድ ጋዜጠኛ ከማሠራቸው ውጪ አህጉሪቱ ሠላማዊ ነች ብሏል – ሪፖርቱ፡፡
የCPJ ሪፖርት እንደሚጠቁመው፤ ከ2012 ወዲህ በመላው ዓለም 220 ጋዜጠኞች የታሰሩ ሲሆን፤ 132ቱ መንግስትን ተቃውማችኋል ወይም ሽብርተኛ ናችሁ በሚል ለእስር ሲዳረጉ፣ 45ቱ የታሠሩበት ምክንያት አይታወቅም ተብሏል፡፡ ከታሣሪዎቹ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት በህትመት ሚዲያዎች ላይ የሚሠሩ ጋዜጠኞች እንደሆኑ የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ቁጥራቸው 83 እንደሚደርስም ጠቅሷል፡፡ የተቀሩት ተቀጣሪ ያልሆኑ እንዲሁም የሬዲዮ፣ ዌብሣይት፣ ቴሌቪዥንና ማህበራዊ ሚዲያ ጋዜጠኞች እንደሆኑ ገልጿል፡፡
የታሳሪ ጋዜጠኞችን ቁጥር በየዓመቱ እያበራከቱ ነው ተብለው ከተጠቀሱት ሃገራት መካከል ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ቻይና፣ ባንግላዲሽ፣ ታይላንድ፣ አዘርባጃን፣ ባህሬን፣ ግብፅ፣ እስራኤልና ሳውዲ አረቢያ እንደየቅደም ተከተላቸው ከ1ኛ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሲሆን ዘንድሮ አንድም ተጨማሪ ጋዜጠኛ ባለማሰራቸው ከተጠቀሱት መካከል ካሜሩን፣ ስዊዘርላንድ፣ ሜክሲኮ፣ ኩባ፣ በርማና ቤላሩስ ይገኙበታል፡ ፡ ሲፒጄ እ.ኤ.አ ከ2009 እስከ 2014 “በአለማቀፍ ደረጃ የጋዜጠኞች ሁኔታ ምን ይመስላል?” በሚል ባካሄደው ጥናት፤ 404 ጋዜጠኞች በደረሰባቸው ጫና የትውልድ ሃገራቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደተገደዱ አረጋግጧል፡ ፡ በእነዚህ ዓመታት ጋዜጠኞች በብዛት ከተሰደዱባቸው ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ በ4ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ፣ 41 ጋዜጠኞች ሃገር ለቀው ወጥተዋል ተብሏል፡፡ 76 ጋዜጠኞችን ለስደት በመዳረግ ፊትአውራሪ የሆነችው ደግሞ ኢራን ናት፡፡ ሶርያ 44፣ ሶማሊያ 42 ጋዜጠኞች እንዲሰደዱ በማድረግ በሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኤርትራ 29፣ ኩባ 18፣ ፓኪስታን 15፣ ሲሪላንካ 14፣ ሩዋንዳ 11፣ ጋምቢያ 10 ጋዜጠኞች ከሃገር እንዲሰደዱ በማድረግ ከ5-10ኛ ያለውን ደረጃ ይዘውታል፡፡ ስደተኛ ጋዜጠኞች የተቀበሉ ሃገራት ተብለው ከተለዩ 10 ሃገራት መካከልም ኢትዮጵያ የምትገኝ ሲሆን ዘጠኝ ስደተኞች በመቀበል ከዓለም በ9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ አሜሪካ፣ ኬንያ፣ ቱርክ፣ ፈረንሳይ፣ ኡጋንዳ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ሱዳን፣ እንግሊዝ ከ1-8ኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ ሊባኖስ 10ኛ ሆናለች፡፡ አፍሪካ ብዙ ጋዜጠኞች ከተሰደዱባቸው አህጉራት ቀዳሚዋ ስትሆን 165 ጋዜጠኞች በተጠቀሱት አመታት አገራቸ ውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ መካከለኛው ምስራቅና የእስያ አገራት ይከተላሉ ተብሏል፡፡ በጥናቱ እንደተጠቆመው፤ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ጋዜጠኞች እስራትና ክስ ሽሽት ከሃገራቸው የወጡ ሲሆን የስደት አገር ከገቡ በኋላ 21 በመቶ ያህሉ ብቻ በሚወዱት የጋዜጠኝነት ስራ የመቀጠል እድል አጋጥሟቸዋል፡፡

temesgen desalegn
ከተሰደዱት ጋዜጠኞች ውስጥ ወደ ትውልድ ሃገራቸው መመለስ የሚፈልጉት 5 በመቶ ብቻ እንደሆኑም ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ ኢትዮጵያን ያላካተተው “ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን” ሪፖርት በአለማቀፍ ደረጃ ጋዜጠኞች በሙያቸው የሚጋፈጧቸውን ጫናና ተግዳሮቶች እየመዘገበ በየዓመቱ ሪፖርት የሚያቀርበው “ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን” (Reporters without Borders) ዘንድሮ (በ2014) በአለም ዙሪያ 66 ጋዜጠኞች መገደላቸውንና 119 ታፍነው መወሰዳቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ መቀመጫውን በፈረንሳይ ፓሪስ ያደረገው ቡድኑ፤ ሶርያን “የጋዜጠኞችን ህይወት የበላች ሃገር” በማለት በቀዳሚነት አውግዟታል፡ ፡ በጦርነትና በእርስ በርስ ግጭት በምትታመሰው ሶርያ ዘንድሮ ብቻ 15 ጋዜጠኞች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
Source: Zehabesha

Saturday, December 20, 2014

Ethiopia: Protester killed, several injured in a clash with the Police [Daniel Birhane – Horn Affairs]]

Daniel Birhane [Horn Affairs]
At least one died and several injured in Bahirdar, the capital of Amhara region, after protestors clashed with police on Friday.
The incident was triggered by a road expansion works on Mulualem Streetwhich will eat into the enclosures in western side – including a green area,Mulualem Conference Hall and the “Mesqel Square”, where Orthodox Christians’ celebratethe Founding of the True Cross for about a decade.
The rumor in the city, however, was that the area was being leased for an investor,HornAffairs learnt from two city residents.
Leaflets were circulated in the vicinity, at least as of Thursday, urging Christians to stand for their religion and the scheme to annex the land, an eyewitness described.
The protestors started at around Papyrus Hotel, around 9-10am, and marched to St. Giorgis Church, on the shore of Tana lake, then went to Mulualem Street, where they clashed with the police.
Bahirdar-city-Mesqel-Square-and-the-clash-areaHornAffairs learnt from an eyewitness that the clash erupted when the protestors reached a crossroad located few meters away from the City Administration, on the east, and the Mesqel Square, on the south.
A version of the incident suggests the protesters clashed with the police, when the later tried to stop them from reaching Mesqel Square, where it was rumored workswere underway.
Another version is that some of the protesters threw stones at the City Administration office which is also on the side of the road.
Gun shots started at around 11 am and continued to be heard until 3-4pm, residents told Horn-affairs.
The exact number of causalities remains uncertain as officials were unreachable.
A source in the City Hospital confirmed at least three persons were being treated for serious injuries, insisting that none were bullet injuries.
A Police source, present in the area, on the other hand, disclosed that two civilians were shot. One was hit in the stomach area, while another was described as “seriously wounded”.
The National TV’s late evening news confirmed the death of one, without providing details.
It was not possible to ascertain whether the causalities referred to by the Hospital source, the Police Source and the state TV were different.
Muslim residents were said to have taken part in the protest, though it could be incidental as a major Mosque is found at the very area of the clash and coincided with Friday prayers.

ባህርዳር እና አምቦ ላይ ለተደገሩ ህዝባዊ ተቃውሞዎች የተሰጠው ምላሽ ከምን ጊዜም በላይ የኢህአዴግን ባህርይ እና ትልም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡


በየትኛውም ሀገር ቢሆን ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች በአደገኛ ሁናቴ ለፖሊስ አስቸጋሪ ቢሆኑ፣ አደለም መጮህ ድንጋይ መወርወር ቀርቶ ለመደባደብ ቢጋበዙ እንኳን፤ ከውሃ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ የፕላስቲክ ጥይት እና የመሳሰሉት ታልፎ የሰው ልጅ ላይ መሳሪያ አይተኮስም፡፡ በፍጹም! የሰው ልጅ ክቡር ነው - አንድያ ህይወቱን እንዲህ በቀላሉ ማጣት የለበትም፡፡ የገደለ እንኳን ምህረት ይደረግለታል፡፡

ሰላማዊ ታጋዮች ነን፣ ድንጋይ ከመወርወር ጀምሮ መኪና ማቃጠልና ንብረት ማውደም ድረስ የሚሄድ ትግል ቢካሄድ እንኳን የሰው ልጅ ክቡር ህይወት ንብረት ወደመ ተብሎ በፍፁም ሊጠፋ አይገባውም!

እርግጥ ኢህአዴግ ከሰብዓዊነት ጋር የማይጣጣም ባህርይ ያለው አገዛዝ ነው፡፡ ይህ ሊገባው አይፈልግም፡፡ ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀ እንደሆነ ቀድሞ በመተኮስ በተደጋጋሚ ጊዜ እያመላከተን ነው፡፡ ከሀይል ውጪ የትኛውንም አማራጭ ለመጠቀም በፍፁም አይፈልግም፡፡ ይህ ባህርይውን በማጋለጥ በተለያየ ጊዜ እና ኮዝ ህይወታቸውን ጭምር በመክፈል ለስርዓት ለውጥ የሚካሄደውን ትግላችንን መልክ እያስያዙት ላሉ ወገኖቼ በሙሉ ፈጣሪ በቀኙ እንዲያውላቸው እመኛለሁ!

በየትኛውም አካባቢ የሚደረገው ትግልም ያለመስዋዕትነት ድል እንደሌለ በመረዳት በቁርጠኝነትና ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ይፋፋም! አገዛዙ ያለርህራሄ ሊገድለን ሲያሰፈስፍ እኛም አንድ ህይወታችንን ለልጅ ልጆቻችን ሰላም ተስፋ እና አንድነት ስንል ለመስጠት እንቁረጥ!

ይህ ከአገዛዝ ወደ ፍትኃዊ ስርዓት የሚደረግ የነፃነት ትግል ነው!

እየሞትን እናሸንፋለን!

Friday, December 19, 2014

በዛሬው ባህርዳር ሰላማዊ ሰልፍ በርካታ ስዎች እንደቆሰሉና እንደሞቱ ከስፍራው ያሉ የአይን እማኞች ማስረጃዎችን አድርሰውናል፡፡

በዛሬው ባህርዳር ላይ በነበረው ግጭት ምክንያት በርካታ ስዎች እንደቆሰሉና እንደሞቱ ከስፍራው ያሉ የአይን እማኞች ማስረጃዎችን አድርሰውናል፡፡
የአስከሬን ክፍል ሃላፊዎችና ተቆጣጣሪዎች ባደረሱን መረጃና ማስረጃ ከሰባት ያላነሱ አስከሬኖች በጥይት ተለያየ ቦታ ላይ ተመትተው እንደመጡና አስከሬን ክፍል የተቀመጡም እንዳሉ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን አስከሬኖችን ፎቶ ለመያዝ ተሞከረው ሙከራ አልተቻለም፡፡
የተወሰኑትን ቁስለኛና አስከሬኖች መያዝ ችለናል፡፡ በጣም አሳዛኝ የሚያደርገው ደግሞ ደካማ እናቶች መኖራቸው ሲሆን ከዚህ ከፎቶውም መረዳት ይቻላል…