Friday, December 4, 2015

የብአዴንን ህዝባዊ ወገንተኝነት ያያችህ?



(ከጠረፈኛው የፍትህ ርሃብተኛ፤ ቂልንጦ ማጎሪያ ቤት)

ህዝባዊ ነኝ ብሎ የሚያወራ ወይም የሚመኝ ሁሉ ህዝባዊ ሊሆን አይችልም፡፡ በተግባር መሬት ላይ ላለው ህዝብ ጠብ የሚል ህዝባዊነትን የሚሸት ተግባራትን ካልፈፀመ፡፡ በእኔ እይታ የብአዴንን ህዝባዊነትና አድርባይነቱን፣ አፋዊና ተግባራዊነቱን መዝኜ ስመለከተው ህዝባዊነቱና ተግባራዊነቱ ቀልሎ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም ብአዴን አድርባይ አፋዊ እና ጥገኛ ፓርቲ እንጂ የራሱን ማንነት ጠብቆ ህዝባዊነቱን ያስቀጠለ ድርጅት አይደለም፡፡ በብአዴን እየተሠራ ያለው ሆድ አደርነት፣ አድርባይነት፣ ግላዊነት፣ የግለሰብ ኪስ አድላቢነትና ማን አለብኝነትን እን በማንኛውም መልኩ ካመጣቸው ለውጦች ይልቅ ያጠፋቸው ታሪካዊ ስህተቶች እና ውድቀቶች ለውጥ የሚለውን ቃል አፈርድሜ አብልተውታል፡፡ 
ህዝባዊነት ሲባል ለህዝብ ሲሉ እንደ ሻማ ቀልጠው ብርሃን መስጠትን፣ ለህዝብ ሲሉ የግል ጥቅም ማጣትን /መተውን/ ለህዝብ ተገቢውን መስዋዕትነት መክፈልን፣ ኃላፊነትን በአግባቡ መውጣትን፣ የህዝብ ሀብትና ንብትን በአግባቡ መጠበቅና መንከባከብን፣ ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ መስጠትን አካባቢውን ወደ ተሻለ የዕድገት ጎዳና መለወጥን፣ በኢኮኖሚያዊ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተራማጅ አስተሳሰቦችን ማምጣትን ይጠይቃል፡፡ በሀሳብና በህግ የበላይነት ማመንን፣ ስለ እውነትና ታሪክ ወግና ባህል መከበር ዘብ መቆምን፣ ድህነትን ድንቁርናና ጦርነትን በማስወገድ የሠላምና የፀጥታ የሠብአዊነት የዲሞክራሲያዊ መብት፣ የእኩልነት የፍትህ፣ የመልካም አስተዳደርና የፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በማድረግ፤ ከህዝብ ፊት ሆኖ መሠናክሎችን በአሳታፊነት፣ በመቻቻልና በውይይት በመፍታት ዋጋ መክፈልን ይጠይቃል፡፡ ህዝባዊነት!
ህዝባዊነት አስፈላጊ ብቻ መሆን አይችልም! መፈለግ አንዱ ቅድመ ሁኔታ ቢሆንም ዋነኛው ነገር በተግባር ማሳየት ነው፡፡ ስለዚህ በቅድሚያ ራስን ማሸነፍ ይጠይቃል፤ ከራስ ጋር መታረቅን ይጠይቃል፡፡ እንዲሁም መቅደም ያለበትን ለይቶ ማስቀደምንና መከተል ያለበትን ማስከተልን ይጠይቃል፡፡
ህዝባዊነት ርዕስ አድርጌ የወሰድኩበት ዋነኛ ምክንያት ኢህዴን - ብአዴን ከሠሞኑ 35 ዓመት የምስረታ በዓሉን በከፍተኛ ድግስ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የተመረጡ ቦታዎችና እስከ ጎረቤት ሀገር ጅቡቲም ድረስ በመሄድእወቁልኝ፣ የመናገር መብቴ 35 ዓመት በወያኔ ተፈቀደልኝ፣ ብሉ ጠጡልኝ፣ ድሌ ዛሬ ነው፣ ሠርጌ ዛሬ ነው ይህ የመጨረሻዬ ነውበሚመስል መልኩ እያከበረ መሆኑ ነው፡፡ ዋናው መፈክሩም ‹‹የብአዴን ህዝባዊነት›› ላይ ያተኮረ በመሆኑ ጭምር ነው ርዕሴ ያደረኩት፡፡ የዘንድሮው በዓል ብአዴን ‹‹ለሠርጌ ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ›› በሚል ከወያኔ ነፃ የወጣ ይመስል፤ ለዚህ ለማይደገመው ሠርጌ ያልሆነ ገንዘብ ለምን ሊሆነኝ ነው በማለት በሩጫ፣ በኳስ ጨዋታ፣ በእስክስታ፣ በስነ-ፁሁፍ ‹‹መስክ ጉብኝነት›› ‹‹ፓናል ውይይት›› በጥያቄና መልስ፣ በውዝዋዜው፣ በከፍተኛ ወጭ ሽልማትና የመጠጥ የምግብ ዝግጅት ‹‹ታጥቄ እንደታገልኩት ታጥቄ እጠጣለሁ እጨፍራለሁ፣ በውስኪና በሻምፓኝ እረጫለሁ›› ሲል ተመልክተናል፡፡
ታጥቄ እስክስታ እመታለሁ፤ ሠልፍ እወጣለሁ፣ ሁሉንም የቴሌቭዥን ጣቢያዎች እቆጣጠራለሁ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ቲሸርቶችን፣ ፓንፕሌቶችን፣ ጋዜጦችን፣ መፅሄቶችንና መፅሀፍቶችን አሳትሜ እየቸበቸብኩ ነው ብሎናል፡፡ ይሄን ነው እንግዲህ ለብአዴን ህዝባዊነት ማለት፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ባሉበት፣ ህፃናት እየሞቱ በሚገኙበት፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች በስደት ላይ ኩላሊታቸውን እየተነጠቁ የባህር አሳዎችና አዞዎች እጣፈንታ እየሆኑ፣ የመኪና አደጋ ሠለባዎች፣ የበርሃ ሲሳዮችና አንገታቸውን እንደ በግ እየታረዱ ባለት አሳዛኝና አሠቃቂ ጊዜ ላይ ይህ ሁሉ ድግስ ህዝባዊነትን ያሳይል? በቁስለኛው ህዝብ ላይ ተጨማሪ ቁስል ማፍራት ሀገር ቀምቶ በማሣደድ፣ ማሣረድ በሀሳብ ልዩነት የተነሣ በየ እስርቤቱ አሸባሪ የሚል ታርጋ በመለጠፍ እያጎሩ ማሰቃየት፣ ማኮላሸት በአካል በሞራሉ በስነ-ልቦናው ጫና መፍጠር ህዝባዊነት ነው ፀረ ህዝብነት?

ከሥራ እያፈናቀሉ፣ የሀሰት/የፈጠራ ወንጀልን እየፈጠሩ፣ በሀሰት አስገድደው እያስመሰከሩ፣ ወጣቱን በአካልና በአዕምኖ እየቀጠቀጡ ማደንዘዝ፣ ያለፍትህ ማጎር ነው የብአዴን ህዝባዊነት የሚባው የተቃርኖ ዓለም፡፡ በእርግጥ የቀጥተኛ አለቃው ወያኔ የተቃርኖ ዓለምም ተመሳሳይ ነው፡፡ በጣም የሚገርመው የአማራን ህዝብና ኦርቶዶክስን ፈርጀው ‹‹አከርካሪውን እንሰብራለን›› ብለው በጫካ ዕቅድ የተነሱት እነ ጄነራል ሳሞራ የኑስ እና አባይ ፀሃዬ ስለ ህዝብ አስተያየት መጠመዳቸው ነው፡፡ ምን የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ?

ይህ ብአዴን ነው በሀገራችን 15 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በድርቅና በረሃብ ላይ ባለበት ሁኔታ 35 ዓመት የአሮጊት (ጋለሞታ) ድሮ ውስኪና ሻምፓኝ የሚራጨው፡፡ ሀገሪቱ አላዋቂ ሰዎች ሞልተውባታል፡፡ ብአዴንም ሆነ መሰል ድርጅቶች በአጉል ድንቁርና፣ ትዕቢትና እብሪት ተወጥረው በአስተሳሰብ ድህነት /ደዌ/ ተይዘው ወደፊት መንቀሳቀስ አቅቷቸው፣ መቆም ተስኗቸው ወደ ኋላ በማፈግፈግ ላይ ናቸው፡፡ 

ደም የገበሩትን አባቶቻችንና እናቶቻችንን ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ግን የምንፈልገው አላማቸውን አስቀጥሎ የኢትዮጵያንና ክልሉን ህዝብ ከድህነት አረንቋ የሚያላቅቅ መሬት ላራሹ ጥያቄን የሚመልስ፣ ፍትህና እኩልነት የሚያሰፍን ነፃነትና ክብርን ሀገርን የማይቀማ፣ መንደርተኛ ያልሆነ፣ ኢትዮጵዊነት ያሠፈረ ድርጅትና አመራር ነበር፡፡ ግን አለመታደል ሆኖ በተቃራኒው ሆነ! ስለመበታተን የሚሰብክ፣ እወክለዋለሁ የሚለውን ህዝብ የሚያስጨፈጭፍ ሆነ! ብአዴን የህዝብ ወኪል ነኝ እያለ ከጥቃት ህዝብን ከመታደግ ይልቅ አላዳንኩሽምን ይዘምራል! የስቃይ ድምፅ እየቀረፀ ያዳምጣል፡፡ 
በአማራ ክልል ብዙ አሣፋሪና አሳዛኝ ድርጊቶችን እየተሰሩ ነው፡፡ ምሳሌዎችን እንመልከት፡- 

በክልሉ ውስጥ ሰዎች በአልሞ ተኳሽ ወታደሮች ተገድለው በመኪና ሲጉተቱ፣ ፀጉራቸው ከእንጨት ጋር ታስሮ በአስፓልት ላይ በህዝብ ፊት ሲጎተቱ አይተናል! አይቀበሩም (በቤተክርስቲያን ስርዓት) ተብሏል፤ ቤተሰብ እንዳያለቅስ የተከለከለ መሆኑን አይተናል (ምሳሌ በታች አርማጭዎ ሳንጃ ከተማ - እነ ሽንኩ ካፌና ዳኛው ይህ አረመኔያዊ ድርጊት ተፈፅሟል) ታዲያ ይህ ህዝባዊነት ወይስ ፀረ-ሕዝባዊነት?)

ሰዎችን ከእስር ቤት አስወጥተው ሲገድሉ አይተናል:: በፍ/ቤት ተከሰው 4 በላይ ሰዎች የምስክርነት ቃላቸውን ቢሰጡም ገዳዩ በሙስና በነፃ ተለቋል፡፡ (ታች አርማጭ ወረዳ ወጣት ጎሹ እያዩ ሲገደል፡፡) በሀሳብ ልዩነት መጠፋፋት የለብንም ይላል የብአዴን መፈክር፡፡ ግን ብአዴን በመቃወማችንና ባለመደገፋቸው የተነሳ የመኖር መብታቸው ተገፎ (ጭቆና ግፍና በደል) በዝቶባቸው ኑሯቸውን፣ የሞቀ ቤታቸውን፣ ሚስታቸውንና ልጃቸውን ትተው ኑሯቸውን ጫካ ያደረጉ ወገኖች እንዳሉ ታዝበናል! የሽፍታ ቤተሰብ /ወገን/ በመሆናቸው ብቻ ‹‹ገደላችህ አስክሬን አምጡ!›› እየተባሉ ልጆቻቸው ለመግደል ፈቃደኛ ባመሆናቸው የተነሳ መሬታቸውን የተነጠቁ፣ እርሻ ቦታቸውን ወደ ከተማ እንዲገቡ የተገደዱ በኑሮ ውድነትና በእስር እየተሰቃዩ ያሉ ሰዎችን አየን፡፡

የህግ የበላይነት ተጥሶ የግለሰብ የበላይነት ሰፍኖ በቂም በቀልና በስነ-ልቦና ሰዎች ተሰቃይተዋል፡፡ የዘር ማጥፋት ድርጊት የተፈፀመባቸውን የወልቃት አርማጭሆ ነዋሪዎችን አይተናል፡፡ በብሎክ የህዝብ መሬትን በመሸንሸን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጥቅመኛ ባለሀብቶች ሲሸጡ አይተናል፡፡ የመኖገር፣ የማሰብ፣ ያለመሰቃየት መብት አላችሁ እየተባለ በተቃራኒው ግለሰቦች በጉባኤ በመናገራቸው በጅምላና በጭፍን ፍርጃ ፀረ-ሠላም፣ ፀረ-ዴሞክራሲ፣ አሸባሪ እያሉ በማሰባቸውም እየታሰሩ ነው፡፡ ሀሰት ነግሶ፣ እውነት ተገርስሶ፣ በውሸት ሪፖርት፣ በፈጠራ ክስ ኑሮአቸውን ያደረጉ ወገኖችን አይተናል፡፡ 


ብአዴን ጥገኛ ሲሆን ወያኔ በበላይነት አገሪቱንም ድርጅቶች ሲያስከብር ኖሯል፡፡ ዛሬ ብአዴን 35 ኣመቷ ዳሩኝ ማለቷ የሀገራችን ባህል ወይም ስርኣትን የጣሰ ነው፡፡ ‹‹የጋለሞታ/ የአሮጌቶች›› ጋብቻ ነው! ስካሁን ድረስ ወያኔ ባሪያ አድርጓት ከቆየ በኋላ ትንፍሽ ብላ የማታውቀ ለመጨፈር አስፈቅዳለች፤ ጎጠኝነት አስተምሯት ቅማንት አማራና አገው ብቻ ሳይሆን በጎጥ እየተከፋፈለ የቀን ሠራኛው ሲገደል አይተናል፡፡ የክልሉ ዜጎች ሲፈናቀሉ ምላሽ መስጠት ሲሳናት አይተናል፡፡ የኮንትሮባንድ ንግድ በመኪና እየነገደች ቲሸርትና ኦሞ የያዘን ድሃ ትወርሳለች፡፡ ታዲያ የብአዴን ዲሞክራሲያዊነትና ህዝባዊነት የት ላይ ነው?

እነርሱ መግደላቸውን አያቆሙም - ግርማ ካሳ

በተለያዩ የኦሮሚያ ቦታዎች የዩኒቨርሲቲና የሃይ ስኩል ተማሪዎች፣ እንዲሁም ነዋሪዎች ሕግ መንግስቱ የሚፈቅድላቸውን መብት በመጠቀም ተቃዉሞ ላለፉት በርካታ ቀናት እይሰሙ ነው።
ለሕገ፣ ለሕገ መንግስቱ፣ ለሰብዓት ምንም ደንታ የሌላቸው የህወሃት/ኢሕአዴግ ታጣቂዎች ላለፉት 24 አመት ሲያደርጉ እንደነበረው ወገኖቻችንን በጥይት ኤያረገፉ ነው።
ብእር ለያዙ እጆች ሰደፍ፣ ወረቀት ለያዙ እጆች ዱላ ፣ መብትን ለሚጠይቁ አንደበቶች ጥይት ሆኗል መልሱ። አሁንም እንዳለፉት አመታት፣ ኢትዮጵያዉይን በኢትዮጵያዉይንን እጅ ደማቸው እየፈሰሰ ነው።
ወያኔዎች ሶስት ተማሪዎች እንደተገደሉ አምነዋል። ቁጥሩ ግን ከዚያ በላይ እንደሆነ በገሃድ እየተዘገበ ነው።
በነገራችን ላይ ወያኔዎች በኦሮሚያ ብቻ አይደለም ጥይት እያረከፈከፉ ያሉት። በጎንደርም ላለፉት ጥቂት ቀናት ወደ 14 የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎንች በታጣቂዎች ተገድለዋል።
ወገኖች እነርሱ ላለፉት 24 አመታት ሲገድሉ ነው የኖሩት። በዘር ከፋፍለዉን እንዳንግባባ አድርገዉናል። “እነርሱና እኛ እንድንባባል” አድርገዉናል። ካልነቃን፣ ካልተስማማን፣ ካልተባበርን፣ እነርሱ ምንም የሚሆኑት ነገር የለም። አሜሪካኖችና ምእራባዉያን ያዝኑልናል ብለን የምናስብ ከሆነ ደግሞ በጣም ተሞኝተናል። ተለያይተን ባለንበት ሁኔታ ምንም የሚሻሻል ነገር አይኖርም። ለትንሽ ጊዜ ጋብ ብሎ ከወራት፣ ከአንድ አመት በኋላ ደግሞ እንደገና ዜጎች ተገደሉ የሚል ዜና እንሰማለን።
እንግዲህ ነጻነት በፉከራና በንዴት አይመጣም። መሰባሰብ ያስፈልጋል። ተግሉን በግብታዊነት ሳይሆን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል። ለዚህ የፖለቲካ ልዩነቶች አሉን፣ በተቻለ መጠን ባሉን ልዩነቶች በሰለጠነ መልኩ መከራከራችን እና መወያየታችንን እየቀጠልን፣ በምንስማማባቸው አጀንዳዎች ዙሪያ ግን የጋራ ትግል ማድረግ እንችላለን። ለዚያም መስራት አለብን።
ከዘር አጥር ወጥተን፣ ፣ ወያኔዎች በማካከላችን ያስቀመጡትን የዘረኝነት ነቀርሳ ነቅለን፣ ኦሮሞ፣ ይሁን ትግሬ፣ ጉራጌ ይሁን ከንባታ፣ ጎንደሬ ይሁን ጎጃሜ፣ ሙስሊም ይሁን ክርስቲያን ሁላችንም እኩል የሆንባትን አገር ለማየት፣ በአዲስ መንፈስ እንነሳ። እንዲህ መቀጠል የለበትም። አንድ በአንድ እኮ እያለቅን ነው !!!!!!
ከዚህ በታች የምታዩት ወያኔዎች በወገኖቻችን ላይ ሰሞኑን ያደረሱት ነው !!!

Thursday, December 3, 2015

የወገኖቻችን ስቃይ፣ ችግርና ብሶት በያለንበት ይሰማን፤ ለመፍትሔውም በጋራ እንነሳ!- የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ


def-thumbበአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሰበብ በከተማዋ ዙርያ ያሉ ወገኖቻችንን ማፈናቀል በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው። በማስተር ፕላኑ ሰበብ የሚፈናቀሉ ገበሬዎች የሁላችን ወላጆች፣ ወንድሞችና እህቶች ናቸው። በማስተር ፕላኑ ሰበብ የምንፈናቀለው ሁላችንም ነን። ይህን መሰሪ ፕላን በመቃወም ላይ ያሉት የኦሮሞ ተወላጅ ወገኖቻችን ትግል ፍትሀዊ በመሆኑ አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከጎናቸው ይቆማል።
በዚሁ ወቅት በጎንደር ሌላ አሳዛኝ ጉዳይ ተከስቷል። ህወሓት ከሶስት ሺህ በላይ ዜጎቻችንን ያጎረበት እስር ቤት በእሳት ሲጋይ ዜጎች ተቆልፎባቸው እንዲነዱ ተደርጓል። ከእሳቱ በእድል ያመለጡት በጥይት ታድነዋል። ኢትዮጵያዊያን እንዲህ ዓይነቱን ጭካኔ የሚያውቁት በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ጊዜ ነው። ይህን ጥቃት በመቃወም ላይ ያሉ የአማራ ተወላጅ ወገኖቻችን ትግል ፍትሀዊ በመሆኑ አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከጎናቸው ይቆማል።
ግፍ ያልተፈፀመበት የኢትዮጵያ ክፍል ባይኖርም ሰሞኑን በአማራና በኦሮሚያ ላይ በርክቷል። በሁለቱም የአገራችን ክፍሎች የንፁሀን ደም እየፈሰሰ ነው፤ በሁለቱም ቦታዎች የእናቶች ዋይታና እሪታ ጎልቶ እየተሰማ ነው። የህወሓት አገዛዝ የትውልድ ቦታ፣ ቋንቋና ዘር ሳይለይ በኢትዮጵያዊያን ሁሉ ላይ የተደቀነ አደጋ መሆኑ ከምንጊዜውም በላይ ዛሬ ግልጽ ሆኗል።
ለዚህ የምንሰጠው ምላሽ ምንድነው? ዛሬም ኦሮሚያ ውስጥ የሚፈፀመው በደል የኦሮሞ፤ አማራ ውስጥ የሚፈፀመው በደል የአማራ ጉዳይ አድርገን እንወስዳለን? መቸ ነው ኦሮሚያ ላይ ለደረሰው ጥቃት አማራዉ፤ አማራ ላይ ለደረሰው ጥቃት ኦሮሞው የሚቆረቆረው?
የሁላችን የጋራ ጠላት የሆነው ህወሓት መኖሩ በዘውግ የተከፋፈለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ አንድነት የሚያመጣ ታላቅ ኃይል ሊሆን ይገባል። ይህ የመከራና የመጠቃት ወቅት የምንቀራረብበት ወቅት ሊሆን ይገባል። ይህ የመከራ ወቅት በህወሓት ላይ በጋራ የምንነሳበት ወቅት ሊሆን ይገባል። ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ ማኅበረሰቦች በሙሉ በፀረ-ህወሓት ትግል መቀናጀት ይኖርባቸዋል። ይህ ማድረግ ግዴታችን ነው።
ለችግሮቻችን መፍትሄ የምናገኘው ችግሮቹ ከተፈጠሩበት እርከን በላይ ሆነን ስናስብ እንጂ ችግሮቹ በፈጠሩበት ደረጃ ላይ ቆመን መሆን አይችልም። ችግሮቹ ከተፈጠሩበት እርከን በላይ ለመሆን አገር አቀፍ እይታ መኖሩ እጅግ ተፈላጊ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያን ሁሉ በተለይም የአማራና የኦሮሞ ልሂቃን ይህንን ጉዳይ አበክረው እንዲያስቡበት አርበኞች ግንቦት 7 በጽኑ ያሳስባል።
ግፍ ሞልቶ የፈሰሰበት ወቅት ላይ እንገኛለን። የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሆኑት ሕፃናት በፌዴራል ፓሊስ ጥይት የሚገደሉበት አሳዛኝ ወቅት ላይ ነን፤ ዜጎች በር ተዘግቶባቸው በእሳት እየጋዩ ነው። ሰፊ እና ለም የእርሻ መሬት ለሱዳን በስጦታነት ለመስጠት ዝግጁቱ የተጠናቀቀበት ወቅት ላይ ነን። ከአስር ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተርቧል። በፍትህ እጦት እስር ቤቶች በንፁሃን ዜጎች ተሞልተዋል። ውሀ፣ መብራትና የቴሌፎን አገልግሎት ብርቅ ሊሆኑ ነው። ይህ ሁሉ እየሆነ ግን የሥርዓቱ አገልጋዮችና ደጋፊዎች በህንፃ ላይ ህንፃ እየገነቡ በድሀው ላይ ይሳለቃሉ። የህወሓት አገዛዝ ድህነትን፣ ችጋርን፣ ስደትን፣ የእርስበርስ ግጭቶችን እያባባሰ ኢትዮጵያን እየጋጠ የሚኖር አገዛዝ ነው። አገዛዙ በቀደደልን ቦይ ከተጓዝን ችግሮችን ማባባስ እንጂ ማርገብ እንኳን አንችልም። ይህንን ሥርዓት በቃህ ማለት የአማራ ወይም የኦሮሞ አጀንዳ አይደለም፤ ይህ የሁላችንም – የኢትዮጵያዊያን – ጉዳይ ነው።
ለቀምት፣ ሀረር፣ ሱልልታ እና ሌሎች በርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ ለደረሱ ጥቃቶች ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ሀዋሳ፣ መቀሌ፣ አሶሳ፣ ሁመራ፣ ጋምቤላ ውስጥ ተቃውሞ መሰማት አለበት። በጎንደርና ባህርዳር ለደረሰውም ጥቃት አዳማ፣ ጅማ፣ ሆሳዕና፣ ጅግጅጋ፣ አክሱም ላይ ተቃውሞ መሰማት አለበት። በማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ለሚደርሰው በደል መላዋን ኢትዮጵያ ሊያሳምም ይገባል። መከፋፈላችን መከራችን አብዝቶታል፤ የህወሓት እድሜን አርዝሟል፤ ይብቃ!
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የመከራ ጊዜዓችን እንዲያጥር በዘውግ ሀረግ፣ በብሔርና እና በሀይማኖትና ሳንታጠር የወገናችን ህመም ይሰማን፤ ተሰምቶንም ለጋራ ትግል እንነሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
Source: patriotg7.org

ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ምስክር ሆነው እንዳይቀርቡ ያቀረበውን ይግባኝ ዛሬ ህዳር 23/2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውድቅ አደርጎታል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ተጠይቆ የነበር ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ በተደጋጋሚ ሳያቀርባቸው ቀርቷል፡፡
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ምስክርነት በተጠሩበት ወቅት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ እና በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መዝገብ ላይ ክስ ቀርቦባቸው በእድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ ተወስኖባቸው የህዝባዊ መብታቸው የተሻረ በመሆኑ በምስክርነት ሊቀርቡ እንደማይችሉ መቃወሚያ አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይሁንና ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡላቸው የጠየቁት ለዋስት አሊያም ልዩ አዋቂ ምስክር ሆነው ሳይሆን ነበሩበት የተባለውን ጉዳይ ለመናገር በመሆኑ ለምስክርነት ሊቀርቡ ይገባል በሚል የፌደራል አቃቤ ህግ ያቀረበውን ተቃውሞ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
የልደታ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ቀርበው ምስክርነት እንዲሰጡ ከወሰነ በኋላ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ‹‹ትዕዛዝ አልደረሰኝም፣ የተፃፈው ለቃሊቲ ሳይሆን ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የሚል ነው›› እና ሌሎችም ምክንያቶች በማቅረብ በተደጋጋሚ አቶ አንዳርጋቸውን ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡ በስተመጨረሻም ጥቅምት 12/2008 ዓ.ም ማረሚያ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ቃሊቲ እንደሌሉ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ከተከሰሱት መካከል አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) ውጭ ያሉት የፍትህ ሂደቱ እየተጓተተባባቸው በመሆኑ የአንዳርጋቸው ፅጌ ምስክርነት ቀርቶ በሌሎች መረጃዎች ውሳኔ እንዲሰጥላቸው ሲጠይቁ ሁለቱ ተከሳሾች ግን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሊመሰክሩላቸው እንደሚገባ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበው ነበር፡፡
በዚህም መሰረት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለፀረ ሽብር ግብረ ኃይልና አቶ አንዳርጋቸውን ጠይቀውታል ለተባሉት የብሪታኒያ አምባሳደር ደብዳቤ መፃፋቸው ይታወቃል፡፡ ይሁንና ተከሳሾቹ ለሶስቱ አካላት ደብዳቤውን በፃፉበት ማግስት የፌደራል አቃቤ ህግ ከወራት በፊት ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መመስከር አይገባቸውም ብሎ አቅርቦት የነበረውን መከራከሪያ መሰረት በማድረግ አቶ አንዳርጋቸው ምስክር እንዳይሆኑ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ነበር፡፡
የአቃቤ ህግን ይግባኝ ያየው ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ዛሬ ህዳር 23/2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ‹‹አንድ ሰው ለምስክርነት ይቅረብ አይቅረብ በሚል ይግባኝ ሊጠየቅበት አይገባም፡፡ ካስፈለገ ግለሰቡ የሰጡት ምስክረነት መረጃው ተመዝኖ የሚሰጠው ፍርድ ላይ ይግባኝ ሊባል ይችላል፡፡ እኛም ጉዳዩን ለማጣራት ምስክርነቱ እንዲቋረጥ አድርገን የነበር ቢሆንም አሁን ግን እንዲቀጥል ወስነናል፡፡ የአቃቤ ህግን ይግባኝም አልተቀበልነውም›› ሲል ይግባኙን ውድቅ አድርጓል፡፡ አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ምስክር መሆን የለባቸውም ብሎ ያቀረበው ክርክር በፍርድ ቤት ውድቅ ሲሆንበት ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡
በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከተከሰሱት በተጨማሪ በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል 1ኛ ተከሳሽ አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት ጠርቷቸዋል፡፡ በሌሎች የክስ መዝገቦች ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር ተገናኝታችኋል የተባሉ ተከሳሾችም አቶ አንዳርጋቸውን የመከላከያ ምስክር አድርገው ሊጠሯቸው እንደሚችሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡

Source: Negere Ethiopia

Wednesday, December 2, 2015

እናንተ እውነትን የምትደባብቁ ነግ በኔ በሉ! !







(አሌክስ አብርሃም)
Bilderesultat for EBCኢቢሲ "በቀኑ ዜና እወጃየ በጎንደር ማረሚያ ቤት ትላንት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሞተ ሰው የለም ብየ የዘገብኩት ኮማንደር ሰይድ ሃሰን የሚባሉ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ "ዋሽተው" መረጃ ስለሰጡኝ ነው,,,,,ሃቁ ግን 17 እስረኞች ከእሳቱ ለማምለጥ ሲሞክሩ እርስ በእርስ ተረጋግጠው ህይወታቸው አልፏል ይህንንም የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሸን ኮሚሽነር አስተዳደር ሃላፊ በላይ ዘለቀ የሚባሉ (ስሙንማ ይዘውታል) ገልፀውልኛል " ሲል ማምሻውን አስተባብሏል,,,,, (አላግጧል) መቸስ የሞተ ሰው የለም ብለው 17 ከሞተ ,,,, 17 ሰው ብለው ካመኑ የሟቹ ትክክለኛ ቁጥርም ሌላ ሊሆን ይችላል! ! የሆነ ሁኖ ከዚህ የተዘበራረቀ አሳፋሪ ዜና,,, ሁለት ነገር ተረዳሁ,,,
1ኛ, ብሔራዊ ቴሌቪዥናችን ያልተረጋገጠ መረጃ የሚያቀርብ ግድ የለሽ ተቋም መሆኑን አውቀናል
2ኛ, ማረሚያ ቤቶቻችን በስራቸው ላሉት ዜጎች ህይዎት እንኳን ግድ በሌላቸው ውሸታም አልያም በስራቸው ባለ ማረሚያ ቤት ስለሚከናወነው ነገር ምንም እውቀት በሌላቸው ሰዎች እንደሚመሩ አጋጣሚው ነግሮናል !!
17 ሰውኮ እጅግ ብዙ ነው,,,, የሃዘን ቀን ሁሉ በመላው ኢትዮጲያ መታወጅ ያለበት ጉዳይ ነው,,,,,17 ኢትዮጵያዊያን የሚያድናቸው አጥተው በማረሚያ ቤት ማለቃቸው ብሔራዊ ውርደት አቅመ ቢስነት ነው! ! በዚህ ላይ የጋዜጠኞቹ ወሽካታነትና ከህዝቡ ሃዘን በላይ ተቋሞቹ ለማይረባ ፖለቲካቸው ማሰብ ያሳፍራል! !

ጋዜጠኞች በተለይ በአል እና ድግስ በያለበት ለመገኘት ማንም የማይቀድመው የክልሉ ቴሌቪዥን በወቅቱ ከማንም በፊት በቦታው መገኘት እና ትክክለኛ መረጃ ማድረስ ነበረበት,,,, ቢሯቸው ተዘፍዝፈው በስልክ ሰው አልሞተም,,, ተሳስተን ነው ሙቷል እያሉ የሚዘላብዱት ምናይነት አሳፋሪ ሙያዊ ስነምግባር ቢኖራቸው ነው?
ደግሞ ኢቢሲ "ስህተቱ የአቶ እከሌ ነው እርማቱ የማንትስ ነው " እያለ የሚቀልደው የመንደር እድር ወይም የቤተ ዘመድ ጉዳይ መሰለው እንዴ ?? ይሄ አንገብጋቢ የሆነ አገራዊ ጉዳይ ነው,,,, መንግስት እኔ እጠብቃቸዋለሁ ብሎ በራሱ ሃላፊነት ስር ያስቀመጣቸውን የህዝብ ልጆች መነሻው ምንም ይሁን ምን የሞታቸው ምክንያት እሳቱም ይሁን "እርግጫ " ወይም ሌላ,,,, ብቻ ሃላፊነቱን ባለመወጣቱ 17 ወገኖቻችን ህይወታቸው አልፏል! !
ለሟች ወገኖች መፅናናትን እየተመኘሁ መንግስትም ሆነ በመንግስት ትዛዝ የምትንቀሳቀሱ የሚዲያ ተቋማት ይህን ጉዳይ በዘገባችሁበት ግዴለሽና አሳፋሪ አዘጋገብ ለእናተም ቤተሰብና ላቆሰላችሁት ኢትዮጲያዊ ሁሉ ፈጣሪ የሚያፅናና ቀን ያምጣ ከማለት ሌላ የምለው የለኝም! !
Source: Alex Abreham

"ሚራክል እድገት,,,,, ሚራክል አዋጅ,,,,, በሚራክሉ ኢቢሲ "


(አሌክስ አብርሃም)
ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ (እንባ ጠባቂ የሚባለው ተቋም ሃላፊ መሰሉኝ)ዛሬ ማታ በኢቢሲ በተላለፈና የመረጃ ነፃነት አዋጅ አፈፃፀም ላይ ለመምከር በተደረገ ስብሰባ ስለመረጃ ነፃነት አዋጁ ዘግይቶ ስራ ላይ መዋል ተጠይቀው ምላሽ ሲሰጡ ይህን በእጃቸው የያዙትን ቀይ መፅሐፍ እያሳዪ,,,,
" እዚህ ውስጥ ሚራክል ነው ያለው,,,, " አሉ!
እኔ ደግሞ ይሄ በጃቸው የያዙት መፅሃፍ ቅዱስ ይሆን ቁርዓን ብየ "ስንቄ ነይ መነፅሬን አቀብይኝ " አልኩና ሳየው,,,,, ሶስት አመት ከርሞ ስራ ላይ የዋለው እንደራሳቸው ክብርት ፎዚያ አባባል ( ገና በደንብ ሳያልቅ የተቀመጠውን ጊዜ ለማክበር ሲባል ስራ ላይ የዋለው) የመረጃ ነፃነት አዋጅ ነው:)
እኔማ "እንባ ጠባቂ ተቋም,,,, እንባ መጠበቁን ትቶ እንደብዙሃኑ ኢትዮጲያዊ ጌታን መጠበቅ የጀመረ መስሎኝ አሁን ዘየደ ብየ ነበር:),,,, እውነቴን እኮ ነው,,,, በዚህ ሰዓት ወደፈጣሪ እንጅ ወደእንባ ጠባቂ ተቋም እንባውን የሚረጭ ዜጋ እንብዛም ነው,,,,,
በነገራቸን ላይ ስለመረጃ ነፃነት "እንመካከር " ብለው ተሰብስበው እርስ በርስ ሲወነጃጀሉና አንዱ አንዱ ላይ ጣቱን ሲቀስር የአገራችን ተቋማት ይሄን የፈረደበት ህዝብ መምከር እንጅ እርስ በርስ መመካከር እንደማይሆንላቸው ፍንትው ብሎ ይታይ ነበር! !
,,,, መንግስት ያስቀመጣቸው ባለስልጣናት ናቸው መረጃ የማይሰጡት,,,,, የለም ጋዜጠኛው ነው ችግር ያለበት,,,, ንትርክ,,,,, ሳምሶን ማሞ "እንባ ጠባቂ እዚህ ውስጥ ምን ጥልቅ አደረገው ይላል,,,,
ክቡር ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው እረዳ " ህዝቡ ስለአዋጁ ምንም ግንዛቤ የለውም እንጅ መስሪያ ቤታችን ያደረጃጀት ችግር የለበትም " ይላሉ,,,,(ማነው ግንዝባቤ መፍጠር ያለበት የሳቸው ቢሮ መስሎኝ ነበርኮ ) ኢቢሲን የወከሉ አንዲት ወይዘሮ ደግሞ ሳምፕል የተወሰዱ ተጠያቂወች ላይ "የሳንፕሉ መቶ ፐርሰንት" ተብሎ የተገለፀው ጉዳይ ትንሽ "ሮኬት ሳይንስ" ነገር ሁናባቸው ነው መሰል,,,, "ህዝቡ መቶ ፐርሰንት ስለአዋጁ እንዴት ሊያውቅ ይችላል ትንሽ አልተጋነነም ?" ይላሉ,,,, እዛጋ የሆነ ሰውየ በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ የሆነ ማዛጋት ያዛጋል,,,,,አንድ ተናጋሪ ግን አሳዘኑኝ "ለጋዜጠኛ መረጃ መስጠትን ምፅዋት እንደመስጠት የሚቆጥሩት ተቋማት አሉ "
ሌላኛው "እና እንደአሁኑ ወሳኝ ስብሰባ ላይ ሁነን መረጃ ስጡን ስትሉንስ ለመረጃ ብለን ስብሰባ ረግጠን ልንወጣ ነው? ,,,, ከበሮ በሰው እጅ ያምር አሉ ,,,, " ብለው ይተርታሉ,,,, ኢቢሲ መረጃውን ሙሉን ያድርሰን አያድርሰን ባናውቅም እኛም ተመልካቾች ከጥርጣሬ ጋር አናያለን,,, ፊት ወንበር ላይ ደግሞ ወ/ ሮ ሚሚ ስብሃቱ "የተመራጭ ተደማጩ " ዛሚ ሬዲዮ ባለቤት "ሚራክል " የሆነ ሽክታ ሽክ ብለው ቁጭ ብለዋል! ! ክብ ጠረጴዛ ላይ ይሄን ጉዳይ አቅርበው ሲያብጠለጥሉት ታየኝ! !
ወ/ ሮ ፎዚያ አዋጁ ውስጥ ሚራክል መኖሩንና በሌላው አለም ካሉ ተመሳሳይ አዋጆች የተሻለ መሆኑን በኩራት ይናገራሉ,,,(በአፍሪካ አንደኛ በአለም ሁለተኛ እንደማለት ነች: )
የሊቢያ አፈር ይቅለላቸውና ሙአመር ጋዳፊ ትዝ አሉኝ ,,,, አንድ ሰሞን ራሳቸው የፃፉትንና "አረንጓዴው መፅሃፍ" የሚባለውን ልክ እንደ ወ/ሮ ፎዚያ ለህዝብ እያሳዮ "አለምን መምራት የሚችል ተኣምራዊ መፅሃፍ " ብለወት ነበር,,, ያንን ፉከራ አፈር በላው!
አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ,,,,
ለምን ይሆን የራበው ሆዴ ! አለ ያ ቴዲ,,,, እሱ ልጅ ግን ውስጡ "ሚራክል" የሆነ ጥበብ ያለበት ልጀኮ ነው! !:)
ለማንኛውም,,,,, ማንኛውም ተቋም ባለስልጣንና የስራ ሃላፊ ለዜጎቹ መረጃ የመስጠት ግዴታ እንዳለበት አዋጁ ላይ መከተቡን ነግረውናል
ለምሳሌ "ክቡር አቶ እንቶኔ እንትን ሆቴል እና እንትን ህንፃ የእርሰዎ ነው ይባላል,,,, ከየት አመጡት ብሩን " ብሎ "በአክብሮት" መጠየቅ ይቻላል እንደማለት ነው,,,:) ታዲያ አዋጁ ጨምሮ እንደሚያትተው,,,, መልሱን በአቶ እንቶኔ ፈንታ ፌዴራል ፖሊስ የመመለስ ስልጣን የለውም:):):)
እስቲ " ሚራክል" የሆነ ጊዜ ይሁንላችሁ! !

Source: Alex Abreham

ሚስ አና ጎሜሽ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ፓርላማ አባላት መጋበዛቸውን አርጋገጡ

 አና ጎሜሽ Ana Gomes [አሶሽየትድ ፕረስ ፎቶ እአአ 2005/AP Photo]

አና ጎሜሽ Ana Gomes [አሶሽየትድ ፕረስ ፎቶ እአአ 2005/AP Photo]

“ድርቅና ረሃብ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ትናንት በአውሮፓ ፓርላማ የተካሄደው ውይይትና ክርክር በጣም ጥሩ እንደነበር የገለጹት የፓርላማው አባል ሚስ አና ጎሜሽ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም በስብሰባው ላይ የተገኙት በአውሮፓ ፓርላማ አባላት ተጋብዘው መኾኑንም አረጋግጠዋል፡፡
የአውሮፓ ሕብረት አባል እና በኢትዮጵያ በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ 97 የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢ ቡድንን የመሩት ሚስ አና ጎሜሽ “ድርቅና ረሃብ በኢትዮጵያ” (Famine and Drought in Ethiopia) በሚል አሁን በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ረሃብ በትናንትናው ዕለት በቤልጅየም ብራስልስ በአውሮፓ ፓርላማ ፊት የተካሄደው ውይይት እና ክርክር ጥሩ እንደነበር ገለጹ፡፡
እንደ ሚስ አና ጎሜሽ ገለጻ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በቤልጅየም ብራስልስ ተገኝተው በአውሮፓ ፓርላማ ትገኝተው ለአውሮፓ ኮሚሽን የውጭ ጉዳዮች አገልግሎት (European External Action Service /EEAS) ገለጻ እንዲያደርጉ እንደጋበዟቸውና በግብዣውም አማካኝነት ተገኝተው ሰፊ ገለጻ እንደሰጡ ተናግረዋል፡፡
ጽዮን ግርማ ሚስ አና ጎሜሽን አነጋግራ ያጠናከርችውን ዘገባ ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡
http://m.amharic.voanews.com/a/ana-gomes-responds-on-eu-invitation-of-berhanu-nega/3084918.html