Wednesday, December 4, 2013

“ኢሕአዳግ ሃገሪቱን ወዯ እርስ በርስ ጦርነት እንዲይከታት እሠጋሇሁ”

“ኢሕአዳግ ሃገሪቱን ወዯ እርስ በርስ ጦርነት እንዲይከታት እሠጋሇሁ”

ድ/ር ዲኛቸው አሰፋ

 ድ/ር ዲኛቸው አሰፋ በአዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍሌስፍና መምህር ናቸው፡፡ ሊሇፉት 30 ዓመታት በአሜሪካ ኖረዋሌ፡፡ የየትኛውም ፖሇቲካ ፓርቲ አባሌ ያሌሆኑትና ሆነውም የማያውቁት ድ/ር ዲኛቸው በሀገሪቱ ፖሇቲካዊ ጉዲዮች ሊይ ግን ምሁራዊ አስተያታቸውን በየጊዜው ይሰጣለ፡፡ ከድ/ር ዲኛቸው ጋር በወቅታዊ ጉዲዮች ዙሪያ የልሚ አዘጋጅ ቶማስ አያላው ያዯረገው ቆይታ ይህንን ይመስሊሌ፡- ልሚ፡- የሃገሪቱን ወቅታዊ ፖሇቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳት እየተመሇከቱት ነው? ድ/ር ዲኛቸው፡- በእኔ አመሇካከት አሁን ሀገሪቱ ያሇችበትን ሁኔታ ከኢህአዳግ አካሔዴ አንፃር ስናየው የስሌጣን ሽግግር ወቅት ነው፡፡ ጠ/ሚ መሇስ ዜናዊ ካረፉ በኋሊ ላሊ ጠቅሊይ ሚኒስትር ተሹሟሌ፡፡ ከጀርባ የኃይሌ ወይም የበሊይነት የማግኘት ትንቅንቅ እየተካሄዯ ሇመሆኑ አንዲንዴ ምሌክቶችም ይታያለ፡፡ ያሇፉትን አስር ዓመታት ፓርቲው ከሇመዯው የቡዴን (ኮላክቲቭ) አመራር ወጥቶ ጠ/ሚ መሇስ ዜናዊ ብቻቸውን በበሊይነት ስሊስተዲዯሩት ያንን ክፍተት መተካት በጣም አስቸጋሪ ስሇሆነ የበሊይነት ቦታውን ሇመውረስ ግብግብ እየተካሄዯ ነው፡፡ ኢሕአዳግ በጣም ምስጢራዊ ስሇሆነ በፊት ሇፊት ምን እንዯሚካሄዴ ማወቅ አይቻሌ ይሆናሌ፡፡ ምሌክቶች ግን አለ፡፡ የበሊይነት ሇማግኘት በፓርቲው አመራር መካከሌ ትንቅንቅ እየተካሄዯ ሇመሆኑ ምንም ጥርጥር የሇውም፡፡ ሆኖም ግን በርግጠኝነት ዘርዘር አዴርጎ ’እንዯዚህ እና እንዯዚያ’ ነው ብል በዴፍረት ሇመናገር በጣም አስቸጋሪ ይሆናሌ፡፡ ልሚ፡- መንግስት ከኃይማኖት ተቋማት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቷሌ፤ “አክራሪነት” የሚሇው ቃሌ ምክንያትና ተገቢነትን እንዳት ያዩታሌ? ድ/ር ዲኛቸው፡- በጣም አሳሳቢ፣ተገቢ ጥያቄ ነው፡፡ በቅርቡ የፌዳራሌ ጉዲዮች ሚኒስትር ድ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም በተከታታይ የፃፉትን አንዴ ፅሁፍ አንብቤያሇሁ፡፡ ፅንፈኝነትን የሚመሇከት ሦስት መሠረታዊ ችግር ያሇው ፅሁፍ ነው ያስነበቡን፡፡ በመጀመሪያ ዯረጃ፡- በኦርቶድክስ ኃይማኖት ሊይ ትሌቅ ጫናና የማይሆን ትችት አቅርበዋሌ፡፡ “ብዙ ሺህ ዓመት ቆየን ብሇው ይከራከራለ” የሚሌ ትችት አሊቸው፡፡ ኦርቶድክስ ተዋህድ ብዙ ሺህ ዓመት አሌቆየም እንዳ? ታሪኩ እንዯሚያመሇክተው ሮም ክርስትናን ሳትቀበሌ፣ ክርስትና የተቀበሇ ሕዝብ መሆኑን ነው፡፡ በዚህ ረዥም የፅናት የክርስትና ታሪክ አንዴ ሕዝብ ቢኮራ እንዳት እንዯ ትምክህት ይቆጠርበታሌ? ሁሇተኛ ሚኒስትሩ ወዯኋሊ ሔዯው ’የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሕድ ኃይማኖት የመንፈሣዊና፣ የአስተዲዯር ሌዕሌና የሇውም ነበር’ ብሇዋሌ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋህድን የቅርብ ታሪክን እንኳን በጥቂቱ ቢመሇከቱ፤ የዛሬ መቶ ዓመት በዘመናዊ ትምህርት ዙሪያ ሉቃውንቱ ነገስታቱን የሞገቱበትን፣ የፓትርያርክ መንበርን በተመሇከተ ቤተ ክርስቲያኗ ለዓሊዊነቷን ያስከበረች መሆኗን ይረደ ነበር፡፡ በተጨማሪም ድ/ር ሽፈራው አይወደት እንዯሁ እንጂ ፤ በቅርቡ በታተመ የብሊቴን መርስኤ ሏዘን ወሌዯ ቂርቆስ መፅሀፍ ሊይ ታሊቁ የ20ኛው ክፍሇ ዘመን ሉቅ አሇቃ ታዬ ከዚህ ዓሇም በሞት በተሇዩ ጊዜ ’አባቶቼ መቃብር አሳርፉኝ’ ብሇው ቢናዘዙም “ፕሮቴስታንት ሆነዋሌ” ተብል ስሇነበር (በንግሥተ-ነገሥታት ዘውዱቱ ዘመነ መንግሥት መሆኑ ነው) በጊዚው የነበሩ ካህናት “ኃይማኖቱን ስሇሇወጠ ሥሊሴ አይቀበርም” ብሇው ከሇከለ፡፡ እቴጌዋ “እባካችሁ” ብሇው ቢሇምኑ “በኃይማኖታችን ዯንብና ሥርዓት ውስጥ አይግቡብን” ብሇው ምሌጃቸውን ሳይቀበሎቸው ቀሩ፡፡ መቼም መንፈሣዊና አስተዲዯራዊ ሌዕሌና የላሇው ቤተክህነት ይህን ማዴረግ አይችሌም፡፡ ሦስተኛ በቅርቡ በተካሔዯው የሲኖድስ ጉባኤ ሊይ ከጳጳሳቱ አንደ እንዲለትና እኔም እንዯምጋራው አንዴ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ኦርቶድክስ ከሆነ ስሇ ኦርቶድክስ፣ ሙስሉም ከሆነ ስሇ ሙስሉም፣ ፕሮቴስታንት ከሆነ ስሇ ፕሮቴስታንት ይናገር እንጂ፤ ከቆምንበት ሃይማኖት እየተነሳን በማንከተሇውና በማናውቀው ሃይማኖት ሊይ ትችት ባንሰነዝር ጥሩ ይመስሇኛሌ፡፡ ሚኒስትሩ በተከታታይ ስሇ አክራሪነትና ፅንፈኝነት የፃፉትን ፅሁፎች አጠቃሇን ስንመሇከተው ሇወጉ ያህሌ የላልቹን ሃይማኖቶች ስም ዘረዘሩ እንጂ በአክራሪነት ተፈርጀው ዋናው ቀስት የተነጣጣረባቸው ግን እስሌምናውና የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋሀድ ሃይማኖት ሊይ መሆኑን እንገነዘባሇን፡፡ ኢህአዳግ የሃይማኖት ጉዲይ በትሌቅ ጥንቃቄ መያዝ ያሇበት ጉዲይ መሆኑን መገንዘብ ይኖርበታሌ፤ እዚህ ሊይ ሰር ዊንስተን ቸርችሌ በሁሇተኛው የዓሇም ጦርነት ወቅት ስሇ ጄኔራልቻቸው “war is too serious a subject to be left for the Generals” (“ጦርነት በትኩረት፣ በጥንቃቄ መያዝ ያሇበት ጉዲይ ስሇሆነ ጄኔራልች ብቻ የሚተው ጉዲይ አይዯሇም፡፡”) ብሇው ነበር፡፡ ከዚህ አባባሌ የምንማረው በአንዴ ሀገር ወሳኝ የሆኑ እንዯ ሃይማኖት ባለ ጥያቄዎች ዙሪያ ’ሙያቸው ነው’ ተብል ብቻ ጉዲዩን ሇካዴሬዎች መተዉ ስህተት ሊይ እንዯሚጥሌ ነው፡፡ በተጨማሪም የሃይማኖትን ጉዲይ በትሌቅ ሃሊፊነት መያዝ ብቻ ሳይሆን ከመንግስት ፖሇቲካዊ ጥቅም ጋር በማያያዝ ብቻ በሌዕሌናቸው ሊይ ተፅዕኖ መፍጠሩ ተገቢ አይዯሇም፡፡ በመሆኑም ኢህአዳግ ብዙ ጊዜ እንዯሚያዯርገው የራሱን ፖሇቲካዊ ጥቅም አስከብራሇሁ በሚሌ ፈሉጥ አገሪቱን ወዯ እርስ በርስ ግጭት እንዲይከታት እሰጋሇሁ፡፡
ልሚ፡- በኢህአዳግ ውስጥ የአመራር ችግሮች እየተስተዋለ ነው ብሇው ያስባለ? ድ/ር ዲኛቸው፡- አቶ ኃይሇማርያም ጠቅሊይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋሊ በአማካሪ ስም በአራትና በአምስት አንጋፋ ኢህአዳጏች መከበባቸው አንዴ ችግር አሇ ማሇት ነው፡፡ አንዴ የአገራችን ሽማግላ በአንዴ ወቅት ሲያጫውቱኝ “አንደ የሌጅ ኢያሱ ችግር የመካሪው መብዛት ነበር” ያለኝ ትዝ እያሇኝ በአቶ ኃይሇማርያም ዙሪያ የተሰሇፉትን የአማካሪዎች ቁጥር ሳይ የሌጅ ኢያሱ ሁኔታ ተመሳሳይ መሌክ ይዞ በዏይነ ሕሉናዬ ይመሊሇሳሌ፡፡ ላሊው የኢህአዳግ ችግር ሥርዓቱ የፈጠረውን የምዝበራና የሙስና ችግር መፍትሄ ሉያበጅሇት አሇመቻለ ነው፡፡ አሁን እንዯምናየው አንዴ የፖሇቲካ ሥርዓት ከሕግ በሊይ የሆኑ አይነኬዎችን ካወጣ ያ ሥርዓት አዯጋ ሊይ ነው ያሇው ማሇት ነው፡፡ የሙስናው ጉዲይ አሳሳቢ ዯረጃ ሊይ መዴረሱን አሌፎ አሌፎ በመገናኛ ብዙሃን መንግስት ራሱ እየነገረን ነው፡፡ በአቀራረብ ዯረጃ ስናየው ግን ሇጉዲዩ ተገቢ አትኩሮት ሳይሰጠው ሇይስሙሊ የተዘጋጀውን ቴአትር ያቀርቡሌናሌ፡፡ ሙስናን በሆነ ዘዳ ሇመከሊከሌ መሞከር ነው እንጂ ቴአትር ማዘጋጀት ተገቢ አይዯሇም፡፡ ልሚ፡- የአፍሪካ መሪዎች አይ.ሲ.ሲ ጫና ይፈጥርብናሌ ይሊለ፡፡ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሉቀመንበር ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ዯሳሇኝ ይህን ጉዲይ በሚመሇከት በተሇያዩ ስብሰባዎች ሊይ በአንክሮ ገሌፀዋሌ፡፡ ይህንን ነገር እንዳት ታዘቡት? ድ/ር ዲኛቸው፡- መቼም አንዲንዴ ጊዜ ሙለ እውነት፣ ሙለ ውሸት የሚባሌ ነገር የሇም፡፡ በተወሰነ ዯረጃ እነኚህ ሰዎች (ፈረንጆቹ) ትንሽ የራሣቸው ጫና የሚፈጥሩበት ነገር አሊቸው፡፡ ይሄ ማሇት ግን የሚመሰርቱት የክስ ሂዯት በሙለ ሀሰት ነው ማሇት አይዯሇም፡፡ የአፍሪካ መሪዎችን ስጋት በምናይበት ጊዜ የ17ኛው ክ/ዘመን ትሌቁ ፈሊስፋ ቶማስ ሆብስ “ሳይኮልጂካሌ ኢጎይዝም” በሚሇው ሃሌዮቱ ሊይ ሲያስረዲ ያሇው ትዝ ይሇኛሌ፡፡ “አንዱት የ14 ዓመት ሌጅ የጓዯኛዋ እናት ስትሞት ስቅስቅ ብሊ ሀዘንተኛዋን አቅፋ የምታሇቅሰው ከሌብ አዝና ሳይሆን የራሷ እናት ሞት በዓይነ ህሉናዋ እየታያት ነው፡፡” አሁን ከአይ ሲሲ ጋር አተካራ የገጠሙት የአፍሪካ መሪዎች በጥቁርነታችን አዴሌዎ ዯረሰ ብን ብቻ ብሇው ሳይሆን ነግ በኔ በሚሌ እሳቤ የራሳቸው ዕጣ ፈንታ እየታያቸው ነው፡፡ ልሚ፡- ተቃዋሚዎች በኢህአዳግ ጫና በዝቶብናሌ ይሊለ፡፡ ይህ ባሇፈው ከተዯረጉ ሰሌፎችና ከተፈጠረው ሁኔታ አንፃር የሚታወስ ነው፡፡ ያሇተቃዋሚ ሃገር መምራት የሚፈሌግ ስርዓት ምን ዓይነት ነው? ድ/ር ዲኛቸው፡- ጫና ማብዛት ብቻ ሣይሆን ኢህአዳግ ከጊዜ ወዯ ጊዜ ፀረ ዳሞክራሲ መሆኑን እያስመሰከረ ነው፡፡ ዴሮ ትንሽ የማስመሰሌ ሁኔታ ነበር፤ አሁን ግን ፈፅሞ የሇም፡፡ አሁን ’እኛ እየሰራን ነው፤ ዝም ብሊችሁ አዴንቁን፤ እነዚህ ተቃዋሚዎች መሰናክልች ናቸው’ ብሇው ያምናለ፡፡ ተቃዋሚ የሚባሌ ፈፅሞ መስማት አይፈሌጉም፡፡ ይሄ የፖሉሲ ሇውጥ አይመስሇኝም፡፡ እርግጠኝነት ጠፍቷቸዋሌ፡፡ ብዙ ቅሬታ አሇ፡፡ በዚህ ጊዜ አመጽ ሉያቀጣጥለብን የሚችለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው ብሇው ስሇሚያስቡ ትሌቅ የክትትሌ ጫና ያዯርሱባቸዋሌ፡፡ እንዯዴሮው ቢሆን ኖሮ በሌበ ሙለነት ሰሊማዊ ሰሌፍ ውጣ፣ ሂዴ ፃፍ ነበር የሚለት፡፡ አሁን ሊይ ግን የኃይሌ ሚዛናቸው ሊይ እርግጠኛ ባሇመሆናቸው ከበፊቱ በባሰ በእንጭጩ አሇች የሚሎት ዳሞክራሲ እንኳን እስትንፋሷን እያፈኗት ነው፡፡ በመሆኑም ተቃዋሚ ፓርቲውን በዯንብ አዴርገው እየተከታተለት ነው፡፡ ነገር የሚቀሰቅስባቸው ይመስሊቸዋሌ፡፡ የአረቡ ዓሇም አብዮት እንዯ ሌምዴ ይታወቃሌ፤ ይህንን ሳስብ እንዯ ፖሇቲካዊ የአመሇካከት ሇውጥ አይዯሇም የማየው፤ የፍርሃት ሁኔታ ነው የሚመስሇኝ፡፡ ልሚ፡- ምን ዓይነት መንግስታዊ ስጋቶች አለ? የኢህአዳግ ስጋትስ የትኛው ጋር ይመዯባሌ? ድ/ር ዲኛቸው፡- የታሰበው፣ የተነገረው ነገር አሌዯርስ ሲሌ ያሇመዯሰትና ያሇመርካት አሇ፡፡ የብክነትም ችግር አሇ፡ ፡ በአፄ ኃ/ሥሊሴ ጊዜ አንዴ ዯጃዝማች ስታይ ምን ዓይነት ሕይወት እና የሃብት መጠን እንዲሇው ትገምታሇህ፡፡ በዯርግም ጊዜ ሀብታሙን መገመት ትችሊሇህ፡፡ አሁን ግን በግሇሰቦች እጅ የሚታየው የሀብት መጠን ከእኛ የግምት አዴማስ ውጪ ነው እየሆነ ያሇው፡፡ እከላ 20 ሺህ፣ 30 ሺህ ብር ሰረቀ ዴሮ የሚያስዯነግጥ ዜና ነበር፡፡ አሁን እኮ በ30 ሚሉዮኖች ነው የሚወራው፡፡ በሂዯት ወዯ ቢሉዮን ነው የሚያመራው፡፡ እንዯውም ይሄ የሽግግር ክፍሇ ጊዜ ስሇሆነ አብሮ የሚመጣ ነገር ነው ይለሀሌ፡፡ አንዴ ስርዓት እንዯዚህ የሚያስብ ከሆነ ስርዓቱ ተበሊሽቷሌ ብዬ ነው የምገምተው፡፡ ልሚ፡- ኢህአዳግና ምሁራን ምን ዓይነት ግንኙነት አሊቸው? ሇምሁራን የተሰጠው ቦታ ምን ዓይነት ነው? ድ/ር ዲኛቸው፡- ጭምት ምሁራን አለ፤ “እኔ አሌናገርም፤ በዯርግም ጊዜ ብዙ አይቻሇሁ” የሚለ፡፡ ኢህአዳግን የሚያገሇግለ ምሁራን አለ፡፡ ሇነዚህ ቦታና ዴጏማ ይሰጣሌ፡፡ በጥቅማ ጥቅም ሇመያዝ ይሞክራለ፤ እንጂ የራሣቸው ኤክስፐርት፣ የራሣቸው ምሁራን ግን አሎቸው፡፡ ምሁራኑ ወዯዚህ ጎራ አሌቀሊቀሌ ሲለ የራሣቸውን ምሁራን ፈጠሩ፤ በየቦታው ያሇውን የጥናት ተቋማትን ዯረጃ አወረደት፡፡ ዴሮ አፄ ኃ/ስሊሴ ሉወርደ ሲለ (እኔ እንዯሰማሁት) “እንዳት ነው ፊውዲሉዝምን የምንመታት” አለና መከሩ አለ፡፡ በመጨረሻ ሹመቷን እናርክሰው ተባሇ፡፡ ወዯ ዘጠኝ ሺህ ዯረጃ አወጡ፡፡ ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች…፡፡ ኳስ ተጫዋቹ ’ፊታውራሪ’፣ ታክሲ ነጂው ’ቀኛዝማች’ እየተባሇ ስያሜ ሲሰጥ ይሄ ዯረጃ ቀዯም ሲሌ የነበራቸው በሙለ በጣም ተበሣጩ፡፡ እኔ አሁንም የምመሇከተው በትምህርት ዘርፍ ማስትሬት ዱግሪ አሇኝ የማይሌ ሰው አታገኝም፡፡ ቢኤማ መጫወቻ ሆኗሌ፡፡ ሌክ ያኔ የፊውዲለን ዘመን እንዯመቱት እነኚህ ዯግሞ ትምህርትን መቱት፡፡ ስሰማ ’የማንንም ገበሬ ሌጅ ማስተርስ አስይዘናሌ’ እየተባሇ ነው፡፡
ከአስራ አንዴ ሰው በሊይ ሁለንም እግር ኳስ ተጫዋች ማዴረግ አይቻሌም፡፡ ዱግሪውን ትርጉም አሌባ አዯረጉት፡፡ እኔ ድክትሬቴን ሰጥቼ ፊታውራሪነቴን መቀበሌ ነው የምፈሇገው፡፡ አያቴም ፊታውራሪ ነበሩ፡፡ ይህንን የተመኘሁት ግን ወዴጄ አይዯሇም፤ ከብስጭት ነው፡፡ እስቲ እግዚአብሔር ያሣይህ የተሌዕኮ ፒ.ኤች.ዱ (“PHD”) የሚባሌ ነገር አሇ? ማንም እንዯሚያውቀው ትምህርት ውይይት ይጠይቃሌ፡፡ ከአንተ ጋር ያዯረግኩትን ቃሇ መጠይቅ በስሌክ ብናዯርገው አያምርም፡፡ ፊት ሇፊት እየተነጋገርን ሲሆን ግን የተሇየ ይሆናሌ፡፡ ኢህአዳግ የትምህርት ጥራትን አውርዶሌ፡፡ ምሁሩን በማውረዴ፣ ማንም ሉያገኘው ይችሊሌ በሚያስብሌ መሌኩ 50 ሺህ ኤም.ኤ፣ አስር ሺህ ፒ.ኤች.ዱ አወጣሇሁ ይሊሌ፡፡ በሦስት ሴሚስተር ኤምኤ እየሰጠ ነው፡፡ በክረምት ሁሇት ሁሇት ወር ይማሩና፣ በስዴስተኛው ወር ማስተርስ ይሰጣቸዋሌ፡፡ ይህ በስዴስት ወሩ ተማሩና የትምህርት ጥራት መጣ ማሇት ይቻሊሌ፡፡ ልሚ፡- የሀገሪቱን ተቃዋሚ ፓርቲዎችስ እንዳት ይመሇከቷቸዋሌ? ድ/ር ዲኛቸው፡- በሃገሪቱ ያለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትሌቅ ችግር ውስጥ ነው ያለት፡፡ የኢህአዳግ ጫና ማዴረግ እንዯተጠበቀ ሆኖ ስሇራሣቸው ማሰብ አሇባቸው፡፡ ባሇ ራዕይ መሆን አሇባቸው፡፡ አርቀው ማሰብ፣ መስማማት፣ የግሌ ንትርካቸውን መተው፣ ጣት መቀሳሰር ማቆም አሇባቸው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሄንን እየጠየቃቸው ነው፡፡ ከመንግስት በኩሌ ያሇባቸው ችግር እንዯተጠበቀ ሆኖ ዋናው ግን የራሣቸውን ችግር መፍታት ነው፡፡ ሌጅ ሆኜ አንዴ የሰማሁት የእንግሉዝ ሃገር ተረት አሇ፡፡ “ጠሊት አሇን ብሇው የአንዴ መንዯር ሰዎች ጫካ ገቡ አለ፤ በኋሊ ሲፈሌጉ ሲፈሌጉ አንደ ወዯ ሰማይ ተኮሰ፤ ጏበዝ ጏበዝ ጠሊታችንን አገኘሁት አሇ፡፡ የታሇ የታሇ ሲለት፣ ጠሊታችንማ እኛ ራሣችን ነን፤ ላሊ ጠሊት የሇንም” አሊቸው፡፡ የተቃዋሚው ጠሊት ራሱ ተቃዋሚውም ጭምር ነው፡፡ ልሚ፡- ድክተር ካሇዎት ሰዓት አጣብበው ሇሰጡን ምሊሽ አመሰግናሇሁ፡፡ ድ/ር ዲኛቸው፡- አመሰግናሇሁ፡፡

Tuesday, December 3, 2013

በቃ ብለን በጋራ እንነሳ

በቃ ብለን በጋራ እንነሳ

(ብርቅአየሁ መቀጫ)
udj 4 19

አኛ ኢትዮጵያዉያን በዚህ ዘመን በተለያዩ ሀገራት በስደት ተበትነን ለዚህ ታላቅ {ብሄራዊ} ዉርደት ለመብቃት የቻልነዉ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለእኛ ለልጆችዋ የምታንስ ሆና ሳይሆን የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዕጦት የፈጠረዉ ችግር መሆኑን የምታዉቁት ይመስለኛል ።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ብዙ የሰዉ ጉልበት፣ የተለያየ የዐየር ፀባይ የአለዉ መልክዐ ምድር የሚገኝባት በመሆኗ በህዝብ የተመረጠ ዲሞክራሲየዊ መንግስት ተመስርቶ መልካም አስተዳደር ቢሰፍን በአጭር ጊዜ ዉሰጥ አለምን የሚያስደምም የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ እንኳን ለእራሷ ዜጎች ስራ መፍጠር ቀርቶ የሌላ ሀገር ዜጎችንም መርዳት የሚያስችል አቅም መገንባት እንደምትችል ኢትዮጵያን ተዘዋዉሮ ያያትና የሚያዉቃት ይመሰክራል።
ይሁን እንጂ ለእዚህ ባለመታደላችንና የህዝብ ፍቅርና የሀገር ክብር በዉስጣቸዉ ያልሰረፀ እና ህዝቡን በዘር በመከፋፈል ተግባር ላይ የተሰማራ ጎጠኛ ቡድን በስልጣን ላይ በመዉጣቱ እና ህዝቡም ከአንዱ ክልል ወደ ሌላዉ ክልል ተዘዋዉሮ መስራት ካለመቻሉም በላይ በሙስና የተጨማለቀ አስተዳደር የሰፈነበት በመሆኑ ሀገሪቱና ህዝቧ በልመና ከመታወቅ አልፎ በየአረብ አገሩ ለግረድናና ለአሽከርነት ሀገሩን እየጣለ ስደተኛ በመሆኑ ለእንደዚህ አይነቱ ሰብዐዊነት ለማይሰማቸዉ መጫወቻ ለመሆን በቃን።
ገዥዎቻችንም ይህ በሳዑዲ አራቢያ እየደረሰ ያለዉ የግፍ ግፍ እንኳን ብሄራዊ ዉርደት በመሆኑ እነሱም የእዚህ ሀገር እና ህዝብ መሪዎች ናቸዉ በመባል ስለሚታወቁ ሌላዉ ቢቀር የእነሱዉ መሰል ጓደኞቻቸዉ እንኳን እንደሚስቁባቸዉ እና እንደሚንቋቸዉ መገንዘብ አልቻሉም። በስራቸዉም የአሉት ደጋፊና ኣጋሮቻቸዉም በሚጣልላቸዉ ፍርፋሪ ተደልለዉ ሆዳቸዉን በመሙላት ብቻ አሜን በማለት በማገልገል ላይ ናቸዉ።
በተለይ የተማሩ ናቸዉ የሚባሉት የገዥዉ ሀይል ደጋፊዎች በሚጣልላቸዉ ፍርፋሪ ተደልለዉ በገሀድ የሚያዩትን እና የሚሰሙትን ዕዉነት በማካድ ነጩን ጥቁር ነዉ ድንጋዩን ዳቦ ነዉ ሲሉ ስሰማ ምንኛ አዕምሮዬ ይደማል።
በተቃዋሚዉ ጎራ ያለዉም ቢሆን በጥቃቅን ልዩነቶች ተወጥሮ ከመናቆር አልፎ የጋራ ሀይሉን በማቀናጀት ለሀገር ትረጉም የሚስጥ ስራ መስራት መጀመር አለመቻሉ ምንኛ እርግማን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም።
የተወሰኑትም ቢሆኑ ከጎሳ ፖለቲካ ተላቀዉ ከወንድሞቻቸዉ ጋር ህብረት ፈጥረዉ በጋራ በመታገል ዲሞክራሲያዊ መንግስት ቢመሰረት ሁላችንም ተጠቃሚ እንደምንሆን እና ከዚህ ስቃይ እንደምንገላገል መገንዘብ ባለመቻላቸዉ የወገኖቻቸዉንና የሀገራቸዉን መከራና ስቃይ እያራዘሙት መሆኑን አልተገነዘቡትም።
አሁን እንኳን በሳዑዲ አራቢያ እየተፈጸመ የአለዉ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ እስራት፣ ግርፋት፣ በእየቤቱ በግዞት አስቀምጦ የባለጌ ጎረምሶች መጫወቻ ማድረግ በአጠቃላይ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ይፈፀማል ተብሎ ሊገመት የማይችል ኢሰብአዊ ድርጊት በጎሳና በቋንቋ ተለይቶ አለመሆኑ ትምህረት ሊሆነን በተገባ ነበር።
http://www.youtube.com/watch?v=sVH70NJcKjk
ማሰቢያ አዕምሮ ያለዉ የሰዉ ልጅ ይህ ሰሞነኛዉ በሳዑዲ አረቢያ በንፁሀን ወገኖቻችን ላይ የደረሰዉን እና እየደረሰ ያለዉን መከራና ስቃይ የተመለከተ የሚበላዉ ምግብ እየጣፈጠዉ በጉሮሮዉ አልፎ እንዴት ሊስማማዉ ይችላል? የሚለብሰዉስ ልብስ ሳይኮሰኩሰዉ እንዴት ተስማምቶት ሊለብሰዉ ይችላል? እንዴትስ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለማለትና በሰዉ መሀል አንገታችንን ቀና አድረገን ለመራመድ እንቸላለን?
በመሆኑም በሀገራቸዉ ምድር ሰርተዉ ኑሮአቸዉን ለማሸነፍ ባለመቻላቸዉ በሰዉ ሀገር ተሰደዉ የእራሳቸዉን እና የቤተሰቦቻቸዉን ህይወት ለመለወጥና የተሻለ ኑሮ ለመኖር ተመኝተዉ በተሰደዱት እህትና
ወንድሞቻችን ላይ እየደረሰ የአለዉን የመከራ ዉርጅብኝ በመመልከት በአገር ዉስጥም በዉጪ አገርም የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን በሙሉ አሁን እንኳን ዉርደት በቃ! ግፍ በቃ! ሰቆቃ በቃ! ብለን በቁጭትና እና ምሬት በተሞላበት ሁኔታ የጀመርነዉ እንቅስቃሴ የአንድ ሳምንት ጫጫታ ብቻ ከመሆን አልፎ የዉሰጥ ችግራችንን በሰከነ ሁኔታ በመወያየት እና በመፍታት ለአፈራሾች እና ለጸጉር ሰንጣቂዎች ጆሮአችንን ሳንሰጥ ወጣቶችና ሴቶችን ወደፊት በማስቀደም በጋራ እጅ ለእጅ ተያይዘን በመታገል ከዚህ ብሄራዊ ዉርደት ለመዉጣት እንቅስቃሴ መጀመር ይኖርብናል።
በስልጣን ላይ የአለዉም ሀይል ቢሆን ስልጣን ዘለአለማዊ አለመሆኑን ተረድተዉ ወደ ህሊናቸዉ በመመለስ ለብሔራዊ ዕርቅ እጃቸዉን በመዘርጋት የትግሉን ጊዜ እንዲያሳጥሩትና ከታሪክ ተጠያቂነት ለመዳን የበኩላቸዉን ድርሻ ቢወጡ ጠቃ

Cholera Outbreak reported in Jigjiga's Jail Ogaden

Cholera Outbreak reported in Jigjiga's Jail Ogaden.

Reports reaching our service desk from the city of Jigjiga confirm the outbreak of cholera in the one of the city's prison called Jail Ogaden. The signs of cholera were evident in the prison for the past couple of days however locals, due to their limited health knowledge and lack of presence of medical personnel in the prison, thought the symptoms were not cholera.

It is reported that civilians numbering between fifty -five and sixty ave so far died due to the cholera outbreak. There are hundreds of civilians still down with early signs of cholera. So far there are no reports of aid either from the Ethiopian government or military stationed in and around the city.
There are rumors swirling in the city and the prison it’s self that the Ethiopian military and its associated Liyu Militia forced prisoners to drink contaminated Water.
It’s also reported that the Ethiopian Military and its local Administration in Jigjiga wants the cholera to affect as many people as possible hence the reason for a gag order on all city dwellers by the Ethiopian military barring the mention of the word cholera.
Our reporter who traveled to the area on foot indicated that the lack of clean drinking water and the availability of basic medical necessities such as glucose have exacerbated the situation. Our source indicated that many people who could have survived this cholera outbreak are dying because of the lack of clean fluids in the jail.

This is not the first time Cholera Outbreak took place in Jigjiga's Jail Ogaden, we reported similar story on April 3rd, 2010.

የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ

የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ

(ዳዊት ተሾመ)
Bridge



1. መግቢያ
ከደርግ የ17 አመታት የአገዛዝ ውደቀት በኋላ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች በስፋት ሲንጸባረቁ ከነበሩ ጥያቄዎች መካከል የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ ዋነኛው ነው:: በዚህ ወቅት ውስጥ ለብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ በፖለቲካ ኃይሎች የቀረቡት የመፍትሔ ሃሳቦች የተለያዩ ቢሆንም የመፍትሔ ሃሳቦቹ የሚመነጩት ግን በዋናነት ከሁለት ተገዳዳሪ አስተሳሰቦች ነው:: አንደኛው አስተሳሰብ የሚያጠነጥነው የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄው የሚካትተው ከኢትዮጵያ ዘመናዊ የሃገር ግንባታ ጋር ተያይዞ የተፈፀሙ ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነትንና በደሎችን እንዲሁም በያ ትውልድ ውስጥ የተፈፀሙ መጠፋፋትን አካቶ ሁሉን-አካታች መድረክ በማዘጋጀት ያለፈውን በደሎች ዕውቅና በመስጠት በፖለቲካ ሊህቃን መካከል መግባባትን ማስፈንን ነው:: ሁለተኛው አስተሳሰብ የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄን የሚመለከተው ኢትዮጵያን እንደ ሀገር በአዲስ መሰረት ላይ የመገንባት ሂደት አድርጎ ነው:: ይህም ማለት የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ የሚያቅፈው ሁሉንም አይነት ማለትም ብሔር፣ ሃይማኖት እንዲሁም መደብ ላይ መሰረት ያደረገ ኢ-ፍትሃዊነትና መገለልን ከኢትዮጵያ ዘመናዊ የሃገር ግንባታ (1855 እ.ኤ.አ) ጀምሮ የኢህአዴግን የአገዛዝም የሚያካትት ነው::
በሁለቱ አስተሳሰቦች መካከል ያለው ልዩነቶች የሚከተሉት ናቸው:: የመጀመሪያው አስተሳሰብ ብሔራዊ ዕርቅን እንደ ፖለቲካዊ መፍትሔ ሲያይ፤ ሁለተኛው አስተሳሰብ ብሄራዊ ዕርቅን እንደ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ጉዳዮችን የሚያካትት እንደ ሁሉን አቀፍ የመፍትሔ ሃሳብ ነው:: በተጨማሪም፣ ብሔራዊ ዕርቅን እንደ ፖለቲካ መፍትሔ የሚያራምዱት በአብዛኛው እራሳቸውን <<የአንድነት ኃይሎች>> ብለው የሰየሙት የፖለቲካ ኃይሎች ሲሆኑ፤ብሔራዊ ዕርቅን እንደ-ሁሉን አቀፍ የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያዩት በአብዛኛው ብሔር ላይ የተመሰረቱ ፖለቲካ የሚያራምዱ ኃይሎች ናቸው:: <በአንድት ኃይሎች> ውስጥም ቢሆን በሀገር ቤት የሚንቀሳቀሱት ኢህአዴግን እንደ አንድ የፖለቲካ ኃይል በብሔራዊ ዕርቅ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንደለበት ሲያመለክቱ(ዕርቅን ከፍትህ ሲያስቀድሙ)፤ከሀገር ውጭ የሚንቀሳቀሱት(ፍትህን ከዕርቅ የሚስቀድሙ ናቸው::) ግን ይህን አይደግፉም:: በብሔር ላይ የተመሰረቱትም ውስጥም ኢህአዴግ የብሔራዊ ዕርቅን አሁን ባለው “ህገ መንግስት” ላይ መግባባትን የመፍጥር ሂደት አድርጎ ሲመለክት (reconciliation as a means of defending the status quo)፣ በተቃዋሚነት ጎራ ውስጥ ያሉት ደግሞ የብሔራዊ ዕርቅ ሂደትን ባለፉት አገዛዞች (የኢህአዴግን ዘመንንም ይጨምራል) ለተፈጸመባቸው በደሎችና መገለሎች ዕውቅና የመስጠትንና ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፍትሃዊነትን (reconciliation as an instrument to create and maintain a system of balance of power) እንደሚያሰፍን ሂደት አድርገው ይገልጹታል::  በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ የሚያራምዱ ቢሆንም የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና አስፈላጊነቱ ላይ ተመሳሳይ ግንዛቤ የላቸውም:: ስለዚህም ሁሉም <የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ> ቢያራምዱም ቃሉ ያዘለው የተለያዩ ትርጓሜዎች ከመሆኑም በላይ የተግባር እንቅስቃሴዎች ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርጓል::
የዚህ ፁሁፍ አላማ ከላይ በተጠቀሱት የአስተሳሰብ ልዩነቶች ምክንያት የብሔራዊ እርቅ ከገባበት ቅርቃር (deadlock) ውስጥ የሚወጣበትንና በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲመሰረት ለምንፈልገው የዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እንደ አንድ ዋና ምሶሶ ጭምር የምንጠቀምበትን አግባብ ለመጠቆም ነው:: ስለዚህም፣ ይህ ጹሁፍ መጀመሪያ የብሔራዊ ዕርቅ ትርጓሜና አስፈላጊነት በአጭሩ ይዳስሳል፤ ቀጥሎም ለምን በኢትዮጵያ የብሔራዊ ዕርቅ አስፋላጊነት እንደሆነ ያመላክታል፣ በመቀጠል የብሔራዊ ዕርቅ ፈተናዎችና የመፍትሄ ሃሳቦችን ያስቀምጣል፤ በስተመጨረሻም የፁሁፉ ማጠቃለያ ሃሳብ ይቀርባል::
2.  ብሄራዊ ዕርቅ ትርጓሜና አስፈላጊነቱ
በአንድ መህበረሰብ ውስጥ ጉልበትን መሰረት ያደረጉ የቅራኔ አፈታት ሂደቶች ከሚያስከትሏቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውሶች በተጨማሪ ውድ የሆነውን የሰው ልጆች ህይወት መጥፋትን፣ በሰዎች ልቦናና ህሊና ውስጥ የበቀልና የጥላቻ ስሜትን ያስከትላሉ::  ብሔራዊ ዕርቅም በሰው ልጆች ልብና አእምሮ ውስጥ የሰረጹትን የበቀልና የጥላቻ ስሜት የሚሻርበትና በምትኩ በሰላምና ፍቅር ላይ የተመሰረቱ ማህበረሰባዊ ግንኙነቶች እንዲያብቡ መንገድ የሚከፍት ነው:: ምንም እንኳን የተለያዩ ምሁራኖች የተለያዩ ፍቺ ቢሰጡትም በአመዛኙ የሚስማሙበት ትርጓሜ- ብሔራዊ ዕርቅ ያለፈውን በደልና ጥላቻ እንዳይደገሙ የሚያረግና የሁሉም  የጋራ የሆነች አገርን የመገንባትና በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ መግባባት መፍጠር ማለት ነው [i]::
የጋራ ነገን የመፍጠር ሂደት የሚመሰረተው ደግም ያለፍን የቁርሾ ማህበረሰባዊ ግንኙነት በመሻርና አዲስ አስተሳሰብና የጋራ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ ማህብረሰባዊ ግንኙነት ሲተካ ነው:: ብሔራዊ ዕርቅ ሀገራዊ መግባባትን ከማስፍን፣ ያለፈን በጎ ያልሆነ ማህበረሰባዊ ክፍፍሎሽንና ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነትን ከማስወገድ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ እና ሁሉን የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ሀገራዊ አንድነትን ከመገንባት አንጻር ያለው ጠቃሚነት ጉልህ ነው [ii]::
ይኸም ማለት ብሔራዊ ዕርቅ የአጭር ጊዜ ፕሮጀክት ሳይሆን የራሱ የሆነ ሂደት ያለው ሆኖ ያለፉት በደሎችና ኢ-ፍትሃዊ የሆኑ ድርጊቶች ለመፈጸማቸው እውቅና መስጠትን (Acknowledgment)፣ የተፈጸሙትን በደሎች ያስከተሉት ውጤቶች ላይ፣ ተጎጂዎች የከፈሉት መስዋትነት እና እንድምታ ላይ ስምምነት መድረስን (Consensus building)፣ የተፈጸሙት በደሎች በድጋሚ እንዳይፈጸሙና የተገለሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ፍላጎትና ደህንነት የሚያረግገጥ ስርአት ለመፍጠር መዋቅራዊ ለውጦችን ማምጣትና የፖለቲካ ውህደትን ማሳለጥን  (Structural changes and institutionalization of the process of political integration)፣  ፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት በማምጣት የኢኮኖሚያዊ ውህደትን ማረጋገጥና (enhancing socio-economic development and economic integration) እንዲሁም በባለፉት ስርአቶች የተገለሉትን የማህበረሰብ ክፍሎች ይበለጥ ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻልን የሚጠይቅ ነው [iii]::
ስለዚህም፣ የብሔራዊ ዕርቅ ስኬታማነትም ሆነ ዘላቂነት የሚወሰነው ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች መሟላት አለሟሟላት ላይ ነው:: በመሆኑም ብሔራዊ ዕርቅ በራሱ እንደ ውጤት የሚታይ ነው:: ብሔራዊ ዕርቅን ከዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ጋር አያይዘን ካየነው፤ ብሔራዊ ዕርቅ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እንደ ግብአትም የሚታይ ነው [iv]:: በአንባገነናዊ ስርአቶች ውስጥ ስርአቶቹ ከሚፈቅዷቸው ውጭ ያሉ ተጻራሪ ፍላጎቶችና ጥቅሞችን ለማዳፈን ጉልበትን መሰረት ያደረገ አካሄድ ይከተላሉ:: ዴሞክራሲያዊ ስርአቶች ከአምባገነን ስርአቶች የሚለዩበት ዋናው ቁም ነገር ተጻራሪ ፍላጎቶችንና ጥቅሞችን ከጉልበት ነጻ በመሆነ መንገድ የማመቻመች (compromise) እና ተቋማዊ ገጽታ በማላበስ (institutionalization of conflicts) ስርአት አልበኝነትና ግጭቶች እንዳይፈጠሩ መድረግ መቻላቸው ነው:: ይኸም ማለት አንባገነናዊ አገዛዞች ልዩነቶችን የሚያስተናግዱበት መንገድ አንዱን ወገን ተጠቃሚ አንዱን ደግሞ አግላይ ያደረገ ሰለሚሆን በማህበረሰቡ ውስጥ የአሸናፊና የተሸናፊን ስነ-ልቦና የሚፈጥር ነው:: አሸናፊው ቡድን አሸናፊ ሆኖ የሚቆየው የራሱን አቅም በቀጣይነት በመገንባትና ተሸናፊውን ይበልጥ አቅመ-ቢስ ለማድረግ በሚደረገው ትግል ውጤታማነት ልክ ነው:: ተሸናፊው ቡድንም ተሸናፊ ሆኖ የሚቆየው የራሱን አቅም በመገንባትና የአሸናፊውን አቅም በማዳከም ተገዳዳሪ ኃይል እስኪሆን ድረስ ነው:: በመሆኑም በአምባገነን ስርአቶች ውስጥ የሚፈጠሩት የማህበረሰባዊ ግንኙነቶች ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ምቹ ያልሆኑ ናቸው::
በዴሞክራሲያዊ ስርአቶች ውስጥ ግን ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ያሏቸውን ፍላጎቶችና ጥያቄዎቻቸውን የሚዳኙባቸውን ህጎችና አግባቦች በስምምነት(ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ወይም አብዛኛው ክፍሎች) የሚያጸድቋቸው በመሆኑ ለነዚህ ህጎችና አግባቦች እንዲሁም እነዚህን ህጎችና አግባቦች ተፈጻሚ ለሚያደርጉ ተቋሞች ስር ለመዳኘት የውዴታ ግዴታ የሚገቡበት ነው[v]:: ብሔራቂ ዕርቅም ባለፉት የአንባገነናዊ የአገዛዝ ስርአቶች የተፈጠሩ ኢ-ፍትሃዊ ድርቶችና በደሎች ያስከተሉትን በጎ ያልሆነ ማህበረሰባዊ ክፍፍሎሽ እና አንዱን የማህበረሰብ ክፍል ጠቃሚ ሌላውን ጎጂ  (win-lose) ያደረገውን የፖለቲካ ባህል በመሻር ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች አሸናፊና ተጠቃሚ የሚያደርግ  (win-win) ፖለቲካዊ ባህል ለመገንባት አስተጽኦው ከፍተኛ ነው:: ስለዚህም፣ ብሔራዊ ዕርቅ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ሂደት መሳካት ከሚጫወተው ሚና አንጻር እንደ አንድ ወሰኝ ምሶሶ የሚታይ ነው::
3. በኢትዮጵያ የብሔራዊ  ዕርቅ  አስፈላጊነት
በኢትዮጵያ ውስጥ ብሔራዊ ዕርቅ የሚስፈልግበት ምክንያቶችን በ ሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል:: እነርሱም:-
ሀ) በኢትዮጵያ የሀገር ምሰረታ ሂደት ውስጥ የተፈጠሩ የተዛቡ ግንኙነቶችን ለማረም
የኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ሌሎች ሀገሮች ታሪክ ለታሪክ ምሁራንና ተመራማሪዎች የተተወ ሳይሆን የፖለቲካ አቋሞች የሚያዝበት ጉዳይ ነው:: ከአጼ ቴዎድሮስ የዘመናዊ መንግስት ምስረታ እንቅስቃሴ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የተነሱ የፖለቲካ ልዩነቶችና የፍላጎቶች ግጭቶች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ሊፈቱ የተሞከሩት ጉልበትን መሰረት ባደረገ የአፈታት ዘዴ ነው:: በዚህም የተነሳ ችግሮች እየተንከባለሉ ሳይፈቱ በመቅረታቸው ውስብስብና በጣም ስር እንዲሰዱ ሆነዋል:: በሌላ በኩል ደግሞ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ሀገር ምስረታ ሂደት ፖለቲካዊው እንድምታው ያልተማከለና በጣም ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት መመስረት ሲሆን፣ ኢኮኖሚያዊው እንድምታው ደግሞ በጦር አሸናፊ ሆነው የማዕከላዊ መንግስት ምስረታን ሂደት የተቆጣጠሩትን ኃይሎች የኢኮኖሚ ጥቅሞችን የማስከበር ሂደት ነበር [vi]:: ይህ የሀገር ምስረታ ሂደት በመሰረቱ ሁለት አይነት ልሂቃንን ፈጥሯል:: አንደኛው የልሂቃን ክፍል እራሱን እንደ <ሀገር አቅኚ> እና <የዘመናዊ ስልጣኔ ምንጭ> ሲቆጥር ሁለተኛው የልሂቃን ክፍል ደግሞ እራሱን <ኢኮኖሚያዊ መሰረቱን> እንደተነጠቀና እና ከፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ስልጣን እንደተገፋ የሚቆጥሩ ናቸው::  ስለዚህም፣ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሀገር አመሰራረት ሂደት ላይ ተቀራራቢ የሆነ አረዳድ በተለያዩ ልሂቃን ውስጥ የለም:: እነዚህ ልሂቃኖች የሚያራምዱት ፖለቲካና በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲገነባ የሚፈልጉት ዴሞክራሲያዊ  ስርአት መነሻ ምንጩ ባላቸው የዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ አረዳድ ነው::
ይህ የልሂቃኖቻችን የዴሞክራሲ አረዳድ በመሰረቱ ለዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸው አረዳድ ነጸብራቅ ነው:: የዘመናዊት ኢትዮጵያ የሀገር ምስረታ ሂደት በጦርነትና በማስገበር የታጀበ ነው:: ምንም እንኳን በኢትዮጵያም እንደሆነው ሁሉ በተወሰነ መልኩ ሁሉም ሀገሮች ሲመሰረቱ ጉልበትን መሰረት ያደረገ አካሄድ ቢጠቀሙም፤ የኢትዮጵያ የሀገር ምስረታ ፕሮጀክት ሲያልቅ የተተከለው የአገዛዝ ስርአት ግን ሄዶ ሄዶ ፍጹም ግለሰባዊ አገዛዝንና ሁሉን አካታች ያልሆነ ማህበረሰዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ስርአቶችን ወልዷል:: ስለዚህም የሀገር ምስረታ ሂደት በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ብሄረሰቦች (ethnic groups) መካከል የተዛባ ግንኙነትን ሲፈጥር በተለያዩ ልሂቃን መሀካል ደግሞ ቁርሾ ላይ ባስ ሲልም ጥላቻ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንዲኖር አስችሏል:: ይህ <እኛ-እነርሱ> አስተሳሰብ ዛሬም ቢሆን በፖለቲካ ልሂቃኖቻችን ውስጥ በስፋት የሚታይ ነው:: ስለዚህም ይህንን ጥላቻ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት በብሔራዊ ዕርቅ ሂደት አድሶ የጋራ የሆነች አገርን ለመገንባት በሚደረገው ሂደት ውስጥ ሁሉም የማህበረሰቦች ክፍሎች አተዋጽኦ እስካላደረጉ ድረስ የተሻለ ብሩህ ቀንና ዴሞክራሲያዊት የሆነች ኢትዮጵያ ሊፈጠሩ አይችሉም:: ለዚህም አላማ ሲባል ብሔራዊ ዕርቅ በጣም አስፈላጊ ነው::
የአገራችን ፖለቲካዊ ባህል ጉልበት ላይ የተመሰረተ ነው:: አጼ ቴዎድሮስ የነጉሰ ነገስትነት ዙፋን ላይ የተቀመጡት በጠበንጃ ኃይል ሁሉንም ተገዳዳሪዎቻቸውን በማንበርከክ ነው:: አጼ ዮሃንስ፣ አጼ ሚኒሊክ፣ አጼ ኃይለ ስላሴ የንጉሰ-ነገስትነት ዙፋኑን የተቆጣጠሩት ከተገዳዳሪዎቻቸው በወታደራዊ ኃይል በተነጻጻሪነት በልጠው ስለተገኙ ነው:: ፕሬዘዳንት መንግስቱ  ሆነ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ የፖለቲካ ስልጣኑን ቆንጮ ቦታ የተቆጣጠሩት በጠበንጃ ኃይል ታግዘው ነው:: ይህ ጉልበትን መሰረት ያደረገ የስልጣን ዝውውር በመሰረቱ በጊዜ ሂደት የሚፈጥረው የፖለቲካ ባህል ሁሉን አካታች የሆነ የአስተዳደር ስርአት ለመዘርጋት አመቺ የሆነ ስነ-ልቦናን አይደለም:: የኛ የፖለቲካ ባህል የጠበንጃ የፖለቲካ ባህል ነው:: ለዚህም ነው ትናንሽ ልዮነቶቻችን ሳይቀር አጉልተን በማውጣት ሊያስተባብሩን የሚችሉትን አያሌ ነገሮች ወደ ጎን በመግፋት ለእርስ-በእርስ መጠላለፍ ቅርብ የሆነው:: ይህ አካሔድ የሚፈጥረው ነገር ቢሆር ሁሉም የየራሱን ትናንሽ ገነት የማደራጀት አካሄድን እንጂ በትልቁ ሊያስተሳስረን የሚችልን አካሄድ አይደለም:: በተወሰነ መልኩም ቢሆን ከ 73 በላይ በሀገር ቤት የተመዘገቡ ትናንሽ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው የሚያመላክተው ቁም ነገር ይሄንኑ እውነታ ነው:: ይህ ትናንሽ ገነቶችን የመፍጠር ሂደት የሀገራችንን የፖለቲካ ዕድገት ወደ ፊት አንድ እርምጃ ከማራመድ አንጻር ምን አስተዋጽኦ አደረገልን? ይህንን በጉልበት ላይ እና የራስን ፍላጎት ብቻ በማየት የሌሎቹን የፖለቲካ ኃይሎች ህልውናን የመካድ ባህልን ለማስወገድና በመተባበርና በተወሰነ መልኩም ቢሆን በመተማመን ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ባህል ከመፍጠር አንጻር ብሔራዊ ዕርቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው::
ለ) በሀይማኖቶች መካከል የተዛባ ግንኙነቶችን ለማስተካከል
የዘመናዊት ኢትዮጵያ ምሰረታ የተመራው <አንድ ሀገር፣ አንድ ኃይማኖት> በሚለው መርህ ነው:: ምንም እንኳን ኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖትን ከተቀበሉት ሀገሮች ቀደምት ብትሆንም፣ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የነበራቸው ሚና በጣም ዝቅተኛ ነበር:: ይህ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሚናን እንዲቀጭጭ ያደረገው ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ መንግስታዊ ሃይማኖት መኖሩና በዚህም ምክንያት ሙስሊሞች በፖለቲካው መስክ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እንዲቆጠሩ ስለሆኑ ነው:: የአጼ ኃይለ ስላሴ የአገዛዝ ዘመን ማክተም ሁለት አበይት ክስተቶችን አስከትሏል:: አንደኛው መንግስታዊ ሃይማኖት በኢትዮጵያ ማክተሙ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የእስልምናን ሃይማኖታዊ በዓላት ብሔራዊ በዓላት በማድረግ በሀገረ-አቀፍ ደረጃ መከበር መጀመሩ ነው:: ሆኖም ግን በደርግ-ዘመነ መንግስትም ሆነ በኢህአዴግ አገዛዝ ሙስሊም ኢትዮጵያውን ከሁለተኛ የዜግነት ደረጃ ወደ እኩል የዜግነት ደረጃ የማምጣቱ ሂደት ግን እምብዛም ግቡን አልመታም[vii]::
ይልቁንም ኢትዮጵያ ከምትገኝበት ጂኦ-ፖለቲካዊ ሁኔታ፣ ከኢህአዴግ መንግስት መሰረታዊ ባህሪና ኢትዮጵያ ተሳታፊ ከሆነችበት አሜሪካ መራሹ አለም አቀፍ የጸረ-ሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ የመግባትና ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችን የመቆጣጠር ሂደት በተወሰነ መልኩ በሀገሪቱ ውስጥ አክራሪነት እንዲስፋፋ አድርጓል:: እዛም እዚ በተወሰኑ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና በክርስቲያን በተለይ ደግሞ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች የሚያመላክቱት ነገር በሃይማኖት ላይ የተመሰረተ ግጭቶች እየተስፋፉ መሆናቸውን ነው:: እነዚህ እየተስፋፉ ያሉ ግጭቶች <<በመቻቻል>> ላይ የተመሰረተ የሃይማኖታዊ ግንኙነቶች እሴቶች እየተሸረሸሩ ስለመሄዳቸው የሚጠቁሙ ናቸው [viii]::
በሌላም በኩል ደግሞ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ የሆነና የሁሉን የማህበረሰብ ክፍሎች ፍላጎቶች ያማከለ አገዛዝ የለም ካልን፣ የሙስሊሞችን እንደ አንድ ማህበረሰብ ክፍል ሃይማኖታዊ ነጻነትን የሚያከብርም ሆነ ማህበረሰባዊ ፍላጎቶችንና ጥያዌዎች የሚመለስ የአገዛዝ ስርአት የለም ማለት ነው:: ይህም ማለት በህዘበ-ክርስቲያኑና በህዘበ-ሙስሊሙ መሀከል ያለው <<በመቻቻል>> ላይ የተመሰረተ ግንኙነት የአገዛዝ ስርአቱን በሚያራምዱት ጥቂት ልሂቃን ምክንያት ሊበረዝ የሚችልበት አጋጣሚ ከፍተኛ ይሆናል:: ምክንያቱም፣ በቀላሉ የእስልምና አክራሪነትን የሚያራምዱ ኃይሎች የሀገሪቱን ስልጣን በተቆጣጠሩትና በህዝቡ መካከል ያሉ ግንኙነቶች (state-society relationships) የአገዛዝ ልሂቃኑን ማህበረሰባዊ መደብ በመውሰድ እንደ ሃይማኖት ላይ የተመሰረተ የጨቋኝ-ተጨቋኝ ግንኙነቶች ሊተረጉማቸው ይችላሉ:: የጽንፈኝነት ማህበረሰባዊ መሰረቱን የሚሰጡት ጭቆና፣ አግላይ ስርአትና ድህነት መኖራቸው ነው:: ስለዚህም፣ በታሪካዊ አጋጣሚም ሆነ በፖለቲካዊ ምክንያት የተፈጠሩ በሀገሪቱ ለረጅም ዘመን ዘልቆ የቆየውን “በመቻቻል” ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለማስቀጠልና ተቋማዊ ገጽታ ሰጥቶ ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ብሔራዊ ዕርቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው::
ሐ) በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ያላቸውን የፖለቲካ ኃይሎች ለማስታረቅ
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህል ጠበንጃ ላይ የተመሰረተ ፓለቲካ ባህል ነው ካልን፣ ይህ ባህል የሚወልዳቸው በጥላቻና እርስ በእርስ ህልውናን በመካካድ ላይ የተመሰረተ ግንኙነቶች መኖራቸው የማይቀር ሃቅ ነው:: እነዚህ ግንኙነቶች አንድም በተለያዩ ልሂቃኖች ውስጥ የተዛባ ግንኙነቶች እንዲስፋፉ ሲያረጉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የፖለቲካ ልሂቃኖቻችን የጋራ ጥቅምን የሚያስከብርንና በመተባበር ላይ የተመሰረተ ህብረትን መመስረት እንዳይችሉ አርጓቸዋል:: ለዚህም ትልቁ ምሳሌ፣ በአንድ በኩል በኢትዮጵያ የመጀመሪዎቹ ፖለቲካ ፓርቲዎች (ኢህአፓ እና መኢሶን) መሀከል ከነበረው  እርስ በእርስ የመጠፋፋት ፖለቲካ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ልዩነቶችን ሰላማዊ መንገድ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ በመሆን በመነጋገር የፈቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሉንም:: ጨካ የነበሩት ልዩነታቸውን የፈቱት በተለመደው በጠበንጃ ነው፤ ከተማ ውስጥ ያሉትም ቢሆን ስም በመጠፋፋት፣ እርስ በእርስ እቅውና በመነሳሳትና አልፎ አልፎም በመደባደብ ነው የፈቱት አሊያም ደግሞ ለመፍታት እየሞከሩ ያሉት::
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የተሞከሩት ጥምረቶች፣ መድረኮች፣ ቅንጅቶች እና በአጠቃላይ ስብስቦች ውጤታማ ያልሆኑበት የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም፤ በዋናነት ግን እነዚህ ስብስቦች የተመሰረቱበት ችግሮች መሰረታዊ ስህተት ስላለበት ነው:: ስብስቦቹ የተቋቋሙበት መሪ መርህ <<ፖለቲካ ፓርቲዎች ለየብቻ ገዢውን ፓርቲ መቋቋምና መገዳደር (<አንድ-ለአንድ>) አንችልም፣ ተሰባስበን (<አንድ-ለብዙ>) ገዢውን ፓርቲ ከስልጣን እናውረደው>> የሚል ነው:: ይህ መርህ በመሰረቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያሏቸውን ልዩነቶች በማጥበብ የተሻለ ብሩህ ቀን ለመፍጠር የሚያደርጉት አካል ሳይሆን (ስብስቦቹ ያወጧቸውን መለስተኛ-ማኒፌስቶዎችና የየፓርቲዎቹን የፖለቲካ ፕሮግራም በመሰረታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች ላይ ያላቸው መልሶች ምን ያህል እንደሚራራቅ ልብ ይሏል)፣ <ትልቁ ጠላት> የሚሉትን ገዢውን ፓርቲ በጋራ ከስልጣን በማውረድ ከዛ በኋላ ደግሞ እርስ በእርስ በመጠላለፍ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት የሚቆምሩት ፖለቲካዊ አካሄድ ነው:: በዚህ ሂደት ውስጥ የተፈጠሩ ስብስቦች ሲፈርሱ የፈጠሩት ትልቁ ፖለቲካዊ ጠባሳ በፖለቲካ ኃይሎች መካከል የጥላቻና እርስ በእርስ የመጠራጠር ባህል ይበልጥ ስር እንዲሰድ ማድረጋቸው ነው::
ስለዚህም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም አካታች የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለመፍጠር እና ፍትሃዊ-ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማስፈን የተሻለ ነገን ለመፍጠር፣ የግዴታ ከአገዛዝ ለውጥ (Regime change) በላይ የሆነ ማህበረሰባዊ ለውጥ ማምጣት ይጠበቅብናል:: በማህበረሰባችን ውስጥ የተፈጸሙ ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነቶችንና በደሎችን እንዳይደገሙ ለማድረግ፣ በሃይማኖቶች መካከል እየተስፋፋ የመጣው ያለመቻቻል ባህልና ለመቀነስ እና በፖለቲካ ልሂቃኖቻችን መካከል ጠልፎ የመጣል የግለኝነት ፖለቲካን ለማስወገድ ብሔራዊ ዕርቅን እንደትልቅ የመፍትሄ ቁልፍ መውሰድ ይገባናል::  ብሔራዊ ዕርቅን በፖለቲካ ሊህቃኖች መካከል ያሉትን ቁርሾዎች ብቻ ለመሻር ሳይሆን ማህበረሰባዊ ለውጥን ለማምጣት ጭምር መጠቀም አማራጭ የሌለው አካሄድ ነው:: ሆኖም ግን፣ ብሔራዊ ዕርቅን ለማስፈን የተጋረጡ ብዙ ፈተናዎች በአገራቸን ውስጥ አሉ:: እነዚህ ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? የመፍትሄ አቅጣጫዎቹስ?smne banner
4. የብሔራዊ ዕርቅ ፈተናዎችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች
በኢትዮጵያ የብሔራዊ ዕርቅ ፈተናዎች የሚመነጩት ስለ ብሔራዊ ዕርቅ ባለን ግንዛቤና እኛ ከለንበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ለመቃኘት በምናደረገው ጥረት ውስጥ ነው:: በኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ብሔራዊ ዕርቅ ሲነሳ እንድ ዋነኛ መነጻጸሪያ ሁኖ የሚቀርበው በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተካሄደውን ብሔራዊ ዕርቅን ነው:: በአብዛኛው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች የሚታሰበው የደቡብ አፍሪካ ዕርቅ ምንም እንከን እንደሌለውና በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታም አንጻር ሊደገም እንደሚችል ነው:: ነገር ግን፣ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ዕርቅ ሂደት የራሱ የሆኑ ጉድለቶች ያሉበት ከመሆኑም በላይ ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ አንጻርም ብዙ ልዩነቶች አሉት:: ስለዚህም፣ በኢትዮጵያ የሚያስፈልገው ብሔራዊ ዕርቅ ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ የሚመጥን መሆን አለበት:: ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ የብሔራዊ ዕርቅ ፈተናዎችንና የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንደሚከተለው ቀርቧል::
ሀ) እውቅና ስለመስጠትና የብሔራዊ ዕርቁ አካሄድ ላይ ያሉ ፈተናዎችና የመፍትሄ ሃሳቦች
ላለፉት ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነቶችና በደሎች እውቅና መስጠት ላይ የሚታዩት ችግሮች ሁለት አይነት ናቸው:: አንደኛው ችግር ያለፉትን በደሎች እውቅና መስጠት በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ መሆኑ ነው:: ይኸ ማለት ላለፉት በደሎች እውቅና መስጠት ማለት በደሎችን የፈጸሙ ኃይሎች  ለፈጸሙት በደሎች ተጠያቂነት ስለሚያመጠና በደሉን ፈጽመዋል የሚባሉት ደግም እንደ <ሀገር-መስራች፣ ስልጣኔ አስተዋዋቂና ሰላምና ብልጽግና አምጪ> በሚል በተለምዷዊው የኢትዮጵያ ታሪክ (meanistream Ethiopian history) ተክለ-ሰውነታቸው ስለተሳለ ነው:: ሁለተኛው ችግር ያለፉት በደሎች ዕውቅና ቢሰጥ ቀጥሎ ሊመጣ የሚችለው ነገር ላይ ብዥታ መኖሩ ነው:: ይህም ማለት ዕውቅና ቢሰጥ ተበድለናል የሚሉ የፖለቲካ ኃይሎች ለራሳቸው ፖለቲካዊ ጥቅም ሊያውሉት ይችላሉ የሚል ፍራቻ መኖሩ ነው:: እነዚህ ዕውቅና በመስጠት ላይ ያሉ ተግዳሮቶች በምንም መልኩ በደሎችን በመካድ ሊፈቱ አይችሉም:: እንደ አቅጣጫ መወሰድ ያለበት አካሄድ ያለፉትን በደሎች አለመካድና በድጋሚ እንዳይፈጸሙ ማድረግን ነው::
በሌላ በኩል ደግሞ፣ በደሎቹ የተፈጸሙበት ወቅት ያለውን የአስተሳሰብ ደረጃና የአገዛዛ ባህሪ ከጭፍን ስሜታዊነት ውጭ መመልከት ተገቢ ነው:: ታሪክ ለፖለቲካዊ ግብ መምቻ ብቻ ከመጠቀም ወጥተን ታሪክን ለታሪክ ተመራማሪዎች መተውን መልመድ መቻል አለብን:: በሀገራችን ሊኖረን የሚገባው ፖለቲካ ትላንትን መሰረት ያደረገ ሳይሆን በነገው ብሩህ ቀንና አብሮነታችን ላይ የተመሰረተ መሆን ይገባዋል:: ይህ ማለት፣ ሙሉ ለሙሉ ታሪክን ከፖለቲካ መነጥል ይቻላል ማለት አይደለም:: ይልቁኑም ፖለቲካችን በባለፈው ታሪካችንና በነገው አብሮነታችን እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነታችን ላይ ያለውን ሚዛን ማስተካከል ቁልፍ መሳሪያ መሆን ይገባዋል::
በአገራችን የነበሩ አገዛዞች ምንም እንኳን ማህበረሰባዊ መሰረታቸውን በስነ-ልቦና ደረጃ ተጠቃሚ ያደረጉ ቢመስልም፣ በሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ህዝቦች በባለፉት አገዛዞች ተበዳዮች ናቸው፤ የበደላቸው መጠንና የበደላቸው አይነት ምንም እንኳን ቢለያዩም:: ያለፉት አገዛዞችም ሆነ አሁን በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ የጠቀሙት ጥቂት ከስርአቱ ጋር ቅርበት ያላቸው ልሂቃንን እንጂ በአጠቃላይ ልሂቃኑ የወጡበትን ወይም እንወክለዋለን የሚሉትን ማህበረሰብ አይደለም:: ስዚህም፣ ያለፉትን በደሎች ዕውቅና መስጠት ማለት ይህ ህዝብ በዚህ ህዝብ ተበድሏል፤ እከሌ የሚባል ህዝብ በዳይ እከሌ የሚባል ህዝብ ተጎጂ በሚል መንፈስ መሆን የለበትም:: ሁሉም ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነቶችም ሆነ በደሎች መታየት ያለባቸው በደሎቹን የፈጸሙት አገዛዞች ከተመሰረቱበት ፓለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረቶች የመነጩ መሆናቸውን ነው::
ይህ አካሄድ አንድ በኩል በህዝቦች መካከል ሊፈጠር የሚችለውን በቂም በቀል የታጀለ ማህበረሰባዊ ግንኙነት መሰረት እንዳይዝ ሲያረግ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከባለፈው ታሪካችን ተምረን የተሻለ ነገን ለመፍጠር ለምናደርገው ሂደት ማህበረሰባዊ መነቃቃትን ይፈጥርልናል:: ስለዚህም፣ በዚህ አካሄድ ላለፉት በደሎች ዕውቅና በመስጠት ሊከሰት የሚችለው የፖለቲካ ኃይሎች ያለፉትን በደሎች ፖለቲካዊ ትርጉም በመስጠት ለፖለቲካ ጥቅም የሚያውሉበትን እድል ማጥበብ ይቻላል::  በመሆኑም፣ የብሄራዊ እርቅ ጉዳይ መታየት ያለበት የባለፈውን ጠበሳ በመነካከት ቅራኔን በማባባስ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማስገኘት ሳይሆን ከባለፈው ታሪክ በመማርና ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነትን በማረም የተሻለ ነገንና ብሩህ-ተስፋን ከመፍጠር አንጻር  መሆን ይገባዋል::
ለ) የተፈጸሙትን በደሎች ያስከተሉት ውጤቶች ላይ፣ ተጎጂዎች የከፈሉት መስዋትነት እና እንድምታ ላይስምምነት መድረስን (Consensus building) በተመለከተ ያሉ ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች
በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር <ብሔራዊ ዕርቅ የሚያስፈልገው ለየትኛው ታሪካዊ በደል ነው> የሚለው ጥያቄ በተፈጸሙ በደሎች ላይ ስምምነት ለመድረስ ወሳኝ ጥያቄ ነው:: ኢትዮጵያ የአሁኗን ቅርጽ እንድትይዝ ካደረጋት የሀገር ግንባታ ሂደት አንስቶ አሁን እስከምንገኝበት ዘመን  ውስጥ የተፈጠሩትን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነትና በደሎችን ማካተት አለበት:: እነዚህን ሁሉ በደሎች አንድ ሰው ወይም አንድ አገዛዝ ሳይሆነ የፈጸመው፣ በየወቅቱ በሀገራችን የሰፈኑት አገዛዛችና አገዛዛቹን የመሰረቱት እና ተጠቃሚ በሆኑት ለአገዛዛቹ ቅርበት ባላቸው ጥቂት ልሂቃን ነው:: ስለዚህም፣ ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት የጎደላቸው ነገሮች ተደግረዋል፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአገዛዛቹ ተበድለዋል፤ የበደሉ አይነትና መጠን ቢለያይም:: ስለዚህም የተፈጸሙት በደሎች ያስከተሏቸው ውጤቶች በደንብ ተመርምረው ለታሪክ መማሪያነት መቀመጥ አለባቸው:: እንደ ሁሉም ሀገር፣ ሀገራችን ኢትዮጵያም ያላት ታሪክ <ጥሩም መጥፎ> ነው:: ከ<ጥሩ> ታሪካችን አንድነታችንን የበለጠ በማጠናከር <ከመጥፎው> ታሪካችን ደግሞ በመማር ማህበራዊ ግንኙነታችንን ይበልጥ በመተማመንና በመከባበር ላይ የተመሰረት ማድረግ እንችላለን:: ስለዚህም፣ የተፈጸሙት በደሎች ያስከተሉት ውጤቶችና ተጎጂዎች የከፈሉት መስዋትነትና እንድምታ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ ተመዝግቦ መያዝ ይገባዋል::
ለዚህም አላማ ሲባል ሊደረጉ የሚችሉ ተግባራት የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ:: አንደኛ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ የነበሩና ያሉ ግንኙነቶች፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በአግባቡ ሳይንሳዊ መሆነ መንገድ ተጠንተው እንዲቀመጡ በየዩኒቨርስቲዎቻችንና መንግስታዊ በሆኑ የምርምር ተቋማት ውስጥ እንደ አንድ ፕሮግራም ተቀርጾ ሊዘረጋ ይችላል:: በዚህም ሂደት የብሔራዊ ዕርቁን ተቋማዊ ገጽታ ማላበስ ይቻላል:: ሁለተኛ፣ ብሄራዊ ዕርቁን የሚመለከት መታሰቢያ ብሄራዊ ቀን ቢመረጥና በየዓመቱ የምርምር ስራዎች የሚቀርቡበት፣ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር፣ በመከባበርና ፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት በማህበረሰባችን ውስጥ ሊመጡ በሚችሉ ተግባራት ታስቢ እንዲውል ማድረግ ይቻላል::  ሶስተኛ፣ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በታሪካዊ በደሎች ምክንያት ውድ ህይወታቸውን ላጡ፣ ከመኖሪያቸውና ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ እና የተለያዩ መሰዋትነት የከፈሉትን ሰዎች ለማስታወስ ሃውልት እንዲቆም ማድረግ የሚቻል ነው::
ሐ) የተፈጸሙት በደሎች በድጋሚ እንዳይፈጸሙና የተገለሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ፍላጎትና ደህንነትየሚያረግገጥ ስርአት ለመፍጠር መዋቅራዊ ለውጦችን ማምጣትና የፖለቲካ ውህደትን ማሳለጥን  (Structural changes and institutionalization of the process of political integration) 
ብሔራዊ ዕርቅ ማህበራዊ ለውጥን ለማማጣትና ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት እንደ ወሳኝ ግብአት የምንጠቀምበት ከሆነ፤ ብሔራዊ ዕርቅ ሂደት በራሱ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ነው:: ይህ ማለት የተፈጸሙት በደሎች በድጋሚ እንዳይፈጸሙና የተገለሉ የማህበረሰቦች ክፍሎች ፍላጎትና ደህንነት የሚያረጋግጥ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መፈጠር አለበት:: ይህን ለማድረግም፣ የፖለቲካ ስርአቱ የሚመራበትን የጨዋታ ህግ ማውጣትና የጨዋታውን ህግ የሚመሩ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት ይጠይቃል:: ይህም ማለት በማህበረሰባችን ውስጥ መዋቅራዊ ለውጦችን ማምጣትን የሚጠይቅ ነው:: የሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ፍላጎቶችና ደህንነት ለማስከበር የፖለቲካዊ ስርአቱ ውስጥ ሁሉንም ተሳታፊ ማድረግ ግድ ነው::
ከዴሞክራሲያዊ ስርአት ውጪ በሀገራችን ያለውን ብዝሃነት ሊያስተናግድ የሚችል ስርአት የለም:: ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በመሰረቱ ሁለት ግቦች ላይ ማነጣጠር አለበት:: አንደኛ፣ በዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ሂደት ውስጥ ተቋማት የሚወክሉት ግለሰቦችን አሊያም የተወሰኑ የልሂቃን ቡድኖችን አይሆንም:: ተቋማት የሚወክሉት ስምምነት የተደረሰባቸውን የጨዋታ ህጎችን ሲሆን እነዚህም ህጎች በልሂቃን ውስጥ የሚፈጠሩ የጥቅምና የፍላጎት ግጭቶችን ለመዳኘት ዋና መሳሪያ ይሆናሉ:: ስለዚህም፣ የብሔራዊ ዕርቅ ሂደት ዴሞክራሲያዊ ተቋማትንና የጨዋታ ህጎችንና ደንቦችን ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች በሚስማሙበት መልኩ ለመቅረጽ የሚያስችል ሂደትን ይፈጥራል:: ይኸም ማለት ብሄራዊ ዕርቅ ከሚመጣባቸው ዋነኛ ሂደቶች መካከል የጨዋታ ህጎቹ የሚወጡበት አግባብና ሂደት ወሳኝ ነው:: ኢህአዴግ ብሔራዊ ዕርቅን የሚመለከትበት አግባብ ማለትም << ብሔራዊ ዕርቅ ማለት አሁን በለው ህገመንግስና ህገመንግስታዊ ስርአቱ ላይ መግባባት መፍጠር ነው::>> የራሱን ፖለቲካዊ የበላይነት ለማስጠበቅ ያለፈ ትርጉም አይኖረውም:: ምክንያትቱም የጨዋታ ህጎቹ የወጡበት አግባብና ሂደት ሌሎች የፖለቲካ ኃይሎችን ያገለለ ከመሆኑም በላይ ዋነኛ ተገዳዳሪ የሚባሉትን በተለይ ደግሞ ሀገር-አቀፍ ፖለቲካ የሚያራምዱትን ያላካተተ ነው::
ሁለተኛ ደግሞ በዴሞክራሲያዊ ስርአት የስልጣን ክፍፍልን ስለሚያመጣ፣ ተጠያቂነትን ስለሚያሰፍንና ፖለቲካዊ ስልጣን በጉልበት ሳይሆን በህዝብ ፍላጎት ላይ በተመሰረተ አካሄድ ስለሚያዝ አዲስ ፖለቲካዊ ባህልን በሃገራችን ውስጥ እንዲሰፍን ያደርጋል:: ስለዚህም፣ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ የስልጣን ክፍፍሎሽ ስለሚኖር በልሂቃኖች መካከል ሊኖር የሚችለው የስትራተጂና የታክቲክ ጉዳይ እንጂ ጫፍ የወጣ ፖለቲካዊ ልዩነት አይሆንም:: በመሆኑም የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ መዋቅራዊ ለውጥ ከማምጣትና ፖለቲካዊ ውህደትን ከማሳለጥ አንጻር መታየት ያለበት ነው:: ይኸም፣ ፖለቲካዊ ውህደት የጋራ ነገን ከመፍጠርና የጋራ ራዕይ እንዲኖረን እና አዲስ ሲቪክ ፖለቲካዊ ባህል እንዲገነባ ከማስቻሉም በላይ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ መሰረት ይሆናል::
መ) ፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት በማምጣት ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ማረጋገጥ (enhancing socio-economic development and economic integration)
በታሪካችን እንደምንመለከተው ከሆነ በአብዛኛው በልሂቆቻችን መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች በፖለቲካ ሃሳቦች ልዩነት ላይ የተመሰረቱ ሳይሆን አንዱ አንዱን ጥሎ በማለፍ የፖለቲካ ስልጣን ለመቆጣጠር በሚደረጉ ግብግቦች ላይ የተመሰረቱ ናቸው:: የፖለቲካ ስልጣን ጥያቄ በዋናነት የሚያያዘው ደግሞ የሀገሪቱን ሀብት ከመቆጣጠር ጋር ነው:: በግልጽ ለማስቀመጥ ያክል የዘመናዊት ኢትዮጵያ ሀገር ምስረታ ሂደት ፖለቲካዊው እንድምታው ያልተማከለና በጣም ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት መመስረት ሲሆን፣ ኢኮኖሚያዊው እንድምታው ደግሞ በጦር አሸናፊ ሆነው የማዕከላዊ መንግስት ምስረታን ሂደት የተቆጣጠሩትን ኃይሎች የኢኮኖሚ ጥቅሞችን የማስከበር ሂደት ነበር:: ይህ ሂደት በደርግ አገዛዛም ሆነ በኢህአዴግ አገዛዝ የተደገመ ነው:: በዘውዳዊው፣ በደርግም ሆነ በኢህአዴግ አገዛዞች የተዘረጉት ኢኮኖሚያዊ ስርአቶች የሰፊውን ህዝብ ተጠቃሚነት ያላረጋገጡና የአገዛዞቹን ቀጣይነት ብቻ ለማረጋገጥ ያለሙ ናቸው:: ይህም በመሆኑ የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ ኢኮኖሚያዊ ፍትሃዊነትንና የህዝብ ተጠቄሚነት ላይ ያነጣጠረ መሆን ይገባዋል::
እንደ ደቡብ አፍሪካ ፖለቲካዊ ስልጣን ላይ ብቻ የተመሰረት የብሄራዊ ዕርቅ ሂደት በኢትዮጵያ ውስጥ ረጅም ርቀት የማይወስድ ብቻ ሳይሆን  ወደ በለጠ ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ችግሮች የሚያጋልጥ ነው:: ስለዚህም የኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አንዱ የብሔራዊ ዕርቅ ዋና አላማ መሆን ይገባዋል:: በሌላ በኩል ደግሞ፣ የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ማረጋገጥ እና በክልሎች መካከል ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው:: ድህነት በራሱ ሰዎች በወደፊት ሕይወታቸው ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ፣ ጨለምተኛ እንዲሆኑ ከማድረጉም በላይ ለዚህ ሁሉ ቀውስ ተጠያቂ የሚያረጉት አንድ ነገር ይፈልጋሉ፤እራስን ከጥፋተኝነት ነጻ ለማውጣት:: ስለዚህም ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነቶችን ለዛሬው ውድቀት ብቸኛ ተጠያቂ እንደሆኑ ሲታሰብ፣ በተወሰኑ ልሂቃን ደግም ይህን ስሜት ለራሳቸው ፖለቲካዊ ጥቅም እንዲውል ያደርጋሉ፣ እያደረጉም ነው:: ስለዚህም፣ ፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ማስፋን የብሔራዊ ዕርቅ ውጤታማነትንና ዘላቂነትን ከማረጋገጥ አንጻር ወሳኝ ነው::
ከዚህ ጎን ለጎን፣ ሙስናን ማስወገድ የሚያስችሉ ተቋማዊ፣ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ ሪፎርሞችን ማካሄድ ግድ የሚል ነው:: በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በቁጥጥር ስር ያዋሉት ሶስት ኢኮኖሚያዊ ሃይላት ናቸው:: እነርሱም፣ መንግስት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚቆጣጠራቸው ድርጅቶች፣ የሚድሮክ ድርጅቶች እና በኢፈርት ድርጅቶች ናቸው:: ይህም፣ የአሁን ኢኮኖሚ ስርአት በዋናነት የፖለቲካ ስልጣን የተቆጣጠሩት ጥቂት ልሂቃን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በቀጥታ የሚቆጣጠሩበትን አግባብ ተቋማዊ ገጽታ የሚያላብስ ነው:: ስለዚህም፣ ፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትና ከዚህ ልማት እኩል ተጠቃሚነትን ከማስፈን አንጻር ሙስናን ማስወገድና ተወዳዳሪነትን የተላበሰ ኢኮኖሚያዊ ስርአት መዘርጋትን ግድ የሚል ነው:: በሌላም በኩል፣ በባለፉት የአገዛዝ ስርአቶች ከኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ትሩፋት የተገለሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል:: ይኸም፣ በባለፉት አገዛዞች ተበድለናል የሚሉ የፖለቲካ ልሂቃን ጫፍ የወጣ የፖለቲካ አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ የሚስገድዳቸው፣ የማያስተካክሉ ከሆነ የማህበረሰባዊ መሰረታቸው እንዲያጡ የሚያደርግ፣ ከተናጥል ጉዞ የአብሮነት ጉዞ እንደሚበልጥ ሰፊው ህዝብ እንዲረዳ የሚደርግ ነው:: በመሆኑም፣ ይህ ሁኔታ የብሄራዊ ዕርቅ ዘላቂነትን ከማረጋገጡም በላይ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ወሳኝ ነው::
ሠ) ለብሔራዊ  ዕርቅ  ምቹ  ሁኔታን  ስለመፍጠርና አማራጭ መፍትሄዎች
እስካሁን ድረስ ብሔራዊ ዕርቅን ለማሳካት ምቹ ሁኔታን አልተፈጠረም:: ይህ ምቹ ሁኔታ አለመኖር የሚመነጨው ከገዢው ፓርቲ ከፋፍሎ የመገዛዝ ባህል እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጣዊ ደካማነትና የጋራ አላማ መፍጠር አለመቻላቸው ነው:: ብሔራዊ ዕርቅ እንዲሳካ ስልጣን ላይ ያሉ ገዢዎችን የሚያስገድድና የሚገዳደር ተቃዋሚ ኃይል መኖርን ግድ የሚል ነው:: ካለ ጠንካራ ተቃዋሚ ኃይል የሚገኝ ብሔራዊ ዕርቅ፣ ዕርቅ ሊባል የሚቻል አይደለም:: ምክንያቱም የዕርቅ ሂደቱ ስልጣን ላይ ያሉ ልሂቃንን ጥቅም የሚያስጠብቅ ነው፤ ሁሉን የፖለቲካና ማህበረሰባዊ ኃይላትን የሚያካትት አይደለም:: ከዚህ ቀደም በወጡ ጹሁፎቼ እንዳመለከትኩት፣ የኢትዮጵያ የተቃውሞ ኃይሎች በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ሀገር ያሉት በብዙ ችግሮች የተተበተቡ ናቸው:: የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ ግማሹ ምላሽ በተቃውሞ ኃይላት ጥንካሬ ላይ የሚመሰረት ነው:: አንድነት ጥንካሬ፣ መከፋፈል ድክመትን እንደሚያመጣ ከባለፈው ታሪካችን በተሻለ ሁኔታ ልንማርበት የምንችልበት መድረክ የለም:: ስለዚህም፣ በተቋማዊ ብቃት፣ በስትራተጂ፣ በታክቲክ እና አባላትን በማፍራት ተቃዋሚ ሃይላት ከገዢው ፓርቲ ጋር ተገዳዳሪ መሆን አለባቸው::
አብዛኞቹ የሀገራችን የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነታቸው ርዕዮተ አለማዊ፣ ስትራተጂያዊ ወይም ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በግለሰቦች ቁርሾ ላይ የተመሰረተ ነው:: ስለዚህም፣ ግለሰባዊ ቁርሾዎችን ከብሔራዊ ፖለቲካ ጥያቄ መለየት መቻል አለብን:: በሌላም በኩል፣ አሁን የሚታየው የፖለቲካ ኃይሎች መሰባሰብ ይበል የሚያስብል ሲሆን፣ እዚያው ሳለም ሁሉን ማህበረሰብ የሚያቅፍና የሚያንቀሳቅስ አጀንዳ መቅረጽ ይጠበቅባቸዋል:: ተቃዋሚ ኃይላት ማህበረሰባዊ መሰረታቸውን መስፋትና ሁሉን የማህበረሰብ ክፍል (cross-cutting social cleavages) ማቀፍና ማንቀሳቀስ መቻል አለባቸው:: ይህን በማድረጋቸው፣ ገዢው ፓርቲ ስልጣን ላይ ብቻውን ለመቀመጥ የሚከፍለው መሰዋትነት በዕርቅ ሂደት ውስጥ በመሳተፍና ፖለቲካዊ ስርአት ለውጥ በመምጣቱ ከሚያጣው ጥቅም ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ እንዲሆን ያደርገዋል:: ይኸም፣ ለዘብተኛ የአገዛዙን ልሂቃን ወደ ብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄን እንዲያራምዱ ሲያስችላቸው፣ አክራሪ ልሂቃንን ደግሞ የበለጠ ደካማ ያረጋቸዋል::
በሌላ በኩል ደግሞ፣ የብሔራዊ ዕርቅ ስትራተጂያዊ ውጤቶችና ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባት ሂደት ተጠቃሚዎች ጥቂት ልሂቃን መሆን የለባቸውም:: በብሔራዊ ዕርቁ ሂደት ማንም የፖለቲካ ኃይል ሳይሆን አሸናፊ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት፣ አንድነት እና ሉአላዊነት ነው:: ስለሆነም፣ የብሔራዊ ዕርቅ ሂደት ማነጣጠር ያለበት ማን ስልጣን ላይ ወጣ የሚለው ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ የጨዋታ ህጎች ማውጣት እና ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት ላይ ነው:: ይኸም፣ የብሄራዊ ዕርቁ ስተራተጂያዊ ውጤቶች (ዴሞክራሲያዊ ስርአት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና ሀገራዊ መግባባት) እና ታክቲካዊ ግቦች መካከል አንድነትንና ሚዛንን የሚያስጠብቅ ይሆናል:: በመሆኑም፣ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ለብሔራዊ ዕርቅ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩም በላይ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ወሳኝ ግብአት ነው::   
5. ማጠቃለያ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በብዙ ውስብስብ ታሪካዊ ሂደት ያለፈች ሀገር እንደመሆኗ መጠን፣ ያሉብን ችግሮች መጠነ ሰፊና ውስብስብ ናቸው:: እስካሁን ድርስ ጉልበት ላይ የተመሰረተ ልዩነቶችን የመፍታት ሂደቶች የበለጥ ልዩነቶችን ውስብስብ እንዲያደርግና ጥላቻ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ስር እንዲሰድ ሆኗል:: ምንም እንኳን ከደርግ ወታደራዊ አገዛዝ ውድቀት በኋላ የተለያዩ የብሔራዊ ዕርቅ አስተሳሰቦች በሙሁሯንና በፖለቲካ ኃይላት ቢራመዱም፣ የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄን የፖለቲካ ኃይላት የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ማሳኪያ መሳሪያ ያደረጉበት አረዳድ እንደሰፈነ መረዳት አያዳግትም:: የብሔራዊ ዕርቅ ሂደት ውስብስብ ችግሮችን የምንፈታበት ሂደት እንደመሆኑ መጠን  በእንዳንዱ ጥቃቅን በደሎች ላይ የምናተኩርበት፣ ፖለቲካዊ ትርፍ የምናሰላበት፣ አግላይ ስርአት የሚመሰረትበት ሂደት ሳይሆን የተሻለች ኢትዮጵያንና ብሩህ ቀን የመፍጠር ሂደት አካል መሆን ይገባዋል::
የተመረጡ ዋቢ መጽሃፍትና ሰነዶች

[i] Bloomfield, David, Teresa Barnes, and Lucien Huyse. 2003. Reconciliation After violent conflict: A Handbook. Stockholm: Interna-tional IDEA.
[ii]  Lederach, John Paul. 1997. Building Peace: Sustainable Reconciliation in Divided Societies. Washington, D.C. : United States Institute of Peace.
[iii] Solimano, Andres (Ed.). 2000. Colombia: Essays on Conflict, Peace and Development. Washington, D.C., The World Bank.
[iv] Liebenberg, Ian and Abebe Zegeye. 1998. “Pathway to Democracy? The Case of the South African Truth and Reconciliation Process.” Social Identities, Volume 4, Number 3, pp. 541-558.
[v] Diamnond, Larry.  2008. The Spirit of Democracy: The Struggle to Build Free Societies Throughout the World. New York, Henry Holt and Company, LLc,.
[vi] Bahru Zewde. 2005. A History of Modern Ethiopia, 1855-1991. Ohio: Ohio University Press. 2nd Edition.
[vii] Dereje Feyissa. 2013.“Muslims Struggle for Recognition in Contemporary Ethiopia”. InMuslim Ethiopia: The Christian Legacy, Identity Politics and Islamic Reformism, eds. Patrick Desplat and Terje Østebø. New York, Palgrave Macmillan.

[viii] Desplat, Patrick; Terje Østebø . 2013. “Muslims in Ethiopia: The Christian Legacy, Identity Politics, and Islamic Reformism”. In Muslim Ethiopia: The Christian Legacy, Identity Politics and Islamic Reformism, eds. Patrick Desplat and Terje Østebø. New York, Palgrave Macmillan.

Monday, December 2, 2013

የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ

የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ

ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በሰላማዊ መንገድ በሚደረግ ትግልና በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ዉይይቶች ቢመጣ የግንቦት 7 ምርጫ መሆኑን ንቅናቄያችን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። ግንቦት 7ን ሁለገብ ትግል ውስጥ እንዲገባ ያስገደደው የወያኔ እምቢተኝነትና እብሪት ብቻ ነው።
የግንቦት 7 ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሰሞኑ የወያኔ የእንደራደር መልዕክት እንደደረሰው በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ባጠቃላይ እንጂ ግንቦት 7ን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ ከድምዳሜ ላይ ደርሷል። ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ከሚያደርገው ትግልና እየከፈለ ካለው መስዕዋትነት ጋር በቀጥታ ግንኙነት አለው። በመሆኑም፤ ለቀረበልን ጥያቄ ግልጽ መልስና፤ ድርድር ስለሚባለው ጉዳይም ያለንን አቋም ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የኢትዮጵያ ሕዝብና የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለማቅረብ የሚያስችል ተጨማሪ አጋጣሚ አድርገን ወስደነዋል። በዚህም መሠረት ለቀረበልን ጥያቄ የሰጠነዉን መልስና አቋማችንን በድርጅታችን ድረ ገጽ ላይና በሌሎች መገናኛ ብዙሀን በኩል በይፋ ለመግለጽ ወስነናል።
በድርድር ስለሚመጣ ለውጥ ያለን የመርህ አመለካከት:
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እንዳደረግነው ድርጅታችን ከምሥረታው ጀምሮ የትግል ስልቱን ሲወስን እምነቱ አድርጎ የተነሳው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በሀገራችን በሰላማዊ መንገድና በድርድር ቢመጣ በእጅጉ የሚፈልገውና የሚመኘው መሆኑን ነው:: ድርጅታችንን ወደ ሁለንተናዊ ትግል የገፋው በመግቢያው ላይ እንደገለጽነው የወያኔ እብሪት ብቻ ነው:: የቀረበልን ምርጫ በባርነትና በውርደት መኖር ወይም ለነፃነት እየታገልን መሞት ቢሆን ኖሮ ንቅናቄያችን የሚመረጠው ምን ግዜም ለነፃነትና ለአገር አንድነት ታግሎ በክብር መሞት መሆኑን በተደጋጋሚ ለሕዝብ ግልጽ አድርገናል። ይህ የማይናወጥ አቋማችን ደግሞ ለይምሰል የተቀመጠ አቋም ሳይሆን ከልባችን የምናምንበትና ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አባላቶቻችንን ያሰባሰብንበት አቋም ነው። ዛሬ በትግሉ ግንባር የምንንቀሳቀሰውና ወደ ግባችን የሚወስደንን ተጨባጭ እርምጃዎች እየወሰድን ያለነውም በዚሁ አቋማችን ዙሪያ ነዉ።
ይህ አቋማችንና እምነታችን በአንድ ላይ ጎን ለጎን የሚሄዱ ሁለት መርሆችን አጣምሮ የያዘ ነዉ። አንደኛው፣ ሂደትን በሚመለከት ሁሌም ለድርድር ክፍት መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፣ ይህ የድርድር ሂደት እንዲያው ለለበጣ የሚደረግ ሳይሆን ወደሚፈለገው ነጻነት በአነስተኛ መስዕዋትነት ሊያደርስ ይችል ከሆነ በሩን ላለመዝጋት እንጂ፣ በምንም አይነት ዋና ውጤቱን፤ ማለትም ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ማድረግን፤ የሚቀይር ወይንም ከዚያ ያነሰ ውጤትን ለመቀበል መፍቀድን ፈጽሞ የማያመለክት መሆኑን ነው::
በእኛ በኩል ድርድሩን አስፈላጊና ጠቃሚ የሚያደርጉት መነሻ የፖለቲካ እሳቤዎችም ከእነኝሁ ሁለት መንታ ገጽታዎች የሚመነጩ ናቸው:: በድርድር ለሚገኝ ፍትሀዊና እውነተኛ ውጤት ክፍት መሆናችንን ሁሌም እናሳያለን፤ ነገር ግን ይህን የምናደርገው የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባትን ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት መከፈል አለበት የሚለውን መሠረታዊ የአካሄድ መርህ በመመርኮዝ እንጂ መርሀችንን ለድርድር ለማቅረብ እንዳልሆነ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል::
ስለዚህም:
ሀ)    የድርድሩ ውጤት የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ያረጋገጠ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በአስቸኳይ እውን ማድረግ መሆን ይኖርበታል:: ይህ ዋናው ግብ ሆኖ ከዚህ በመለስ የሚኖሩ በሂደት የሚገኙ አነስተኛ ግቦች ሊኖሩ ይችላሉ (ለምሳሌ የፖለቲካ እስረኞች ማስፈታት…ወዘተ):: ሆኖም በምንም አይነት ለእነኝህ መለስተኛ ግቦች ተብሎ ዋናውን ግብ የሚያሳጣ ወይንም ጊዜውን ያላግባብ የሚያስረዝም ድርድር፣ ድርድር ነው ብሎ ድርጅታችን አይቀበልም። ስለዚህም ዋናው የድርጅታችን ዓላማና ግብ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ፣ በፍጹም ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም:: በሥልጣን ላይ ባለው ኃይል በኩል ወደዚህ ግብ ለመድረስ ቁርጠኝነቱ በሌለበት ሁኔታ በሚደረግ ማንኛውም አይነት ድርድር ውስጥ ግንቦት 7 አይሳተፍም::
ለ)  በግንቦት 7 እምነት ማንኛውም ድርድር ወያኔ ከግንቦት 7 ጋር በተናጠል የሚያደረገው ሳይሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች ያካተተ መሆን ይኖርበታል:: ድርጅቶችን በተናጠል እየለያዩ “እንደራደር” ማለት በራሱ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ስሌትን የያዘ እሳቤ እንጂ፣ በዘላቂነት አገሪቱን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አገር ለማድረግ መፈለግን አያመለክትም:: ለአንድ ድርጅት ለብቻው የሚመጣ ወይም የሚጠቅም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የለም:: ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመፍጠር ፍላጎት ያለው ድርድር በአገሪቱ ያሉትን የተለያዩ የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ኃይሎችን ያካተተና ያመኑበት መሆን ይኖርበታል:: የሚደረገው ድርድርም ማን በስልጣን ላይ ይውጣ ወይንም የፖለቲካ ስልጣንን ባሉት ኃይሎች መሀከል እንዴት እናከፋፍለው የሚል የስልጣን ቅርምት ድርድር ሳይሆን፤ ሕጋዊና የሕዝቡን የሥልጣን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ ሁኔታ የፖለቲካ ስልጣን እንዴት እንደሚያዝ ፍትሀዊ የሆነ ሂደትን ለማስጀመር የሚደረግ ድርድር መሆን አለበት::
ሐ) ቀደም ብለን እንደጠቀስነው ይህ ጉዳይ የሚመለከተው አንድን ድርጅት ወይንም የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ነው:: ይህ እስከሆነ ድረስ እንዲህ አይነት ድርድር ከሕዝቡ በተደበቀ ሁኔታ በሚስጥር የሚካሄድበት ምንም ምክንያት የለም::
2)   ከዚህ በፊት ከወያኔ ጋር ከተደረጉ ድርድሮች ያገኘናቸው ተመክሮዎችና ከዚህ በመነሳት ወደፊት በሚደረጉ ምንም አይነት ድርድሮች እንዳይደገሙ ለመጠበቂያ የሚሆኑ ከአሁኑ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች
ከማንኛውም ወገን ጋር የሚደረግ ድርድር የተደራዳሪዎቹ ምንነት፤ ውስጣዊ ባህርያቸውን፤ ከተለምዶ ተግባራቸው ያላቸውን ተአማኒነትና ወደዚህኛው ድርድር ያመጣቸውን ምክንያቶች በበቂ ከመገንዘብ ጋር ተያይዞ የሚታይ ጉዳይ ነው:: ቃሉን አክባሪና ተዓማኒ ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ድርድርና ያለፈው ታሪኩ ምንም አይነት የተዓማኒነት ባህርይ ከማያሳይ ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድርም ሆነ ለድርድሩ የሚደረግ ዝግጅት ለየቅል ናቸው:: ይህ ማለት ግን ተዓማኒነት ካለው ኃይል ጋር ብቻ ነው ድርድር የሚካሄደው ማለት አይደለም:: በፍጹም ተዓማኒ ካልሆነ ኃይል ጋር የሚደረግ ማንኛውም ድርድር ግን ድርድሩ በእርግጥም ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መሆኑን የሚያሳዩ ጠንካራ መጠበቂያዎች (System of Verification) እንዲሁም ግልጽ የመተግበሪያ ሥርዓቶች (Implementation Mechanism) ሲደረጉለት ብቻ ነው ከምር ሊወሰድ የሚችለው:: ከዚህም ባሻገር ግን መጀመሪያውኑ ወደ ድርድር የሚመጣው ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሳይሆን በእዉነተኛ መንፈስ ከድርድር የሚመጣውን ውጤት በመፈለግ መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” ምልክቶች ሲያሳይ ነው በእርግጥም ወደ ድርድር የመጣው ከልቡ ድርድሩንና ከድርድሩ የሚመጣዉን ዉጤት ፈልጎ መሆኑን ለማመን የሚያስችለው::
ወያኔ ከተቀናቃኝ ወገኖች ጋር “ድርድር” ሲያደርግ የመጀመሪያ ጊዜዉ አይደለም:: እኛ እስከምናውቀው ድረስ ምናልባት በኃይል ይበልጡኛል ብሎ ከሚያምናቸው ወገኖች ጋር ካልሆነ በስተቀር፣ በረሃ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በማንኛውም ጊዜ ለቃሉ ታማኝ፤ ለመርሁ እውነተኛ፤ ለደረሰበት ስምምነት ተገዢ ሆኖ አያውቅም:: ይልቁንም ሶስተኛ አደራዳሪ ወገኖችን በሚያሸማቅቅና በሚያሳፍር መልኩ ውሸትን እንደ አዋቂነት፤ ማጭበርበርን እንደ ብልጠት፤ የተስማማበትን በገሀድ ማፍረስን እንደ የአመራር ብልሀት አድርጎ የሚያይ፤ ምንም እፍረትና ጨዋነት የሚባል ነገር ያልፈጠረበት እኩይ ኃይል ነው:: ከራሱ የድርጅት ጥቅምና በስልጣን ከሚገኝ የዝርፊያ ሀብት ማካበት ባሻገር፤ ለአገር ዘላቂ ጥቅም ብሎ የራሱን ጥቅም አሳልፎ የሚወስደው ምንም እርምጃ እንደሌለ በተግባር በተደጋጋሚ ያረጋገጠልን ኃይል ነው:: በግንቦት 7 ውስጥ ያለን ወገኖች ይህንን የወያኔ ባህርይ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ሌሎች ጽፈውት ያነበብነው ሳይሆን፣ እራሳችን በተግባር በተሳትፈንበት ሂደት ያገኘነው ጥልቅ ግንዛቤ ነው:: ይህንን ደግሞ በአንድ አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ከድርጅቱ ታሪክ ጋር የተጣበቀ፤ በአመራር አባላቱ ላይ እንደ ግል ባህርይ የሰረጸ መሆኑን እስክንገነዘብ ድረስ በተደጋጋሚ የተመለከትነው ነው:: ስለዚህም ከዚህ ኃይል በኩል የሚመጣን የ “እንደራደር” ጥያቄ ከዚህ በፊት እንዳደረገው ለገባበት የፖለቲካ ውጥረት ማስተንፈሻ፣ ለውሸት ፕሮፓጋንዳው መጠቀሚያ፤ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ መሰብሰቢያ፤ የዴሞክራሲ ታጋዮችን ትጥቅ ማስፈቺያና ወኔ መስለቢያ አድርጎ እንዲጠቀምበት በፍጹም አንፈቅድለትም:: ስለዚህም ከላይ በመርህ ደረጃ ከጠቀስናቸው ሶስት ጉዳዮች በተጨማሪ ምንም ዓይነት ድርድር ከመደረጉ በፊት ወያኔ ጉዳዩን ከምር የወሰደው መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” እርምጃዎች መውሰድ አለበት ብለን እናምናለን::
እነኝህም፣
ሀ)  ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት:: ይህ ደግሞ በግልጽ     የሚታወቁ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን በድብቅ የተቋቋሙ ማጎሪያና ማሰቃያ ቤቶች ያሉትን ሁሉ ማጠቃለል አለበት።
ለ)  በሕዝብ በተለይ በተቃዎሚ ኃይሎች ላይ ወያኔ በየቀኑ እያካሄደ ያለውን ወከባና እንግልት ባስቸኳይ ማቆም፣ ሰብዓዊና የዜግነት መብታቸውን ማክበር አለበት።
ሐ)   በፖለቲካ ምክንያት ከዚህ በፊት የተወሰዱ ሁሉም ዓይነት ፍርድ ተብዮ ውሳኔዎች እንዲሻሩ ማድረግ፤ በሂደት ላይ ያሉ ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ምንም አይነት ክሶችን ማቋረጥ አለበት።
መ)   ሕዝብን በፍርሃትና በስጋት ለማቆየት ሆነ ተብለው የወጡ አፋኝ ህጎችን በአስቸኳይ ማንሳት አለበት።
ሠ)   ማንኛውም ድርድር ገለልተኛ የሆኑ ሶስተኛ ወገኖች ባሉበት፤ የድርድሩ ሂደት በምስልና በድምጽ ተቀርጾ በገለልተኛ ወገኖች እጅ ብቻ የሚቀመጥ፣ የድርድሩ ቦታም የተደራዳሪ ወገኖች በጋራ በሚስማሙበት ቦታ መሆኑን መቀበልና ይህንንም በግልጽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቅ አለበት።
እነኝህ ከላይ ያስቀመጥናቸው በወያኔ በኩል የሚወሰዱ “የመተማመኛ” እርምጃዎች ለተቃዋሚዎች ተብሎ የሚወሰዱ እርምጃዎች አይደሉም:: ወያኔ እነዚህን እርምጃዎች ለመውሰድ ቁርጠኝነት ሳይኖረው ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት የሚደረግ ድርድር ላይ ከምር ይሳተፋል ብለን ማመን በፍጹም ስለማንችል ነው ::
እስከዚያው ድረስ ግን ግንቦት 7ም ሆነ ሌሎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት በቁርጠኝነት የምንታገል ኃይሎች፣ ወያኔ እነኝህን የመተማመኛ እርምጃዎች እስኪወስድና ቀደም ብለው በተቀመጡት መርሆች መሠረት በሚደረግ ድርድር በተግባር ሊመነዘር የሚችል ስምምነት፣ አልፎም ለምንም አይነት ማጭበርበርና መንሸራተት እድል የማይሰጥ ጠንካራ መጠበቂያዎች መኖራቸው እስኪረጋገጥ ድረስ፣ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን የምንገፋበት እንጂ በምንም አይነት ለአንድ አፍታም ቢሆን በድርድር ስም የማንዘናጋ መሆኑን አበክረን እናስታውቃለን::
የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣
ኅዳር 23፣ 2006 ዓ:ም

Ethiopia: Saudi Arabia – Labor Crackdown Violence – Ethiopian Workers Allege Attacks, Poor Detention Conditions –

Ethiopia: Saudi Arabia – Labor Crackdown Violence – Ethiopian Workers Allege Attacks, Poor Detention Conditions –


Diretribune Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.
hrwPRESS RELEASE
Beirut — Ethiopian migrant workers have been the victims of physical assaults, some of them fatal, in Saudi Arabia following a government crackdown on foreign workers. Many workers seeking to return home are being held in makeshift detention centres without adequate food or shelter.
Human Rights Watch spoke to five Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia. Four Ethiopians in Riyadh told Human Rights Watch that the attacks began after November 4, 2013, when authorities resumed a campaign to arrest foreign workers who they claim are violating labor laws. Security forces have arrested or deported tens of thousands of workers. Saudi officials and state-controlled media have said that migrant workers have also been responsible for violence, including attacks on Saudi citizens, in the wake of the crackdown.
“Saudi authorities have spent months branding foreign workers as criminals in the media, and stirring up anti-migrant sentiment to justify the labor crackdown,” said Joe Stork, deputy Middle East director. “Now the Saudi government needs to rein in Saudi citizens who are attacking foreign workers.”
Saudi authorities should immediately investigate assaults on Ethiopian and other migrant workers by security forces and Saudi citizens, and hold those responsible for violent crimes to account, Human Rights Watch said. Saudi and Ethiopian authorities should work to speedily repatriate undocumented foreign workers waiting in makeshift holding centers, if they have no fear of returning home, and ensure that they get adequate food, shelter, and medical care.
The most violent attacks occurred on the evening of November 9 in areas around the Manfouha neighborhood of southern Riyadh, where Ethiopian residents make up a majority of residents, according to local activists. Two Ethiopian migrant workers told Human Rights Watch that they saw groups of people they assumed to be Saudi citizens armed with sticks, swords, machetes, and firearms, attack foreign workers.
One of the Ethiopians, a 30-year-old supervisor at a private company, said he heard shouts and screams from the street, and left his home near Manfouha to see what was happening. When he arrived near Bank Rajahi on the road to the Yamama neighborhood, west of Manfouha, he saw a large group of Ethiopians crying and shouting around the dead bodies of three Ethiopians, one of whom he said had been shot, and two others who had been beaten to death. He said six others appeared to be badly injured.
He said he saw Saudis whom he called shabab (“young men” in Arabic), and uniformed security forces attack the Ethiopians who had gathered. The shabab were using swords and machetes, while some of the uniformed officers were beating the migrants with metal police truncheons, and other officers were firing bullets into the air to disperse the crowd. He said that he narrowly escaped serious injury when a Saudi man swung a sword at his head. It missed, but hit his arm, requiring stitches to close the wound.
The other Ethiopian witness, a 26-year-old undocumented day laborer who lives in Manfouha, told Human Rights Watch that he was sitting among a group of 23 Ethiopians in a private home on Street 20 on the evening of November 9 when a group of 20 shabab with machetes and pistols broke down the door and attacked the people inside. He and five other Ethiopians escaped by climbing to the roof, but he does not know what happened to the other 17 men.
Another Ethiopian worker who lives nearby, but who did not witness the violence, told Human Rights Watch that on the afternoon of November 9, he was sitting inside the Ethiopian community center and school compound five kilometers from Manfouha when 35 Ethiopian men came to the center.
The Ethiopian men said that groups of armed men were forcing their way into homes in Manfouha, removing the men, and holding the women inside. The person who spoke with Human Rights Watch said that the men showed him as proof a mobile phone video they said they surreptitiously filmed from a distance that appeared to show a Saudi man raping one of the Ethiopian men’s wives. He said the group told him that 10 other women were missing.
Since the evening of November 9, Ethiopian activists have circulated dozens of YouTube videos and other photos purporting to show Saudi men in civilian clothes and security forces attacking Ethiopian workers in Manfouha. Human Rights Watch cannot confirm the authenticity of these videos, though the incidents they purport to show largely match the witness accounts.
Saudi authorities should ensure that all incidents of apparent use of violence and abuse in Manfouha are swiftly and transparently investigated, and that anyone who committed a crime is brought to justice, including members of the security forces, Human Rights Watch said. The authorities should both address any unnecessary and unlawful use of force by security forces and take steps to prevent ordinary citizens from harassing or molesting migrants based on suspicions that they are violating labor laws.
Some Saudi sources blame the migrants for instigating the violence. Arab News, a local English-language newspaper, said that Saudi security forces entered Manfouha on the evening of November 9 to restore the peace after a group of Ethiopian men “went on a rampage in anger at the Kingdom’s ongoing campaign against illegal foreign workers.” It stated that one Saudi man died after “rioters” hit him with rocks, and that the 65 injured were “mostly Saudis and legal residents.” The Sabq news website reported on November 14 that Ethiopian migrants had stabbed to death a 14-year-old Saudi boy in Manfouha, reportedly asking him, “Are you Saudi?” before attacking him.
The five Ethiopian migrant workers who spoke to Human Rights Watch said that many undocumented Ethiopian workers in Manfouha have turned themselves in to the authorities since November 9, fearing violence from police and groups of Saudi citizens. One worker described the atmosphere in Manfouha as a “battleground.” The Ethiopian ambassador to Saudi Arabia, Muhammed Hassan Kabiera, toldArab News on November 13 that at least 23,000 Ethiopians, many from the Manfouha area, had surrendered to Saudi authorities for repatriation.
The Ethiopian workers said that authorities transported the Ethiopians to makeshift holding facilities across the area, including a large wedding hall and the campus of Princess Nora Bint Abdul Rahman University. One man told Human Rights Watch that he visited the wedding hall and saw thousands of foreign workers detained there, men in one area, and women and children in another, both inside and outside the building.
He said that Saudi guards give the detainees only one small meal of rice per day, and provide no access to medical attention. He said that other Ethiopians in the neighborhood are trying to help the detainees by bringing food, and that many at the hall had been left without shelter during recent heavy rainfall in Riyadh. One Ethiopian in Riyadh said he escaped from the wedding hall after officials held him in an area outside the building for 10 days, failing to supply the detainees with sufficient food, which forced them to buy food from Saudi guards.
Two Ethiopians in Riyadh told Human Rights Watch that people they knew who turned themselves in had not known that authorities would hold them in makeshift detention centers. They said that Saudi officials told them they would take them directly to Ethiopia. Saudi police officials say that the kingdom is spending one million Saudi Riyals (US$267,000) per day to house and feed thousands of detained Ethiopians.
On November 19, the Ethiopian foreign minister, Dr. Tedros Adhanom, announced that the government is doing “everything possible to repatriate citizens from Saudi Arabia within 14 to 25 days.”
“Saudi authorities say they are carrying out a crackdown on migrant workers humanely, but keeping thousands of people in makeshift centers without adequate food, shelter, or medical attention could lead to humanitarian disaster,” Stork said. “Saudi officials should release the detainees or send them home immediately.”
Migrant Worker Campaign Background
Over nine million migrant workers in Saudi Arabia-more than half the work force-ill manual, clerical, and service jobs. Many suffer multiple abuses and labor exploitation, sometimes amounting to forced labor, Human Rights Watch said.
Saudi officials say that the ongoing labor crackdown against foreign workers, which includes road checkpoints and raids on businesses, is part of Saudi Arabia’s effort to combat high levels of unemployment among Saudi citizens by opening jobs previously filled by undocumented workers. Those targeted include workers who do not have the proper residency or work permits, and workers who are caught working for an employer who is not their legal sponsor. According to local media outlets, authorities have arrested and deported thousands of workers since November 4.
The violence between Saudis and Ethiopians follows months of local press reports blaming Ethiopian female domestic workers for brutal attacks against Saudi employers. In July, Saudi officials claimed that over 200 Ethiopian women had been detained in two months for “psychological problems,” leading the labor ministry to temporarily ban the recruitment of Ethiopian workers to the country.
In October, the Ethiopian Ministry of Foreign Affairs, in turn, stopped processing applications for Ethiopians to travel to Saudi Arabia, citing concerns over poor labor conditions for Ethiopian migrants.
Human Rights Watch has repeatedly called on the Saudi government to abolish aspects of the kafala or “sponsorship” system that create conditions for abuse, including rules requiring a worker to obtain permission from his or her employer to change jobs or leave the country. These rules leave foreign workers with little option for redress in cases of abuse or labor violations and force them into under-the-table work.

አንድነት የአገርን ጥቅምና ህልውና የሚመለከቱ ጉዳዮች በተመለከተ በስትራቴጂ ሰነዱ ምን ይላል?

አንድነት የአገርን ጥቅምና ህልውና የሚመለከቱ ጉዳዮች 

በተመለከተ በስትራቴጂ ሰነዱ ምን ይላል?

1. አጠቃላይ የኢትዮጵያ ሁኔታ ግምገማ


1.1. የአገርን ጥቅምና ህልውና የሚመለከቱ ጉዳዮች

ገራችን ኢትዮጵያ በሰው ዘር መገኛነትዋ የምትታወቅ ሀገር ናት፡፡ በአካባብያችንም በስልጣኔ ማእከልነት ታሪክ 


ከሚያውቃቸው ጥቂት አገሮችም አንዷ ነች፡፡ ኩሩና አገር ወዳድ ዜጎች፣ ነጻነትን ጠብቀው ያወረሱን ጀግኖች 

አባቶችን ያበቀለች፣ በነጻነቷ፣ በመንፈሳዊ ሃብቷና uስልጣኔዋ የምትታወቅ' ልጆችዋ የሚኮሩባትና እሷን 

ላለማስደፍር የሚሞቱላት አገር ነች፡፡ 

የቅርቡ የአገራችን ገጽታ ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል፡፡ ያለፉት ሰላሳና አርባ ዓመታት ታሪካችን ረሃብና ጦርነት 

የነገሱበት ነበር፡፡ አገራችን አሁን ድረስ በዜጎችዋ ሰቆቃና የመብት ጥሰት በተደጋጋሚ የምትጠቀስ አገር ሆናለች፡፡ 

ድህነቱና የመብት ጥሰቱ ተጣምረው አገራችንን “ዜጎችዋ ሊኖሩባት የማይመርጡዋት” አገር እያሰኛት ነው፡፡ 

የተማሩት ዜጎች ካገር ለመውጣት አጋጣሚውን ባገኙ ቁጥር በየደረሱበት የውሃ ሽታ ሆነው ለመቅረት ይፈልጋሉ፡፡ 

ወይም በሃገር ውስጥ እያሉ እንደሌሉ ሆነው ይኖራሉ፡፡ የኮሌጅ ተማሪዎች ሳይቀሩ ትምህርታቸውን ቸርሰው ፤ 

በአገራቸው ለቁምነገር ከመብቃት ይልቅ ከኢትዮጵያ የሚወጡበትን አጋጣሚ የሚመርጡበት ሁኔታ ተከስቷል፡፡ 

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሕዝብ እድገት ካለባቸው አገራት አንዷ መሆንዋ ቢታወቅም በቅርቡ የወጣ ዘገባ 

እንደሚያመለክተው ዜጎችዋ እንደፈለጉት አገራቸውን መልቀቅ ቢችሉና ወደፈለጉት አገር ለመግባት እድል 

ቢሰጣቸው ሀገራችን ከፍተኛ የሕዝብ ፍልሰት ሊያጋጥማት እንደሚችል አመላክተዋል፡፡ የሕዝቧ ብዛት መሆን 

ከሚገባው በ46% ሊቀንስ እንደሚችልም ተገምቷል ፡፡ አገሩን የሚለቀው የተማረውና አምራቹ ትኩስ ሃይል መሆኑ 

ሲታሰብ፣ በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ምክንያት የሰው ዘር መገኛ የሆነችው አገራችን ሰው የሚሸሻት አገር 

ትሆናለች ሲባል ዘራችንና ማንነታችን ሊጠፋ እንደሚችል አመልካች ሊሆን ይችላል፡፡ 

አገራችን ኢትዮጵያ በግዙፍ ብዝሃ-ሕይወት ባለቤትነትዋ ትታወቃለች፡፡ ይህም ሆኖ አካባቢያችን ከፍተኛ የአየር 

ንብረት መዛባት የሚታይበትና ውሃ የጠማው መሬትና ፈጣን የበረሃነት መስፋፋት የሚታይበት መሆኑ ሌላው 

ኢትዮጵያውንን ሊያሳስበን የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ውሃችን እየቀነሰ፣ ጫካዎቻችን እያነሱ፣ አፈራችን እየተከላ፣ 

አካባቢያችን ህይወትን ለመሸከምና ለማቆየት ያለው እድል እየተመናመነ ሲሄድና አገራችን የብዝሃሕይወት ጸጋዋን 

እያጣችና በዚያውም ሰውንም የማኖር ችሎታዋ እየተመናመነ እንደሚሄድ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡


አገራችን ውሃ በተጠማ በረሃማ አካባቢ የምትገኝ ብትሆንም በዚህ አካባቢ ብቸኛ የበርካታ ትላልቅ ወንዞች መነሻ/

አመንጪዋ አገር ናት፡፡ ይህ ዕውነታ በአንድ በኩል ለመኖርና ለማደግ እድል ያለን መሆኑን ሲያመለክት በሌላ በኩል 

ደግሞ በዚህ ሳብያ ከጎረቤትና የአካባቢ አገራት ጋራ ትልቅ ፍጥጫ ውስጥ ሊያስገባን የሚችል መሆኑን መገንዘብ 

ይኖርብናል፡፡ ከዚህ በመነሳት የአገራችን የመሬት ገጽታ፣ የአየር ንብረትና እደምታውን መመልከቱ ለሀገራችን 

ፖለቲካ ትንተና አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ወንዞቻችን የሚፈልቁት ከከፍተኛውና ደጋማው የአገሪቱ አካባቢ ነው፡፡ ይህ አካባቢ አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ 

እጅጉን በተጣበበ ሁኔታ የሚኖርበት፣ በብዝሃ ህይወት ተሸካሚነቱም ከፍተኛ ድርሻ ያለው ነው፡፡ አብዛኛዎቹ 

ወንዞች ደጋውን ለቀው ሜዳማውንና ቆላማውን የአገራችንን አካባቢ አቆራርጠው ድንበር ይሻገራሉ፡፡ ቆላማው 

የአገራችን አካባቢ ውሃ የተጠማ ቢሆንም በጣም ለም አፈር ያለውና ለዘመናዊ ሰፋፊ እርሻ ምቹ ነው፡፡ ይህም ሆኖ 

በአሁኑ ወቅት ለኑሮ አስቸጋሪ በመሆኑ በእንስሳት እርባታ የሚተዳደር አነስተኛ ሕዝብ የሚኖርበት አካባቢም ነው፡፡ 

ውሃውን በደጋው በመያዝ ለመለስተኛ መስኖዎችና ለሃይድሮ አሌክትሪክ ሃይል አመንጪነት መጠቀም የምንችልበት 

ዕድል አለን፡፡ በቆላው አከባቢም እንደዚሁ ለሃይድሮ አሌክትሪክ ሃይል፤ ለሰፋፊ የመስኖ እርሻዎችና አግሮ 

ኢንዱስትሪ የማዋል ተስፋውና እድሉ ያለን ቢሆንም የአገራችን የውስጥ ፖለቲካዊ ችግሮችና ከውሃ ጋር የተያያዘው 

የአካባቢ አታካራ ትልቅ ፈተና እንደሚሆኑብን መገንዘብ ይገባል፡፡

እኛ የምንገኝበት ከአፍሪቃ ቀንድ ማዶ የባሕረ ሰላጤ (የጋልፍ) አገሮች ይገኛሉ፡፡ በመካከላችን የቀይ ባሕርና 

የባብኤል መንደብ መተላለፍያ ውሃዎች ይገኛሉ፡፡ የገልፍ አካባቢ ትልቁ የነዳጅ አመንጪ አካባቢ መሆኑ 

ይታወቃል፡፡ ከዚህ አካባቢ የሚቀዳው ነዳጅ፤ ከአውሮፓ ወደ ምስራቅ አፍሪቃና ኤስያም ሆነ ከምስራቅ አፍሪካና 

እስያ ወደ አውሮፓ የሚደረገው የመርከብ ምልልስ በቀይ ባሕርና በባብኤል መንደብ ውሃዎች ያልፋሉ፡፡ ይህ 

አካባቢ ቀውስ ውስጥ ቢገባ የዓለም ኢኮኖሚ”ና ህይወት” የሚያቆም አካባቢ እንደመሆኑ የዓለም ሃያላን ጥቅም 

ያለበትና እጅጉን የእነሱን ትኩረት የሚስብ አካባቢ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ያለን ብንሆንም ግን 

የባሕር በር የሌለን ብቸኛ አገር ነን፡፡ እነዚህ ዕውነታዎች ስለ እኛ ህልውናና ደህንነት የሚሉት ብዙ ነገር አላቸው፡፡ 

በዚህ አካባቢ በርካታ ትናንሽ አገሮች ባለ ወደብ የሆኑበት፣ ኢትዮጵያ ደግሞ ወደብ አልባ የሆነችበት ሁኔታ መኖሩ 

አጅግ የተወሳሰበ ሁኔታ የመፍጠር አደጋ አለው፡፡ በዚህ አካባቢ የሚከሰት የአገሮች የጥቅም ግጭት የሚቀሰቅሰው 

አምባጓሮ እኛንም ጎትቶ ችግር ውስጥ የማስገባት አደጋ አለው፡፡ ስለሆነም ሌሎች ጭረውት በሚነድ ሰደድ እሳት 

ውስጥ እንዳንገባ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ የመሆኑን ያክል ጥቅማችን እንዳይነካብንም በትኩረትና በጥንቃቄ 

መከታተል ይጠበቅብናል፡፡

የምንገኝበት የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ በድህነት፣ በበረሃማነትና በደፈረሰ ጸጥታው የሚታወቅ ቢሆንም ትልቅ የነዳጅና 

የማዕድን ይዞታ አለው ተብሎ የሚገመት አካባቢ ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው በርካታ ወንዞችና እጅግ ለም አፈር 

ባለበት በዚህ አካባቢ አገራችን ኢትዮጵያ ቁልፍ ስፍራ ያላት መሆኑም አንድና ሁለት የለውም፡፡ ምክንያቱም 

ሌላውን እምቅ ሃብትዋን አቆይተን ለም መሬትዋንና የውሃ ሃብትዋን ብቻ ለማቀናጀት ብነችል ትልቅ የኢኮኖሚ 

ኃይል የመሆን ዕድል አላት፡፡ በሌላ በኩል ይህ እውን እንዳይሆን የሚፈልጉ ወገኖች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ በዚህ 

ሁኔታ እነዚህ ትናንሽ ባለወደብ አገሮች የሚኖራቸው ሚና እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ አማራጮቹን ስንመለከት እነዚህ 

አገሮች አንድም የኢትዮጵያ እሴቶች የመጀመርያ ደረጃ ባለመብት ነን በማለት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ኢትዮጵያ 

ሰላምና ልማት እንድታገኝ፤ እነሱም ከዚህ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራሉ፡፡ አልያም ጊዚያዊ ጥቅሞችን በማገትና 

ኢትዮጵያን መተንፈሻ በማሳጣት፤ እድገትዋን በማገትና ሰላምዋን በማወክ የበለጠ እንጠቀማለን ከሚሉ ሃይሎች ጋር 

ይሰለፉና በኢትዮጵያ ላይ ችግር መፍጠርን እንደዋነኛ ተልእኮ ይወስዳሉ፡፡ የኢትዮጵያ የባህር በር መብት ጥያቄ እና 

የአካባቢው ልማትና መረጋጋት እጅግ የተሳሰሩ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸውም ይኸው እውነታ ነው፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች አገር የመሆንዋን ያክል የተለያዩ የሃይማኖት እምነት ተከታዮች 

የሚኖሩባት ሃገር ነች፡፡ ፖለቲካችን እነዚህን እውነታዎች የሚገነዘብ እና መቻቻልና እኩልነትን የሚቀበል እንዲሆን 

ማድረጉ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በሌላ ወገን መረን የለቀቀ የብሄርና የሃይማኖት አክራሪነት የአገራችንን ፖለቲካ 

እንዳያናጋብን በጥንቃቄና በብስለት መጓዝ ግድ ይለናል፡፡ ከፍ ብሎ ከተገለጸው የውሃ ፖለቲካና በአካባቢያችን 

እየታየ ካለው ሴኩላሪዝምን የመጋፋት አዝማሚያ አንፃር ሲታይ ብዙIነታችን የሚፈጥራቸው አንዳንድ ቅራኔዎች 

የሚስተናገዱበት ሁኔታ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ይሆናል፡፡


በዚህ የተወሳሰበ ከባቢ ውስጥ መገኘታችን ሳያንስ የአገራችን የውስጥ ፖለቲካም እጅጉን የተወሳሰበ ነው፡፡ በስልጣን 

ላይ ያለው መንግሥት (ፓርቲ) uውሃ ሃብት፣ uባሕር በር፣ uአገር ዳር ድንበር፣ uአገርና የሕዝቧ ደህንነትና 

በመሳሰሉት መሰረታዊ የአገር ጥቅም ጥያቄዎች ላይ የተአማኒነት ችግር ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመላው 

ኢትየጵያውያን ዘንድ ዕምነትና ተቀባይነት ያጣ ጠባብ ሕዝባዊ መሰረት ያለው አገዛዝ ነው፡፡ ሕዝባዊ መሰረቱ ደካማ 

መሆኑን በመገንዘብ ስጋትና ጭንቀት ውስጥ የሚኖር እና ከዚህ መዳኛየ ጉልበትና አፈና ብቻ ነው ብሎ የተሳሳተ 

አቋም የወሰደ አገዛዝ ነው ያለን፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ በዓለም በአምባገነናዊ አገዛዝ መዳፍ ስር ከሚገኙ አገሮች 

ውስጥ 9ኛ ደረጃን በመያዝ በአምባገነንነት የምትገዛ አገር ናት፡፡ በዚህ የደረጃ ሰንጠረዥ የአንደኝነት ደረጃውን 

የወሰደችው ሰሜን ኮርያ ስትሆን ኤርትራ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀም»ለች፡፡


ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያውያን የአገራችን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ/ግልጽ ሀብትነት እንዲለወጥ ማድረግ 

ይጠበቅብናል፡፡ ይህንን ለማሳካት መጀመርያ የአገራችንን ውስጣዊ ሁኔታ ማስተካከል ፈፅሞ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ 

አይደለም፡፡