Sunday, September 1, 2013

OPPOSITION: ETHIOPIA POLICE BLOCK RALLY, BEAT SOME

OPPOSITION: ETHIOPIA POLICE BLOCK RALLY, BEAT SOME

ADDIS ABABA, Ethiopia (AP) -- An opposition leader in Ethiopia says police have prevented his group from staging a rally to demand the release of jailed activists.
Yilkal Getnet, who heads the opposition Blue party, said Sunday that police raided their headquarters in the capital, Addis Ababa, on Saturday night and beat up some party members. He said police also seized banners and equipment that would have been used during a street protest on Sunday.
He said the rally was meant to highlight the continued detention of some journalists and Muslim activists.
Ethiopia has charged at least 28 Muslims activists with terrorism. But those activists say they have been unfairly targeted by the government, which they accuse of harassment.
A spokesman for Ethiopian police was not immediately available for comment.
http://hosted.ap.org

ዴሞክራሲ በተግባር: ‘ሰለማዊ ሰልፍ መከልከል’!!!

ዴሞክራሲ በተግባር: ‘ሰለማዊ ሰልፍ መከልከል’!!!



Abraha Desta
ዛሬ እሁድ ነሓሴ 26, 2005 ዓም ሰማያዊ ፓርቲ (ና ሌሎች ድርጅቶች) በአዲስ አበባ ከተማ ሰለማዊ ሰልፍ መጥራቱ ሰምተን ነበር። በሕገ መንግስታችን መሰረት ዜጎች ወይ ድርጅቶች ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲፈልጉ የአከባቢው አስተዳደር ማሳወቅ (ከተቻለም ማስፈቀድ) ይጠበቅባቸዋል። ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ ግን ሕገመንግስታዊ መብታቸው ነው። 

የሰማያዊ ፓርቲ የሰልፍ ጥሪ ተከትሎ መንግስት በሀይማኖታዊ ጉዳዮች ዙርያ በተመሳሳይ ቀን የሆነ ሰልፍ ነገር ዘመቻ መጥራቱ ተሰማ። በ አንድ ከተማ በተመሳሳይ ቀን ሁለት ተቃራኒ ሰልፎች ስለመካሄዳቸው ስናብሰለስል መንግስት ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ለማድረግ እንደማይፈቀድለትና ካደረገ እርምጃ ሊወሰድበት እንደሚችል ትናንት ከወጣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ መረዳት ይቻላል።

ሰለማዊ ሰልፍ (የተለየ ሁኔታ ካላጋጠመ በቀር) በመንግስት አዋጅ ወይ በተቋሞች መግለጫ ሊከለከል አይችልም፤ ምክንያቱም የዜጎች መብት መሆኑ በሕገ መንግስቱ ተቀምጧል። ሕገመንግስት ደግሞ የሁሉም ሕጎች የበላይ ነው።

መንግስት የተቃዋሚ ሰልፉ ከለከለው (ቢያንስ በፖሊስ መግለጫ)። ራሱ መንግስት የጠራው ሰልፍ ግን ይካሄዳል ማለት ነው። ‘እኔ ስልጣኑ ስላለኝ ሰልፍ መጥራት እችላለሁ፤ እናንተ ዜጎች ግን አትችሉም ‘ እያለን ነው። ዴሞክራሲ በተግባር እንዲህ ነው። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀፅ 30፣ "ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና፤ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡" ብሎ ይደነግጋል።

……………..

መንግስት ፍቃድ መከልከሉ የሀገራችን ሕገመንግስት የጣሰ ነው። መንግስት የራሱን ሕገመንግስት በራሱ ከጣሰ ዜጎች መንግስት የጣሰውን ሕገመንግስት እንዲያከብሩ እንዴት ማስገደድ ይቻለዋል? ዜጎች ብቻ ሕገመንግስቱ ቢያከብሩ እንዴት ዉጤት ማምጣት ይቻላል? በዴሞክራሲያዊ ሀገር ሕገመንግስት የበላይ ሕግ ነው፤ በመንግስትም በዜጎችም መከበር አለበት። ሕገመንግስቱን በመጣስ ኢህኣዴግ የሚመራው የኢትዮዽያ መንግስት ከሕግ በላይ እየሆነ ነው። መንግስት ሕግን በሚጥስበት ሀገር ዴሞክራሲ አለ ማለት አይቻልም። ዴሞክራሲ ከሌለ የኢትዮዽያ መንግስት ‘አምባገነን ነው’ ብንል እንዴት ስሕተት ሊሆን ይችላል?

መንግስት አምባገነን ከሆነ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚገነቡበት አጋጣሚ ለመፍጠር ብንቀሰቅስ ኃጥያት ይሆናል? መሪዎቻችን ለስልጣን ሲታገሉ ለዴሞክራሲ ግንባታ ብንታገል መልካም አይደለምን? ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ ህዝቦች ሓሳባቸውንና ያላቸው ቅሬታ (በመንግስት ይሁን በሌላ) የሚገልፁበት መድረክ እስከሆነ ድረስ የዴሞክራሲያዊ አሰራር መገለጫ ይሆናል ማለት ነው።

ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ የዴሞክራሲ መገለጫ ከሆነ ታድያ ለምን ሰለማዊ ሰልፍ እንፈራለን? ሰለማዊ ሰልፍ ባለመፍቀድ የህዝብን ብሶት ያቃልላል ያለው ማነው? ህዝብን ማፈን የህዝብን ቅሬታ እንዲጨምር እንደሚያደርግና ህዝቡ ሌላ አማራጭ (ሰለማዊ ያልሆነ መንገድ) ተጠቅሞ ፀረ መንግስት ሊነሳ እንደሚችል ኢህኣዴጎች ከደርግ አገዛዝ ትምህርት አለመቅሰማቸው ግርም ይለኛል። ሰለማዊ መንገድ መዝጋት የሃይል ወይ የዓመፅ መንገድ መክፈት ማለት ነው።

እኛ የምንፈልገው ግን የዓመፅ መንገድ ሳይሆን ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ነው። ኢትዮዽያ በሃይል ስልጣን የመያዝ የብዙ ዓመት ልምድ አላት። እስካሁን ድረስ የኢትዮዽያ ገዢዎች ስልጣን የያዙት በሃይል ነው። ባለስልጣናቱ (ሰዎቹ) ይቀያየሩ እንደሆኑ እንጂ ፖለቲካዊ አገዛዛቸው ተመሳሳይ ነው፤ ስልታቸው ጭቆና ነው። የሚገለገሉበት ስልጣን ከህዝብ ተውሰው የያዙት ሳይሆን በጠመንጃ አፈሙዝ የነጠቁት ነው፤ ለዚህም ነው ለስልጣናቸው እንጂ ለህዝብ ነፃነት ግድ የሌላቸው።

ሰለማዊ ሰልፍ የምንፈራበት አንድ ምክንያት ሊኖር ይችላል። ይሄም ‘ሰለማዊ ሰልፉ’ እንደስሙ ‘ሰለማዊ’ ላይሆን ይችላል። መፍትሔው ግን ቀላል ነው። በሕገ መንግስቱ የተቀመጠ ‘ሰለማዊ ሰልፍ’ ነው። ሰዎቹም የጠሩት ‘ሰለማዊ ሰልፍ’ ነው። ፍቃድ የተጠየቀው ‘ለሰለማዊ ሰልፍ’ ነው። መንግስት ይሄንን ፍቃድ መስጠት ነበረበት። ሰልፉ ሰለማዊ መሆኑ ቀርቶ የዓመፅ መንፍስ ከታየበት ‘ሕገ ውጥ ሰልፍ’ እየሆነ ነው ማለት ነው። በዚህ ግዜ መንግስት ‘ሕገመንግስቱን ለማስከበር’ ጣልቃ ሊገባ ይችላል። ‘ሕገ ወጥ ድርጊት’ የፈፀመ አካል ካለ ወደ ሕግ ቀርቦ በሕግ ይፈረዳል። (የሕግ የበላይነት ይከበራል)።

ገና ለገና ‘ዓመፅ ሊቀሰቅሱ ይችላሉ’ በሚል ስጋት (ይህን ያልኩበት ምክንያት መንግስት ዓመፅ ፈርቶ ካልሆነ በቀር ሰለማዊ ሰልፍ የማይፈቅድበት አሳማኝ ምክንያት ስላልመጣልኝ ነው) ሰለማዊ ሰልፍ መከልከል የዜጎች መብት መጣስ ስለሆነ አግባብነት የለውም። ባጭሩ መንግስት በሕገወጥ ተግባር ተሰማርተዋል ማለት ነው።

ሰለማዊ ሰልፍ መጥራት የመብት ጥያቄ እንጂ የአቋም ጉዳይ አይደለም።

ዓፈና ዓመፅን ይወልዳል።

ሙስሊም ወገኖች ሆይ!


ሙስሊም ወገኖች ሆይ!

ላለፈው አንድ አመት ተኩል ያደረጋችሁት ሰላማዊ እንቅስቃሴ በተለያየ እምነት ያለነውን ሁሉ አኩርቶናል:: ወያኔ ዛሬ ህዝብ 

በነቂስ ወጥቶ እንዲያወግዛችሁ ፈልጎ የነበረው እናንተን ለመምታት ለሚወስደው እርምጃ ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት የሚያስችል 

ድጋፍ ፈልጎ ነው እንጂ የት አገር ነው መንግሥት ሰላማዊ ሰልፍ አደራጅቶ ሽብርተኝነትን አውግዙልኝ የሚለው? ሰማያዊ 

ፓርቲን አግቶ በጠራው ሰልፍ ላይ የፈለገውን ድል እንዳያገኝ ሆ ብላችሁ ወጥታችሁ ስላደናቀፋችሁበት ቂም እንደተያዘባችሁ 

አትዘንጉ:: 

ወያኔ ሥልጣን ላይ ከመጣበት ዕለት ጀምሮ የሃይማኖት ተቋሞች የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው አስፈጻሚ አካላት መካከል አንዱ 

ሆነው ቆይተዋል:: ጳጳስ በህይወት እያለ ሌላ ጳጳስ ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በመሾም እስከዛሬ ያልበረደ ክፍፍል 

በተከታዮቹ መካከል መፍጠሩን ታውቃላችሁ:: ውሎ ይደር እንጂ በእናንተንም ላይ የተወሰደው የመከፋፈል እርምጃ ቀደም 

ብሎ በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ከተወሰደው የሚለይ አልሆነም:: ልብ ባንለው ነው እንጂ እየተደረገብን ያለው መከፋፈል 

ያለምክንያት አይደለም:: በዘርና በቋንቋ አልከፋፈል ያለን ህዝብ ለመለያየት ከሃይማኖት የተለየ ምን ሊመጣ ? ::

በመሠረቱ "መንግሥት በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ አይግባ" የሚል ጥያቄ ከመብቶች ጥያቄ አንዱ ቢሆንም በሃይማኖት ጉዳይ 

ጣልቃ የማይገባ መንግሥት የዜጎቹን መብት ለማክበር ግዴታ ያለበት መንግሥት ብቻ መሆኑን መዘንጋት አያስፈልግም :: 

የዚህ አይነቱ መንግሥት ቀድሞውኑም ወደ መንግሥት ሥልጣን የሚመጣው በህዝብ ድምጽ ስለሆነ ወደሥልጣን ያመጣውን 

ህዝብ መብት ረግጦ አንድም ቀን ሥልጣን ላይ መቆየት አይችልምና በተዘናጋባቸው ጉዳዮች ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ ያቀረበው 

ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ለማግኘት ጊዜ አይወስድበትም:: ምክንያት የህዝብ ጥያቄ የማይመልስ መንግሥት በቀጣዩ ምርጫ እዚያች 

ስልጣን ቦታ ድርሽ እንደማይል ስለሚያውቅ:: በኛ አገር እየሆነ ያለው ተቃራኒ ነገር ነው:: 

በጠመንጃ ሃይል ሥልጣን መቆናጠጡን ሊዘነጋ ያልቻለን ቡድን እርሱ ራሱ ለፈረንጆች ፍጆታ ሲል በየ5 አመቱ በሚያዘጋጀው 

የምርጫ ቲያትር ላይ ተገደን ስለተሳተፍን ብቻ የሥልጣን መሠረቱ የህዝብ ድምጽ በሆነበት አገር እንደሚሆነው "ድምጻችን 

ይሰማ " ብለን በመጮህ ለውጥ የምናመጣ እየመሰለን መጥቶአል::
ላላፈው አንድ አመት ተኩል እያነሳነው ያለነው " መንግሥት በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ አይግባ" ጥያቄ የሃይማኖት 

(የእምነት) ነጻነት ጥያቄ አካል ነው:: የሃይማኖት ነጻነት ደግሞ ዜጎች በአገራቸው በህግ ሊከበርላቸው ከሚገባቸው መብቶች 

አንዱ እንጂ ብቸኛው አይደለም:: ለምሳለ የዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብት ፤ የመጻፍ፤ የመሰብሰብ ፤ የመደራጀት፤ 

ተቃውሞ ሰልፍ የማድረግ የመሳሰሉት መብቶች ሳይከበሩ የሃይማኖት ነጻነት ተነጥሎ ሊከበር እንደማይችል እየገጠመን ካለው 

ችግር መረዳት ይቻላል::
የመንግሥትን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት እርምጃ ለማስቆም የተቃውሞ ድምጻቸውን በአደባባይ ያሰሙና ሠላማዊ 

ሠልፍ ያስተባበሩ ወንድሞቻችን ሃሳባቸውን በነጻነት ለመግለጽ ያደረጉት ሙከራ እንደወንጀል ተቆጥሮባቸው ከርቼሌ 

ከተወረወሩ ቦኋላ "ጀሃዳዊ አራካት" የሚል የፈጠራ ፊሊም ተቀነባብሮባቸው "ሽብርተኝነት" የሚል ታርጋ የተለጠፈላቸው ፡ 

የእምነት ነጻነት ሌሎች መሰረታዊ የፖለቲካ መብቶች ባልተከበሩበት ብቻውን ሊቆም ወይም ሊከበር አለመቻሉን አመልካች 

ነው:: ነጋ ጠባ እስኪሰለቸን ድረስ ስለ” ሽብርተኝነት” በመንግሥት ሚዲያዎች የሚላዘንብንም ህገመንግሥታዊ መብታችን 

የሆኑትን እነዚህን የማይነጣጠሉ መብቶቻችንን ለማፈን እንደሆነ አውቀናል:: "ድምጻችን ይሰማ" ብለው በቅርቡ በአርሲ 

አሳሳና በደሴ በወጡት ወገኖቻችን ላይ የተወሰደው ድብደባ ፤ግድያና እስራት በምርጫ 97 "በመረጥናቸው የህዝብ 

ተመራጮች እንመራ " ብለው ጥያቄ ባነሱት ዜጎቻችን ላይ ከተወሰደው ጭካኔያዊ እርማጃ የሚለይ አይደለም::

ስለዚህ ወያኔ የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም ሲል ጡንቻውን ተራ በተራ እያፈራረቀ አንድ ባንድ ከሚደፈጥጠን ጥያቄያችንና 

ዋንኛው የመታገያ መፈክራችን መሆን ያለበት በአገራችን የተሟላ የዜጎች መብት የሚያከብር መንግሥት በአስቸኳይ ቋቋም ! 

ነው:: ለዚህ ሁላችን በጋራ ከታገልን ክርስቲያን ፤ ሙስሊም፤ አይሁድ፤ ዋቄፋታ ፤ ወይም እምነት የሌለው ሁሉ አንድ ላይ 

አርነት ይወጣል :: ይህ ሲሆን እስከ ዛሬ የምንታወቅበት ችጋር፤ ኋላቀርነትና እፍትሃዊነት ተወግዶ በምትኩ ፍትህ፤ እኩልነትና 

ነጻነት የሰፈነበት የበለጸገችና የተከበረች አገር ይኖረናል::
አላህ አንድ ያርገን
ኢትዮጵያ አገራችንን ይጠብቅልን

በፖሊሶች የታፈኑ በርካታ ሙስሊሞች በጊዜያዊነት ከነበሩበት ኤግዚብሽን ማእከል በአውቶብስ ተጭነው ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ ነው፡፡

ዛሬ ከሰልፉ ላይ ታፍነው የተወሰዱ ሙስሊሞች በከፊሉ (ድምፃችን ይሰማ)

September 1, 2013

ዛሬ ከሰልፉ ላይ ታፍነው የተወሰዱ ሙስሊሞች አብዛኞቹ በኤግዝቢሽን
ማእከል ግቢ ውስጥና ከዋናው መድረክ ጀርባ ካለው የኢትዮጵያ የሰላም እና የልማት
ኢኒስቲትዩት ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡Ethiopian Muslims 1
ሙስሊሙ እየተነጠለ ሲወሰድ
በፖሊሶች የታፈኑ በርካታ ሙስሊሞች በጊዜያዊነት ከነበሩበት ኤግዚብሽን ማእከል በአውቶብስ ተጭነው ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ ነው፡፡

ጽንፈኞችን እና አሽባሪዎችን እንቃወማለን በማለት ሰልፍ የወሙት ሙሰሊሞች በቁጥጥር ከዋሉት በከፊሉ !!






በከፍተኛ የመንግስት አካላት ጭንቀት እና ውጥረት የተካሄደው ሰልፍ ተጠናቀቀ

በከፍተኛ የመንግስት አካላት ጭንቀት እና ውጥረት የተካሄደው ሰልፍ 

ተጠናቀቀ:;

ጅምሩም መጨረሻውም በውል ያልተለየው የዛሬው ሰልፍ ከፍተኛ ውጥረት የነገሰበት ነበር፡፤ህብረተሰቡ አክራሪነትን 

ለመቃወም ሙሉ እምነት እና ሞራሉ ያለው ቢሆንም በደረሰበት ግዳጅ እና ማስፈራሪያ በዝናብ ከቤቱ ተገዶ በመውጣቱ 

በተሳታፊው ላይ ድብርትን እና መሰላቸን አስከትሏል፡፤ተፈጥሯዊው የሆነውም ዝናብ ሰልፉ አንዲቀዛቀዝ እና ህዝቡ በሰልፉ 

ላይ ተገዶ መሰለፉን በውስጡ አንዲያማርር ከፍተኛውን ድርሻ ወስዷል፡::


ሰልፉ የተጠራበት አጀንዳ ታላቅ እና አገራዊ አጀንዳ ቢሆንም ህብረተሰቡ ላይ በተፈፀመበት የማስገደድ ተግባር ሰልፉ ላይ ውሃ 


ሊከልስበት ችሏል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙም ጉዳዩ ከማንም በፊት ይመለከተኛል በማለት በሰልፉ ላይ ተገኝቶ አክራሪነትን 

ለመቃወም ቢያስብም አብዛኛውን ሙስሊም ማህበረሰብ መንገድ በመዝጋት እንዳይካፈል አድርገውታል፡፡ የተካፈሉትንም 

ሙስሊሞች ህገ ወጡ የመጅሊስ ሹመኛ ንግግር ሲያቀርቡ ጆሯቸውን በመያዛቸው ካሉበት በደህንነቶች እየታፈኑ ተወስደዋል፡፤ 

እስካሁን ቁጥራቸው ከ 50 የሚበልጡ ሙስሊሞች ከህዝብ መሃል ታፍነው ተወስደዋል፡፤


ሰልፉ በመንግስት እንደሚካሄድ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ከባድ ቅሰቀሳ በሚዲያዎች እና ቤት ለቤት ቅስቀሳ ቢካሄድም በዛሬው 


|ዕለት ግን ሚዲያዎች የቀጥታ ስርጭት እንኳን ሳይሰጡት ቀርተዋል፡፡ፕሮግራሙ ስለመጠናቀቁ ከማብሰር ውጪ ሌላ ያሉት 

ነገር የለም፡፤ይህ የሚያሳው ሙስሊሙ ማህበረሰብ አክራሪነትን ለመቃወም በነቂስ እንደሚወጣ ጥሪ በመደረጉ በመንግስት 

በኩል ከፍተኛ ድንጋጤ በመፈጠሩ ነው፡፤ 


ሰላማዊ ሰልፍ ተብሎ በአካባቢው ግን የጦር አወድማ እስኪመስል በወታደር እና በጦርመሳሪያ አካባቢውን መጨናነቁ 


በመንግስት በኩል የተፈጠረውን መሸማቀቅ እና ፍርሃት ቁልጭ እርጎ ያሳየ ነበር፡፤ ህዝበ ሙስሊሙ በሰልፉ ላይ የሚሳተፍበትን 

ምክንያት ጥርት ባለ መልኩ ማስቀመጡ የሚታወስ ቢሆን ሰላም ወዳዱን ሙስሊም ማህበረሰብ በሰልፉ ላይ እሳተፋለው 

በማለቱ ብቻ ለማሸማቀቅ ተሞክሯል፡፤

የሰልፉ ስነ ስርአት መጀመሩ ከተነገረ ቡሃላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተገዶ ተሰላፊዎች ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሰልፉን 

በመተው ወደመጡበት ሲመለሱ ነበር፡፤ሰልፉም ከተተናቀቀ ቡሃላም በሰልፉ ላይ ተሳተፉ ሙስሊሞችን የማደኑን ስራ በከፍተኛ 

ሁኔታ ተጧጡፎ ቀጥሏል፡፡


ህዝበ ሙስሊሙ አክራሪነትን ከማንም በፊት እኛም እንቃወማለን በማለት በነቂስ ለመውጣት ለመሳተፍ መወሰናቸውን 


ከተገለጸ ቡሃላ በመንግስት ላ|ይ በተፈጠረበት ጭንቀት ብዙ የተደከመለት ሰልፍ ተሰላፊዎችንም አሰላችቶ በብርድ እና በዝናብ 

አስደብድቦ ያለምንም ትርፍ ተጠናቋል፡፤


ህብረተሰቡ አክራሪነትን ለመቃወም ሰልፍ ሲወጣ ይዞት ሊመለስ የሚችለውን ግንዛቤ በሙሉ በተፈጸመበት የማስገደድ እና 


የማስፈራራት እርምጃ ዜሮ አስገብቶታል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ እና ህዝበ ክርስቲያኑ መቼም ቢሆን በማንም ሴራ ሊለያዩ እና 

ሊከፋፈሉ እንደማይችሉ በዛሬው በትካዜ እና በቁዘማ መልክ በተካሄደው ሰልፍ ላይ አሳይተዋል፡፤

በመንግስት ብዙ የተዘፈነለት፣ብዙ ገንዘብ የተፈሰሰለት፣ብዙ የመንግስት ስራዎች ተበድለው ለዚህ ሰልፍ ቅስቀሳ በዋሉለት 


የተቃውሞ ሰልፍም ለመንግስት እራስ ምታት እና ውጥረት ብቻ ፈጥሮ ሚዲያዎቹም ከዚህ ቀደም ሲፎክሩበት የነበረውን ወኔ 

አጥተው ሰልፉ እንደደበዘዘ ተጠናቋል፡፤ 

TORTURE ONGOING ON BLUE PARTY MEMBERS RIGHT NOW:


TORTURE ONGOING ON BLUE PARTY MEMBERS 

RIGHT NOW:

Beating –on victim’s sensitive body parts, arms and legs 


mainly, some on head. Threatening to kill their families


A witness at 4 kilo stated he saw 15 police officers beat 

young females for approximately 15 minutes. Many of them 

had bruises on head, face, chest and shoulders when they 

were taken to imprisonment. Some of them are apparently 

placed in solitary confinement but we don't know who they 

are. Two persons were blindfolded and detainees forcing 

them to stand for prolonged periods; beating, punching, and 

hitting them with rubber hoses, whips, wooden planks or 

other objects. This is done by the order of the current Prime 

Minister Hailemariam Dessalegn and the TPLF cadres.


አረመኔው የሕወሐትና የደሕንነት ሹም Police Arrest Senior Intelligence Official Over Corruption


አረመኔው የሕወሐትና የደሕንነት ሹም

Police have arrested high-ranking Ethiopian intelligence official on allegations of corruption.
According to the Federal Ethics and Anti-corruption Commission, Woldeselassie Woldemichael, senior official of the nation's intelligence agency was arrested on graft charges.
He was charged with abusing public authority to accumulate wealth whose source is unclear.


የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ የነበረው ወ/

ስላሴ ወ/ሚካኤል ከያዘው ስልጣን መነሳቱን ምንጮች 

በመጥቀስ ከሁለት ወር በፊት ዘገባ አቅርበን ነበር። በጭካኔው 

የሚታወቀውና በሙስና የተነከረው ወ/ስላሴ በሙስና ዘብጥያ 

ወርዷል።


በእስር ቤት በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖችን ያሰቃይ የነበረው ወ/


ስላሌ ከበረሃ ጀምሮ በርካታ የድርጅቱን ታጋዮች በመረሸን 

እንደሚታወቅ ባለፈው ዘገባ መገለፁ ይታወሳል። በትግሉ ዘመን 

የፓርቲው አባለት « ፆታዊ ግንኙነት ስታደርጉ 

ተገኝታችኋል…» በሚሉና ሌሎች ተልካሻ ምክንያቶች 

እንዲረሸኑ በበላይ አመራር ውሳኔ የተላለፈባቸው በመቶዎች 

የሚቆጠሩ 

የፓርቲው አባላት (ታጋዮች) ለመግደል ይጣደፉ ከነበሩት 

መካከል ኢሳያስና ወ/ስላሴ ዋናዎቹ ነበሩ ።


አቶ መለስ ሁለቱን አባላት ወሳኝ በሆነው የደህንነት ቢሮ ቁልፍ ስልጣን የሰጧቸው « አድርጉ » የተባሉትን ያለማመንታት 


ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነበር። ወ/ስላሴ ስልጣን በጨበጠ ማግስት በአንድ ቀን አርባ የቢሮው 

አባላትን ( መኮንኖች ተብለው ነው የሚጠሩት) እንዳባረረ የገለፁት ምንጮቹ፣ በየጊዜው በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላትን « 

ተሃድሶውን አልተቀበላችሁም፣ የቅንጅት ደጋፊዎች ናችሁ..» በሚሉና ሌሎች ምክንያቶች ከማባረር - እስር ቤት 

እስከመወርወር የደረሰ እርምጃ ሲወስድ ቆይቷል።


ከመለስ ጋር በሃሳብ ያለተስማሙ ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናትን በገዛ መኖሪያ ቤታቸው በገመድ በማነቅና በስለት በማረድ 


የጭካኔ ተግባር ያስፈፀሙት ወ/ስላሴና ኢሳያስ መሆናቸውን ተገልጧል። በግፍ የተገደሉት የመገናኛ ሚ/ሩ አቶ አየነውና 

የቤተመንግስት የደህንነት ሹም አቶ ዘርኡ ናቸው።
መስከረም 2 ቀን 1996ዓ.ም የኢትኦጵ ጋዜጠኛን ቢሮው በማስጠራት ለሁለት ሰአት ያክል ካስፈራራው በኋላ እንደሚገድሉት 

ዝቶ አሰናበተው።

ጋዜጠኛው በ15 ቀን ውስጥ አቋሙን አስተካክሎ፣ የመረጃ ምንጮቹን አሳልፎ ካልሰጠ እንደሚገደል ነግሮ ያሰናበተው 


አረመኔው ወ/ስላሴ፣ መስከረም 20 ቀን 1996ዓ፣ም ሰባት የፌደራል ፖሊሶችን በማሰማራት ጋዜጠኛው የግድያ ሙከራ 

እንዲፈፀምበት አድርጓል። ፖሊሶቹ አካሉን ካጎደሉትና ክፉኛ ከደበደቡት በኋላ ድልድይ ውስጥ ወርውረት እንደሄዱ 

ይታወቃል። በ1997 እና 98 ዓ.ም በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተወሰደውን ጭፍጨፋ፣ እስርና ድብደባ ከጠ/ሚ/ሩ ትእዛዝ 

በመቀበል ተፈፃሚ ያደረገና ዋና ተዋናይ የነበረው ወ/ስላሴ፥ ዜጎች ያሰቃይበት ወደነበረው ማእከላዊ እስር ቤት ተወርውሯል። 

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)