Wednesday, November 2, 2016

2000 ብቻ ነበር የታሰሩት እነሱንም ፈትቻለሁ ይላል ሕዉሐት!



በኦክቶምበር 8 2016 በታወጀዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጀ ከታወጀ ጀምሮ የታሰሩት 2000 ብቻ እንደሆነና እነሱንም ሕዉሐት እንደለቀቃቸዉ አገር ቤት ባሉት ሚዲያዎች መግለጫ መሰጠቱን ዋሽንግተን ፖስት  አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስከትሎ 40 የበለጡ በኦሮሞ ማሕበረሰብ ብቻ መታሰሩ የተዘገበ ሲሆን አዲስ አበባንና ሌሎች የአማራዉን ማሕበረሰብ ጨምሮ ታፍሰዉ ወደ ማሰቃያ የተወሰዱት ኢትዮጵያዉያኖች ቁጥር 50 በላይ ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል።
ባለፈዉ እሑድ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተክትሎ ታስረዉ የነበሩትን 2000 ወጣቶች መፈታታቸዉን ለሚዲያዎች ሲገልፁ ሌሎች ቁጥራቸዉን ለመናገር ፈቃደኛ ባይሆኑም በወታደራዊ ማሰቃያዉ ካምፕ ዉስጥ የሚሰቃዩ እስረኞች እንዳሉ የገለፁት የመከላከያ ሚኒስትሩ አያይዘዉም አዲስ አበባ 1500 ሕጋዊ ያልሆኑ ጠብ መንጃዎችን መስብሰብ መቻላቸዉንም ገልፀዋል።
ከኢሬቻ እልቂት በኋላ በኦሮምያም ይሁን በአማራዉ አካባቢ መረጋጋት እንደሌለና በተቃራኒዉ በነዚህ ቦታዎች ችግሮች እየተበራከቱ መምጣታቸዉን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሰሞኑን ብቃት የለህም ተብሎ ከስልጣኑ የተገለለዉ ጌታቸዉ ረዳ ስልጣኑን ከመልቀቁ በፊት ሰኞ ዕለት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አሁን በኢትዮጵያ ያለዉን ችግር መፍትሔ ለመስጠት የኃይለማርያም ካቢኔ አዳዲስ ሚኒስትሮችን እንደሚመድብ ቢገልፅም አብዛኛዉን በተቃዋሚ በኩል ያሉት የፖለቲካ ሰዎች ግን ይህ በምንም ዓይነት በኢትዮጵያ ላይ የተጋረጠዉን ፈተና ሊመልስ የማይችል መሆኑን ይስማሙበታል። ሕዉሐት እዉነተኛ መፍትሔ ካሰበ መፍትሔዉ ሊሆን የሚችለዉ ስልጣኑን መልቀቅ ብቻ ነዉ የሚለዉ ሁሉንም የሚያስማማ ነዉ ሲሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።
የሕዉሐት ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ ሙላቱ ተሾመ ችግሩን ለመፍታት የፖለቲካ ተሃድሶ እንደሚደረግ ቢገልፅም የተካሔደዉ አዳዲስ ባለስልጣናትን በመሾም የተጠናቀቀዉ ይኸዉ ተሃድሶ ከድጡ ወደ ማጡ የተሔደበት መሆኑን ብዙዎች የሚስማሙበት መሆኑም ታዉቋል። 
ናትናኤል ኃይለማርያም

አባይ ሚዲያ

No comments: