የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በደረሱ ግጭቶች የሞቱ የቆሰሉና የደረሱበት የማይታወቅ ሰዎችን በሚመለከት አብዛኛዎቹን በማስረጃዎች በተደገፈ ከነፎቶግራፋቸዉ በሰንጠረዥ ይፋ አድርጎአል።
በመግለጫዉ ላይ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ የሰመጉ ዳይሬክተር አቶ ብፅዓት ተረፈ እንደተናገሩት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ለተቃዉሞ በወጡ ዜጎች ላይ በወሰዱት ከመጠን ያለፈ የኃይል ርምጃ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ጠፍቶአል በርካታ ሰዎች በጥይት ተመተዉ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ በርካታ ሰዎች ታስረዋል፤ ቁጥራቸዉ በዉል የማይታወቁ ሰዎች የደረሱበት አይታወቅም ከፍተኛ ኪሳራ ያስከተለ ከባድ የንብረት ዉድመት ደርሶአል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈዉ ሳምንት የግማሽ ዓመት ዘገባ ሲያቀርቡ ባደረጉት ንግግር በሃገሪቱ ዉስጥ በነበረዉ ተቃዉሞ ለተከሰተዉ ሞት ለፓርላማዉ ይቅርታ መጠየቃቸዉን አሶሲየትድ ፕረስ ዘግቧል። ሰመጉ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኘዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ
Source: DW
No comments:
Post a Comment