Monday, February 24, 2014

ስለ ማዕከላዊ እስር ቤት ይህንን ያውቁ ነበር?

ስለ ማዕከላዊ እስር ቤት ይህንን ያውቁ ነበር?

በማዕከላዊ በሚገኙት አራቱ ዋና የማሰሪያ ብሎኮች አሉ። ሆኖም በየብሎኩ ያለው ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ይለያያል፡፡ "ጨለማ ቤት" በመባል በሚታወቀው በጣም የከፋ ብሎክ የቀን ብርሃን እና የመፀዳጃ አገልግሎት ማግኘት በእጅጉ የተገደበ ነው። "ጣውላ ቤት" በሚባለው ብሎክ በተባይ የተወረረ ነው። እስረኞቹ ለመርማሪዎቹ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በሚያደርጉት ትብብር መሰረት በቅጣት ወይም በማበረታቻ መልኩ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውንና ሌሎች የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሊከለከሉ ወይም ሊፈቀዱላቸው ይችላል፡፡ ይህም ታሳሪዎቹን ከአንዱ ብሎክ ወደ ሌላ ማዘዋወርን ይጨምራል፡፡ "ሸራተን" በመባል ወደሚታወቀው ብሎክ ሌላው ቀለል ያለ ድብደባ እና አካላቸው በደም ተጨማልቆ በጣም ለደከሙ ማረፊያ ቦታና ለመዛወር የተሻለ የመንቀሳቀስ እድል ስለሚያስገኝ ከመፈታት ቀጥሎ እስረኞች እጅግ የሚናፍቁት ነገር ነው።

እስረኞ እርቃናቸው ሆነው እጆቻቸው ከግድግዳ ጋር ታስረው እንዲንጠለጠሉ ተደርጎ ለሶስት ሰዓታት ያለማቋረጥ ይደበደባሉ።

በጨለማ ቤት እና በጣውላ ቤት የሚታሰሩ እስረኞች በተለይ በመጀመሪያዎቹ የእስር ወቅቶች የህግ ጠበቃ እና ዘመዶቻቸውን እንዲያገኙ አይፈቀድላቸውም፡፡ የታሰሩ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ በየቀኑ ወደ ማዕከላዊ ቢሄዱም ምርመራው እስኪያልቅ በሚል ለተራዘመ ጊዜ ከእስረኞቹ ጋር ለመገናኘት ሃላፊዎቹ እንደማይቅዱላቸው የማይፈቀደው እስረኞቹ በስቅይ ብዛት ሰውነታቸው ስለተበላሽ ነው። በምርመራ ወቅት የህግ ጠበቃ አለመኖሩ ታሳሪዎቹ ላይ የሚፈፀመውን በደል እንዲጨምር ያደርጋል፣ በመርማሪዎቹ የሚፈጸሙ ጎጂ አያያዞችና ማሰቃየትን የሚመለከቱ መረጃዎች እንዳይመዘገቡ ያደርጋል።


No comments: