Tuesday, August 6, 2013

የህዝብ ወገን ማነው ?

Samsson Dechassa
***
የህዝብ ወገን ማነው ?

ሃውዜን ላይ ከሰላሳ ጫማ በተጣለ ቦምብ ደማቸው ለፈሰሰ ህጻናት ለሃያ አምስት አመታት እያለቀሰ ያለ መንግስት እንዴት በየአመቱ እና በየሰላማዊ ሰልፉ የሌሎችን ኢትዩጵያውያን ልጆች እንደ እንሰሳ በየሜዳው እያደነ ለመግደል የሚጨክን አንጀት ይኖረዋል? እንዴትስ ያለ ልብ ያለው ኢትዩጵያዊ ወገን ነው አልሞ ተኳሸ ነፍሰገዳዩች ከአዲስ አበባ እስከ አርሲ፣ ከዩንቨርስቲ እስከ አምልኮ ቤቶች ቅጥር ግቢ ኢትዩጵያውያንን እየታደኑ ሲገሉ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በንጹህ ህሊናው ማታ መተኛት የሚችለው? እነዚህ ያለፍርድ በየሜዳው በሰበብ ባስባቡ ደማቸው የሚፈስ ወገኖችስ የዝህች ኢትዩጵያ የምንላት ሃገር ልጆች አይደሉምን? የነሱ ደም በሃውዜን ከፈሰሰው ኢትዩጵያውያን ደም ይቀጥናል ወይንስ ይጠቁራል?

የአዲስ አባባ ዩንቨርስቲ ተማሪወች ሰልፍ ወጥተው ተገደሉሲባልጥጋበኖች ናቸው ይበላቸው “208 ወጣት፣ህጻናት እና አረጋውያን ምርጫ ተጭበረበረ ብለው ሲቃወሙ በየመንደሩ ተረሸኑየሚል ዜና ETV ሲሰማየታባታቸው ስራ ያጡ ቦዘኔወች ናቸው። እንኳን ተገደሉ “ 10 ሙስሊም ኢትዩጵያውያን በአሰላ መስጊድ ውስጥ በፌደራል ፖሊስ ተገደሉመባልን ሲሰማ ከዜና አንባቢው ቀድሞአክራሪወች ናቸው ይገባቸዋልእያለ ለሚፈስ ደም ሰበብ የሚሰጥ፣ ለሚጠፋ ህይወት ስም የሚያወጣ ወገን ወገንነቱ ምን ላይ ነው ?? ወገን ደማሁ፣ተገፋሁ፣በገዛ ሃገሬ ሰላም አጣሁ እያለ የሚሳቀቅ ህዝብን እና የመንግስት ያለህ ልጆቻችን በየአረቡ ሃገር ባደባይ እየታፈኑ ተገደሉ ብሎ የሚያለቅስን ወላጅ አሮሮ ጆሮ ዳባ ብሎእና መንገድ ሰርተናል፣ ህንጻ አቁመናል፣ ሌላውን ተውን፣የልማት መንግስት ነንእያለ በሌላውን በወገኑን ሰቆቃ የሚሳለቅ የሰው ፍጡር ወገንቱ ምኑላይ ነው?

አንድ አድሮጎ ያኖረን ምድርዋ በወገን እንባ እረጥቦ ሊሰነጠቅ እንደሚችል፣ ባንድ ላይ ስንለብሰነው የሚያሞቀን ባንዲራዋን የወገን ደም በልቶት ሳስቶ ሊቀደድ እንደሚችል፣ የምንኮራበት ታሪክዋ ግፍ በሰፈነበት ፖለቲካዋ በስብሶ ሊጠፋ እና ሊደበዝዝ እንደሚችል ማገናዘብ እንዴት ተሳነን? በቀልን ሰንቆ የሌሎች ወገኖቹን ታሪክ ስራዬ ብሎ ማጉደፍ፣ ትውልድን ባልዋላበት የበደል እና የግፍ አራጣ ማስከፈል እንደ ፖለቲካ እርዩት ተቆጥሮበምን ታመጣለህእብሪት ወገንን ማሳደድ ቂምን እንጂ ፍቅርን እና አንድነትን እንደማይወልድ ማወቅ ምነው ከበደን? ዛሬ በግፍ እና በጫና ጀርባው ደክሞ የተንበረከከ ወገን ነገ እግሩ ጠንቶ ሊነሳ እንደሚችል፣ ዛሬ ደሞ ጡንቻዬ ፈርጥሟል ብሎ ሌሎችን እየተጫነ ያለው ወገን ነገ ጉልበቱ ዝሎ መሬት ሊወርድ ነጋሪ ያሻል ወይ? ቂም እና በቀል የቁልቁለት እሩጫ ነው። ቁልቁል ቀድሞ የተንደረደረው ሲወድቅ በቂም ከኋላው ተንደርድሮ የሚመጣው በላዩ ላይ እየወደቀ መጨረሻ የሌለው የመከራ እና የሃዘን ወንዝ የማንንም ልጆች አይምርም፣ የቂም በቀል ውርስ ለዘር ማንዘሩ እና ለልጅ ልጆቹ ማስተላለፍ የሚፈልግ ከሃላችን የተረገመ እሱ ነው !!


No comments:

Post a Comment