Samsson Dechassa
***
የህዝብ ወገን ማነው ?
ሃውዜን ላይ ከሰላሳ ሺ ጫማ በተጣለ ቦምብ ደማቸው ለፈሰሰ ህጻናት ለሃያ አምስት አመታት እያለቀሰ ያለ መንግስት እንዴት በየአመቱ እና በየሰላማዊ ሰልፉ የሌሎችን ኢትዩጵያውያን ልጆች እንደ እንሰሳ በየሜዳው እያደነ ለመግደል የሚጨክን አንጀት ይኖረዋል? እንዴትስ ያለ ልብ ያለው ኢትዩጵያዊ ወገን ነው አልሞ ተኳሸ ነፍሰገዳዩች ከአዲስ አበባ እስከ አርሲ፣ ከዩንቨርስቲ እስከ አምልኮ ቤቶች ቅጥር ግቢ ኢትዩጵያውያንን እየታደኑ ሲገሉ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በንጹህ ህሊናው ማታ መተኛት የሚችለው? እነዚህ ያለፍርድ በየሜዳው በሰበብ ባስባቡ ደማቸው የሚፈስ ወገኖችስ የዝህች ኢትዩጵያ የምንላት ሃገር ልጆች አይደሉምን? የነሱ ደም በሃውዜን ከፈሰሰው ኢትዩጵያውያን ደም ይቀጥናል ወይንስ ይጠቁራል?
“የአዲስ አባባ ዩንቨርስቲ ተማሪወች ሰልፍ ወጥተው ተገደሉ” ሲባል “ጥጋበኖች ናቸው ይበላቸው”፣ “208 ወጣት፣ህጻናት እና አረጋውያን ምርጫ ተጭበረበረ ብለው ሲቃወሙ በየመንደሩ ተረሸኑ” የሚል ዜና በETV ሲሰማ “የታባታቸው ስራ ያጡ ቦዘኔወች ናቸው። እንኳን ተገደሉ”፣ “ 10 ሙስሊም ኢትዩጵያውያን በአሰላ መስጊድ ውስጥ በፌደራል ፖሊስ ተገደሉ” መባልን ሲሰማ ከዜና አንባቢው ቀድሞ “አክራሪወች ናቸው ይገባቸዋል” እያለ ለሚፈስ ደም ሰበብ የሚሰጥ፣ ለሚጠፋ ህይወት ስም የሚያወጣ ወገን ወገንነቱ ምን ላይ ነው ?? ወገን ደማሁ፣ተገፋሁ፣በገዛ ሃገሬ ሰላም አጣሁ እያለ የሚሳቀቅ ህዝብን እና የመንግስት ያለህ ልጆቻችን በየአረቡ ሃገር ባደባይ እየታፈኑ ተገደሉ ብሎ የሚያለቅስን ወላጅ አሮሮ ጆሮ ዳባ ብሎ “እና መንገድ ሰርተናል፣ ህንጻ አቁመናል፣ ሌላውን ተውን፣የልማት መንግስት ነን” እያለ በሌላውን በወገኑን ሰቆቃ የሚሳለቅ የሰው ፍጡር ወገንቱ ምኑላይ ነው?
አንድ አድሮጎ ያኖረን ምድርዋ በወገን እንባ እረጥቦ ሊሰነጠቅ እንደሚችል፣ ባንድ ላይ ስንለብሰነው የሚያሞቀን ባንዲራዋን የወገን ደም በልቶት ሳስቶ ሊቀደድ እንደሚችል፣ የምንኮራበት ታሪክዋ ግፍ በሰፈነበት ፖለቲካዋ በስብሶ ሊጠፋ እና ሊደበዝዝ እንደሚችል ማገናዘብ እንዴት ተሳነን? በቀልን ሰንቆ የሌሎች ወገኖቹን ታሪክ ስራዬ ብሎ ማጉደፍ፣ ትውልድን ባልዋላበት የበደል እና የግፍ አራጣ ማስከፈል እንደ ፖለቲካ እርዩት ተቆጥሮ “በምን ታመጣለህ” እብሪት ወገንን ማሳደድ ቂምን እንጂ ፍቅርን እና አንድነትን እንደማይወልድ ማወቅ ምነው ከበደን? ዛሬ በግፍ እና በጫና ጀርባው ደክሞ የተንበረከከ ወገን ነገ እግሩ ጠንቶ ሊነሳ እንደሚችል፣ ዛሬ ደሞ ጡንቻዬ ፈርጥሟል ብሎ ሌሎችን እየተጫነ ያለው ወገን ነገ ጉልበቱ ዝሎ መሬት ሊወርድ ነጋሪ ያሻል ወይ? ቂም እና በቀል የቁልቁለት እሩጫ ነው። ቁልቁል ቀድሞ የተንደረደረው ሲወድቅ በቂም ከኋላው ተንደርድሮ የሚመጣው በላዩ ላይ እየወደቀ መጨረሻ የሌለው የመከራ እና የሃዘን ወንዝ የማንንም ልጆች አይምርም፣ የቂም በቀል ውርስ ለዘር ማንዘሩ እና ለልጅ ልጆቹ ማስተላለፍ የሚፈልግ ከሃላችን የተረገመ እሱ ነው !!

No comments:
Post a Comment