Wednesday, July 10, 2013

ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲን ያለ ደም ማምጣት ይቻላል ወይስ?

 ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲን ያለ ደም ማምጣት ይቻላል ወይስ?
ያስተሰርያል
ምናልባትየጠፋውን ትውልድፖለቲካዊ ምኞት የሚወክል አንድ ነገር ጥቀስ ብባል መጀመሪያ ከሚመጡልኝ ነገሮች አንዱ የቴዲ አፍሮያስተሰርያልነው። የዚህ ዘፈን ልቀት ግጥሙ ወይም ዜማው አይመስለኝም፤ መልእክቱ ነው። አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ የምርጫ 97 መንፈስ ቀደም ሲል እንዳልኩት በመሆኑ ይፈልግ የነበረውስርየትንነበር፤ ደም የማይፈስበት ስርየት። አለመታደል ሆኖ መሣሪያውን የታጠቀው የፖለቲካ ቡድን ስርየትን ያለደም ማሰብ የማይችል ድንጉጥ አማኝ ነው፤ ስለዚህም ደም ፈሰሰ፣ ለዚያውምስርየትላያመጣ።

የነጻነትን እና የዴሞክራሲንስርየትያለ ደም መፍሰስ ማግኘት እንዳልቻለ የተመለከተውየጠፋው ትውልድበምርጫው ማግስት ብዙ ዋጋ ከፈለ። ይህን ተከትሎም እንደገና ወደ ጥንቸል ስጋቱ ተመለሰ። ኢሕአዴግም አገዘው፤ በአንድ በኩል ከጥቅማ ጥቅም ጋራ የተያያዘ የምልመላ ስትራቴጂ አምጥቷል፤ በሌላ በኩል ደግሞ በተቃዋሚነት ቀርቶ ብዙዎችን ሊያደራጅ በሚችል መልኩ የተለየ አስተያየት መያዝ የሚያስከፍለው ዋጋ ከፍ እንዲል አድርጓል። በቤተሰብ፣ በንግድ፣ በትምህርት ወዘተ ሐላፊነቶች የተያዘውየጠፋ ትውልድፖለቲካን በጥንቸላዊ ጥንቃቄ ወደማየቱ መመለሱ ወደ ቀደመ ቤቱ እንደመመለስ ነው። ነገር ግን የአሁኑ ዘመን የተለየ ነው፤ አፈናውን ማቅለልና ማለፍ የሚችልባቸው አማራጮች አሉ። ስለዚህም እንደ ደርግ ዘመን መንግሥት የሚለውን ብቻ የመስማት ግዴታ የለበትም፤ ፖለቲካዊ ተሳትፎውንም በተለያየ መልኩስሙን ሳይገልጽ፣ ድሙጹን ሳያሰማበለሆሳስ መቀጠል ችሏል።
የኢሕአዴግ አያያዝያለደም ስርየት የለምየሚለውን የብሉይ ሕግ የሚያጸና ሆኗል። ለታይታና ለዲፕሎማሲያዊ ፍጆታ ከሚሆነው በቀር እውነተኛ የዴሞክራሲ እና የመቻቻል ምልክቶች ጨርሰው ሊጠፉ የቀራቸው እጅግ ጥቂት ነው።ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲን ያለ ደም ማምጣት ይቻላል ወይስ አይቻልም?” የሚለውን ክርክር በድጋሚ የፖለቲካችን ቁልፍ አጀንዳ እያደረገው ያለውም ራሱ ኢሕአዴግ ነው።የጠፋው ትውልድተስፋውን አልጣለም፤ ከደርግ ጊዜ በተለየ ፖለቲካዊ ሐሳቡን በሰላምና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ማረመድ ስለመቻል አለመቻሉ ግን እርግጠኛ አይደለም። ስለዚህም በክርክሩ መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆሟል። በፖለቲካው ተስፋ ቆርጦ ሌላ ሕይወቱን ስለማሸነፍ ብቻ ለማሰብ የወሰነ አለ፤ ፖለቲካውን እንደ ትግል በማየት ተሳትፎውን የቀጠለ ጥቂት አለ፤ የሚከፍለውን ዋጋ በሚቀንስ መንገድ በዴሞክራሲ ግንባታ መሳተፍ የሚመኝ ነገር ግን መንገዱ ጠፍቶት ግራ የተጋባ አለ፤ ራሱን ኢሕአዴግን በመቀላቀል ጥቅማ ጥቅሞችን እያገኙ በዚያውም ከውስጥ ለውጥን መጀመር ይቻል እንደሆነ ብሎ የሚያስብም አይጠፋም የኢሕአዴግን አመራር እያደነቀሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባርየሚል የዚሁ ትውልድ አባል የማያውቅ ሰው ካለ አንዱን ድረ ገጽ ይጎብኝ።
የጠፋው ትውልድየሽግግር ዘመኖች ትውልድ ነው፤ ለዚያውም የከሸፉ ሽግግሮች። ይህ ጠቃሚ ጎኖች ቢኖሩትም ጉዳቶችም አሉት። አንዱ ጉዳቱ ትውልዱ በፖለቲካው ውስጥ አሻራውን የሚተውበት እድልና ጊዜ ማጣቱ ነው። ሆኖም ይህ ትውልድ ደርግ እና ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ መኖር ያልነበረባቸው፣ ድጋሚም መምጣት የሌለባቸው የፖለቲካ ስርአቶችና አመራሮች መሆናቸውን ኖሮ አይቷቸዋል። ይህ ትውልድ ሁሉንም ፖለቲካዊ ጽንፎች በአያቶላዎቹ ሲተነተኑ ሰምቷል፤ በፊት አውራሪዎቹ ሲተገበሩ አይቷል፣ ኖሯቸዋልም። ይህ ትውልድ የፖለቲካ ሐላፊነቱን ካልተወጣ አገራችን አዳዲስ ደርጎች እና አዳዲስ ኢህአዴጎችን ማስተናገዷ እንደማይቀር እሰጋለሁ። ያን ጊዜ ብዙ መንግሥቱዎች ወይም ብዙ መለሶች ይወሩናል፤ አያርግብንና! “የጠፋው ትውልድከዚህ ልምድ የሚቀስመው ትምህርት አገሪቱን ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚያሸጋገር ቀመር እና ፖለቲከኞች እንዲያፈራ ይረዳው ይሆን? እስከዚያ ድረስእንደ ጠፋትውልድ እንቆጥረዋለን፤ ልክ በጣም አልፎ አልፎ እንደምናገኘው ሰው፤ምነው ጠፋህ?” እንደማለት! አይዞን!
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ


ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

No comments: