የነጻ” አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሚዲያ
የእነዚህ
ሕጎች መጽደቅ
በዴሞክራሲ ማበብ
ተስፋ ላይ
ውኃ የቸለሱ
ሲኾን አቶ
መለስ ወደ
ሚፈልጉት የአንድ
ፓርቲ ፍጹም
አምባገነንነት ሥርዐት
ለመግባት ሕጋዊ
የሚመስል ጭብጦ
እና አለንጋ
መጠቀምን እንደ
አቅጣጫ አስቀምጧል።
የኢሕአዴግን ሐሳብ
የማይጋሩ ነጻ
ሚዲያዎች የኢኮኖሚያዊ
አቅማቸውን በመቆጣጠር፣
በማዳከም፣ እና
በማስፈራራት ለዘላቂው
እንዳያብቡ በእንጭጩ
የመከላከል ተግባር
ላይ ተጠምዷል።
አቶ በረከት
የሚመሩት የኮሚዩኒኬሽን
ጽ/ቤትም
ዋና ሥራ
ይህ ነው።
ከ2000 ዓ.ም በኋላ
ብቅ ያሉትን
የተለያዩ ጋዜጦች
አዲስ ነገር፣
አውራምባ ታይምስ
ከመሳሰሉ ጋዜጦች
የሁለት ገጽታ
ያለው ግንኙነት
ለመፍጠር ሞክሯል።
አንዳንድ
ጋዜጦች በተደጋጋሚ
ከፍትህ ሚኒስቴር
እና ከኮሚዩኒኬሽን
ጉዳዮች ቢሮ
በደረሰባቸው ማስፈራሪያ
ልካቸውን አውቀው
የተሸማቀቁ ሲኾን
የአዲስ ነገር
ጋዜጠኞች ደግሞ
ለስደት ተዳርገዋል።
ከመንግሥት ሚዲያ
ባሻገር “ልማታዊ
እና ዴሞክራሲያዊ
አስተሳሰብ የሚዲያ
ዕድል አጥቶ
እንዳይደርቅ ለመከላከል”
አዳዲስ ደጋፊ
የፕሬስ ውጤቶች
ወደ ገበያው
እንዲገቡ፣ በኢኮኖሚ
አቅማቸው ደካማ
የኾኑ ነባር
ሚዲያዎችን “ማቀፍ”
አዲሱ የኢሕአዴግ
የፕሬስ ኮንትራት
ውል ነው።
ባለፉት ጥቂት
ወራት በገበያው
ባይቀናቸውም የኢሕአዴግን
ሐሳብ የሚያቀነቅኑ
አዳዲስ ፕሬሶች
ወደ ገበያው
ጎራ ብለዋል።
አንዳንዶችም ነባር
ጋዜጦች በፊት
ከሚታወቁበት አሠራር
በመለወጥ “ልማታዊ”
ወደ ሆነ የአዘጋገብ
ዝንባሌ ውስጥ
እየገቡ ነው።
አንዳንዶችም የኢሕአዴግን
አሠራር ባይደግፉትም
ቢያንስ ተቃዋሚ
ሆነው ራሳቸው
ላይ አደጋ
መጋበዝ አይፈልጉም።
እጅግ ጥቂቶች
አሁንም ኤዲቶሪያል
ነጻነታቸውን ላለማስደፈር
እየታገሉ ነው።
ነጻው
ፕሬስ ተዳክሟል።እንዲያውም ጠፍቷል
ማለት ይቻላል፡ ይህች የኢሕአዴግ
ኢትዮጵያ ናት።
የነጻውን ፕሬስ
መዳከም የተመለከቱ
ታዛቢዎች ጀንበሯ
በነጻ ፕሬስ
ላይ አዘቅዝቃለችን?
ሲሉ ጥያቄ
ያነሳሉ። አንዳንዶች
ደግሞ “ጌታ
ኾይ ምልክቶቹ
እነዚህ ብቻ
ናቸውን?” ይላሉ።
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ
ኢትዮጵያ
በክብር ለዘላለም ትኑር!


No comments:
Post a Comment