Friday, June 26, 2015

አየር ሀይል ሃላፊዎች በዘረኝነትና በሙስና ተዘፍቀዋል ተባለ

ኢሳት ዜና (ሰኔ 18፥ 2007)
በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ባለው ዘረኝነትና አስተዳደራዊ በደል በመንገፍገፍ ከሰዊራቱ የሚለዩት የበረራ ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መገኘቱን እንዲሁም ሙስና በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱን የአየር ሀይል ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። በህገ-ወጥ የሰው ዘውውር የአየር ሀይል አባላት የታሰሩ መሆናቸውንም ለመረዳት ተችሏል።
በ2007 አ/ም ብቻ አስር የበረራ ባለሙያዎች ስርአቱን በመክዳትና ወደ እስር ቤት በመጋዝ ከአየር ሀይሉ የተለዩ ሲሆን ፤ በአየር ሀይሉ ውስጥ የሰፈነው የአንድ ብሄር የበላይነት ወደ መንደር እየወረደ ስለመሆኑም በአስረጂነት ይጠቅሳሉ። የምስራቅ አየር ምድብ ሙሉ በሙሉ በበላይነት የሚቆጣጠሩት የትግራይ ክልል ውቅሮ ተወላጆች እንደሆኑ ተጠቅሷል።
የአየር ምድብ አዛዥ ኮሎኔል አበበ ተካ፣ የዘመቻ መኮንን ኮሎኔል ሙሉ ገብሬ፣ የዊንግ አዛዥ ሻለቃ ጸጋኣብ ካሳ፣ የስኳድሮን አዛዥ መቶ አለቃ አማኑኤል ወ/ገብርኤል ሁሉም የውቅሮ ተወላጆች መሆናቸን ከአየር ሃይል ምንጭ መረዳት ተችሏል። በማእከላዊ ሆነ በአየር ምድብ ከምእራብ አየር ምድብ ውጭ በሁሉም የሃላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙት የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ፣ በተመሳሳይ ወደታች ወደ መንደር እየተሳሳሳቡ መሆኑንም ተመልክቷል።
በኢትዮጵያ አየር ሃይል ውስጥ ከአየር ምድብ አዛዦች ብቸኛ የሌላ ብሄር ተወላጅ የምእራብ አየር ምድብ አዛዥ ኮሎኔል ይልማ መርዳሳ ብቻ መሆናቸውን መረዳት ተችሏል።
በሙስና ረገድም ያለጠያቂ በዘረፋ ውስጥ የተዘፈቁት የህወሃት ታጋይ የነበሩ መሆናቸው የተገለጽ ሲሆን፣ በ 2006 አም SF-260 የተባለ የመለማመጃ አውሮፕላን ጥገና ተብሎ 1.5 ሚሊዮን ዶላር የወጣ ሲሆን፣ ጥገናው የተካሄደበት በሃገር ቤት ባለሙያና ቁሳቁስ ቢሆንም በዘረፋው የተጠረጠሩት አልተጠየቁም።
በተመሳሳይም በቀድሞ አየር ሃይል ኣዛዥ ሜጀር ጄነራል ሞላ ሃይለማሪያም ትእዛዝ በ 20 ሚሊዮን ብር መለዋወጫ እንዲገዛ ተወስኖ፣ በሳምንት ጊዜ ውስጥ በኪሳራ ተመልሶ እንዲሸጥ ሲደረግ የጠየቀ ሰው አልነበረም።
በኢትዮጵያ አየር ሃይል ውስጥ በሃላፊነት ቦታ ላይ ያሉት የህወሃት ታጋዮች፣ የመንግስት ሄሊኮፕተሮችን ሴቶችን ለማዝናናት እንደሚጠቀሙበትና፣ አብራሪዎችም ለዚህ ተግባት ተመድበው ሲሰሩ መቆየታቸውን የአየር ሃይል ምንጮቻችን ይገልጻሉ።
በአሁኑ ወቅት ግንቦት ሰባትን ልትቀላቀሉ ስትሉ ተደርሶባችኋል በሚል ከታሰሩት አብራሪዎች አንዱ፣ የአንድን ባለስልጣን ወዳጅ ከደብረዘይት ወደባህርዳር፣ ከባህርዳር ወደአዋሳ እንደሚያመላልስ ለ10 ቀን ግዳጅ ተሰጥቶት ይህንኑ ሲፈጽም መቆየቱን ምንጮች ያስታውሳሉ። የትራስፖርት ሄሊኮፕተር በተለይ ወደሶማሊያ ሄደው ሲመለሱ የኮንትሮባንድ እቃ ጭነው የሚመለሱ ሲሆን፣ ንብረትነቱ የበረራ ሃላፊዎች ይሆናል።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል በላስልጣኖች ኮንትሮባንድን ጨምሮ በልዩ ልዩ ሕገወጥ ተግባሮች በሙስና ሲዘፈቁ፣ በተዋረድ ያለ ግለሰብም በህገወጥ የሰዎች ማዘዋወር ድርጊት ተሳታፊ በመሆን፣ እንደአቅማቸው ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ ለኢሳት የደረሰው ማስረጃ ያስረዳል።
በዚህ ድርጊት ተዋናይ ናቸው የተባሉ መቶ አለቃ ዳንኤል ገ/መድህን፣ መቶ አለቃ ተክሌ አብርሃ የተባሉ የህወሃት አባላት፣ ከደላሎቹ ጋር የታሰሩ ቢሆንም፣ በኮሎኔል አበበ ተካ ጣልቃ-ገብነት ሁለቱ በነጻ ሲለቀቁ ደላላው 20 ኣመት ተፈርዶበታል።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከ ምርጫ 1997 ወዲህ ከ 30 የሚበልጡ አብራሪዎች የከዱት ሲሆን፣ በ 2007 አም ብቻ ከስርአቱ የተለዩትና የታሰሩት ደግሞ 10 ያህል መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። ባለፈው ታህሳስ MI-35 ሄሊኮፕተር ይዘው ሁለት አብራሪዎችና አንድ ቴክኒሺያን መክዳታቸው ይታወቃል።
ሌሎች አምስት አብራሪዎች ማለትም መ/አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ መ/አለቃ ዳንኤል ግርማ፣ መ/አለቃ ብሩህ አጥናዬ፣ መ/አለቃ አንተነህ ታደመ ደግሞ ስርኣቱን ከድታችሁ ግንቦት ሰባትን ልትቀላቀሉ ኣስባችኋል በሚል ታስረዋል።

የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እየታደኑ እየታሰሩ ነው

• ከታሳሪዎቹ መካከል ሶስቱ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ናቸው
በአማራ ክልል የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በአዲስ መልክ እየታደኑ እየታሰሩ መሆኑን የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በምዕራብ ጎጃም ዞን ወንበርማ ወረዳ ከትናንት ሰኔ 18/2007 ዓ.ም ጀምሮ የሰማያዊ፣ የቀድሞው አንድነትና የመኢአድ አመራሮች እየታደኑ እየታሰሩ መሆኑ ታውቋል፡፡ ትናንት ሰኔ 18/2007 ዓ.ም የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው አዳነ አለሙ እና የመኢአድ አመራር የነበረው አቶ አበባው የተባለ ግለሰብ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ ሰኔ 19/2007 ዓ.ም በወንበርማ ወረዳ ሸንዲ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ የተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የነበረው አቶ ፈንታሁን ብዙአየሁና አንድ የቀድሞው አንድነት አመራር ከወንበርማ እንዲሁም በአዴት የሰማያዊ ፓርቲ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው አቶ ሞላ የኑስ መታሰራቸው ታውቋል፡፡
ሁለቱም የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ያለ አግባብ በዕጩነት ተሰርዘናል በሚል ክስ መስርተው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረዛቸው አግባብ አለመሆኑን ወስኖ ወደ ዕጩነት ሲመልሳቸው የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ከዕጩነት እንዲሰረዙ አድርጓል፡፡ አቶ ፈንታሁን ብዙአየሁ እና አዳነ አለሙ እነሱን ጨምሮ ሌሎች የተሰረዙ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ወደ ዕጩነት እንዲመለሱ ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ተገልጾአል፡፡
በተጨማሪም በምስራቅ ጎጃም ዞን የቀድሞ አንድነት አስተባባሪ የነበሩት አቶ ልዑልሰገድ እምባቆም በደብረማርቆስ ከተማ ፖሊስ መያዛቸው ታውቋል፡፡ አቶ ልዑልሰገድን ዛሬ ሰኔ 19/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ የያዛቸው የደብረማርቆስ ፖሊስ እስከ ቀኑ 5 ሰዓት ደብረማርቆስ ከተማ ውስጥ ካሰራቸው በኋላ ‹‹የያዝነህ እኛ አይደለንም፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ይፈልግሃል!›› በሚል ወደ ባህርዳር ከተማ ወስዷቸዋል ተብሏል፡፡
በየ አካባቢው በፖሊስ የተያዙት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ለጥቂት ጊዜ በየአካባቢያቸው እስር ቤቶች ከቆዩ በኋላ ወደ ባህርዳር ከተማ መዛወራቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በጥቅምት ወር 2007 ዓ.ም መጀመሪያ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የመኢአድ አመራሮችና አባላት ከየ ክፍለ ሀገሩ ተይዘው መታሰራቸው ይታወቃል፡፡

Thursday, June 25, 2015

በአዲስ አበባ ፖሊሶች ላይ የሚደረገው ግምገማ ከባድ መሆኑን ምንጮች ገለጹ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንም አይነት መረጃ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግበት ከሰኔ አንድ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አዘጋጅነት የተጀመረው ግምገማ ፈታኝ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ግምገማውን ተከትሎ አንዳንድ ፖሊሶች በደህንነቶች ተደብድበዋል። በጉለሌ ክፍለከተማ መምሪያ ስር የሚገኙ አንድ የሳጅን ማእረግ ያለውና አንድ ተራ ፖሊስ የአቶ አንዳርጋቸውን ፎቶ ሞባይላቸው ላይ ተገኝቶባቸዋል እንዲሁም የግንቦት7 ደጋፊዎች ናቸው ተብለው ከተገመገሙ በሁዋላ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግባቸው ተወስኗል። ከግምገማው በሁዋላ ሳጅኑ በቀጥታ በቁጥጥር ስር ውሎ በደህንነት ሃይሎች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመበት ምርመራ ሲካሄድበት፣ ኮንስታብሉ ፖሊስ ግን በሌሎች ባልደረቦቹ ድጋፍ አምልጧል።ይህንን ተከትሎም ፖሊስ የማደኛ ትእዛዝ ከ ፎቶግራፍ ጋር በመያያዝ ሰርኩላር ደብዳቤ ቢበትንም ኮንስታብሉ ግን እስካሁን አልተያዘም። የኮንስታብሉ ማምለጥ ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓም በጉለሌ ፖሊስ መምሪያ ግምገማ ላይ የቀረበ ሲሆን፣ ግምገማውን የመራው ታጋይ ኮማንደር ወጋየሁ ወይም በቅጽል ስሙ ጦና ፣ አዲሱ ገበያ እየተባለ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ የሆነው ኮማንደር አብደላ እንዲሁም የሰው ሃይል አስተዳደር ሃላፊ ሳጅን ቢኒያም ፣ ለኮንስታብሉ መሰወር ተጠያቂዎች ናቸው በሚል በሁለቱም ላይ ጥብቅ ግምገማ እንዲደረግ ትእዛዝ አስተላልፏል። ግመገማውን ተከትሎ በሁለቱ ፖሊሶች ላይ ከባድ ቅጣት ሊጣል እንደሚችል ምንጮች ገልጸዋል። ግምገማው ጥብቅ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ አልተጠበቁ መረጃዎች እንዲወጡ ጫና ሲደርግና የስለላ ስራ ሲሰራ ቆይቷል። ሆኖም መንግስት የተፈለገውን መረጃ እስካሁን ሊያገኝ እንዳልቻለ ምንጮች ገልጸዋል። ከምርጫ 97 ጀምሮ በአዲስ አበባ ፖሊስና በመንግስት መካከል መተማመን አይታይም። በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌንና የሌሎች ተቃዋሚ መሪዎች ፎቶዎች እንዲሁም የመብት ጥያቄዎችን የሚያቀነቅኑ ዘፈኖችን በሞባይላቸው አስቀምጠው ከተገኙ በሁዋላ፣ በመንግስት በኩል ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል። የአሁኑ ግምገማም ይህንኑ ተከትሎ የመጣ ነው። ግምገማው በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መካሄዱ ነው። አምና ሁሉም ፖሊሶች የፖለቲካ ስልጣና እንዲሰጣቸው ተደርጎ ነበር። በ10 ክፍለ-ከተማዎች የሚደረገውና ሰኔ 20 የሚጠናቀቀው ግምገማ በኮሚሽን ደረጃ ፣ በሃይል መድረክ እየተባለ እንደገና ይቀጥላል።

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ ዙሪያ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው የህግ ድጋፍ በማያገኙበትና ይግባኝ ሊጠይቁ በማይችሉበት ሁኔታ በአስከፊ ሁኔታ መታሰራቸውን የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሀሞንድ አውግዘዋል።
የአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ እና ደህንነት እንደሚያሳስበን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ብንገልጽም ከቃል ያለፈ መልስ አለገኘንም፣ የምክር እና ራሳቸውን መከላከል የሚችሉበት መብትም አላገኙም ሲሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በተደጋጋሚ ለቀረበው ጥያቄ ኢትዮጵያ መልስ መንፈጓ ከፍተኛ ዋጋ በሚሰጠው የእንግሊዝና የኢትዮጵያ ግንኙነት ላይ ጥላ አደጋ ያስከትላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ የህግ ድጋፍና ምክር እንዲያገኙ፣ በቤተሰቦቻቸውም እንዲጎበኙ መንግስት እንዲፈቅድ ለቴዎድሮስ አድሃኖም መናገራቸውንም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ባወጠው መግለጫ ጠቅሷል።
አቶ አንዳርጋቸው በየመን ተላልፈው ከታሰሩ ልክ አንደኛ ዓመት መሆናቸውን አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ በአዲስ አበባው መንግስት የተወሰደው እርምጃ ተቀባይነት እንደሌለው በግልጽ ያመላከተ ነው ተብሏል።
የውጪ ጉዳይ ቢሮው ጉዳዩን ከዲፕሎማሲያው ልውውጥ በላይ በማድረግ ለአደባባይ ማብቃቱን ዘጋርዳያን ዘግቧል።
ከእንግሊዝ መንግስት ከፍተኛ እገዛ የሚያገኘው ኢህአዴግ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለሰጡት ማስጠንቀቂያ የሰጠው መልስ በመግለጫው አልተጠቀሰም።
ኢህአዴግ በውጭ ሃይሎች ግፊት እንደማይንበረከክ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። አቶ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት የኢህአዴግን እጅ ሊጠመዝዙ የሚፈልጉ ሁሉ ገንዘባቸውን ይዘው በሊማሊሞ መሄድ ይችላሉ ብለው ነበር።
Source: Ethsat

UK tells Ethiopia its treatment of opposition official imperils ties

The British government told Ethiopia on Thursday its treatment of an imprisoned opposition figure, who is also a British national, was unacceptable and that the case risked hurting ties between the two countries.
Andargachew Tsige was sentenced to death in 2009 in absentia over his involvement with an opposition political group and another trial handed him life behind bars three years later. He was arrested in Yemen in 2014 and extradited to Ethiopia.
British Foreign Secretary Philip Hammond said on Thursday he had discussed the matter with Tedros Adhanom Ghebreyesus, his Ethiopian counterpart, and delivered a stern message.
"I am deeply concerned that, a year after he was first detained, British national Andargachew Tsige remains in solitary confinement in Ethiopia without a legal process to challenge his detention," Hammond said in a statement after the call.
"I am also concerned for his welfare and disappointed that our repeated requests for regular consular access have not been granted, despite promises made."
Britain summoned Ethiopia's chargé d'affaires in August last year to seek assurances that Tsige would not be put to death.
Secretary-general of the Ginbot 7 political group, he was among 20 opposition figures and journalists charged with conspiring with rebels, plotting attacks and attempting to topple the government.
Hammond said Britain's ties with Ethiopia were at risk.
"Ethiopia's failure to grant our repeated and basic requests is not acceptable," he said. "The lack of progress risks undermining the UK’s much valued bilateral relationship with Ethiopia."

(Reporting by Andrew Osborn; Editing by Stephen Addison)
Source: Reuters

እነ ወይንሸት ሞላ ላይ ድጋሜ የቀረበውን መዝገብ ዳኞች አንቀበልም አሉ

በእነ ወይንሸት ሞላ የክስ መዝገብ መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ በእስር ላይ የሚገኙት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለወርቅ ላይ ፖሊስ በድጋሜ ያቀረበውን የምርመራ መዝገብ ዳኞቹ አንቀበልም ብለዋል፡፡
እነ ወይንሸት ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ቀርበው እንዲፈቱ ተወስኖ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ፖሊስ ከእስር ሲወጡ በር ላይ በድጋሜ አስሮ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዳቸው ይታወቃል፡፡
ዛሬ ሰኔ 18/2007 ዓ.ም ቀደም ብለው ተከሰውበት በነበረው ተመሳሳይ ‹ወንጀል› ፖሊስ የምርመራ መዝገብ ይዞ ቀደም ብለው ውሳኔ ባገኙበት በተመሳሳይ ቄራ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበር ቢሆንም ዳኞቹ ‹‹እኛ ፈርደናል፤ እንዲለቀቁም ወስነናል፣ ከዚህ በኋላ ይህን ጉዳይ አናይም›› በሚል መዝገቡን እንደማያዩ ገልጸው መልሰዋቸዋል፡፡
ፖሊስ ፍርድ ቤቱ ክሱን እንደማያይ ከገለጸ በኋላ እነ ወይንሸትን ወደ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የመለሳቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ እንዲፈቱ የወሰነላቸው አራቱም እስረኞች ጉዳይ ምን ሊሆን እንደሚችል ግን ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አልታወቀም፡፡

የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ የጉብኝት በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ተቃውሞ አስነሳ

ኢሳት ዜና (ሰኔ 17 2007)
በቀጣዩ ወር በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ተቃውሞ እንደገጠማቸው የእንግሊዙ ዘጋርዲያ ጋዜጣ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ዛሬ ረቡእ ዘገበ።
አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፕሬዚዳንቱ በሰብአዊ መብት ረገጣና አፈና የምትታወቅ ሃገርን ለመጎብኘት መወሰናቸው ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ላይ መሆናቸውንም ጋዜጣው አስነብቧል።
የፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስደንጋጭ ዜና ሆኗል ያለው የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ተቋማቱ የኦባማ ጉብኝት ጨቋኝ ለሆነው የኢትዮጵያ መንግስት የተሳሳተ መልእክት ሊያስተላልፍ እንደሚችል ስጋት እንዳደረባቸው አመልክቷል።
የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬዚዳንቱ የምስራቅ አፍሪካ ጉብኝት በቀጠናው ስላለው የኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የዲሞክራሲ ተቋማትና የደህንነት ሁኔታዎች እንዴት መጠናከር እንዳለበት ያለመ መሆኑን ገልጿል።
ይሁንና ፕሬዚዳንቱ በሰብአዊ መብት ረገጣዋ የቆየ ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያ መጎብኘታቸው ተገቢ አለመሆኑን በርካታ ድርጅቶች በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ከእንግሊዙ ጋዜጣ በተጨማሪ ሌሎች አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ዘግበዋል።
የሂዉማን ራይትስ ዎች ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኬኔት ሮስ አሜሪካ በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማካሄዱዋ ተገቢ አለመሆኑን እና በተዘዋዋሪ እውቅና የመስጠት ድርጊት ተደርጎ እንደሚታይ ገልጸዋል።
ፍሪደም ሃውስ የተሰኘ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጀት በበኩሉ ኢትዮጵያ ሁሉንም የተቃዋሚ ድርጅቶች ከፖለቲካ ተሳትፎ ዉጭ አድርጋ ባለበት ወቅት ፕሬዚዳንቱ በሃገሪቱ ጉብኝት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን አስታውቀዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ሰፊ ረፖርትን ያወጣው ግሎባል ቮይስ የተሰኘ አለም አቀፍ ድርጅት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሊጎበኟቸው ካቀዷቸው ሃገራት መካከል የኢትዮጵያው ጉብኝት ከፍተኛ ተቃውሞ ማስነሳቱን ገልጸዋል።
ተቃውሟቸውን በማቅረብ ላይ የሚገኙት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፕሬዚዳንቱ ከጉብኝታቸው እንዲታቀቡ ጥያቄ በማቅረብ ላይ መሆናቸውንም ግሎባል ቮይስ በሪፖርቱ አመልክቷል።
በቀጣዩ ወር የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ጉብኝታቸውን የሚያድርጉት ኦባማ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት እና ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።