Friday, April 25, 2014

በማንነት ጥያቄ የተወጠረው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሽናል እግር ኳሰኛ ቤተሰቦቹን ማግኘት ይሻል

ይሁን በሕፃናት ማሳደጊያ በነበረበት ወቅት
በሙሉ ስሙ ሲሞን ይሁን ስቶለን ማርኬንግ በመባል የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በኖርዌይ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ትራኤፍ ለሚባል ክለብ በአጥቂነት በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ በ2009 በወጣት ቡድን ደረጃ የእግር ኳስ ተጫዋችነት ሕይወትን አሀዱ ብሎ ወደጀመረበት ትራኤፍ ክለብ ተመልሶ በመጫወት ላይ የሚገኘው ይሁን በኖርዌይ ፕሪምየር ሊግ (ቲፐሊጋ) ላይ በሚወዳደረው ሞልደ ክለብ ውስጥም ለአስር ወር የቆየበትን ዕድል አግኝቶ ነበር፡፡ ሞልደ በቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ድንቅ አጥቂ እና በአሁኑ የካርዲፍ ሲቲ አሰልጣኝ ኦሌጉናር ሶልሻየር እየተመራ የቲፐሊጋው ሻምፒዮን መሆን የቻለ ትልቅ ክለብ ነው፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወጣት በ2010 በሞልደ እያለ ለኖርዌይ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተመርጦ ከጀርመን ጋር በተደረገ አንድ ጨዋታ ላይ መሰለፍ ችሏል፡፡ ሶልሻየር ክለቡን ከያዘ ከጥቂት ግዜ በኋላ በውሰት በወቅቱ በሁለተኛ ዲቪዚዮን ይወዳደር ለነበረው (በዓመቱ መጨረሻ ወደ አንደኛ ዲቪዚዮን አድጓል) ክርስቲያንሱንድ ክለብ በውሰት የተሰጠ ሲሆን ክለቡ ወደአንደኛ ዲቪዚዮን ካደገ በኋላም በቋሚነት አስፈርሞታል፡፡
በ2013 የውድድር ዓመት በክርስቲያንሱንድ ክለብ ውስጥ በአብዛኛው ተጠባባቂ ሆኖ መጀመሩ ያላስደሰተው ይሁን ዘንድሮ በብዙ ጨዋታዎች ላይ የመሰለፍ ዕድል ለማግኘት ሲል በሁለተኛ ዲቪዚዮን ወደሚወዳደረው የመጀመሪያ ክለቡ ትራኤፍ ተመልሷል፡፡ ይሁን የሚጫወትበት የኖርዌይ ሁለተኛ ዲቪዚዮን የ2014 የውድድር ዓመት ባለፈው ሰኞ የተጀመረ ሲሆን ክለቡ ትራኤፍ ከሜዳው ውጭ ከሮዘንበርግ 2 ጋር ባደረገው ጨዋታም 1-1 በመለያየት ዓመቱን ጀምሯል፡፡ በሞልደ እያለ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ሲሳተፍ ለነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ፍላጎቱን በወኪሉ በኩል ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቅርቦ እንደነበረ የጠቀሰው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ተጫዋች ከፌዴሬሽኑ ጋር የነበረው ግንኙነት በመሀል በመቋረጡ ፍላጎቱን እውን ማድረግ አለመቻሉንም አሳውቋል፡፡ ‹‹ወደኖርዌይ ያቀናሁት እ.አ.አ በ1995 (ከዛሬ 19 ዓመት በፊት) ገና የሁለት ዓመት ልጅ እያለሁ አምባ ከሚባል ሕፃናት ማሳደጊያ በጉዲፈቻ ተሰጥቼ ነበር›› የሚለው ይሁን በአሁኑ ሰዓት በአዕምሮው ውስጥ ለሚመላለሰው የማንነት ጥያቄ ምላሽ የማግኘት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንደሆነ እና የዘንድሮው የውድድር ዓመት ሲጠናቀቅም ለዚሁ ጉዳይ ወደኢትዮጵያ የመምጣት ዕቅድ እንዳለው ለEthiotube.net በሰጠው አስተያየት ገልጿል፡፡‹‹በ1995 ዓ.ም (በኢትዮጵያ 1987) ወደኖርዌይ ከመጣሁ ወዲህ ወደኢትዮጵያ ተመልሼ አላውቅም፡፡ ያን ግዜ ገና የሁለት ዓመት ልጅ ስለነበርኩም ምንም አይነት መረጃ አልነበረኝም፡፡ ትክክለኛ መረጃ ወይም ሰዎች ዝም ብለው የፃፉት መሆኑን ባለውቅም የልደት ሰርተፊኬቴ ላይ የትውልድ ከተማ ጅማ ይላል፡፡ ሰዎች ተመልክተውት እንዲያስታውሱኝ ቢረዳኝ ብዬ በሕፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ሳለሁ የተነሳኋቸውን ፎቶዎች ይዣለሁ፡፡ ቤተሰቦቼን ፈልጌ ለማግኘት ያለኝ ተስፋ ዝቅተኛ ቢሆንም ፍለጋውን አድርጌ ቁርጤን እስካላወቅኩ ድረስ አዕምሮዬ እረፍት አያገኝም፡፡ ፎቶዬን ተመልክቶ የሚያስታውሰኝ ሰው ቢገኝ ጥሩ እገዛን ያደርግልኛል›› ያለው ይሁን በጉዲፈቻ ስለተሰጠበት ሁኔታ ሲገልፅም ‹‹ለኖርዌያውያኑ አሳዳጊዎቼ ልሰጥ ስል ሜይ 25/1995 (ግንቦት 17/1987 ዓ.ም) በፎርም ቁጥር 75 አዲስ ልሳን ጋዜጣ ላይ ተቃዋሚ ካለ የሚል ማስታወቂያ ወጥቶ የነበረ ቢሆንም ተቃዋሚ ሆኖ የቀረበ ሰው አልነበረም፡፡ የዛን ግዜ ይጠሩኝ ነበረው ይሁን ብለው ነው፡፡ ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት በህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ የቆየሁት ለስድስት ወር ብቻ የነበረ መሆኑ ከዛ በፊት ቤተሰብ እንደነበረኝ የሚጠቁም ነው፡፡ ስያሜው እስካሁን ድረስ ተመሳሳይ ስለመሆኑ እርግጠኛ ባልሆንም የነበርኩበት ማሳደጊያ ካልተሳሳትኩ ‹አምባ› የሚባል እና በፎቶው ላይ አቅፋኝ የምትታየው አሰፋሽ የምትባል ሰው የምታስተዳድረው ነበር›› ብሏል፡፡ ይሁን ስለኋላ ታሪኩ የሚያውቀው ካደገ በኋላ ጠይቆ የተረዳቸውን ጥቂት ነገሮች ብቻ መሆኑ ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቹን የማግኘት ዕድሉን የጠበበ እንደሚያደርግበት ቢያስብም ‹‹እግዚአብሔር ከፈቀደ የማይሆን ነገር የለም›› ብሎም ያምናል፡፡ ዘንድሮ በዝቅተኛ ዲቪዚዮን ውስጥ ቢጫወትም በብዙ ጨዋታዎች ላይ የመሰለፍ ዕድልን በማግኘት ብዙ ጎሎችን ማስቆጠርን እና ወደተሻለ የብቃት ደረጃ መሸጋገርን የሚያልም ሲሆን በዓመቱ መጨረሻም ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቹን የማግኘት ፍላጎቱ እንዲሳካለት በትንሹ ተስፋ ያደርጋል፡፡
* ከዚህ ዜና ጋር የተያያዙትን የልጅነት ፎቶዎቹን ተመልክታችሁ የምታስታውሱትና መረጃ ልትሰጡት የምትፈልጉ ካላችሁ በሞባይል ቁጥር 0920550862 ደውላችሁ ልትተባበሩት ትችላላችሁ፡፡
http://www.ethiotube.net

Ethiopia Prison Alert: Journalist in danger – An Urgent Appeal from Professor Mesfin Woldemariam

To

The UN Human Rights Commission
The African Union Human Rights Commission
The International Red Cross
Amnesty International
Human Rights Watch &
All Men and Women of GOOD WILL
Reeyot Alemu is a budding Ethiopian poet, essayist, and journalist. There are not many Ethiopians of her caliber inside the country. She has been languishing in the famous Ethiopian Prison in Qalliti for almost three years. She was charged of terrorism, a crime she totally abhors. She was sentenced first for eighteen years but later reduced to three.Reeyot Alemu is a budding Ethiopian poet, essayist, and journalist.
With the exception of her mother and father, she is not allowed to communicate with anyone, including her sisters, brothers as well as her fiancée.
Reeyot, although constantly in agonizing pain and in need of help, is held in solitary confinement with a very old and sickly foreign woman who herself requires assistance.
Reeyot is suffering from some growth in her breasts. The prison authorities have been reluctant to take her to hospital for medical checkup, even when her parents were prepared to pay the bill. When she became seriously ill she was allowed to see a doctor as a result of which she was taken to the hospital and operated upon. But no sooner had the surgeon finished the operation than she was immediately taken back to prison even before she had fully recovered from the Anastasia.
She now suffers from a relapse on the operated breast and similar growth in her other breast. The prison authorities still demonstrate their reluctance to provide medical treatment even at the expense of her parents.
May God provide the necessary courage to all those institutions and organizations to cry out effectively for this young lady who is suffering at the hands of insensitive prison administration.
Mesfin Woldemariam
http://ecadforum.com/

Thursday, April 24, 2014

አስፈላጊው ለውጥ ፣ መጭው ምርጫና የተቃዋሚዎች “መሳተፍ” ጉዳይ

አስፈላጊው ለውጥ ፣ መጭው ምርጫና የተቃዋሚዎች “መሳተፍ” ጉዳይ

(ናትናኤል ካብትይመር ኖርዌይ)
ethiopian_election_ballot_box



የሰው ልጅ ግላዊና ማህበራዊ ህይወቱን ለማሻሻል እንዲሁም የለት ተለት ህይወቱን የተሻለ ለማድረግ በአካባቢው ወይም በሚኖርበት ሃገር ያለውን አካባቢያዊና መንግስታዊ ስርዓት ጤናማ መሆኑ ግድ ነው። የማህበረሰቡም የለት ተለት ህይወት ከግዜ ወደ ግዜ አስቸጋሪ እየሆነ ሲሄድ የዛ ማህበረሰብ መንግስት ወይም አገዛዝ መቀየሩ አንደኛው መፍትሄ ነው። እንደሁለተኛ አማራጭ መፍትሄ  የሚወሰደው ደግሞ የነበረውን አገዛዝ ለአነስተኛና ከፍተኛ ለውጦች ካለው ምቹነት አንፃር ተመዝኖ አስፈላጊ የሚባሉ የፖሊሲና የመንግስታዊ አወቃቀር ለውጦችን መተግበር ሲሆን ይህም በሌሎች ሃገራት ተሞክሮ ጥሩ ሊባል የሚችል ለውጥ ሲያስገኝ ተስተውሏል።
ነገር ግን ወደ ሃገራችን መንግስት ስንመጣ ከበድ ያሉ የማስተካከያ መፍትሄዎችን ቀርቶ እጅግ አነስተኛ የሚባሉ የማህበረሰብ የመብት ጥያቄዎችን እንኳን በሃይል በመጨፍለቅ ሃገራዊና ማህበረሰባዊ ችግሮችን ይበልጡን እያወሳሰበ ይገኛል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ የአለማችን ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አቅጣጫ ዝንባሌው ከታችኛ ረድፍ ላይ ያሉትን ሃገራት የወደፊት እጣ ፈንታ እጅግ የከፋ ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ እንድምታ እየተስተዋለበት ነው። ባለፉት ግዜያት በመጨረሻው ረድፍ ላይ ያሉ ሃገራት “ከድህነት ወለል በታች ያሉ ሃገራት” ተብለውም ቢሆን እንደሃገር ይመደቡ ነበር። ነገር ግን ከግዜ ወደ ግዜ ይህ እየተቀየረ እየሄደ ይገኛል። “ከድህነት ወለል በታች ያሉ ሃገራት” ከሚባሉት ውስጥ የተወሰኑ ሃገራት (Failed States) የሚባለው ምድብ ውስጥ እየገቡ ነው። ይህ ማለት በቀላል ማጠቃለያ በሚመጡት ግዜያት እንደ ከዚህ ቀደሙ ደሃ ሃገር ሆኖ መኖር ወደ የማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ገብቷል ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከመቼውም ግዜ በላይ የለውጥን አፋጣኝ አስፈላጊነት የሚያመላክት ነው።
ከዚህ ቀደም በአለማችን ታሪክ ለውጥ በተለያዩ መንገዶች ሲካሄድ አስተውለናል ፡ ለአብነት ለመጥቀስም ያህል የነበሩትን ስርዓቶች ጭርሱን በማጥፋት ሌላ ስርዓት መገንባት አንዱ ሲሆን ሌላው ደግሞ በነበረው ስርዓት ላይ ግጭቶችንና የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶችን አቻችሎ ህዝብ በምርጫ መሪዎቹን የሚመርጥበትን መንገድ ማመቻቸት ነው። በወያኔ ኢህአዴግ  ስርዓት ህዝባችን በትዕግስትና በጨዋነት የለውጥን አስፈላጊነት አምኖ ፣ የምርጫን ምንነት ተረድቶ ፣ ይሆኑኛል ያላቸውን መሪዎቹን በተስፋ ሲመርጥ በምርጫ 97 አይተናል። ነገር ግን አሁንም ባባሰ መልኩ የህዝብ መብትና ፍላጎት ታፍኖ ህዝብና ሃገር በጉልበተኞች አምባገነናዊ ጭቆና ስር እየማቀቁ ይገኛሉ።
የወያኔ መንግስት ምርጫውን ብቻውን ሊያረገው አይፈልግም የተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለይስሙላና ለውጭ ታዛቢዎች ማታለያ እንደሚጠቀመው የሚጠበቅ የተለመደ አካሄዱ ነው። የወያኔ መንግስት ለሃገር እድገትና ለህዝብ መብት መከበር ለሚጥሩ አማራጭ ሃይሎች ህዝብ የሰጣቸውንና የሚገባቸውን የህዝብ ውክልና መቀመጫ በጉልበት እንደነጠቃቸውም የከዚህ ቀደም ተሞክሮን ማስታወስ በቂ ነው። ታዲያ በዚህ መሰል የይስሙላ ምርጫ መሳተፍ ፋይዳው ምንድነው።
መጭው ምርጫን መሳተፍ ማለት ለወያኔ የኢትዮጲያን ህዝብ በረሀብ ፣ በጥማት ፣ በእርዛትና በዲሞክራሲ እጦት አሰቃይ ብሎ ፍቃድ እንደመስጠት ነው፡፡ ምርጫ እኮ የህዝብን ፍላጎት መጠየቂያ ነፃ የሆነ የዲሞክራሲ መንገድ ነው እንጂ የመርሀግበር ማሟያ አይደለም፡፡ እዚህ ላይ ካለፉት ምርጫዎች የተወሰኑ ኩነቶች ማንሳት ይቻላል።
ምርጫ 97፡ በተነጻጻሪ የተሻለ ዲሞክራሲ የታየበት ነው ሲባል ይደመጣል ፡ በእርግጥ ወያኔ ለዲሞክራሲ እና ነፃ ምርጫ ዝግጁ ስለነበር ነው ወይስ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አካሄድኩ ብሎ ደጅ የሚጠናቸውን ምዕራብያዊያንን ልብ ለማለስለስ?  ለዚህ ጥያቄ አዘል እይታ እንደ  ዋና ማሳያ ሊሆነን የሚችለው ከምርጫው በኋላ ወያኔ የተከተለው የጭካኔ ግድያ ነው፡፡ ስለዚህም ወያኔ ምርጫን መሰረት አድርጎ ለሚመጣ ማንኛውም የስልጣን ሽግግር ያልተዘጋጀና ተቃዋሚዎችም ህዝቡ በሰጣቸው ድምጽ ሳይሆን ወያኔ ተምኖ በሰጣቸው ወንበር ፓርላማ ተቀምጠው ምንም ፋይዳ የሌለው የተቃውሞ እና የድምጸ ተዓቅቦ እጅ የማስቆጠር ስራ ብቻ እንዲሰሩ ስለሚፈልግ ነው፡፡
ምርጫ 2002፡ ወያኔ ከምርጫ 97 ትምህርት በመውሰድ ከምርጫ በኋላ የሚመጣን ስልጣን የማጣት ስጋት ለማስወገድ በከፍተኛ ሁኔታ የተዘጋጀበት ነው፡፡ ይህ ምርጫ ወያኔ ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያልተዘጋጀ መሆኑ በተጨባጭ የታየበት እና ምርጫ 97 ካጋለጠበት ትክክለኛው ፀረ-ደሞክራሲያዊነት ባህሪው በባሰ መልኩ ምርጫውን ከጅምሩ በቁጥጥር ስር በማዋል ጭቆና እና የመብት ረገጣ እለታዊ የኑሮ አካል በሆነባት ኢትዮጲያ  በምርጫ ታሪክ ያልታየ የምርጫ ውጤት ሲመዘገብ አይተናል፡፡
መጭው ምርጫ 2007፡ ምርጫ 2002 በአጠቃላይ ሲታይ ለወያኔው ጨቋኝ መንግስት ከጠበቀው በላይ ቢሆንም ውጤቱ ፀረ-ዲሞክራሲያዊነቱን ፍንትው አድርጎ ያሳየበት መሆኑ ለመጭው ምርጫ 2007 እንዳንድ ማስተካከያ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ ለመገመት ያህልም በመጭው ምርጫ ወያኔ የተወሰኑ ወንበሮችን “ታማኝ” ለሚላቸው ተቃዋሚዎች ለመስጠት የሚያስብ ይመስለኛል፡፡ በዚህ መሰረተ የስልጣን እድሜውን እያራዘመ እና የውሸት ፕሮፓጋንዳውን እየነዛ በኢትዮጵያውያን ላይ ገደብ አልባ ገዥነቱን የሚያውጅ መሆኑ ማንም ሊገነዘበው የሚችል ሀቅ ነው፡፡
ናትናኤል ካብቲመር
ናትናኤል ካብቲመር
ተቃዋሚዎች ለመጭው ምርጫ መዘጋጀት ያለባቸው እንደቀድሞው “ተሳትፎ ለመሸነፍ” ከሆነ የወያኔ የጭቆና አጋፋሪ ከመሆን የዘለለ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈይዱለት አንዳች ነገር የለም፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የህዝቡን ሮሮ፣ ችግር፣ የመብት ረገጣ እና ጭቆና ማዳመጥ እና ታግሎ ህዝብን በማታገል መፍትሄ የማምጣት ታሪካዊ ግዴታ አለባቸው፡፡ ስለዚህም መጭውን ምርጫ አለመሳተፍ ብቻ ሳይሆን ምርጫው እንደቀደሙት ምርጫዎች የህዝብ መብትን ማፈኛ እንዳይሆን መታገል አለባቸው፡፡ ከወያኔ በስተቀር ለማንኛውም የኢትዮጲያን ህዝብ እወክላለው ለሚል ተቃዋሚ ፓርቲ የጋራ አጀንዳ መሆን ያለበት በህዝብ እየተቀለደ የሚደረግ የይስሙላ ምርጫ እንዳይካሄድ ማድረግ ነው፡፡ ሥለዚህም መጭው ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የታሰሩ የፖለቲካ መሪዎችና ለህዝብ የቆሙ ሀቀኛ ጋዜጠኞች ሳይፈቱ ፣ ለወያኔ በግልጽ የሚያዳሉና አሳሪ የሆኑትን “የምርጫ ህጎች” ሳይሻሻሉ እንዲሁም ሌሎች  መሻሻል ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ አለመሳተፍ ብቻ ሳይሆን የምርጫው ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ በመሆኑ ምርጫው እንዳይካሔድ ህዝቡን በነቂስ በመቀስቀስ የታሰበውን የይስሙላ ምርጫ ማስቆም አለባቸው፡፡ አዎ ይህ ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ የሚቀለድበት እንዲሆን ማናችንም መፍቀድ የለብንም፡፡ ይህ ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ምርጫዎች ከሚካሄድ ይልቅ ምርጫው ቀርቶ ለአለም የኢትዮጵያዊያንን ችግርና የጨቋኙን የወያኔን ትክክለኛ ማንነት ማሳወቅ እንዲሁም የአትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ የስልጣን ባለቤትነቱን ወያኔ ባዘጋጀው የይስሙላ ምርጫ ሳይሆን ነፃ የሆነ በሁሉም ተወዳዳሪዎች ይሁንታ ያገኘ አካል በሚያካሂደው እውነተኛ ምርጫ እንዲሆን ማድረግ የሁላችንም ግዴታ ነው፡፡ ምክንያቱም ወያኔ ነጻ ምርጫ ለማካሄድ ጭርሱንም ፍላጎት ስለሌለው።
ውድቀት ለአምባገነኖች !!
http://www.goolgule.com

AN URGENT APPEAL – From Mesfin Wolde-Mariam

AN URGENT APPEAL – From Mesfin Wolde-Mariam

The UN Human Rights Commission
The African Union Human Rights Commission
The International Red Cross
Amnesty International
Human Rights Watch
And
All Men and Women of GOOD WILL
Reeyot Alemu
Reeyot Alemu
Reeyot Alemu is a budding Ethiopian poet, essayist, and journalist. There are not many Ethiopians of her caliber inside the country. She has been languishing in the famous Ethiopian Prison in Qalliti for almost three years. She was charged of terrorism, a crime she totally abhors. She was sentenced first for eighteen years but later reduced to three.
With the exception of her mother and father, she is not allowed to communicate with anyone, including her sisters, brothers as well as her fiancée.
Reeyot, although constantly in agonizing pain and in need of help, is held in solitary confinement with a very old and sickly foreign woman who herself requires assistance.
Reeyot is suffering from some growth in her breasts. The prison authorities have been reluctant to take her to hospital for medical checkup, even when her parents were prepared to pay the bill. When she became seriously ill she was allowed to see a doctor as a result of which she was taken to the hospital and operated upon. But no sooner had the surgeon finished the operation than she was immediately taken back to prison even before she had fully recovered from the Anastasia.
She now suffers from a relapse on the operated breast and similar growth in her other breast. The prison authorities still demonstrate their reluctance to provide medical treatment even at the expense of her parents.
May God provide the necessary courage to all those institutions and organizations to cry out effectively for this young lady who is suffering at the hands of insensitive prison administration.
http://ethioforum.org

Tuesday, April 22, 2014

Stop military aggression against civilians in Afar Region of Ethiopia!


Afar People’s Party (Qafar Ummattah Party)
PRESS RELEASEAfar People’s Party's logo
The ongoing atrocities committed by the TPLF/EPRDF regime are reaching the limit in Ethiopia in general and that of the Afar region in particular. April 20, 2014 the regime instigated conflict flared around Awash killing 12 Afar civilians. This act of state terror was committed by the federal polis. Outraged by this act of terror, the civilians in Awash blocked Addis Ababa-Djibouti road causing stop for all gods coming from Djibouti port demanding the of removal corrupt army from the locality. Likewise, in March 2014 the militia of the Tigray Region besieged Konnaba district in North West of the Afar Region, which also ended in blocked road to Tigray Region until today. As usual, the Afar regional officials seem to be paralyzed to act on behalf of the Afar civilians. Hence, TPLF/EPRDF regime and its army should be held accountable for the brutal crime against humanity. Since Woyane seized power in Ethiopia, the Afar population is harassed, humiliated and hundreds of them have been killed by the army throughout these years.
In addition, displacement of thousands of Afar pastoralists continues due to land grabbing for Woyane affiliated investors in vicinities Afdera, Dallol, Teru and along the Awash Valley. The pastoralists have been evicted to desert areas without access to water and other facilities. Afar People’s Party condoms the killing of the civilians, forced displacement, land grabbing, social injustices with strongest possible terms. Afar People’s Party also shares the concerns of Horn of African analysts who indicate that the situation in the Afar region could lead to a civil war and destabilize Ethiopia. We encourage the civilian to continue their peaceful demonstrations to denounce the state terror in different places for the coming two weeks.
  • We call on the army to immediately end the act of terror on civilian!
  • We call on Amnesty International and Human Rights Watch and Journalists to investigate the situation in Afar regional state.

Sunday, April 20, 2014

የአፍሪካ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የታሰሩ ሙስሊሞችን ክስ ተቀበለ

ጋምቢያ የሚገኘው የአፍሪካ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሽብር ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙ “የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ” አባላት ያቀረቡትን የክስ አቤቱታ እንደተቀበለ ምንጮች ገለፁ፡፡
የኮሚቴው አባላት የክስ አቤቱታውን ያቀረቡት ከወራት በፊት ሲሆን በእነ አቡበከር አህመድ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት 28 ግለሰቦች፤ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከአወሊያ ት/ቤት እና ሌሎች ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው አለመግባባት በመፍትሔ አፈላላጊነት የመረጣቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ መግባቱን በመቃወማቸው “አሸባሪ” ተብለው ለእስር መዳረጋቸውን ለኮሚሽኑ አመልክተዋል፡፡
“አህባሽ” የተሰኘውን የሊባኖስ አስተምህሮ በግድ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ለመጫን የተለያዩ ስልጠናዎች መሠጠታቸውን የጠቆመው የክስ አቤቱታው፤ ይህን “የመንግስት አካሄድ” የታሠሩትን ጨምሮ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በሠላማዊ መንገድ ቢቃወሙም መንግስት የተቃወሙትን በማሰር፣ የሃይማኖት መሪዎችን ከሃላፊነታቸው በማንሣት፣ እስላማዊ ት/ቤቱን በመዝጋት መንግስት አፀፋዊ እርምጃ እንደወሰደ ያስረዳል፡፡
በጥር 2004 ዓ.ም “የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ” አባላት በችግሩ ዙሪያ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር ለመነጋገር መንግስት ከተስማማ በኋላ ቃሉን በማጠፍ፣ የኮሚቴውን አባላት እና ተቃውሞ ያሰሙትን አስሮ በአሸባሪነት ክስ እንደመሠረተባቸውም የክስ ማመልከቻው ያብራራል፡፡
በማረሚያ ቤት ሆነው የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ መሆናቸውን የገለፁት ተከሳሾቹ፤  ከቤተሰቦቻቸው፣ ከህግ አማካሪዎቻቸው እና ከህክምና ባለሙያዎች ጋር እንዳይገናኙ መደረጉን፣ ቤተሰቦቻቸውም በፖሊስ ወከባ እንደደረሰባቸው በክስ ማመልከቻቸው ጠቁመዋል፡፡
ተቀማጭነቱን ጋምቢያ ያደረገው የአፍሪካ ሰብአዊና ህዝባዊ መብቶች ኮሚሽን የቀረበለትን የክስ አቤቱታ መርምሮ የሚያስተላልፈው ውሣኔ የሚጠበቅ ሲሆን የፍርድ ሂደቱን እስከማቋረጥ ሊደርስ የሚችል ውሣኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚገመት ምንጮዎች ጠቁመዋል፡፡
በ1987 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ስር የተቋቋመው ኮሚሽኑ፤ የህብረቱ አባል አገራት የህዝባቸውን ሰብአዊ መብት ማስጠበቅ አለማስጠበቃቸውን የመመርመር ስልጣን ያለው ፍ/ቤት እንደሆነ ያመለከቱት ምንጮች፤ ከሌሎች መሰል የሰብአዊ መብት ተቋማት በተሻለ ውሳኔው በአባል ሀገራቱ ተቀባይነት እንዳለው ገልፀዋል፡፡
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት፣ የተከሣሾቹን ቃል የመስማት ሂደት ባለፈው አርብ ሚያዚያ 3 የተጠናቀቀ ሲሆን የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ለግንቦት 4 ተቀጥሯል፡፡

Source: http://www.addisadmassnews.com

ሁለት : ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? እሱ ሲፈቅድ ነው? ወይስ ጌታው ሲፈቀድለት?

ሁለት : ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? እሱ ሲፈቅድ ነው? ወይስ ጌታው ሲፈቀድለት?


መስፍን ወልደ ማርያም
 አንድ በሀርቫርድ የኒቨርሲቲ ያጋጠመኝን ነገር መግቢያ ላድርገውና ልቀጥል፤ በአንድ ሴሚናር (የጥናት ውይይት) ላይ አንድ ጥቁር አሜሪካን ፕሮፌሰር ወደአሜሪካ በባርነት በመጡት አፍሪካውያን ላይ የተፈጸመውን ግፍ በመዘርዘር አስረድቶ አሁን ለእነሱ ልጆችና የልጅ ልጆች ካሣ መከፈል አለበት የሚል ክርክር አነሣ፤ ካሣውን የመክፈል ግዴታ የሚጣለው ማን ላይ ነው? ካሣውንስ የመቀበል መብት የሚሰጠው ለማን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ሳናነሣ ብዙ ሌሎች ጥያቄዎች ይኖራሉ፤ — እነዚያ ከአፍሪካ በባርነት ተይዘውና ተሸጠው የመጡት ሰዎች ዛሬ የሉም፤ እነሱ በባርነት ሞተዋል፤ ዛሬ በሕይወት የሚገኙት ጥቁር አሜሪካውያን ነጻነታቸውን አግኝተው ባለሙሉ መብት ዜጎች ሆነዋል፤ በአንጻሩ ደግሞ ለባሪያዎች ነጻነት የተጋደሉ ነጮች አሉ የእነዚህ ልጆች ከባሪያዎቹ ወይንስ ከጌቶቹ ወገን ይመደባሉ? ዛሬ ለልጆቻቸው ካሣ ይከፈል ማለት ልጆቹ የራሳቸውን ነጻነት ችላ ብለው ከአባቶቻቸው ባርነት ጋር እንዲቆራኙ ማድረግ አይሆንም ወይ? የባርነት ምልክቶችን ሁሉ ደምስሰው ነጻ ሰዎች ለመሆን የመጀመሪያው ግዴታ ራስን ችሎ በሁለት እግሮች መቆም ነው፤ ካሣ ክፈሉን ማለት አንደኛ ዋጋ ለማይሰጠው ነጻነት ዋጋን በማውጣት ማርከስ ነው፤ ከሰውነት ወደቤት እንስሳነት መውረድ ነው፤ ሁለተኛ በጌታና በባርያ መሀከል ያለው ግንኙነት መልኩን ለውጦ እንዲቀጥል መድረግ ነው፤ የውይይቱ ባለቤት እኔ ያቀረብሁትን ሀተታ እንዳላሰበበት ቢናገርም የእኔ ጥያቄ የተወደደ አልመሰለኝም፤ ካሣ ተቀባዮች ባርነታቸውን ካሣ ከፋዮች የባሪያዎች ባለቤትነታቸውን ጠብቀው እንደተቆራኙ መቀጠላቸው ባርነትን አያጠፋም፤ ለእኔ ጤናማ አልመሰለኝም።
ባሪያና ኃላፊነት አይተዋወቁም፤ ባሪያ ለገዛ ራሱ ኑሮም ቢሆን ኃላፊነት የለውም፤ ለምግቡም ሆነ ለልብሱ፣ ለመጠለያውም ሆነ ለቀብሩ ኃላፊነት የለበትም፤ ለሁሉም ነገር ኃላፊነቱ የጌታው ነው፤ ከባርነት መውጣት ማለት፣ ከባርነት መላቀቅ ማለት ነው፤ ለገዛ ራስ ሕይወት፣ ለገዛ ራስ ኑሮ ሙሉ ኃላፊነትን መሸከም ነው፤ ስለዚህም ከባርነት ወደነጻነት መሻገር ከግድዴለሽነት ወደኃላፊነት መሻገር ነው፤ ስለዚህም ከግዴለሽነት ወደኃላፊነት ሳይሻገሩ ከባርነት ወደነጻነት መሻገር አይቻልም! ኤልሪድጅ ክሊቨር የሚባል ጥቁር አሜሪካዊ በእስር ቤት ሆኖ የጻፈው (Soul on Ice) የሚል መጽሐፍ በዚህ ጉዳይ ላይ አፍአዊ ምልክቶችን ዘልቆ የሚገባ የነጻነትንና የባርነትን ባሕርያት ያሳያል፤ በአንድ በኩል በሴት ባርያና በወንድ ጌታ መሀከል ያለውን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በወንድ ባርያና በሴት እመቤት በኩል ያለውን ግንኙነት በግላጭ ያወጣዋል፤ ባርነትን የባሕርዩ ያደረገ መገለጫው ለምንም ነገር ኃላፊነት የማይሰማው መሆኑ ነው፤ ለምንም ነገር ሳያስብ፣ በትእዛዝ ብቻ መመራት የተመቸው ባርያ ነው።
ደግ ጌታ በራሱ ተነሣሺነትና በራሱ ፈቃድ ባሪያውን ነጻ ቢያወጣው ባሪያው ሙሉ በሙሉ ነጻ የሚሆን አይመስለኝም፤ በሕግ ነጻ ይሆናል፤ በውስጡ ግን ገና ከባርነት አልተላቀቀም፤ ከጌታው ጥገኛነት ለመውጣት ባለመዘጋጀቱ በኑሮውም ቢሆን ከጌታው አልተላቀቀም፤ ሳይለቀለቅ ከነእድፉ እንደተሰጣ ልብስ ነው፤ ተፈቅዶለት ከባርነት የወጣ ገና ነጻነትን አላገኘም፤ ከባርነት ለመላቀቅ በፍላጎቱና በፈቃዱ ወስኖ ነጻነቱን ከጌታው በግድ ፈልቅቆ ማውጣት አለበት፤ ለምን? የነጻነቱንና የሰውነቱን ቁርኝት ተገንዝቦ፣ የዜግነት እኩልነቱን ተረድቶ፣ በሰውነትም በዜግነትም ጌታህ-ነኝ ከሚለው የማያንስ መሆኑን አምኖ በቆራጥነት ሲነሣ ነው፤ የሰውነቱንና የዜግነቱን ልክ፣ የነጻነትን ትርጉምና ጣዕም አውቆ በትግል ነጻነቱን ሲያገኝ ያለጥርጥር ከባርነት ወጣ ማለት ይቻላል፤ አለዚያ ነጻነቱን በስጦታ፣ በጌታው መልካም ፈቃድ የሚያገኘው የነጻነት ሙሉ ባሕርይ አይኖረውም።
የአፍሪካን አገሮች ብንመለከት የመረረ የነጻነት ትግል የተካሄደባቸው ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ አልጂርያ፣ ዚምባብዌ ናቸው፤ እንደሚታወቀው እነዚህ አራቱም አገሮች ለአውሮፓውያን ሰፈራ የታጩ ነበሩ፤ ምናልባት በእነዚህ ዘገሮች ለነጻነት የተደረገውን ትግል መራራ ያድረገው ዋናው ምክንያት አፍሪካውያኑ አገር-አልባ ሆነው እንዳይቀሩ የነበረው ስጋት ሊሆን ይችላል፤ በአንጻሩ ሱዳን የነጻነት ትግል አልነበረም፤ የኢትዮጵያ ጎረቤት ስለሆነ ቶሎ ነጻነትን በመስጠትና ወዳጅ በመፍጠር፤ በሶማልያም በኩል እንዲሁ ቶሎ ነጻነትን በማሸከም ምዕራባውያን ወደፊት ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት እየቀረጹ ነበር ለማለት ይቻላል፤ ግብጾች ከስንት ሺህ ዓመታት በኋላ ነው አሁን በዘመናችን ወንዶችና ሴቶች በአደባባይ ወጥተው እምቢ! በማለት ሙባረክን ያስወረዱት! ለነጻነት የመታገሉ ልምድ ስለሌላቸው፣ በዚያም ላይ ባህልና ሃይማኖት ተጨምሮበት ሙባረክን አስወርደው ነጻነትን አላገኙም፤ እንደዚሁም የኢትዮጵያ ሕዝብም አጼ ኃይለ ሥላሴን አስወርዶ ነጻነቱን አላገኘም::
እያንዳንዱ ሰው የተፈጠረው ከነፍላጎቱና ፍላጎቱን ለማሟላት ካለው አዛዥነት ጋር ነው፤ ባርያ ፍላጎቶቹን ለማሟላት አዛዥነቱ የለውም፤ አዛዡ የራሱ ፈቃድ ነው፤ የራሱ ፈቃድ የሌለው ሰው ወና ሰው ነው፤ ዋናውን የሰውነት ባሕርዩን ያጣ ባዶ ዕቃ ነው፤ ከባዶ ዕቃ ውስጥ የሚወጣ ነገር የለም፤ ለዚህ ነው ለነጻነቱ መታገልና በራሱ ጥረት ድልን ለመጎናጸፍ የማይችለው።
http://mesfinwoldemariam.wordpress.com