Tuesday, May 3, 2016

የመገናኛ ብዙሃን ቀንደኛ አፋኝ ተብለው ከተፈረጁ ሃገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት

ኢሳት (ሚያዚያ 25 2008) በአለማችን ግንባር ቀደም የመገናኛ ብዙሃን አፋኝ ተብለው ከተፈረጁ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን በሃገሪቱ ያለው ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትም እየተባባሰ መምጣቱን የተለያዩ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ተቋማት ገለጡ። በየአመቱ በአለም ዙሪያ የሚከበረውን የፕሬስ ነጻነት ቀን አስመልክቶ ሪፖርታቸውን ያወጡት እነዚሁ ተቋማት በኢትዮጵያ 14 ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። ሃገሪቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን መቀመጫ ብትሆንም ጋዜጠኞች መረጃ የማግኘት መብታቸውና ሃሳባቸው በነጻነት የመግለጽ መብታቸው ተገድቦ እንደሚገኝ ሃፊንግተን ፖስት ጋዜጣ የፍሪደም ሃውስ እና የድንበር የለሽ የሪፖርተሮች ቡድን (Reporters Without Borders) መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ለንባብ ባበቃው ትሙ አስነብቧል። 20 አመት በላይ በስልጣን ላይ የቆየው የኢህአዴግ መንግስት በተለያዩ ጊዜያት አዋጆችን በማውጣት የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን እያፈነ እንደሚገኝም ጋዜጣው ዘግቧል። በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት የማሳተሚያ ተቋማትን በብቸኝነት በመቆጣጠር ለህትመት በሚበቁ ጋዜጦችና መፅሄቶች ላይ ቁጥጥርን እያደረገ መሆኑንም አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገልጸዋል። ከአመታት በፊት ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የሃገሪቱ የፀረ-ሽብርተኛ አዋጅ ህግም ሃሳብን በነጻነት በመግለጽ መብት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮ መቀጠሉን ሃፊንግተን ፖስት ጋዜጣ በሪፖርቱ አስፍሯል። ግብፅ 23 ጋዜጠኞችን በማሰር፣ እንዲሁም ጎረቤት ኤርትራ 17 ጋዜጠኞችን ለእስር በመዳረግ በአፍሪካ ግንባር ቀደም የመገናኛ ብዙሃን አፋኝ ሃገራት መሆናቸውንም የጋዜጠኞች ተከላካይ ድርጅት (Committee to Protect Journalist, CPJ) ገልጿል። የፕሬስ ነጻነት ቀን አስመልክቶ መልዕከትን ያስተላለፉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ሙን በበኩላቸው ሃገራት የመገናኛ ብዙሃንና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲያከብሩ አሳስበዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየአመቱ እንዲከበር የተወሰነው የዘንድሮው የፕሬስ ነጻነት ቀን በፊንላንድ መዲና ሄሊሲንኪ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች የተከበረ ሲሆን፣ በሙያቸው ግድያ የተፈጸመባቸውና ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞችም ልዩ አክብሮት ተሰጥቷቸዋል።

በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት አፈናው ተባብሷል- የጥናት ባለሞያዎች

ፍሌክስ ሆርን እና ሃሌሉያ ሉሌ

ዛሬ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ቀን ነው። ይህን ቀን ምክንያት በማድረግ “በኢትዮጵያ ያለው የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ምን ይመስላል?” ስትል ጽዮን ግርማ የሂዩማን ራይትስ ዎች የጥናት ባለሞያ ፍሊክስ ሆርንና የደህንነት ጥናት ተቋም የጥናትና ምርምር ባለሞያ ሃሌሉያ ሉሌን ጠይቃለች። ሁለቱም ባለሞያዎች በኢትዮያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት እጦት ተባብሷል ይላሉ። ሙሉ ዘገባውን ከዝግጅቱ።
የሂዩማን ራይትስዎች የጥናት ባለሞያ ፍሌክስ ሆርን በኢትዮጵያ የታፈነ ድምፅ አለ ሲል በቅርቡ አንድ ጥናት አቅርቦ ነበር። ለጹሑፉ በግብዓትነት ከተጠቀማቸው ማስረጃዎች መካከል 100 ሰዎችን ማነጋገሩን ገልጿል። በ1997 ዓ.ም ምርጫውን ተከትሎ ከተነሳው ተቃውሞ ቀጥሎ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ለአምስት ወራት ያህል የተደረገው ተቃውሞ ትልቁ ቢሆንም መረጃው ወደ ውጭ እንዳይወጣና ከውጭ ወደ ውስጥ እንዳየሰራጭ መንግሥት ከፍተኛ አፈና አድርጓል ይላል።
የደህንነት ጥናት ተቋም የጥናትና ምርምር ባለሞያ ሃሌሉያ ሉሌ በበኩሉ በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ ነፃንት ካለፈው ዐሥር ዓመት ወዲህ ያለው ሁኔታ ቢታይ እንኳን የአሁኑ በጣም የባሰ እንደሆነ ይናገራል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

በኢትዮጵያ በሕግ ሽፋን የዜጎችን መብት መጣስ ተባብሶ መቀጠሉን ሂውማን ራይት ሊግ አስታወቀ

ሚያዚያ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያ ውስጥ የፀረ ሽብር ሕግን ከለላ በማድረግ መብታቸውን የሚጠይቁ ዜጎችን ማሰር፣ መግደልና ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን መፈጸም ተጠናክሮ መቀጠሉን የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ሊግ ገልጿል። ድርጅቱ በኦሮሚያ ክልል የበርካታ ንጹሃንን ሕይወት የቀጠፈው ዘግናኝ እልቂት በህወሃት ኢህአዴግ መራሹ ገዥ ቡድን የተቀነባበረ መሆኑን አስታውቋል።
ይህን ኢሰብዓዊ እልቂት ተቃውመው ለመብታቸው የታገሉት ከ 22 በላይ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች የሃሰት ክስ እንደተመሰረተባቸው አመልክቶ ፣ በህወሃት የተቀነባበረ ሴራ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ካለ ፍትሕ በእስር ቤት እየማቀቁ ነው ብሎአል።
በኢትዮጵያ ያለው የፀረ ሽብር ሕግ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በሚጻረር መልኩ የወጣ ሲሆን ይህም የዜጎችን የመጻፍ፣ የመናገርና የመቃወም ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በሚጥስ መልኩ ሆን ተብሎ ተረቆ በሥራ ላይ መዋሉን አስታውቋል።
በኦሮሚያ የተነሳውን ሰላማዊ የዜጎችን ጥያቄ በመደገፍ ከሕዝባቸው ጋር በመሆን ሲቃወሙ ከነበሩት ውስጥ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ የፓርቲው ፀሃፊ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ አቡላና ሌሎችም በፈጠራ የሽብር ክስ መከሰሳቸውንና የመብት ጥሰቱ ተባብሶ መቀጠሉን ሪፖርቱ አመላክቷል።
መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ በሽብር ሕግ ስም አላግባብ ታስረው የሚገኙ ንጹሃን ኢትዮዮጵያዊያንን ህወሃት መራሹ መንግስት ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታዎች ክሳቸውን በማንሳት ሊፈታቸው ይገባል ብሎአል።

Ethiopia: Endless Injustices against Oromo Nation in the Name of Law Enforcement

HRLHA Press Release
May 3, 2016
The Human Rights League of the Horn of Africa (HRLHA) strongly condemns the TPLF/EPRDF Government’s endless manipulations of the justice system to its own political ends, which was once again manifested in the fully fabricated allegations and charges filed against 22 (twenty-two) Oromo nationals. It surprised no one that the TPLF/EPRDF Government, as usual, used the infamous legal tool of the Anti-Terrorism Law, as a result of which thousands of innocent Oromos and other nationals have been victimized, to arrest, detain and take to court another batch of Oromo activists. These newest allegations and attempts of abusing the justice system are taking place following the months-long and region-wide public protests in Oromia; and are, undoubtedly, parts of the heavy-handed crackdown, which included the imposition of martial law in the Regional State in an effort to suppress the public anger and demands for change.ETHIOPIA-UNREST
As described by some international legal analysts, the Ethiopian Anti-Terrorism Law “… criminalizes basic human rights, especially freedom of speech and assembly. The law defines terrorism in an extremely broad and vague way so as to give the government enormous leeway to punish words and acts that would be perfectly legal in a democracy”. This is the reality that came into play in the case of these newly made allegations against 22 Oromo nationals.
According to documents obtained by HRLHA, the 22 Oromo nationals, including top political leaders of the opposition Oromo Federalist Congress party, such as Mr. Bekele Gerba (Deputy Chairman) and Mr. DejeneTafa (Deputy Secretary General), Addisu Bulala and others have been charged with allegedly conspiring to overthrow the government by means of instigating a public revolt and protests as well as collaborating with other political organization called Oromo Liberation Front. The new creation in this case is that attempts were made to associate the officially registered and legally operating political parties like the OFC with opposition political organizations that were deemed outlaw by the Ethiopian Government in order to criminalize their legitimate existence and activities.
It is so unfortunate that Mr. Bekele Gerba is being subjected to such politically and racially motivated injustice and the resultant sufferings in Ethiopian substandard jails for the second time in a matter of two years.
The HRLHA has ample documents that hundreds of thousands of innocent Oromos and members of other nationalities have already fallen victims of such injustices and dictatorship committed particularly using this Anti-Terrorism Law, described by some as “a tool to stifle dissent”, as a legal weapon.
Local, regional and international communities have repeatedly witnessed over the past twenty-five years that the TPLF/EPRDF Government of Ethiopia misuses the political power, the justice system, and other public resources to silence and/or eliminate all forms of oppositions and political descents, despite the constitutionally declared democracy, in order to ensure monopoly and lasting partisan political goals. But, no tangible and effective actions are taken so far to make the Ethiopian Government refrain from punishing its own citizens just for exercising or attempting to exercise some of their basic and constitutionally provided democratic rights.
The HRLHA, first of all, calls upon the Ethiopian Government to unconditionally release these Oromo nationals detained and charges for allegedly committing acts of terrorism; as their words and/or acts are undoubtedly legal and, above all, constitutional. HRLHA also calls upon the international community’s so that they condemn the Ethiopian Government, acts of injustices against innocent citizens, and request that these unjustly detained and falsely charged Oromos are freed unconditionally.
RECOMMENDED ACTION: Please send appeals to the Ethiopian Government and its concerned officials as swiftly as possible, in English, Amharic, or your own language expressing:
For the immediate and unconditional release of prisoners illegally detained
Urging the Ethiopian authorities to ensure that these detainees would be treated in accordance with the regional and international standards on the treatment of prisoners,
 Source: zehabesha

Monday, May 2, 2016

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደኢትዮጵያ እየተላለፉ መሰጠታቸው አሳስቦኛል አለ

የኬንያ የደህንነት ሃይሎች በሃገሪቱ የፖለቲካ ጥገኝነትን ፈልገው የሚሰሰዱ ኢትዮጵያውያንን ለኢትዮጵያ መንግስት እያሳለፉ መስጠታቸው አሳስቦት እንደሚገኝ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። ይኸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ኬንያ መዲና ናይሮቢ ድረስ በመጓዝ ከኬንያ አጋሮቻቸው ጋር በመተባበር ድርጊቱን እየፈጸሙ እንደሚገኝ የተለያዩ አካላትን ዋቢ በማድረግ ይፋ አድርጓል።
ባለፉት አራት ወራቶች ብቻ በኬንያ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁ 25 ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ ተላልፈው የተሰጡ ሲሆን፣ የኬንያ የስደተኞች ጉዳይ መምሪያ ድርጊቱን እንዳስተባበለ ዘስታር የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል።
ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ የፖለቲካ ስደተኞችም አብዛኞቹ የኦሮሞ ተወላጆች ሲሆኑ፣ በቅርቡ በክልሉ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በርካታ ወጣቶች ወደጎረቤት ሃገራት እንዲሰደዱ ማድረጉን የተለያዩ አካላት ሲገልጹ ቆይተዋል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሌሎች አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ቅሬታን ሲያቀርቡ የነበረ ሲሆን በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር እንዲመለሱ ከተደረገ በኋላ በእስር ቤት መሞታቸውም ይታወቃል።
ድርጊቱ አሁን ድረስ መቀጠሉን ያስታወቁት በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የስደተኞች ኦፊሰር የሆኑት ቢላቶር ኒያምሪ በርካታ ቤተሰቦች የጠፉ ሰዎች ስለመኖራቸው አቤቱታን እያቀረቡ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በኬንያ ከ160ሺ በላይ ስደተኞችና የፖለቲካ ጥገኛ ፈላጊዎች እንደሚኖሩ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል። የኬንያ የፓርላማ አባላት የሃገራቸው የደህንነት ሃይሎች ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የፖለቲካ ስደተኞችን ወደሃገራቸው መመለሳቸው አግባብ አይደለም ሲሉ በተደጋጋሚ ቅሬታ ማቅረባቸውም የሚታወስ ነው።
የኬንያ መገናኛ ብዙሃን በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ገንዘብን በመመደብ የፖለቲካ አባላትን መልሶ ለመውሰድ ከኬንያ የደህንነት ሃይሎች ጋር በድብቅ እንደሚሰራ በቅርቡ ይፋ ማድረጋቸውም ይታወቃል።
የኬንያ ባለስልጣናት ድርጊቱን ቢያስተባብሉም የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽን ከመስጠት ተቆጥቦ ይገኛል።
ESAT

በኢትዮጵያ እውነተኛ ለውጥ እንዲመጣ ይፈልጋሉ?

በኢትዮጵያ እውነተኛ ለውጥ እንዲመጣ ይፈልጋሉ?
ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከዚህ ከፋፋይ የዘረኛ ሥርዓት ለማላቀቅ የሚደረገው ትግል ለጥቂት የህብረተሰብ ክፍል የሚተው ሳይሆን ኢትዮጵያ እንደ ሃገር እነድትቀጥል የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ማድረግ የሚችለውን በማድረግ ሃገራዊ ግዴታውን የሚወጣበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የተደረሰበት ወቅት ነው፡፡
ስለሆነም በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያዊያን የነጻነት ትግሉ የሚጠይቀውን ሃገራዊ ጥሪ እንደ ከዚህ ቀደሙ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ጁን 4 ፣2016 በዓይነቱ ልዩ የሆነ የነጻነት ትግሉን የሚያግዝ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቤያ ና ሕዝባዊ ስብሰባ አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል ፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮች ከውድ ኢትዮጵያውያን ጋር ስለኢትዮጵያ እንዲወያዪ በዝግጅቱ ላይ ተጋብዘዋል!
13092166_985186504905105_8569136456686886415_n
ቦታ ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋር በቅርብ ቀን ይገለጻል
የፌስቡክ ኤቨንት ገጻችንን ይጎብኙ እንዲሁም በዝግጅቱ ላይ እንደሚመጡ ያረጋግጡ በተጨማሪም ጓደኛዎትን በዚህ ሃገራዊ ጥሪ ላይ ይጋብዙ፣

ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ደምና አጥንት መስዋዕትነት ለዘላለም ተከብራ ትኖራለች !!!
የዲሞክራሲዊለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !!

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የኦሮምያ ተቃውሞ ሪፖርትን ለፓርላማ ማቅረብ አልቻለም

ሚያዚያ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሀት አባል እንደሆኑ በሚነገርላቸው ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን
በኦሮሚያ ግጭት የደረሰውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ቢያጣራም ለፓርላማው ለማቅረብ አለመቻሉ ታውቋል።
ኮምሽነር ዶ/ር አዲሱ ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሪፖርቱን ለፖርላማው ለማቅረብ እየተዘጋጁ መሆኑን ለመንግስት መገናኛ ብዙሀን ቢናገሩም፣ ባለፉት ስድስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥም ማቅረብ አልቻሉም።
ምንጮቻችን እንደጠቆሙን ሪፖርቱ ሊዘገይ የቻለበት ዋና ምክንያት መንግስት አስቀድሞ ማጣራት ሳይካሄድ “ቀውሱ የተቀሰቀሰውና ሰዎች እንዲገደሉና ንብረት እንዲወድም ያደረጉት የኦፌኮ አመራሮች አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 ሰዎች ናቸው” በሚል ፈርጆ ሰዎቹ ላይ ክስ በማቅረቡ ነው።
ኮምሽኑ ገለልተኛ አለመሆኑ በብዙዎች ዘንድ የሚገመት ቢሆንም ለታሪክ ፍርድም እንኩዋን ግጭቱ የትና መቼ እንደተነሳ፣ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ፣ ለጉዳቱ ተጠያቂዎቹ እነማን እንደሆኑ መግለጽ ነበረበት ያሉት ምንጮቹ፣
ኢህአዴግ የራሱን ምርመራ ውጤት እንኩዋን የፈራበት ጊዜ ላይ ደርሶአል ብለዋል።
ከምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢነት ባለፈው ነሃሴ ወር ተነስተው የሰብአዊ መብት ኮምሽነር ሆነው የተሾሙት ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር በኦሮሚያ ክልል በመንግስት ታጣቂዎች ከ240 በላይ ሰዎች መሞታቸው በገለልተኛ ተቋማት
ከተገለጸ በሁዋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ መሻሻል እያሳየ ነው በሚል ውግንና ያዘለ ምስክርነት መስጠታቸውን ያስተዋሉ ወገኖች በማህበራዊ ድረገጾች “ምን አይነት ሪፖርት ያቀርቡ ይሆን?” የሚል ጥያቄ ሲያነሱ ቆይተዋል።
በኦሮምያ በመንግስት ታጣቂዎች ለተፈጸመው ግድያ ጥፋቱ ሙሉ በሙሉ የመንግስት ነው በማለት አቶ ሃይላማርያም ከተናገሩ በሁዋላ፣ መንግስት እንደገና መልሶ በእነ አቶ በቀለ ገርባ ላይ ክስ መመስረቱና ለተፈጠረው ውድመትና ለተቃውሞው መነሻ አድርጎ ማቅረቡ፣ በአንድ አገር ውስጥ ስንት መንግስት ነው ያለው የሚል ጥያቄ አስነስቷል።