Saturday, October 5, 2013

ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰልፍ ላይቀጥል ይችላል አሉ

ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰልፍ ላይቀጥል ይችላል አሉ


ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚያደርጓቸው የተቃውሞ ሰልፎች ተደጋጋሚና መንግስት አቋም የያዘባቸውን ጉዳዮች የሚያነሱ እንደሆኑ የጠቆሙት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፤ መንግስት ለእያንዳንዱ ሰልፍ ጥበቃ ማድረግ ስለማይችል ሰልፎቹ በተለመደው መልኩ ላይቀጥሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት በጽ/ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች የራሳቸው የፓርቲዎቹ ሳይሆኑ የሌሎች ሃይሎች እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
ፓርቲዎቹ ሰልፍ ማካሄድ ህገመንግስታዊ መብታቸው መሆኑን የጠቀሱት ጠ/ሚኒስትሩ፤ መንግስት በተደጋጋሚ ጥበቃ ሲያደርግ ቢቆይም፣ በሰልፎቹ የሚነሱት ጥያቄዎች ፋይዳ ቢስ ከመሆናቸውና ከፓርቲዎቹ ብዛት አንፃር መንግስት በቀጣይ ለሰልፎች ጥበቃ ለማድረግ የሚቸገርበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
 ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ መንግስት በተደጋጋሚ ምላሽ የሰጠባቸውን ጥያቄዎች መላልሰው የሚያቀርቡት በመንግስት ላይ ጫና በመፍጠር አቋሙን ለማስቀየር በማሰብ ሊሆን ይችላል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ ይሄ ግን በፍፁም የማይሳካ ሃሳብ ነው ብለዋል፡፡ “ግንቦት ሰባት” በቅርቡ መንግስትን ለመጣል ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ በይፋ መግለፁን በተመለከተ ተጠይቀው ሲመልሱም፣ የፓርቲው አመራሮችና ደጋፊዎች ተጨባጭ ያልሆነ ህልም ውስጥ ሆነው የተናገሩት ነገር እንደሆነና ከህልማቸው ሲነቁ እውነታውን እንደሚገነዘቡት ጠ/ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ መከፋፈልና የሃይል መጠባበቅ አለ የሚለውን መረጃ በተመለከተም “ይህ የአንዳንድ አፍራሽ ሃይሎች ከንቱ ምኞትና ተጨባጭ ያልሆነ አሉባልታ ነው” ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

ወያኔ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በማጓጓዝ ስራ መጠመዱ ተሰማ

ወያኔ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በማጓጓዝ ስራ መጠመዱ ተሰማ

Official Site for Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy
ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚወስዱ አዉራ መንገዶች ታንኮችን፤ መድፎችንና ሌሎችም ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በተሸከሙ ከባድ ወታደራዊ የጭነት ማመላለሻ ከሚዮኖች እየተጨናነቁ መሆኑን ኢሳት ቴሌቪዥንና ሬድዮ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘገበ። ወያኔ ከኤርትራ ጋር ባለበት የድንበር አተካሮ ብዙም ዉጥረት በማይታይታይበት በአሁኑ ወቅት የጦር መሳሪያዎቹን በዚህ ደረጃ ለማንቀሳቀስ ለምን እንዳስፈለገ ብዙም የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አንዳንዶች ወይኔ ሀይሉን ለማሳየት የሚያደርገዉ ከንቱ የእዩኝ እዩኝ ዘመቻ ነዉ ሲሉ ሌሎች ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን እያየለ የሚጣዉን የአማጽያን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ነዉ ይላሉ። ያም ሆነ ይህ ወታደራዊ እንቅስቃሴዉን አስመልክቶ ከአገዛዙ ባለስልጣናት የተሰጠ መግለጫ ካለመኖሩም በላይ ሦስተኛ አካላት ጉዳዩን ለማጣራት ከመንግስት ጋር ያደረጉት ግንኙነትም ፍሬ አልባ ሆኗል።
ሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ፤ ጎንደርና አፋር ዉስጥ የወያኔን ስርዐት በኃይል ለመናድ የሚንቀሳቀሱ አያሌ መሳሪያ ያነገቡ ድርጅቶች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ላለፉት ሃያ አመታት በተናጠል ወያኔን የተዋጉ ኃይሎች ከቅርብ ግዜ ወዲህ የጋራ ግንባር እየፈጠሩ መምጣታቸዉ ወያኔን እንዳሳሰበዉና ክፉኛ እንዳስደነገጠዉም ታዉቋል። እንደብዙ የፖለቲካ ተንታኞች ግምት ይህ ከሰሞኑ የታየዉ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴም የዚሁ ድንጋጤ ዉጤት ነዉ የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በየክልሉ የነጻነት ኃይሎችን ለመቀላለቀል የሚደረገዉ እንቅስቃሴ እያደገ መምጣቱ ሌላዉ የወያኔ ስጋት ስለሆነ የሰሞኑ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረገዉ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከመሀል የአገሪቱ ክፍሎች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የድንበር አካባቢዎች የሚወስዱ መንገዶችንና ኬላዎችን ለመዝጋት ነዉ የሚሉም አልታጡም። በዚህ ተኬደ በዚያ የሰሞኑ የወያኔ ወታደራዊ ሩጫ አላማዉ ባዕዳንን ለመከላከል ሳይሆን ለአገር አንድነትና ለህዝብ መብትና ነጻነት የሚታገሉ ኃይሎችን ለማፈን ነዉ።

ግንቦት7 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለወገኑ ነጻነት የሚቆምበትን መንገድ እያዘጋጀ መሀኑን ገለጸ

ግንቦት7 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለወገኑ ነጻነት የሚቆምበትን መንገድ እያዘጋጀ መሀኑን ገለጸ

Official Site for Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy
ንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወያኔ የዘረኝነት አለንጋ የሚለበለበዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እራሱንና ወገኑን ነጻ የሚያደርግበትን መንገድ መከላከያ ሰራዊቱ ዉስጥ እየቀየሰ መሆኑን የንቅናቄዉ ዋና ጸሀፉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ። ዋና ጸሀፊዉ ይህንን የተናገሩት ኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ዉስጥ የግንቦት ሰባት ኃይሎችን ለመርዳት በተደረገዉ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ባሰሙት ንግግር ነዉ። አቶ አንዳርጋቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱን አስመለሰክተዉ ባደረጉት ንግግር እንደዚህ አይነቱ ወገናዊ ዝግጅት በአንድ በኩል በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አባላት ዉስጥ ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ወራዊቱ የተጣለበት ህዝባዊ አደራ ምን ያክል ከፍተኛ መሆኑን የሚያስታውሰን ነው ብለዋል።
በቅርቡ ከኢትዮጵያ አየር ሀይል ከድተው ህዝባዊ ሰራዊቱን ስለተቀላቀሉት ጀግኖች ተጠይቀዉ በሰጡት መልስ የአየር ኃይል አባላቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዉ ንቅናቄያቸዉ በመከላከያ ሰራዊት፤ በደህንነት መስሪያ ቤትና በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ዉስጥ ወያኔ ሊደርስበት በማይችልበት መልኩ የግንኙነት መስመር እየዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል።
ኖርዌይ ኦስሎ ዉስጥ የተካሄደዉን አይነት የግንቦት ሰባት ኃይሎች የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሌሎች አገሮችና ከተሞች ዉስጥ ለማድረግ እቅድ አላችሁ ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ አንዳርጋቸው፣ ህዝባዊ ሀይሉ ከተግባር ጋር በተዛመደ መልኩ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት መርሀ ግብሩን ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ በህዝባዊ ሀይሉ ወይም በግለሰቦች ስም ምንም አይነት የገቢ መሰባሰቢያ ዝግጅት እንደማይደርግ ገልጸዋል። በሌላ ዜና ደግሞ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኖርዌ፤ ሲዉድንና በአካባቢዉ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር እንደተወያዩ ለማወቅ ተችሏል። በዚህ ዉይይታቸዉ ወቅት አቶ አንዳርጋቸው የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይልን ዓላማዎች፤ ተልዕኮዎችና ራዕይ በማስተዋወቅ ህዝባዊ ሃይሉ ከምስረታው ጀምሮ አሁን ድረስ ያለበትን ደረጃ በምስልና በጽሁፍ በተደገፈ ገለጻ ለተሰብሳቢው አቅርበዋል።
ከአቶ አንዳርጋቸው እስካሁን ድረስ የተካሄደዉ የህዝባዊ ኃይሉ ስልጠና የንቅናቁዉን የአመራር አካላት ያካተተ መሆኑን ጠቅሰዉ ወታደራዊ ስልጠናዉ የበታችና የበላይ የሚባል ልዩነት እንደሌለበት አስገንዝበዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተዉ ቤተሰባቸውን፤ ስራቸውን፤ገንዘባቸውንና የተደላደለ ኑሯቸውን ትተው ከኢትዮጵያና ከመላው ዓለም በተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን እንደሆነ እንደሆነ ገልጸዋል። የግንቦት ሰባት ዓላማ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ማስፈን ብቻ ሳይሆን ባለፉት 22 ዓመታት ኢትዮጵያውያን የተገፈፉትን ክብራቸውን ማስመለስ ጭምር መሆኑን አቶ አንዳርጋቸው አስምረውበታል።

Friday, October 4, 2013

ሕዝባዊ ጥያቄዎችን ማፈንና አደባባይ መከልከል በህግም በታሪክም ያስጠይቃል ሲል አንድነትና 33 ፓርቲዎች በጋራ አስታወቁ


ሕዝባዊ ጥያቄዎችን ማፈንና አደባባይ መከልከል በህግም በታሪክም ያስጠይቃል 

ሲል አንድነትና 33 ፓርቲዎች በጋራ አስታወቁ


መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲዎቹ ባወጡት 

መግለጫ የሶስት ወር ሕዝባዊ ንቅናቄችን ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በአዲስ 

አበባ ለማጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የከንቲባው ጽ/ቤት መስከረም 3 

ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ሠላማዊ ሠልፉን በመስከረም 19 ቀን ማድረግ እንደምንችል 

የሚገልፅ የዕውቅና ደብባቤ ቢሰጠንም ፣ በእጅ አዙር ሠልፉን በመስቀል አደባባይ 

እንዳናደርግ ከመከልከሉም በላይ ከሕግ ውጨ በመከላከያ በፀጥታ ተቋማት አካባቢ 

እንድንሰለፍ ለማስገደድ በመሞከርና ቅስቀሳ እንዳናደርግ ክልክሎናል ብለዋል።


ፓርቲዎቹ አያይዘውም ፖሊስ ህገ መንግስቱንና ህዝቡን መጠበቅ ሲገባው 

ለመቀስቀስ፣ ፖስተር ለመለጠፍ፣ በራሪ ወረቀቶችን ለማሰራጨት ፈቃድ ያስፈልጋል 

ትዕዘዝ አልደረሰንም በሚል ተልካሻ ምክንያት ህገ-መንግስታዊ መብታችንን በመጣስ 

የአንድነትን ሊቀመንበር ጨምሮ በአጠቃላይ 101 አባላትን ከማክሰኞ እስከ እሁድ 

አስሮብናል ብለዋል፡፡

ፖሊስ ለህግ የበላይነት መቆም ሲገባው በድብቅ ለተሰጠው ትዕዛዝ ተገዥ በመሆኑ 

ለደረሰው ህገ-ወጥ እስር ፣ ካላግባብ ስለደረሰው የንብረትና የገንዘብ ጉዳት 

እንዲሁም የሞራል ካሳ የአዲስ አበባ ፖሊስንና የአዲስ አበባ መስተዳድርን በሕግ 

ለመጠየቅ ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።


አንድነት እና 33 ፓርቲዎች በጋራ ባዘጋጁት የተቃውሞ ሰልፍ በ10 ሺዎች 


የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መንግስት እየፈጸመ ያለውን ሰብአዊ መብቶች 

ጥሰት አውግዘዋል።ሰልፈኞቹ በአገሪቱ ውስጥ እየታየ ላለው የኢኮኖሚ ችግር 

መንግስት አፋጣኝ መልስ እንዲሰጥም ጠይቋል

ከሙስና ተጠርጣሪው የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ ጋር በተያያዘ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ተያዘ

ከሙስና ተጠርጣሪው የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ ጋር በተያያዘ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ተያዘ

ከሙስና ተጠርጣሪው የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ ጋር በተያያዘ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 24 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ ከነበሩት ተመስገን ስዩም ጋር በተያያዘ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ ሲያዝ 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ዶዘር ደግሞ ማሳገዱን የፌዴራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ገለፀ፡፡
የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአቶ ተመስገን ስዩም ላይ ያካሄደው ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያመለክተው ግለሰቡ በሃላፊነት ላይ በነበሩበት ወቅት 12 የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴዎችን በሌላ ሰው ስም ገዝተው ለተገዙት መኪኖች ውክልና በመውሰድ መኪኖቹን ለሌሎች ሰዎች ሸጠዋል፡፡
ከሽያጩ በተገኘው ገንዘብ ደግሞ ሁለት ዶዘሮችን ለመግዛት ከ15 ሚሊዩን ብር በላይ ለአንድ ድርጅት ክፍያ ፈፅመዋል፡፡
ግለሰቡ ክፍያ ከፈፀሙባቸው ዶዘሮች መካከል አንዱን በ7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በመረከብ ለአንድ ድርጅት ያከራዩ ሲሆን ሌላውን 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጣውን ዶዘር ለመረከብ በዝግጅት ላይ እንደነበሩ የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡
ግለሰቡ ይህን ያደረጉት ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ በመያዝ ከሚመጣ ተጠያቂነት ለማምለጥ እና በሙስና የተገኘን ህጋዊ አስመስሎ ለማቅረብ እንደሆነ በጉዳዩ ዙሪያ እስካውን የተደረገው ምርመራ ያመላክታል፡፡
እነዚህን የተጠቀሱትን ገንዘብና ንብረት ህጋዊ በማስመሰል ሂደት ተሳትፎ ነበራቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ነጋዴዎች ከ14 ቀን በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ፥ ነጋዴዎቹ አቶ ተመስገን ስዩምን ለመርዳት የፈለጉት ቀደም ሲል ግለሰቡ በሃላፊነት ላይ በነበሩበት ወቅት ነጋዴዎቹ በህገ ወጥ መንገድ ዕቃዎችን እንዲያስገቡ ይጠቅሟቸው ስለነበር እንደሆነ ምርመራው ያስረዳል፡፡
በመሆኑም ገንዘቡና ንብረቱን ከሙስና ጋር የተያያዘ ነው በሚል ጥርጣሬ ግለሰቡ አንድ ዶዘር የገዙበት 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ከተገዛበት ድርጅት እንዲመለስ ተደርጎ ኮሚሽኑ የተረከበው ሲሆን ፥ ሌላው 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚያወጣው ዶዘር እንዲታገድ ተደርጓል ፡፡
በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዳማ ጉምሩክ የህግ ማስከበር ሃላፊ የነበሩት አቶ ተመስገን ስዩም ባለፈው ሰኔ በርካታ የገቢዎችና ጉምሩክ የስራ ሃላፊዎች ፣ ነጋዴዎችና ትራንዚተሮች በሙስና ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ሲፈለጉ ከአዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ በመሸሽ ደቡብ ሱዳን ለመግባት ሲሉ መያዛቸው ኢሬቴድ በዘገባው አስታውሷል ።      

ምክትል ጠ/ሚሩ በአቶ መለስ ዜናዊ አሰራር ላይ የመጀመሪያውን ትችት አቀረቡ

ምክትል ጠ/ሚሩ በአቶ መለስ ዜናዊ አሰራር ላይ የመጀመሪያውን ትችት አቀረቡ




አቶ መለስ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት  ብዙ ስራዎችን መሸከማቸው አፈጻጸም ላይ ድክመት ማምጣቱን በመገምገም የማሻሻያ እርምጃ መወሰዱን  ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር   አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ፡፡ አቶ ደመቀ ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉትና ትላንትናና ዛሬ ታትሞ በወጣው ቃለምልልሳቸው ላይ አቶ መለስ ብዙ ስራዎችን መሸከማቸው አንዳንድ ዘርፎችን በሚፈለገው ደረጃ ያለመፈተሸ ችግር እንዳጋጠመ አምነዋል፡፡  “ባለፉት ዓመታት ሥራዎቻችንን ስንገመግም ጠቅላይ ሚኒስትራችን ብዙ ስራ ተሸክመው ይሰሩ በነበረበት ወቅት ዋና ዋና የልማት ስራዎች ላይ በማተኮር አንዳንድ የሚኒስቴር መ/ቤቶችና የልማት መስኮች በሚፈለገው ደረጃ ያለመፈተሽ በዝርዝር ዕቅድ ግምገማና ድጋፍ ያለማድረግ ክፍተቶች እንደነበሩ እንደ ችግር በጋራ ያገኘናቸው ነጥቦች አሉ”፡፡ ብለዋል ምክትል ጠ.ሚኒስትሩ ጋዜጣው ከአቶ መለስ ሕልፈት በኋላ በተካሄደው የስልጣን ሽግሽግ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ደረጃ የክላስተር አስተባባሪዎች መሾማቸው በአራቱ ብሔራዊ ድርጅቶች መካከል ያለውን አለመተማመን የሚያሳይና ምክትል ጠ/ሚኒስትርነቱን ስልጣን ለሁሉም ለማዳረስ የተደረገ ነው ስለመባሉ ጥያቄ ቅርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ “አቶ መለስ ታግሎ የሚያታግል ጠንካራ መሪ ነው፡፡እሱን ማጣት ትልቅ ጉድለት ነው፡፡ጉድለቱን ዝም ተብሎ እዚያና እዚህ በዘመቻ የሚሞላ አይደለም” ሲሉ የተናገሩት አቶ ደመቀ፣ ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ አንድ ሰው በቀጥታ አቶ መለስን ባይተካም የጋራ አሰራርን በማጠናከር የተለያዩ የስራ ክፍፍሎች በማድረግ የጋራ አቅም አጎልብቶ እንዴት የህዳሴውን ጉዞ አጠናክሮ መቀጠል ይቻላል የሚለው በስፋት የተመከረበት ጉዳይ እንደነበር አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም በሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደረጃ በመሰየም የተለያዩ ክላስተሮችን እንዲያስተባብሩ ማድረግ ያለመተማመን መገለጫ አይደለም በማለት ወቀሳውን አስተባብለዋል፡፡  እነዚህን  ችግሮች በመፍታት ድጋፍ ለማድረግ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ደረጃ የክላስተር አደረጃጀት ማስፈለጉን የጠቀሱት አቶ ደመቀ የበለጠ አቅም ለማሳደግ፣የተሟላ የመሸከም ብርታት ለመስጠት ይህ የጋራ አሰራር መተግበሩን አስረድተዋል፡፡

Thursday, October 3, 2013

የ 22 አመታት የጭቆና ገመድ ሊበጠስ ተቃርብዋል :: !!!


የ 22 አመታት የጭቆና ገመድ ሊበጠስ ተቃርብዋል :: !!!


ይህ ! ትውልድ ኢትዮጲያዊ እንጂ ኢህአዲጋዊ አይደለም :: ሚሊዮኖች ዛሬ 

ያሰሙት ድምፅ የመላው ኢትዮጵያዊ ድምፅ ነው :: ዛሬ የተሳካው ሰላማዊ 

የተቃውሞ ድምፅ መልስ አልባ ከሆነ ! ነገ አምባገነኖችን ወደ መቃብራቸው 

የሚወረውር ህዝባዊ ንቅናቄ የለውጥ ማእበል ይወለዳል :: ኢህአዲግ ህውሐት ሆይ 

!!! ጊዜው በሀይል ለማፈን እና ረግጦ ለመግዛት ረፍድዋል:: ሰላማዊ በሆነ መንገድ 

ስልጣን ወደ ህዝብ መልስ :: የታሰሩ ተፈተው ብሔራዊ እርቅ እና ሰላም ይስፈን 

!!! ህዝብ ያመነበትን መርጦ ሀገሪትዋ በሰላም ልማትና እድገትዋ ይፋጠን :: 

የተከበራችሁ የአንድነት ፓርቲ መሪ እና አባላቶች በዛሬው ሰልፍ ላይ የታደማችሁ 

ውድ ወገኖቼ በሙሉ የናንተ ትውልድ መሆኔ አኮራኝ ኮራውባችሁ :: ህልማችን 

ሀገራችን ነፃ ወጥታ የምናይበት ቀን ቅርብ ነው :: ድል ለተጨቆኑ ህዝባች !!!!