Thursday, October 3, 2013

Another Azeb Mesfin’s business partner arrested on corruption charges.

Another Azeb Mesfin’s business partner arrested on corruption charges.

Gebreselassie Hailemariam, now in custody, is a close friend of Azeb Mesfin, according to some sources. Azeb’s confidantes and business associates like Woldeselassie and Gebrewahd are behind bars on corruption charges.
Source-ethiomedia

ከአንድነቶች ሶስት ወር ዘመቻዎች የተማርናቸው!

ከአንድነቶች ሶስት ወር ዘመቻዎች የተማርናቸው!

udj 4 19



የህውሃት/ኢህአዴግ ጠንካራ ጎኑ እስከ ጥርሳቸው ድረስ የታጠቁት ፖሊስ፣ ድህንነት፣ ምድር ጦር፣ አየር ኃይል፣ አየር ወለድ፣ ካድሬ እና ቅጥረኛ ወርበሎችን ያካትታል። የሚያውቀው የፖለቲካ ትግል ዘዴ በጫካ መገዳደልን እንጂ በከተሞች ሰላማዊ ትግሎች ማድረግ አይደለም። ስለዚህ ሰላማዊ ትግል ህውሃት/ኢህአዴግን በማያውቀው የትግል ሜዳ፣ የትግል ዘዴ እና በደካማ ጎኑ እንዲታገል እንደሚያስገድደው እና የህዝብ ድጋፍ የሚያሳጡ ስህተቶች እንደሚያሰራው የአንድነቶች የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ወለል አድርጎ አስተምሮናል።
ስለዚህ በእነዚህ ሶስት ወሮች ህውሃት/ኢህአዴግ ማለቂያ የሌለው ፖለቲካዊ እና ህገ-መንግስታዊ ስህተቶች ፈጽሟል። ከፈጸማቸው ስህተቶች ውስጥ ከግብር የሚሰበሰብ ገንዘብ የሚከፈላቸውን የከተማ አስተዳደሮች፣ ፖሊሶች፣ ደህንነቶች ፣ ካድሬዎች እና ቅጥረኛ ወረበሎች በመጠቀም እውቅና የሰጠውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ፣ ቅስቀሳ መከልከል፣ የቅስቀሳ መኪናዎችን ከማሰር አልፎ ጎማቸውን ማስተንፈስ፣ በቅስቀሳ ላይ የተሰማሩ ሰላማዊ የነፃነት ሐዋሪያትን ማሰር፣ መደብደብ፣ እጃቸውን መስበር እና መሰረተ ቢስ ምክንያቶች በመፍጠር በየፖሊስ ጣቢያው በማቆየት የቅስቀሳ ጊዜያቸውን ማቃጠል የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህ ስህተቶች ብዙዎች ሰላማዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ምክንያት ሰጥቷቸዋል። ስለዚህ ህውሃት/ኢህአዴግ ቀደም ብሎ የፖለቲካ ጥንካሬ (የህዝብ ድጋፍ መጠን) ከነበረውም ባለፉት ሶስት ወሮች ሲሸረሽረው እና የአንድነቶችን የፖለቲካ ኃይል (የህዝብ ድጋፍ) ሲያሳድግ ቆይቷል። እራስን በመጉዳት የፖለቲካ ተቀናቃኝን አቅም ከፍ ማድረግ ማለት ይኽ ነው። በማያውቀው የትግል ሜዳ፣ የትግል ዘዴ እና በደካማ ጎኑ እንዲታገል በመደረጉ ነው ይኽ ሊሆን የቻለው። ስለዚህ አንድነቶች የፖለቲካ ኃይል አቅማቸው እድገት ቀጣይነት እንዲኖረው ህውሃት/ኢህአዴግ ስህተት መስራቱን እንዲቀጥል ማድረግ አለባቸው። ሰላማዊ ትግላቸው ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረግ ብቻ! የአንድነቶች የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ሌሎች ሁለት ተጨማሪ ነገሮችን አስተምሮናል። እነሱም፥
(1ኛ) እርግጥም ዜጎች ነፃነት እንደሌላቸው በተግባር አስተምሮናል። ህውሃት/ኢህአዴግ ሰላማዊ ሰልፍ እና ህዝባዊ ስብሰባ በሚያደርግበት መስቀል አደባባይ ሳይቀር ተመሳሳይ ስብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነት እንደሌለህ አስተምሮሃል። ስለዚህ የሰላማዊ ትግላችን ግቡ እራሳችንን ነፃ ማውጣትም መሆን እንዳለበት ባለፉት ሶስት ወሮች በተጨባጭ ተምረናል። እውቅና አግኝተን በነፃነት ቅስቀሳ ማድረግ ቢያቅተን ሊደንቀን አይገባም። በነፃ ቅስቀሳ ማድረግ አቃተን ብሎ ማልቀስ ትርጉም የለውም። ነፃ እስክንወጣ ድረስ ላለው ጊዜ ጽናት እና ብስለት ኖሮን ሰላማዊ ትግላችን ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረግ በመንገዳችን ላይ የሚደቅንብንን መሰናክሎች እየተራመድን ቅስቀሳ ማድረጋችንን መቀጠል ይገባናል። እራሱ ህውሃት/ኢህአዴግ በሚፈጽማቸው ስህተቶች ሰላማዊ ትግላችንን ከተቃውሞ እና ማግባባት (Protest and Persuasion) ወደ ትብብር መንፈግ (Non-cooperation) እና ጣልቃ መግባት (Intervention) ደረጃ እንዲያሸጋግረው መንገዱን በዘዴ ልንጠርግለት ይገባል።
(2ኛው) የሰላማዊ ትግል መሪዎችን ጀግንነት፣ ግንባር ቀደምነት፣ ለመታሰር ዝግጁነት፣ ሳይገድሉ ሞተው ህዝብን የመንግስት ስልጣን ባለቤት ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኛነት የአንድነት መሪዎች እራሳቸውን ምሳሌ በማድረግ አስተምረውናል። በዚህ ረገድ የአንድነቶች ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የማይረሳ እና ወደፊት ከፖለቲካ ትግል መሪዎቻችን የምነጠይቀው ታሪክ ሰርተዋል። ታሪኩ ባጭሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፥
መስከረም 16 ቀን 2006 ዓ.ም. የአንድነት ፓርቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ 28 ያህል የታሰሩ የፓርቲውን የቅስቀሳ ቡድን አባላት ለማስፈታት ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ የሽሮ ሜዳ ፖሊስ ማዘዣ ጣብያ በማምራት ለፖሊሶቹ ‹‹ልጆቹ የፈጸሙት ህገ ወጥ ድርጊት የለም፣ ሲቀሰቅሱ የነበሩትም እውቅና የተሰጠውን ሰላማዊ ሰልፍ ነው፡፡ ቅስቀሳው ህገ ወጥ ነው የምትሉም ከሆነ እነርሱን የላኳቸው እኔ በመሆኔ እኔን ልታስሩኝ ትችላላችሁ ››ብለዋል፡፡ ፖሊስ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት እና የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን በማሰር ወጣቶቹን ለቅቋቸዋል፡፡ ፖሊስ እሳቸውን ለአጭር ጊዜ አቆይቶ ከለቀቃቸው በኋላ ከዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ጋር ባደረጉት አጭር ምልልስም “ከዚህ በኋላ መታሰር ያለብን እኛ ነን እንጂ አባሎቻችን አይደሉም” ብለዋል።

Wednesday, October 2, 2013

ህወሓቶች/ኢህአዴጎች ዉስጣዊ ችግራቸው ለመሸፈን በተቃዋሚዎች ላይ አላስፈላጊ እርምጃዎች ሊወስዱ ይችላሉ ተባለ

ህወሓቶች/ኢህአዴጎች ዉስጣዊ ችግራቸው ለመሸፈን 

በተቃዋሚዎች ላይ አላስፈላጊ እርምጃዎች ሊወስዱ ይችላሉ 

ተባለ



ህወሓቶች በዉስጣዊ ቀውስ እየታመሱ ነው። ከታሪካቸው እንደምንረዳው 

ዉስጣቸው ሲበሰብስና የመውደቅ አደጋ ሲደቀንባቸው የዉጭ "ጠላት" ያፈላልጋሉ። 
ጠላት ከዉጭ መጣ ሲባል የርስበርስ ንትርኩ ለግዜው ይተውታል፤ ምክንያቱም 

ሁላቸውም የሰሩት የጋራ ጥፋት አለ። ለውድቀት ከተዳረጉ ጉዳቸው ይወጣል። 

ስለዚህ የውጭ ጠላት ሲመጣ ለጋራ ህልውናቸው ሲሉ ይተባበራሉ።


ስለዚህ ህወሓቶች የዉጭ ጠላት ይፈልጋሉ፤ ከሌለም ራሳቸው ይፈጥራሉ። በነሱ 


እምነት የዉጭ ጠላቱ ህልዉናቸው የሚፈታተን ግን መሆን የለበትም። በኢህአዴግ 

ደረጃ ጠላታቸው ለይተዋል። አንድነቶች፣ ሰማያዊዎችና ሙስሊም የመብት 

ጠያቂዎች ለኢህአዴግ ህልውና አስጊ የሆኑ የውጭ "ጠላቶች" ናቸው። ግን 

በኢህአዴግ የሚፈለጉ ዓይነት ጠላቶች አይደሉም፤ ምክንያቱም ለፓርቲው በትክክል 

አስጊ በመሆናቸው ለኢህአዴግ ዉስጣዊ ትብብር የሚረዱ ሳይሆን ክፍፍሉ 

የሚያባብሱ ናቸው።


በህወሓት ደረጃም ጠላት ተለይተዋል። የህወሓት ጠላት ተደርጎ የተወሰደው ዓረና 


ፓርቲ ነው። ዓረና እንደ ዋነኛ አስጊ ጠላት ተይዞ እርምጃ እንዲወሰድበት 

ተመካክረውበታል። እንደዉጤቱም የዓረና ፓርቲ አባላት ማሰርና ማንገላታት 

ጀምረዋል።

ለምሳሌ፦በተምቤን ቀሲስ ሃይላይ አረጋይ፣ በራያ ደግሞ ወጣት አድሃና ንጉሰ 

ያለምንም ጥፋት በህወሓት ታስረዋል። በመቐለም ይርጋ ገብሩ የተባለ የኮሌጅ 

መምህር ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ከስራው እንዲባረር ተደርጓል። ስለዚህ 

ህወሓቶች/ኢህአዴጎች ዉስጣዊ ችግራቸው ለመሸፈን በተቃዋሚዎች ላይ አላስፈላጊ 

እርምጃዎች ሊወስዱ ስለሚችሉ ከወዲሁ መጠንቀቅ ጥሩ ነው።




It is so!!!


~~አብርሃ ደስታ መቐለ~~

አንድነት በመንግስት ዛቻ አንደናገጥም አለ::

አንድነት በመንግስት ዛቻ አንደናገጥም አለ::

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በቀበና አካባቢ በተወሰነው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በሽብርተኝነት ጥፋተኛ ተብለው የታሰሩ ሰዎችን ይፈቱ ማለቱ፣ እንዲሁም ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያለን የሙስሊም ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ መጠየቁና ባልተፈቀደ ቦታ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጓል በሚለውን የመንግስት ምላሽ ማዘኑንና በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ዛቻ እንደማይደናገጥም አስታወቀ።

የፓርቲው ምክትል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ጉዳዩን በማስመልከት በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በመንግስት በኩል ሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ ፈጣን ምላሽ በአቶ ሽመልስ ከማል በኩል መገለፁን ፓርቲው መገንዘቡን ከገለፁ በኋላ በሚኒስትር ዲኤታው በኩል የተገለፀው ነገር የመንግስት አቋም ስለመሆኑ ቢያጠራጥርም ምላሹ ግን የህግ ትርጓሜን በማዛባት የቀረበ ነው ብለዋል።

“አቶ ሽመልስ ከመዛት ግላዊ ባህሪያቸው ተነስተው “ሕግ የሚያመጣውን መዘዝ ለመቀበል ይዘጋጁ” ማለታቸው ሁላችንንም ያሳዘነ አገላለፅ ነው። እኛ ሕግ አስተማሪና ቀጪ መሆኑን እንጂ መዘዝ መሆኑን አናውቅም። ካጠፋን ልንማር እንችላለን መንግስትም ካጠፋ ከስህተቱ ሊማር ይገባል ብለን እናምናለን። ስለዚህ የህግ መዘዝ አለው ማለት ለእኛ ከዛቻ የተሻለ ትርጉም የለውም” ብለዋል። አቶ ሀብታሙ ጨምረው እንደገለፁት የሚኒስትር ዲኤታው ንግግር በፖለቲካ ይዘትም ሆነ ከህግ አንፃር መሰረት የሌለው ነገር ከመሆን በዘለለ ይሄንን ሀገር በተሻለ ብቃት የመምራት አቅም ማጣታቸውን ማሳያ ነው ብለዋል።

አቶ ሽመልስ ከማል ካነሱዋቸው ነጥቦች መካከል “ሰልፉ ባልተፈቀደ ቦታ ተካሂዷል” የሚለው ወቀሳ ነው ያሉት አቶ ሀብታሙ “በእርግጠኝነት የአዲስ አበባ አስተዳደር ለአንድነት ፓርቲ በፃፈው ደብዳቤ የሰላማዊ ሰልፉ መነሻ ከፓርቲው ጽ/ቤት ተነስቶ በቀበና አደባባይ አድርጎ፣ ወደ ጃንሜዳ አምርቶ፣ ሰልፉ እዛው ጃንሜዳ እንዲጠናቀቅ የሚል ነው። ይህ ውሳኔ የደረሰንም የእኛን ሰልፍ ለማደናቀፍ፣ ያቀረብናቸውን ዘጠኝ አማራጮችንም በመቀልበስ፣ ባልፈለግነውና ባልመረጥነው ቦታ እንዲፈፀም ነው የተደረገው። ይህ ነገር ከሞራልም ከህግም አንፃር ተቀባይነት ባይኖረውም ለህግ ተገዢ በመሆን ወደ መስቀል አደባባይ የምናደርገውን ጉዞ በፖሊስ በከፍተኛ ኃይል መጥቶ መንገድ በመዘጋቱ፤ ከፖሊስ ጋር ግብግብ መፍጠሩን በመተው ወደቀበና አደባባይ በመዞር ቀበና አደባባይ ላይ ሰልፉን ለማጠናቀቅ ተገደናል። ወደጃንሜዳ ያልሄድንበት ምክንያት ኢህአዴግ ህግ እንድንጥስ በር ሲከፍትልን ህግ ላለመጣስ ብለን ወደጃንሜዳ አልሄደንም። ጃንሜዳ ያልሄድነው ቦታው ከጦር ካምፕ በ20 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ የሀገሪቷ ህግ ደግሞ ማናቸውም ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከጦር ካምፕ ካለበት ቢያንስ 500 ሜትር ርቆ መካሄድ አለበት ስለሚል ነው” ብለዋል። ይህም ባልተፈቀደ ቦታ ሰልፍ ማካሄድ ሳይሆን ለሀገሪቱ ህግ ያለንን ተገዢነት ያሳየንበት ስለሆነ ሁኔታው የእኛን ሕጋዊነት ያሳየ ሲሆን በአንፃሩ እነ አቶ ሽመልስ የሚመሩት መንግስት ሕገ-ወጥነት ማረጋገጫ እንደሆነ ጠቅሰዋል። በሕግ አግባብ ሲታይ ሃያ ሜትር የጦር ካምፕ ስር ሄዶ መሰለፍ ነው ወይስ እንዲሰለፉ ፈቃድ የሰጠው አካል የሚጠየቀው? ሲሉ ጥያቄውን በጥያቄ መልሰዋል።

“ሌላው በነፃ ፍርድ ቤት አሸባሪ የተባሉትን ሰዎች እንደ ሰማዕት አስመስለው መልዕክቶቻቸውን አንብበዋል” የሚለው የአቶ ሽመልስ ማስፈራሪያ ከሀገሪቱ ሕገ-መንግስት ጋር ይጋጫል የሚሉት አቶ ሀብታሙ የሀገሪቱ ሕገ-መንግስት በግልፅ እንዳስቀመጠው ማንኛውም የፍርድ ቤት ውሳኔ ከፍርድ ውሳኔ በኋላ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ መቃወም ወንጀል ሳይሆን መብት ነው ብለዋል። እንኳንስ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ቀርቶ አንድ ግለሰብ ከፍርድ ውሳኔ በኋላ ውሳኔውን መቃወም መብት ሆኖ ሳለ አቶ ሽመልስ ግን ነፃ በሚሉት ፍርድ ቤት የተወሰነውን ውሳኔ ጥሳችኋል ማለታቸው ተገቢም ተቀባይነትም የለውም ብለዋል።

“አቶ ሽመልስ የሚመሩት ድርጅት በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ነፃ ናቸው ብሎ ያምናል። በአንፃሩ የእኛ ፓርቲ ደግሞ ነፃ ፍርድ ቤት የለም ብሎ ያምናል። በዚህ ረገድ የአቋም ልዩነት አለን። ነፃ ፍርድ ቤት የለም ብለን አቋም መያዝ የፖለቲካ መብታችን ነው። አቶ ሽመልስ ይሄ የፖለቲካ መብት መሆኑ ካልገባቸው በቀር ነፃ ፍርድ ቤት የለም ብለን ስናበቃ፤ ነፃ ያልሆነ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ አንቀበልም ማለት በእኛ እምንት ተገቢ ነው። ህግ መጣስ የሚመጣው ያ ነፃ አይደለም ያልነው ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ በኃይል ለመቀበልስ ከሄድን ብቻ ነው። እኛ ግን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በሰላማዊ መንገድ ነው የተቃወምነው። ይሄ ደግሞ መብት ነው እንጂ ወንጀል አይደለም” ሲሉ አቶ ሀብታሙ መልሰዋል።

በተጨማሪ አቶ ሽመልስ “በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ሽብርተኝነት አበረታተዋል” ሲሉ ከሰውናል ያሉት አቶ ሀብታሙ በመጀመሪያ ደረጃ እኛ የታሰሩት ሰዎች ሽብርተኛ ናቸው ብለን አናምንም። አለማመን ደግሞ መብት ነው። ፍርድ ቤቱ የሰጠውንም ውሳኔ ተገቢ ነው ብለን አናምንም። እንደ ፓርቲም መቃወማችንን እንቀጥላለን። እነሱ ሽብርተኛ ያሉዋቸው ሰዎች ቀደም ሲል እስር ቤት ሆነው ኀሳባቸውን በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሔቶች ሲገልፁ ቆይተዋል። ነገር ግን ለኢህአዴግ ህመም የፈጠረበት በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ሲገለፅ ነው። ይሄ ደግሞ የሰልፉ ውጤት ኢህአዴግን ስላስከፋው እንጂ ህግ መጣስ አይደለም። በተጨማሪም አንድ ሰው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ኃይሉ ዜሮ በሆነበት ሁኔታ “አበረታታችኋል” ማለቱ ትርጉም የለውም። ስለዚህ ሽብርተኝነትን የምናበረታታበት ምንም ዕድል የለም ብለዋል።

የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በተመለከተም በትክክልም በፍርድ ሂደት ላይ ያለ ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሀብታሙ በፍርድ ሂደት ላይ ያለን ነገር መቃወም ተገቢ አይደለም ብለዋል።

“ነገርግን አቶ ሽመልስ የተረዱን አይመስለኝም” ያሉት አቶ ሀብታሙ እኛ እየተቃወምን ያልነው ፍ/ቤቱን ሳይሆን ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን “ጀሀዳዊ ሀረካት” የሚል ዘጋቢ ፊልም ሰርቶ ተጠርጣሪዎቹን “አሸባሪ” ብሎ ከፍርድ ቤቱ በፊት መወሰኑን ነው። ይሄንን ደግሞ በአደባባይ መቃወም አሸባሪን መደገፍ አይደለም። ፍርድ ቤቱ የሚወስነውን ከወሰነ በኋላ ደግሞ የምንይዘውን አቋም እንይዛለን። ነገር ግን አሁን ፍርድ ቤቱ “ተጠርጣሪ” እያላቸው ኢቲቪ ግን “አሸባሪ” ብሏቸዋል። እኛ ደግሞ “የለም እነዚህ ሰዎች ተጠርጣሪ እንጂ አሸባሪ አይደሉም” ብለን ተሟግተናል። የምንቃወም ይሄንኑ ነው በማለት አስረድተዋል።

“ሌላው በሽብርተኝነት የታሰሩ ይፈቱ ብላችኋል” የሚለው የአቶ ሽመልስ ከማል ክስ በተመለከተም ፍ/ቤት በነፃነት የመወሰን መብቱ ኢቲቪ ባስተላለፈው ፊልም ነፃነቱን በመጋፋቱ በተያዙት ሰዎች ላይ ነፃ ፍርድ ይሰጣል ብለን አናምንም። ስለዚህም ሰዎች በነፃ ይለቀቁ ብለን መጠየቃችንን የሕግ መዘዝ ያመጣል ማለት የመንግስት ስልጣናቸውን ከመመካት የሚመነጭ እንጂ የሕግ መሰረት የለውም ብለዋል። በአጠቃላይ የአቶ ሽመልስ ምላሽ በግብታዊነት ፓርቲው ላይ እርምጃ ለመውሰድና ሰላማዊ ትግሉን ለማዳፈን በመሆኑ መዘዙ የከፋ ነው ሲሉ በበኩላቸው መልሰዋል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማል እሁድ ዕለት ማምሻውን ለኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት በሰጡት ማብራሪ አንድነት ፓርቲ ባልተፈቀደለት ቦታ ሰልፍ ማካሄዱን እንዲሁም በሰልፉ ላይ በሽብርተኝነት ጥፋተኛ ተብለው የታሰሩ ሰዎችን በማወደስና እንዲፈቱ በመጠየቅ ሽብርተኝነት ማበረታታቱን በመግለፅ ህገ ወጥ ተግባር መፈፀማቸውንና ፓርቲውም ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ መጠየቃቸው አይዘነጋም::

በኖርዌይ ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ በስኬት ተከናወነ::

በኖርዌይ ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ በስኬት ተከናወነ::


ሴፕቴምበር 28,2013 በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልን ለመርዳት በኖርዌ ኦስሎከተማ የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የህዝባዊ ሃይሉ ከፍተኛ አመራር ኮማንደር አሰፋ እና የግንቦት 7የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲሁም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳዊት መኮንንና ጥሪ የተደረገላቸ እንግዶችና ከተለያየ የአውሮፓናስካንዴኔቪያን ሃገሮች መጡና በጣም በርካታ የሆኑ በኖርዌ በሚኖሩ ከተለያየ ከተማ የመጡ ሀገር ወዳድኢትዮጵያውያን በተገኙበት በታላቅ ወኔና የሃገር ፍቅር ስሜት በስኬት ተከናወኖ አመሸ።


በዝግጅቱ ላይ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይሉ አመራር ስለድርጅታቸው በሰፊው ህዝቡን ያስደሰተ ማብራሪያ የሰጡሲሆን ከታዳሚው የቀረባላቸውንም ጥያቄዎች በስፋት በማብራራት ለታዳሚው ከፍተኛ ግንዛቤአስጨብጠዋል። በተመሳሳይ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በምስል የተደገፈ ከፍተኛ ማብራሪያ ሰጥተው ከህዝብየቀረበላቸውን ጥያቄዎች ሰፋ አድርገው አስረድተዋል።

በአንፃሩ እጃችን እረጅም ነው ብለው የሚያስቡ ጠባብ አስተሳሰብ ያላቸው የወያኔ ተላላኪ ቡድኖች ዲሞክራሲባለበት በኖርዌ ምድር መጥተ እንኳን የማይቀየሩ አምባገነኖች እዚህም ዝግጅታችን እንዳይሳካ ለማበላሸትእንቅልፍ ሳይተኙ የሃሰት ፕሮፓጋንዳቸውን እየነፉ ህዝብ ለማደናገር የአሸባሪ ድርጅት ለመርዳት የገቢማሰባሰቢያ ሊያደርጉ ነበር ነገር ግን ፕሮግራሙ ተሰረዘ በማለት ዜና ቢያሰራጩም እኛ ግን እየረዳን ያለነውየግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል በየትኛውም አለም በአሸባሪነት መዝገብ ውስጥ ያልተመዘገበ ድርጅት መሆኑን የኖርዌፕሮፌሰር በሃገሪቱ ውስጥ ለሚታተም አንድ ጋዜጣ አስተያየታቸውን የገለፁ ሲሆን በእለቱም ዝገጅቱ በደማቅሁኔታ ተከናውኖ ከዚህ ቀደም በየተኛውም የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮገራም ያልታየ ከፍተኛ የገንዘብ ገቢምተደርጓል።

በአጠቃላይ በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ጨረታዎች፤ ቀስቃሽ ሙዚቃ፤ ባህላዊ ምግብና መጠጥ እንዲሁም የተለያዩቁሳቁሶች ለሽያጭ ቀርበው የነበረ ሲሆን በተጨማሪም የትጥቅ ትግል ለምን አስፈለገ በሚል አጭር ገላጭ ድራማቀርቦ ህዝቡን በጣም አስደስቷል። በዝግጅቱ መክፈቻና መዝጊያ ላይም የህዝባዊ ሃይሉ መዝሙር ላንቺ ነው ሃገሬላንቺ ነው የሚለው በህዝቡ ተዘምሮ ዝገጅቱም እኩለ ለሊት በድምቅት ተጠናቋል፡፡
http://ethsat.com/video/esat-fundraising-event-for-g7-popular-force-in-oslo-oct-6-2013-ethiopia/
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ሞት ለወያኔ

ስለህወሓት ፀረ-ኢትዮጵያ አካሄድ የተሸፈኑ ምስጢሮች

ስለህወሓት ፀረ-ኢትዮጵያ አካሄድ የተሸፈኑ 

ምስጢሮች

የህወሓትን ፀረ-ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት ማስዋዕትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው?
ገብረመድህን አርኣያ ከአስውትራሊያ
ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪ ተክሌ፣ አጽብሃ ዳኛው እና ዶ/ር አታክልት ቀጸላ Gessesew Ayele, Agazi Gessese, Musse Mahri Tekle, Atsbeha Dagnachew and Dr. Atakilt Ketswela
ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት ያለውን ነው።

በህወሓት የተፈጸመው እውንተኛ ታሪክና አሰቃቂ ወንጀሎች፣ የህወሓት አመራር በኢትዮጵያ ሀገራችን አሁንም እየፈፀሙት የሚገኘው ግፍ በግልጽ ተጽፎ የወያኔ ጥቁር ታሪክ ለሕዝብ የሚቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። አሁንም እየቀረበ ነው።
ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ለትግል የተሰማራው በየካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት በረሃ እንደመሸገ ማሀብር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) የተዘጋጀው ፕሮግራም የተረከበው ተሓህት ወይም የዛሬው ስሙ ሀወሓት ነው።
ተሓህት ትግሉን በጀመረበት ወቅት ጥቂት ከነበሩት ታጋዮች ሊመሩን ይችላሉ ብሎ ከመረጣቸው መካከል፤ 1. አረጋዊ በርሄ፣ ሊቀመንበር 2. ዘርኡ ገሰሰ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4. ገሰሰው አየለ 5. አባይ ፀሃየ 6. ሥዩም መስፍን 7. አለምሰገድ መንገሻ 8. አስፍሃ ሃጎስ ተመርጠው ተሓህትን መርተዋል።
በዚህ ጊዜ ነበር የማገብትን ውርስ ተሓህት ተረከበው ብሎ በጊዜው የነበረ ታጋይ ደስታውን የገለጸው። ውርስ ማለት ፕሮግራሙ ነው። በጊዜው የነበረ ሁሉም ታጋይ ግን የፕሮግራሙን ይዘትና ምንነትቱን አያውቅም ነበር። ይህ ፕሮግራም ነበር በ1968 ቀስ በቀስም ተሓህትን ለሁለት የመሰንጠቅ አደጋ የፈጠረበት። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!) 

Tuesday, October 1, 2013

Human Rights Advocacy Group (HRAG)

Human Rights Advocacy Group (HRAG)


Press Statement
HRAG Launching Conference-Communities initiate to confront perpetrators of Human Rights Crimes in Ethiopia
Benshangul, Gambela, Ogaden Somali, Oromo, Shakacho and Sidama.
28 September 13
We, the peoples of Benshangul, Gambella, Ogaden Somali, Oromo, Shakacho and Sidama nations unanimously agree to form Human Rights Advocacy Group (HRAG) in order to advocate for the Human Rights of the member communities and other oppressed peoples by the Ethiopian government.

HRAG will tirelessly campaign harnessing the combined resources of the aforementioned communities and other support groups. It will expose the crimes the Ethiopian government is committing against the defenceless communities of these peoples, including land grabbing and displacement, mass executions, extra-judicial killings, rampant rape, mass detentions and use of aid as a weapon to gain compliance to the regime marginalization policies.

HRAG will conduct targeted advocacy campaign that includes data gathering, advocacy works directed at countries of the world, Human Rights defenders, the AU and the United Nations, and will encourage more vigorous and joint campaigns by all the communities concerned.

HRAG informs that the current situation in Ethiopia is very dire and unless urgent measures are taken, a crisis far worse than any seen so far in Africa will unfold. Therefore, HRAG calls the international community, in particular Donor countries, the AU and the UN and EU to make the Ethiopian government accountable for its flagrant Human Rights violations.
Finally, HRAG calls upon all peoples in Ethiopia to stand up together and confront the perpetrators.

Justice for all nations and nationalities.


Human Rights Advocacy Group (HRAG)
September 28, 2013, London