"በሠላማዊው የሙስሊም ማኅበረሰብ ላይ እየተወሰደ ያለው ዘግናኝ እና አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንዲሁም ግድያ የመበስበስ እና የሥርዐት አልበኝነት መገለጫዎች ናቸው።
በ97 ለተፈጸመው ግድያ አቶ መለስ መልስ ሲሰጡ “ፖሊስ ደንግጦ ነው” ብለው ነበር። ይህን ይበሉ እንጂ አዲስ አበባን በሰባት ኮማንድ ከፍለው ትዕዛዙን ያስተላለፉት እሳቸው ናቸው። በሥልጣን የሞት ሽረት አጣብቂኝ ውስጥ ስለነበሩ አማራጫቸው ገድሎ በሌላው ላይ ማለከክ ኾነ። ዛሬ ድንጋይ የሚወረውር በሌለበት፣ ጎማ የሚያቃጥል በማይታይበት እና በሰላም ለአንድ ወር በጾም እና በጸሎት ከቆየበት በዐል ተመልሶ ከቤተሰቡ ጋራ ለማሳለፍ ወደ ቤቱ የሚተምን ሕዝብ በቆረጣ ገብቶ መደብደብ፣ ማሳቃየት እና መግደል ምን የሚሉት ርምጃ ነው? አቶ ኀይለማርያም መቼም በአደባባይ ወጥተው “ፖሊስ ደንብሮ” ነው አይሉም አይባልም። እንደ ራዕይ አስፈጻሚ “መለስ እንዲህ ዐይነት ነገር ሲገጥመው ምን ነበር የሚለው?” ብለው አሰላለስለው ከመመለስ ወደ ኋላ የሚሉ አይመስለኝም። ምክንያቱም የራሳቸው ሕልም፣ የራሳቸው ራዕይ፣ እና የራሳቸው አንደበት የላቸውማ! ይህ ግድያ እና ሰቆቃ እየተፈጸመ ያለው ግን እርሳቸው የአገሪቱ መሪ ናቸው ተብለው በሚታሰቡበት እና በሚቆጠሩበት ሰዓት ስለኾነ ቀጥተኛ ሐላፊነቱን ማንም አይወስደውም።
የእነ ሽብሩ ነገር አስገራሚ ነው። አንድ የፌዴራል ፖሊስ በቅርቡ ባህር ዳር ላይ ብዙ ሰው ፈጀ። ይህ ሰው አጠቃላዩን የፌዴራል ፖሊስ አይወክልም አሉና አለቆች ተሰባስበው በአባላቶቻቸው ላይ የማሳመን ሥራ ሠሩ። የሕዝብ ግንኙነቱን ሥራ አጧጧፉት። እኛ ለሕዝብ ደህነነት ከጎኑ የቆምን ሐቀኞች ነን ብለው በፖሊስ ፕሮግራም ላይ ቀርበው ቤተሰቦቻቸውን ላጡት ሰዎች ካሳ ሰፈሩላቸው። ረብጣ ረብጣ የተዋጣ ብር ሰጡ እና የመልካም ስነምግባር ምልክቶች እንደኾኑ ለፈፉ። የልፈፋቸው ጩኸተ ገደሉን መትቶ የገደል ማሚቶው እነሱ ጆሮ ሳይደርስ እነርሱ በቡድን ኾነው ኮፈሌ ዘመቱ፤ አሁን ደግሞ አዲስ አበባ ላይ መጡ። ቅጣ ያጣ ጩኸት ማለት ታዲያ ይኼ አይደል።
የባህር ዳሩን ገዳይ ፌዴራል ፖሊስ ጥፋት ለመሸፋፈን ረብጣ ብር ይዞ የሰላም ጠባቂ፣ የሰላማውያንን ድምፅ ለማፈን ደግሞ በዱላ እና በጥይት አራቂ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ድኻ ነው እንጂ ሞኝ አይደለም። ሕዝብን በሐይል ለጥቂት ጊዜ መግዛት ይቻላል፤ ነገር ግን የሕዝብ ሐይል ሲያይል ብሶት በየአቅጣጫው ይወለዳል። ብሶት ሲያድግ ጦር አይመልሰውም።
በሠላማዊ ትግል ጋንዲ ታላቋን ብሪታንያን አሸንፏታል። ለሕዝቡ ነጻነትን አውጇል። በሰላማዊ ትግል ብዙ ሌሎች ሐያላን ወድቀዋል። ሠላማዊ ዜጎችን በማፈን፣ በደብደብ፣ በማሰቃየት እና በመግደል ጥያቄን ማቆም አይቻልም። በተቃራኒው ለጥያቄው የዓላማ ልብስ ያለብሰዋል እንጂ።
ማስታወሻ፦ ሙስሊም ወንድሞቼ እና እህቶቼ ኾይ፤ እናንተ ያነሳችሁት የእምነት ነጻነት ጥያቄ የሥርዐቱ መበስበስ ማሳያ ምልክት ኾኗል እና ደስ ሊላችኹ ይገባል። ነጻነታችኹን እስክትቀዳጁ ድረስ ኹሌም ልቤ ከእናንተ ጋራ ነው። የእናንተ ጥያቄ የነጻነት ናፋቂዎች ሁሉ ጥያቄ ነው። ዛሬ በአምባገነኖች የተወሰደባችሁ ርምጃ የሚያጸናችሁ እንጂ ወደ ኋላ የሚጎትታችሁ እንደማይኾን አስባለሁ። በአሰቃቂ ኹኔታ ቤተሰቦቻችሁን ላጣችሁ እና ዘግናኝ የኾነ ድብደባ እና እንግልት ለደረሰባችሁ ሁሉ መጽናናትን እመኝላችኋለሁ። ምንም እንኳ በሐዘን ድባብ ውስጥ ያለፈ ቢሆንም ለሁላችኹም ኢድ ሙባረክ ብያለሁ!!

Masresha Mamo
No comments:
Post a Comment