Thursday, August 8, 2013

ግማሽ ደስታ ግማሽ ለቅሶ ዛሬ ወልቂጤ አነባች!!!


ግማሽ ደስታ ግማሽ ለቅሶ ዛሬ ወልቂጤ አነባች!!! 

ከሁለት ቀን በፊት ከተማዋ ላይ ፈሰው የነበሩት የፌደራል ፖሊሶች(አውሬዎች)ን 

ዛቻ ማስፈራርያ ሳይበግረው ከዒድ ሰላት በፊት ተቃውሞን ጀምሮ የነበረው 

ጀግናውና ታሪክ አይረሴው የወልቂጤ ሙስሊም በከፍተኛ ወኔና ተቃውሞ 

በማሰማት ወደ ዒድ ሰላት ካመራ ቡላና በድጋሚ የዒድ ሰላት መጠናቀቁን ተከትሎ 

የተጀመረው ተቃውሞ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ካመራ ቡጋላ ነገሮች ተለዋውጠው ህዝቡ 

ዒድ ሰላት በሚሰግድ ጊዜ መንገዱን በድንጋይ በመዝጋትና አሰለቃሽ ጭሳቸውን 

አዘጋጅተው ሲጠባበቁ የነበሩት የመንግስት አውሬዎች ሰላማዊ ሰልፉኛውን ከፍተኛ 

ሀይል በተቀላቀለበት ህዝቡን መጨፍጨፉን ተያይዘውት እናቶች፣ አባቶች ህፃናትን 

እንኳ ሳይተዉ አረመኔያዊ ደብብደባ አከናውናዋል ፡፡ በሰው ላይ ደረሰ ጉዳት 

አስካሁን በውል አልታወቀም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ኒቃቢስ ጅልባቢስቶችና 

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች በቁጥጥር ስር እያዋለ ነው!!! የከተማዋ 

ሙስሊሞችም ሰላማዊ መሆናችንን ዳግም ማረጋገጥ ይኖርብናል

No comments: