የዛሬውን ጨምሮ አስካሁን በተፈጸሙ ሀላፊነት የጎደላቸው የመንግስት የሀይል እርምጃዎች የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ቀጥፈዋል፡፡ የመንግስት ፍላጎት በሐይል እርምጃው እኛን መበተን፣ በተስፋ መቅረጥ ውስጥ ማዋለል፣ በሽንፈት ማፍረክረክ ነበር፡፡ ይህ የመንግስት ፍላጎት ህልም ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡ የጀመርነው ሰላማዊ ትግል ብዙ መስዋእትነት እንደሚጠይቅ ገና ከጅምሩ ተረድተነዋል፤ በእስር የሚገኙት መሪዎቻችን ይህንኑ ደጋግመው ነግረውን ነበር፡፡ ግና በደልን አይተን በፍርሃት የምንቀመጥ አይደለንም፡፡ ሁሌም እንደምንለው በበደል ብዛት አፋችን አልተለጎመም! በመንግስት የሽብር እወጃ ተሸማቀን ከጓዳ አልተሸሸግንም! በፍርሃት አልተሸበብንም! የፍትህ መጓደል አንደበታችንን አልዘጋውም! የእምነት መብት ሲጣስ ‹‹ምን ገዶን›› አላልንም! ዛሬም በጦርነት ቀጠና ውስጥ፣ በዚህ ፈታኝ ወቅት የኢስላማዊ አንድነታችን ትርጉም ደማቅ መሆኑ ታይቷል፡፡ መሪዎቻችንን እስር ቤት ጥለን ቤታችን አልተሸሸግንም! ከምንም በላይ በደል በነገሰበት አገር ስለ ፍትህ የምንሟገት ዜጎች ነን - እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች!
አላሁ አክበር!
አላሁ አክበር!
No comments:
Post a Comment